የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቅያስ፣ ይሖዋ እንዲረዳው ጠየቀ (1-7)

      • ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ዛተ (8-13)

      • ሕዝቅያስ ያቀረበው ጸሎት (14-19)

      • ኢሳይያስ አምላክ የሰጠውን መልስ ነገረው (20-34)

      • አንድ መልአክ 185,000 አሦራውያንን ገደለ (35-37)

2 ነገሥት 19:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 37:1-4

2 ነገሥት 19:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤተ መንግሥቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:1

2 ነገሥት 19:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የስድብና።”

  • *

    ቃል በቃል “ልጁ ወደ ማህፀኑ አፍ መጥቶ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 26:17, 18

2 ነገሥት 19:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 17:45፤ 2ነገ 18:35
  • +2ሳሙ 22:7፤ 2ዜና 20:9፤ 32:20፤ መዝ 50:15

2 ነገሥት 19:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 37:5-7

2 ነገሥት 19:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 20:3፤ 2ነገ 18:17፤ ኢሳ 41:10፤ 51:7

2 ነገሥት 19:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እነሆ፣ መንፈስ አስገባበታለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:21፤ ኢሳ 37:37, 38

2 ነገሥት 19:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:14
  • +ኢሳ 37:8-13

2 ነገሥት 19:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:17

2 ነገሥት 19:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:15

2 ነገሥት 19:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:5፤ 2ዜና 32:10, 13፤ ኢሳ 10:8-11

2 ነገሥት 19:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 11:31

2 ነገሥት 19:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:24፤ 18:33, 34

2 ነገሥት 19:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ደብዳቤውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:30፤ ኢሳ 37:14-20

2 ነገሥት 19:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በኪሩቤል መካከል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:20
  • +ዘፀ 25:22
  • +1ዜና 29:10, 11

2 ነገሥት 19:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:29፤ መዝ 65:2
  • +2ዜና 16:9፤ ዳን 9:18

2 ነገሥት 19:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:8, 9፤ 17:6, 24

2 ነገሥት 19:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 10:3
  • +ኢሳ 41:29

2 ነገሥት 19:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 83:17, 18፤ ኢሳ 45:5, 6

2 ነገሥት 19:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:15፤ ኢሳ 37:21, 22

2 ነገሥት 19:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:10
  • +2ነገ 18:30፤ ኢሳ 10:12, 13
  • +ኢሳ 37:23-25

2 ነገሥት 19:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:17
  • +2ዜና 32:17፤ ኢሳ 10:10, 11

2 ነገሥት 19:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የአባይንም የመስኖ ቦዮች።”

2 ነገሥት 19:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የተደረገ።”

  • *

    ወይም “ሠርቻለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 14:24
  • +መዝ 33:11
  • +ኢሳ 46:10
  • +ኢሳ 10:5፤ 37:26, 27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    2/2024፣ ገጽ 30

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/1999፣ ገጽ 14

2 ነገሥት 19:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 40:7

2 ነገሥት 19:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 5:21፤ ኢሳ 37:28, 29፤ ዕብ 4:13

2 ነገሥት 19:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 46:6፤ ኢሳ 10:5, 15
  • +2ነገ 18:35፤ ኢሳ 10:12, 13
  • +መዝ 32:9
  • +2ነገ 19:33

2 ነገሥት 19:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ለሕዝቅያስ የተነገረ ነው።

  • *

    ሰብል በሚሰበሰብበት ጊዜ ማሳው ላይ ረግፎ እንደገና የሚበቅለውን እህል ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:4-6
  • +ኢሳ 37:30-32

2 ነገሥት 19:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:22፤ ኢሳ 10:20

2 ነገሥት 19:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 59:17፤ ዘካ 1:14, 15

2 ነገሥት 19:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 10:24
  • +2ዜና 32:22
  • +ኢሳ 37:33-35

2 ነገሥት 19:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 12:22፤ ኢሳ 43:25፤ ሕዝ 36:22
  • +2ነገ 20:6፤ ኤር 23:5
  • +ኢሳ 31:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 12

2 ነገሥት 19:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:21፤ ኢሳ 31:8
  • +ዘፀ 12:30፤ ኢሳ 37:36-38

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/1993፣ ገጽ 6

2 ነገሥት 19:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮናስ 1:2
  • +2ነገ 19:7, 28

2 ነገሥት 19:37

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:21
  • +ዘፍ 8:4
  • +ዕዝራ 4:2

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 19:1ኢሳ 37:1-4
2 ነገ. 19:2ኢሳ 1:1
2 ነገ. 19:3ኢሳ 26:17, 18
2 ነገ. 19:41ሳሙ 17:45፤ 2ነገ 18:35
2 ነገ. 19:42ሳሙ 22:7፤ 2ዜና 20:9፤ 32:20፤ መዝ 50:15
2 ነገ. 19:5ኢሳ 37:5-7
2 ነገ. 19:6ዘዳ 20:3፤ 2ነገ 18:17፤ ኢሳ 41:10፤ 51:7
2 ነገ. 19:72ዜና 32:21፤ ኢሳ 37:37, 38
2 ነገ. 19:82ነገ 18:14
2 ነገ. 19:8ኢሳ 37:8-13
2 ነገ. 19:92ነገ 18:17
2 ነገ. 19:102ዜና 32:15
2 ነገ. 19:112ነገ 17:5፤ 2ዜና 32:10, 13፤ ኢሳ 10:8-11
2 ነገ. 19:12ዘፍ 11:31
2 ነገ. 19:132ነገ 17:24፤ 18:33, 34
2 ነገ. 19:141ነገ 8:30፤ ኢሳ 37:14-20
2 ነገ. 19:152ዜና 32:20
2 ነገ. 19:15ዘፀ 25:22
2 ነገ. 19:151ዜና 29:10, 11
2 ነገ. 19:161ነገ 8:29፤ መዝ 65:2
2 ነገ. 19:162ዜና 16:9፤ ዳን 9:18
2 ነገ. 19:172ነገ 16:8, 9፤ 17:6, 24
2 ነገ. 19:18ኤር 10:3
2 ነገ. 19:18ኢሳ 41:29
2 ነገ. 19:19መዝ 83:17, 18፤ ኢሳ 45:5, 6
2 ነገ. 19:202ነገ 19:15፤ ኢሳ 37:21, 22
2 ነገ. 19:222ነገ 19:10
2 ነገ. 19:222ነገ 18:30፤ ኢሳ 10:12, 13
2 ነገ. 19:22ኢሳ 37:23-25
2 ነገ. 19:232ነገ 18:17
2 ነገ. 19:232ዜና 32:17፤ ኢሳ 10:10, 11
2 ነገ. 19:25ኢሳ 14:24
2 ነገ. 19:25መዝ 33:11
2 ነገ. 19:25ኢሳ 46:10
2 ነገ. 19:25ኢሳ 10:5፤ 37:26, 27
2 ነገ. 19:26ኢሳ 40:7
2 ነገ. 19:27ምሳሌ 5:21፤ ኢሳ 37:28, 29፤ ዕብ 4:13
2 ነገ. 19:28መዝ 46:6፤ ኢሳ 10:5, 15
2 ነገ. 19:282ነገ 18:35፤ ኢሳ 10:12, 13
2 ነገ. 19:28መዝ 32:9
2 ነገ. 19:282ነገ 19:33
2 ነገ. 19:29ዘሌ 25:4-6
2 ነገ. 19:29ኢሳ 37:30-32
2 ነገ. 19:302ዜና 32:22፤ ኢሳ 10:20
2 ነገ. 19:31ኢሳ 59:17፤ ዘካ 1:14, 15
2 ነገ. 19:32ኢሳ 10:24
2 ነገ. 19:322ዜና 32:22
2 ነገ. 19:32ኢሳ 37:33-35
2 ነገ. 19:341ሳሙ 12:22፤ ኢሳ 43:25፤ ሕዝ 36:22
2 ነገ. 19:342ነገ 20:6፤ ኤር 23:5
2 ነገ. 19:34ኢሳ 31:5
2 ነገ. 19:352ዜና 32:21፤ ኢሳ 31:8
2 ነገ. 19:35ዘፀ 12:30፤ ኢሳ 37:36-38
2 ነገ. 19:36ዮናስ 1:2
2 ነገ. 19:362ነገ 19:7, 28
2 ነገ. 19:372ዜና 32:21
2 ነገ. 19:37ዘፍ 8:4
2 ነገ. 19:37ዕዝራ 4:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 19:1-37

ሁለተኛ ነገሥት

19 ንጉሥ ሕዝቅያስ ይህን እንደሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶም ወደ ይሖዋ ቤት ገባ።+ 2 ከዚያም የቤቱ* አስተዳዳሪ የሆነውን ኤልያቄምን፣ ጸሐፊውን ሸብናህን እንዲሁም የካህናቱን ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ+ እንዲሄዱ ላካቸው። 3 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የዘለፋና* የውርደት ቀን ነው፤ መውለጃዋ ደርሶ* ለማማጥ የሚያስችል አቅም እንዳጣች ሴት ሆነናል።+ 4 ምናልባት አምላክህ ይሖዋ፣ ሕያው የሆነውን አምላክ እንዲያቃልል ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራብሻቁን ቃል ሁሉ ይሰማ ይሆናል፤+ ደግሞም አምላክህ ይሖዋ፣ የተናገረውን ቃል ሰምቶ ተጠያቂ ያደርገው ይሆናል። ስለዚህ በሕይወት ለተረፉት ቀሪዎች ጸልይ።’”+

5 በመሆኑም የንጉሥ ሕዝቅያስ አገልጋዮች ወደ ኢሳይያስ ሄዱ፤+ 6 ኢሳይያስም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታችሁን እንዲህ በሉት፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች እኔን በመሳደብ የተናገሩትን ቃል በመስማትህ አትፍራ።+ 7 እነሆ፣ በአእምሮው አንድ ሐሳብ አስገባለሁ፤* እሱም ወሬ ሰምቶ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ በገዛ አገሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።”’”+

8 ራብሻቁም የአሦር ንጉሥ ለኪሶን+ ለቆ እንደሄደ ሲሰማ ወደ ንጉሡ ተመለሰ፤ ከሊብናም ጋር ሲዋጋ አገኘው።+ 9 ንጉሡ የኢትዮጵያው ንጉሥ ቲርሃቅ “ከአንተ ጋር ሊዋጋ ወጥቷል” የሚል ወሬ ሰምቶ ነበር። በመሆኑም ለሕዝቅያስ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት በድጋሚ መልእክተኞች ላከ፦+ 10 “የይሁዳን ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፦ ‘የምትታመንበት አምላክህ “ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” ብሎ አያታልህ።+ 11 እነሆ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን አገሮች ሁሉ ፈጽመው በማጥፋት ያደረጉትን ነገር ሰምተሃል።+ ታዲያ አንተ ብቻ ከዚህ የምታመልጥ ይመስልሃል? 12 አባቶቼ ያጠፏቸውን ብሔራት አማልክታቸው ታድገዋቸዋል? ጎዛን፣ ካራን፣+ ረጼፍና በቴልአሳር የነበሩት የኤደን ሕዝቦች የት አሉ? 13 የሃማት ንጉሥ፣ የአርጳድ ንጉሥ፣ የሰፋርዊም ከተሞች ንጉሥ እንዲሁም የሄና እና የኢዋ+ ነገሥታት የት አሉ?’”

14 ሕዝቅያስ ደብዳቤዎቹን ከመልእክተኞቹ እጅ ተቀብሎ አነበበ። ከዚያም ወደ ይሖዋ ቤት ወጥቶ ደብዳቤዎቹን* በይሖዋ ፊት ዘረጋ።+ 15 ሕዝቅያስም በይሖዋ ፊት እንዲህ ሲል ጸለየ፦+ “ከኪሩቤል በላይ* የምትቀመጥ፣+ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ እውነተኛ አምላክ አንተ ብቻ ነህ።+ ሰማያትንና ምድርን ሠርተሃል። 16 ይሖዋ ሆይ፣ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ!+ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይንህን ገልጠህ እይ!+ ሰናክሬም ሕያው የሆነውን አምላክ ለማቃለል የላከውን ቃል ስማ። 17 ይሖዋ ሆይ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን ብሔራትና ምድራቸውን እንዳጠፉ አይካድም።+ 18 አማልክታቸውንም እሳት ውስጥ ጨምረዋል፤ ምክንያቱም የሰው እጅ ሥራ፣+ እንጨትና ድንጋይ እንጂ አማልክት አይደሉም።+ ሊያጠፏቸው የቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። 19 አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ፣ አንተ ብቻ አምላክ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ከእጁ አድነን።”+

20 ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ሕዝቅያስ ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ ያቀረብከውን ጸሎት ሰምቻለሁ።+ 21 ይሖዋ በእሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦

“ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ትንቅሃለች፤ ደግሞም ታፌዝብሃለች።

የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ራሷን ትነቀንቅብሃለች።

22 ያቃለልከውና የሰደብከው ማንን ነው?+

ድምፅህን ከፍ ያደረግከው፣+

እብሪተኛ ዓይንህንም ያነሳኸው በማን ላይ ነው?

በእስራኤል ቅዱስ ላይ እኮ ነው!+

23 በመልእክተኞችህ+ በኩል ይሖዋን አቃለሃል፤+ እንዲህም ብለሃል፦

‘ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎቼ፣

ወደ ተራሮች ከፍታ፣

ርቀው ወደሚገኙትም የሊባኖስ ስፍራዎች እወጣለሁ።

ረጃጅሞቹን አርዘ ሊባኖሶች፣ ምርጥ የሆኑትንም የጥድ ዛፎች እቆርጣለሁ።

ርቆ ወደሚገኘው ማረፊያ ቦታ፣ በጣም ጥቅጥቅ ወዳለው ጫካ እገባለሁ።

24 ጉድጓድ ቆፍሬ የባዕድ አገር ውኃዎችን እጠጣለሁ፤

የግብፅንም ጅረቶች* ሁሉ በእግሬ ረግጬ አደርቃለሁ።’

25 አልሰማህም? ይህ ከጥንት ዘመን ጀምሮ የተወሰነ* ነው።+

ከድሮ ጀምሮ ይህን አስቤአለሁ።*+

አሁን እንዲፈጸም አደርጋለሁ።+

አንተም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር ታደርጋለህ።+

26 ነዋሪዎቻቸው አቅመ ቢስ ይሆናሉ፤

ይሸበራሉ፤ ደግሞም ያፍራሉ።

እንደ ሜዳ ተክል፣ እንደ ለምለም ሣር፣+

እንዲሁም የምሥራቅ ነፋስ እንዳቃጠለው በጣሪያ ላይ የበቀለ ሣር ይሆናሉ።

27 ይሁንና መቼ እንደምትቀመጥ፣ መቼ እንደምትወጣና መቼ እንደምትገባ፣

እንዲሁም መቼ በእኔ ላይ እንደተቆጣህ በሚገባ አውቃለሁ፤+

28 ምክንያቱም በእኔ ላይ የተቆጣኸው ቁጣና+ ጩኸትህ ወደ ጆሮዬ ደርሷል።+

ስለዚህ ስናጌን በአፍንጫህ፣ ልጓሜንም+ በአፍህ አስገባለሁ፤

በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።”+

29 “‘ይህም ምልክት ይሆንሃል፦* በዚህ ዓመት የገቦውን እህል* ትበላላችሁ፤ በሁለተኛውም ዓመት ከዚያው ላይ የበቀለውን እህል ትበላላችሁ፤+ በሦስተኛው ዓመት ግን ዘር ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁም፤ እንዲሁም ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።+ 30 ከይሁዳ ቤት ያመለጡትና በሕይወት የቀሩት ሰዎች+ ወደ ታች ሥር ይሰዳሉ፤ ወደ ላይም ያፈራሉ። 31 ከኢየሩሳሌም ቀሪዎች፣ ከጽዮን ተራራም በሕይወት የተረፉ ሰዎች ይወጣሉና። የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።+

32 “‘ስለዚህ ይሖዋ ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦+

“ወደዚህች ከተማ አይመጣም፤+

ፍላጻም አይወረውርባትም፤

ጋሻም ይዞ አይመጣባትም፤

ከበባ ለማድረግም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል አይደለድልም።+

33 በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤

ወደዚህች ከተማ አይገባም” ይላል ይሖዋ።

34 “ስለ እኔና+ ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊት ስል+

ይህችን ከተማ እጠብቃታለሁ፤+ ደግሞም አድናታለሁ።”’”

35 በዚያም ሌሊት የይሖዋ መልአክ ወጥቶ በአሦራውያን ሰፈር የነበሩትን 185,000 ሰዎች ገደለ።+ ሰዎችም በማለዳ ሲነሱ ሬሳውን አዩ።+ 36 በመሆኑም የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከዚያ ተነስቶ ወደ ነነዌ+ ተመለሰ፤ በዚያም ተቀመጠ።+ 37 ሰናክሬም በአምላኩ በኒስሮክ ቤት* እየሰገደ ሳለ አድራሜሌክና ሳሬጸር የተባሉት የገዛ ልጆቹ በሰይፍ መትተው ገደሉት፤+ ከዚያም ወደ አራራት+ ምድር ሸሽተው ሄዱ። ልጁም ኤሳርሃደን+ በእሱ ምትክ ነገሠ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ