መዝሙር ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር። 131 ይሖዋ ሆይ፣ ልቤ አይኩራራም፤ዓይኖቼም አይታበዩም፤+እጅግ ታላላቅ ነገሮችን ወይምከአቅሜ በላይ የሆኑ ነገሮችን አልመኝም።+ 2 ይልቁንም እናቱ ላይ እንደተቀመጠ ጡት የጣለ ሕፃንነፍሴን አረጋጋኋት፤* ደግሞም ጸጥ አሰኘኋት።+ጡት እንደጣለ ሕፃን ረካሁ።* 3 እስራኤል ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ።+