የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ የፍርድ መልእክት (1-14)

      • መጋቢው ሸብና በኤልያቄም ተተካ (15-25)

        • ምሳሌያዊው ማንጠልጠያ (23-25)

ኢሳይያስ 22:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኢየሩሳሌምን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 6:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 231-232

ኢሳይያስ 22:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 3:1፤ ኤር 38:2፤ ሰቆ 4:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 233-234

ኢሳይያስ 22:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:4, 5
  • +2ነገ 25:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 231, 234

ኢሳይያስ 22:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በሰውኛ ዘይቤ የተገለጸ ቅኔያዊ አነጋገር፤ አዘኔታን ወይም ርኅራኄን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:19፤ 8:18, 19፤ 9:1
  • +ሚክ 1:8, 9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 234-235

ኢሳይያስ 22:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እርዳታ ለማግኘት ወይም በጦርነት ወቅት የሚሰማን ጩኸት ሊያመለክት ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 7:4
  • +2ነገ 25:10፤ ነህ 1:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 234-235

ኢሳይያስ 22:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በፈረሰኞች።”

  • *

    ወይም “ጋሻውን አዘጋጀች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:22
  • +2ነገ 16:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 235

ኢሳይያስ 22:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ረባዳማ ሜዳዎችሽ።”

  • *

    ወይም “ፈረሰኞቹም።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 235-236

ኢሳይያስ 22:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መከላከያ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 7:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 235-236

ኢሳይያስ 22:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:9, 10፤ ኤር 52:7
  • +ነህ 3:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 236

ኢሳይያስ 22:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 236

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/1997፣ ገጽ 10-11

ኢሳይያስ 22:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 237

ኢሳይያስ 22:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዩ 2:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 237

ኢሳይያስ 22:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 5:12፤ 56:12፤ አሞጽ 6:1, 4፤ ሉቃስ 17:27፤ ያዕ 5:5
  • +1ቆሮ 15:32

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 237

ኢሳይያስ 22:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:31፤ ኢሳ 1:11፤ ኤር 15:1፤ ሕዝ 24:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 238

ኢሳይያስ 22:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቤተ መንግሥቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:37፤ 19:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    3/2018፣ ገጽ 25

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 238-239

ኢሳይያስ 22:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “መኖሪያ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 238-239

ኢሳይያስ 22:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 239

ኢሳይያስ 22:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 239, 243

ኢሳይያስ 22:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2007፣ ገጽ 9

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 239

ኢሳይያስ 22:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:26, 37

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 240, 241-243

ኢሳይያስ 22:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ግዛትህንም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 41:41, 42፤ አስ 8:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 240

ኢሳይያስ 22:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 3:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2009፣ ገጽ 31

    ራእይ፣ ገጽ 63

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 240, 241-242

ኢሳይያስ 22:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 239-241

ኢሳይያስ 22:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ክብደት።”

  • *

    ወይም “ቅርንጫፎቹን።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 240-243

ኢሳይያስ 22:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 22:15, 17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 240-242

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 22:1ኤር 6:6
ኢሳ. 22:2ኢሳ 3:1፤ ኤር 38:2፤ ሰቆ 4:9
ኢሳ. 22:32ነገ 25:4, 5
ኢሳ. 22:32ነገ 25:11
ኢሳ. 22:4ኤር 4:19፤ 8:18, 19፤ 9:1
ኢሳ. 22:4ሚክ 1:8, 9
ኢሳ. 22:5ሚክ 7:4
ኢሳ. 22:52ነገ 25:10፤ ነህ 1:3
ኢሳ. 22:6ዘፍ 10:22
ኢሳ. 22:62ነገ 16:9
ኢሳ. 22:81ነገ 7:1, 2
ኢሳ. 22:92ነገ 25:9, 10፤ ኤር 52:7
ኢሳ. 22:9ነህ 3:15
ኢሳ. 22:12ኢዩ 2:17
ኢሳ. 22:13ኢሳ 5:12፤ 56:12፤ አሞጽ 6:1, 4፤ ሉቃስ 17:27፤ ያዕ 5:5
ኢሳ. 22:131ቆሮ 15:32
ኢሳ. 22:14ዘሌ 26:31፤ ኢሳ 1:11፤ ኤር 15:1፤ ሕዝ 24:13
ኢሳ. 22:152ነገ 18:37፤ 19:2
ኢሳ. 22:202ነገ 18:26, 37
ኢሳ. 22:21ዘፍ 41:41, 42፤ አስ 8:15
ኢሳ. 22:22ራእይ 3:7
ኢሳ. 22:25ኢሳ 22:15, 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 22:1-25

ኢሳይያስ

22 ስለ ራእይ ሸለቆ* የተነገረ የፍርድ መልእክት፦+

ሁላችሁም ጣሪያ ላይ የወጣችሁት ምን ሆናችሁ ነው?

 2 አንቺ ሁከት የነገሠብሽ መዲና፣ የፈንጠዝያም ከተማ፣

በትርምስ ተሞልተሻል።

ነዋሪዎችሽ ያለቁት በሰይፍ

ወይም በጦርነት ተገድለው አይደለም።+

 3 አምባገነን መሪዎችሽ ሁሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል።+

ሆኖም ቀስት መጠቀም ሳያስፈልግ ተማርከዋል።

ወደ ሩቅ ቦታ ሸሽተው ቢሄዱም

የተገኙት ሁሉ ተማርከዋል።+

 4 ስለዚህ እንዲህ አልኩ፦ “ዓይናችሁን ከእኔ ላይ አንሱ፤

እኔም አምርሬ አለቅሳለሁ።+

የሕዝቤ ሴት ልጅ* ከደረሰባት ጥፋት የተነሳ

እኔን ለማጽናናት አትድከሙ።+

 5 ከሉዓላዊው ጌታ፣ ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ዘንድ

በራእይ ሸለቆ

ግራ የመጋባት፣ የሽንፈትና የመደናገጥ ቀን ሆኗልና።+

ቅጥሩ ይፈርሳል፤+

ወደ ተራራውም ይጮኻሉ።*

 6 ኤላም+ ሰዎችን ባሳፈሩ ሠረገሎችና በፈረሶች* ላይ

የፍላጻ ኮሮጆዋን ይዛለች፤

ቂርም+ የጋሻውን ልባስ አወለቀች።*

 7 ምርጥ የሆኑት ሸለቆዎችሽ*

በጦር ሠረገሎች ይሞላሉ፤

ፈረሶቹም* የከተማዋ በር ላይ ይቆማሉ፤

 8 የይሁዳም መከለያ*+ ይወገዳል።

“አንተም በዚያ ቀን የደኑን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ትመለከታለህ፤ 9 እናንተም በዳዊት ከተማ ቅጥር ላይ ያሉትን በርካታ ክፍተቶች ትመለከታላችሁ።+ በታችኛውም ኩሬ ውኃ ታጠራቅማላችሁ።+ 10 የኢየሩሳሌምን ቤቶች ትቆጥራላችሁ፤ ቅጥሩንም ለማጠናከር ቤቶቹን ታፈርሳላችሁ። 11 በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በድሮው ኩሬ ላለው ውኃ የሚሆን ማጠራቀሚያ ትሠራላችሁ፤ ይሁንና ይህን ወዳደረገው ታላቅ አምላክ አትመለከቱም፤ ከዘመናት በፊት ወደሠራውም አምላክ አታዩም።

12 በዚያም ቀን ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ

እንድታለቅሱና እንድታዝኑ፣+

ፀጉራችሁን እንድትላጩና ማቅ እንድትለብሱ ይጠራችኋል።

13 ይሁን እንጂ ድግስና ፈንጠዝያ፣

ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣

ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት ሆኗል።+

‘ነገ ስለምንሞት እንብላ፣ እንጠጣ’ ትላላችሁ።”+

14 ከዚያም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በጆሮዬ ይህን ገለጠልኝ፦ “‘እናንተ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል አይሰረይላችሁም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።”

15 ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በቤቱ* ላይ ወደተሾመው ወደ መጋቢው ወደ ሸብና+ ሄደህ እንዲህ በለው፦ 16 ‘በዚህ ለራስህ የመቃብር ቦታ የወቀርከው፣ የአንተ የሆነ ምን ነገር ቢኖርህ ነው? በዚህስ የአንተ የሆነ ማን አለ? በከፍታ ቦታ የራሱን መቃብር ወቅሯል፤ ቋጥኝ ጠርቦ ለራሱ ማረፊያ ስፍራ* አዘጋጅቷል። 17 ‘አንተ ሰው፣ እነሆ፣ ይሖዋ በኃይል አሽቀንጥሮ ይጥልሃል፤ ጨምድዶም ይይዝሃል። 18 ጠቅልሎና አጡዞ እንደ ኳስ ወደ ሰፊ ምድር ይወረውርሃል። በዚያ ትሞታለህ፤ ያማሩ ሠረገሎችህም በዚያ ለጌታህ ቤት ውርደት ይሆናሉ። 19 እኔም ከሹመትህ እሽርሃለሁ፤ ከኃላፊነትህም አባርርሃለሁ።

20 “‘በዚያም ቀን አገልጋዬን የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን+ እጠራለሁ፤ 21 ቀሚስህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህንም በደንብ አስታጥቀዋለሁ፤+ ሥልጣንህንም* በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። እሱም ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና ለይሁዳ ቤት አባት ይሆናል። 22 የዳዊትንም ቤት ቁልፍ+ በትከሻው ላይ አደርጋለሁ። እሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ እሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም። 23 በአስተማማኝ ቦታ ላይ እንደ ማንጠልጠያ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት እንደ ክብር ዙፋን ይሆናል። 24 በእሱም ላይ የአባቱን ቤት ክብር* በሙሉ፣ ልጆቹንና ዘሮቹን* ይኸውም ትናንሾቹን ዕቃዎች በሙሉ፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹንና ትላልቆቹን እንስራዎች ሁሉ ይሰቅሉበታል።

25 “‘በዚያም ቀን’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስተማማኝ ቦታ ላይ የተተከለው ማንጠልጠያ ይነቀላል፤+ ተቆርጦም ይወድቃል፤ በላዩ ላይ የተንጠለጠለው ሸክምም ወድቆ ይከሰከሳል፤ ይሖዋ ራሱ ተናግሯልና።’”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ