የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢዮዓካዝ በእስራኤል ላይ ነገሠ (1-9)

      • ኢዮዓስ በእስራኤል ላይ ነገሠ (10-13)

      • ኤልሳዕ የኢዮዓስን ቅንዓት ፈተነ (14-19)

      • ኤልሳዕ ሞተ፤ የኤልሳዕን አፅም የነካው ሰው ከሞት ተነሳ (20, 21)

      • ኤልሳዕ የተናገረው የመጨረሻው ትንቢት ፍጻሜውን አገኘ (22-25)

2 ነገሥት 13:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 8:26፤ 9:27
  • +2ነገ 11:2, 21
  • +2ነገ 10:30, 35

2 ነገሥት 13:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28-30፤ 13:33፤ 14:16

2 ነገሥት 13:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 12:29
  • +ዘሌ 26:14, 17
  • +1ነገ 19:17፤ 2ነገ 8:12
  • +2ነገ 13:24

2 ነገሥት 13:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:7፤ መሳ 10:16፤ 2ነገ 14:26, 27

2 ነገሥት 13:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ተረጋግተው በሰላም መኖራቸውን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:27

2 ነገሥት 13:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እሱ በዚያ ተመላለሰ።”

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 10:29፤ 17:21
  • +ዘዳ 7:5፤ 1ነገ 14:15፤ 16:33

2 ነገሥት 13:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 8:12፤ 10:32፤ አሞጽ 1:3

2 ነገሥት 13:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 10:35

2 ነገሥት 13:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 14:1

2 ነገሥት 13:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በእነዚህ ኃጢአቶች መመላለሱን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 10:29

2 ነገሥት 13:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 14:8, 13

2 ነገሥት 13:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዳግማዊ ኢዮርብዓምን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 14:28
  • +2ነገ 10:35፤ 13:9

2 ነገሥት 13:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 19:16
  • +2ነገ 2:11, 12

2 ነገሥት 13:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የማዳን።”

  • *

    ወይም “የማዳን።”

  • *

    ወይም “ታሸንፋቸዋለህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 29:1፤ 1ነገ 20:26

2 ነገሥት 13:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 13:25

2 ነገሥት 13:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በዓመቱ መግቢያ።” በበልግ ወቅት ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 1:1፤ 24:2

2 ነገሥት 13:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 11:44፤ ዕብ 11:35

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2017፣ ገጽ 5

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2005፣ ገጽ 11

    11/15/1991፣ ገጽ 4

2 ነገሥት 13:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 19:15
  • +2ነገ 8:12፤ 10:32

2 ነገሥት 13:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 13:14-16
  • +ዘፍ 26:3
  • +ዘፍ 28:13፤ መዝ 105:8፤ ሚክ 7:20
  • +2ነገ 14:26, 27

2 ነገሥት 13:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አሸነፈው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 13:19

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 13:12ነገ 8:26፤ 9:27
2 ነገ. 13:12ነገ 11:2, 21
2 ነገ. 13:12ነገ 10:30, 35
2 ነገ. 13:21ነገ 12:28-30፤ 13:33፤ 14:16
2 ነገ. 13:3ዕብ 12:29
2 ነገ. 13:3ዘሌ 26:14, 17
2 ነገ. 13:31ነገ 19:17፤ 2ነገ 8:12
2 ነገ. 13:32ነገ 13:24
2 ነገ. 13:4ዘፀ 3:7፤ መሳ 10:16፤ 2ነገ 14:26, 27
2 ነገ. 13:5ነህ 9:27
2 ነገ. 13:62ነገ 10:29፤ 17:21
2 ነገ. 13:6ዘዳ 7:5፤ 1ነገ 14:15፤ 16:33
2 ነገ. 13:72ነገ 8:12፤ 10:32፤ አሞጽ 1:3
2 ነገ. 13:92ነገ 10:35
2 ነገ. 13:102ነገ 14:1
2 ነገ. 13:112ነገ 10:29
2 ነገ. 13:122ነገ 14:8, 13
2 ነገ. 13:132ነገ 14:28
2 ነገ. 13:132ነገ 10:35፤ 13:9
2 ነገ. 13:141ነገ 19:16
2 ነገ. 13:142ነገ 2:11, 12
2 ነገ. 13:171ሳሙ 29:1፤ 1ነገ 20:26
2 ነገ. 13:192ነገ 13:25
2 ነገ. 13:202ነገ 1:1፤ 24:2
2 ነገ. 13:21ዮሐ 11:44፤ ዕብ 11:35
2 ነገ. 13:221ነገ 19:15
2 ነገ. 13:222ነገ 8:12፤ 10:32
2 ነገ. 13:23ዘፍ 13:14-16
2 ነገ. 13:23ዘፍ 26:3
2 ነገ. 13:23ዘፍ 28:13፤ መዝ 105:8፤ ሚክ 7:20
2 ነገ. 13:232ነገ 14:26, 27
2 ነገ. 13:252ነገ 13:19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 13:1-25

ሁለተኛ ነገሥት

13 የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ+ ልጅ ኢዮዓስ+ በነገሠ በ23ኛው ዓመት የኢዩ+ ልጅ ኢዮዓካዝ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በሰማርያም ሆኖ ለ17 ዓመት ገዛ። 2 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ እንዲሁም የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ያደረገውን ኃጢአት መሥራቱን ቀጠለ።+ ከዚያም አልራቀም። 3 በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ+ በእስራኤል ላይ ነደደ፤+ በዘመናቸውም ሁሉ በሶርያ ንጉሥ በሃዛኤል+ እጅና በሃዛኤል ልጅ በቤንሃዳድ+ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።

4 ከጊዜ በኋላ ኢዮዓካዝ የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት ለመነ፤ ይሖዋም ሰማው፤ ምክንያቱም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ ያደረሰውን ጭቆና አይቶ ነበር።+ 5 ስለሆነም ይሖዋ ለእስራኤላውያን ከሶርያውያን እጅ ነፃ የሚያወጣ አዳኝ ሰጣቸው፤+ እስራኤላውያንም እንደቀድሟቸው በየቤታቸው መኖር ጀመሩ።* 6 (እነሱ ግን የኢዮርብዓም ቤት እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ካደረገው ኃጢአት ዞር አላሉም።+ ይህን ኃጢአት መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤* የማምለኪያ ዓምዱም*+ በሰማርያ እንደቆመ ነበር።) 7 ኢዮዓካዝ የቀረው 50 ፈረሰኞች፣ 10 ሠረገሎችና 10,000 እግረኛ ወታደሮች ብቻ ያሉት ሠራዊት ነበር፤ ምክንያቱም የሶርያ ንጉሥ በአውድማ ላይ እንዳለ እብቅ ረጋግጦ ደምስሷቸው ነበር።+

8 የቀረው የኢዮዓካዝ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉና ኃያልነቱ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? 9 በመጨረሻም ኢዮዓካዝ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ቀበሩት፤+ ልጁም ኢዮዓስ በምትኩ ነገሠ።

10 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓስ+ በነገሠ በ37ኛው ዓመት የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በሰማርያም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። 11 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሟቸው ካደረጋቸው ኃጢአቶች ሁሉ ዞር አላለም።+ እነዚህን ኃጢአቶች መፈጸሙን* ቀጠለ።

12 የቀረው የኢዮዓስ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉና ኃያልነቱ እንዲሁም ከይሁዳ ንጉሥ ከአሜስያስ ጋር እንዴት እንደተዋጋ+ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? 13 በመጨረሻም ኢዮዓስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ኢዮርብዓምም*+ በዙፋኑ ተቀመጠ። ኢዮዓስም ከእስራኤል ነገሥታት ጋር በሰማርያ ተቀበረ።+

14 ኤልሳዕ+ ለሞት በዳረገው በሽታ ተይዞ በነበረበት ወቅት የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ወደ እሱ ወርዶ “አባቴ፣ አባቴ! የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞች!”+ በማለት ላዩ ላይ ተደፍቶ አለቀሰ። 15 ኤልሳዕም “በል ደጋንና ቀስቶች አምጣ” አለው። እሱም ደጋንና ቀስቶች አመጣ። 16 ከዚያም ኤልሳዕ የእስራኤልን ንጉሥ “ደጋኑን በእጅህ ያዝ” አለው። ንጉሡም ደጋኑን በእጁ ያዘ፤ በመቀጠልም ኤልሳዕ እጆቹን በንጉሡ እጆች ላይ ጫነ። 17 ከዚያም “በምሥራቅ በኩል ያለውን መስኮት ክፈት” አለው። እሱም ከፈተ። ኤልሳዕም “አስፈንጥር!” አለው። እሱም አስፈነጠረ። ኤልሳዕም “የይሖዋ የድል* ቀስት፤ በሶርያ ላይ የሚወነጨፍ የድል* ቀስት! ሶርያውያንን ድምጥማጣቸውን እስክታጠፋ ድረስ አፌቅ+ ላይ ትመታቸዋለህ”* አለው።

18 ኤልሳዕ በመቀጠል “ቀስቶቹን ያዝ” አለው፤ እሱም ያዘ። ከዚያም የእስራኤልን ንጉሥ “መሬቱን ውጋ” አለው። እሱም መሬቱን ሦስት ጊዜ ወግቶ አቆመ። 19 በዚህ ጊዜ የእውነተኛው አምላክ ሰው በእሱ ላይ ተቆጥቶ እንዲህ አለው፦ “መሬቱን አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መውጋት ነበረብህ! እንደዚያ ብታደርግ ኖሮ ሶርያውያንን ሙሉ በሙሉ ድምጥማጣቸውን ታጠፋ ነበር፤ አሁን ግን ሶርያን የምትመታው ሦስት ጊዜ ብቻ ነው።”+

20 ከዚያም ኤልሳዕ ሞተ፤ ተቀበረም። በዓመቱ መጀመሪያ* ላይ ወደ ምድሪቱ ዘልቀው የሚገቡ የሞዓባውያን ወራሪ ቡድኖች+ ነበሩ። 21 የተወሰኑ ሰዎች አንድ ሰው ሊቀብሩ ሲሉ ወራሪውን ቡድን ተመለከቱ፤ ስለዚህ ሰውየውን ኤልሳዕ የተቀበረበት ቦታ ውስጥ ወርውረው እየሮጡ ሄዱ። ሰውየውም የኤልሳዕን አፅም በነካ ጊዜ ሕያው ሆነ፤+ በእግሩም ቆመ።

22 የሶርያ ንጉሥ ሃዛኤል+ በኢዮዓካዝ ዘመን ሁሉ እስራኤልን ይጨቁን ነበር።+ 23 ሆኖም ይሖዋ ከአብርሃም፣+ ከይስሐቅና+ ከያዕቆብ+ ጋር ስለገባው ቃል ኪዳን ሲል ሞገስና አሳቢነት አሳያቸው፤ ምሕረትም አደረገላቸው።+ ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከፊቱ አላስወገዳቸውም። 24 የሶርያ ንጉሥ ሃዛኤል በሞተ ጊዜ ልጁ ቤንሃዳድ በእሱ ምትክ ነገሠ። 25 ከዚያም የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ፣ ሃዛኤል ከአባቱ ከኢዮዓካዝ ላይ በጦርነት የወሰዳቸውን ከተሞች ከሃዛኤል ልጅ ከቤንሃዳድ አስመለሰ። ኢዮዓስ ሦስት ጊዜ መታው፤*+ የእስራኤልንም ከተሞች መልሶ ያዘ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ