ኤርምያስ
13 ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና ከተልባ እግር የተሠራ ቀበቶ ግዛ፤ በወገብህም ላይ ታጠቀው፤ ሆኖም ፈጽሞ ውኃ አታስነካው።” 2 ስለዚህ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ቀበቶውን ገዝቼ ወገቤ ላይ ታጠቅኩት። 3 የይሖዋም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጣ፦ 4 “የገዛኸውንና የታጠቅከውን ቀበቶ ይዘህ ተነስ፤ ወደ ኤፍራጥስም ሄደህ በቋጥኝ ስንጥቅ ውስጥ ደብቀው።” 5 ስለዚህ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ሄጄ በኤፍራጥስ አጠገብ ደበቅኩት።
6 ሆኖም ከብዙ ቀናት በኋላ ይሖዋ “ተነስ፤ ወደ ኤፍራጥስ ሄደህ፣ በዚያ እንድትደብቀው ያዘዝኩህን ቀበቶ አምጣ” አለኝ። 7 እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፣ ቀበቶውን ከደበቅኩበት ቦታ ቆፍሬ አወጣሁ፤ ቀበቶው ተበላሽቶና ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ አገኘሁት።
8 ከዚያም የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦ 9 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የይሁዳን ኩራትና የኢየሩሳሌምን እብሪት ልክ እንደዚሁ አጠፋዋለሁ።+ 10 ቃሌን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ያለው፣+ ግትር ሆኖ የገዛ ልቡን የሚከተለው+ እንዲሁም ሌሎች አማልክትን የሚከተለው፣ የሚያገለግለውና ለእነሱ የሚሰግደው ይህ ክፉ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ እንደሆነው እንደዚህ ቀበቶ ይሆናል።’ 11 ‘ቀበቶ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፣ መላው የእስራኤል ቤትና መላው የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋር እንዲጣበቅ አደረግኩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ይህም ሕዝቤ፣+ ስሜ፣+ ውዳሴዬና ውበቴ እንዲሆኑ ነው። እነሱ ግን አልታዘዙም።’+
12 “አንተም ይህን መልእክት አክለህ ንገራቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ “እያንዳንዱ ትልቅ እንስራ በወይን ጠጅ ይሞላል” ይላል።’ እነሱም ‘እያንዳንዱ ትልቅ እንስራ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ መች ጠፋን?’ ብለው ይመልሱልሃል። 13 በዚህ ጊዜ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናቱንና ነቢያቱን እንዲሁም የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች በሙሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።+ 14 እነሱንም እርስ በርሳቸው፣ አባቶችንና ልጆችንም አጋጫለሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ምንም ዓይነት ርኅራኄም ሆነ አዘኔታ አላሳይም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነሱን ከማጥፋት ምንም ነገር አያግደኝም።”’+
15 ስሙ፤ ልብ በሉ።
ትዕቢተኞች አትሁኑ፤ ይሖዋ ተናግሯልና።
16 ጨለማን ከማምጣቱ በፊትና
ጨለምለም ባሉት ተራሮች ላይ እግሮቻችሁ ከመደናቀፋቸው በፊት
ለአምላካችሁ ለይሖዋ ክብር ስጡ።
17 ለመስማት አሻፈረን ካላችሁ፣
በኩራታችሁ የተነሳ በስውር አለቅሳለሁ።*
19 የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፤* የሚከፍታቸውም የለም።
መላው ይሁዳ በግዞት ተወስዷል፤ ሙሉ በሙሉም ተግዟል።+
20 ዓይንሽን አንስተሽ ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቺ።+
ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣ ያማሩት በጎችሽ የት አሉ?+
21 ከመጀመሪያው አንስቶ የተወዳጀሻቸው የቅርብ ጓደኞችሽ
አንቺን ለመቅጣት ሲነሱ ምን ትዪ ይሆን?+
ልክ እንደምትወልድ ሴት ምጥ አይዝሽም?+
22 በልብሽም ‘እነዚህ ነገሮች የደረሱብኝ ለምንድን ነው?’ በምትይበት ጊዜ፣+
ቀሚስሽን የተገፈፍሽውና+ ተረከዝሽ ለሥቃይ የተዳረገው
በፈጸምሽው ታላቅ በደል የተነሳ መሆኑን ልታውቂ ይገባል።
23 ኢትዮጵያዊ* መልኩን፣ ነብርስ ዥጉርጉርነቱን መለወጥ ይችላል?+
እንዲህ ማድረግ የሚችል ከሆነ፣
ክፉ ነገር መሥራት የለመዳችሁት እናንተም መልካም ማድረግ ትችላላችሁ ማለት ነው።
24 ስለዚህ የበረሃ ነፋስ ይዞት እንደሚሄድ ገለባ እበትናቸዋለሁ።+
26 በመሆኑም ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልባለሁ፤
ኀፍረትሽም ይታያል፤+
27 የፈጸምሽው ምንዝር፣+ በፍትወት ማሽካካትሽ፣
ጸያፍ* የሆነው ዝሙት አዳሪነትሽ ይገለጣል።
አስጸያፊ ምግባርሽን
በኮረብቶቹና በሜዳው ላይ አይቼአለሁ።+
ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ወዮልሽ!
ርኩስ ሆነሽ የምትኖሪው እስከ መቼ ድረስ ነው?”+