የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • አሜስያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-6)

      • ከኤዶምና ከእስራኤል ጋር የተደረገ ውጊያ (7-14)

      • የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ሞተ (15, 16)

      • አሜስያስ ሞተ (17-22)

      • ዳግማዊ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ (23-29)

2 ነገሥት 14:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 13:10

2 ነገሥት 14:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 25:1-4

2 ነገሥት 14:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:5
  • +2ዜና 24:2

2 ነገሥት 14:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:14
  • +2ነገ 12:1, 3

2 ነገሥት 14:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 12:20፤ 2ዜና 24:25

2 ነገሥት 14:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 24:16

2 ነገሥት 14:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 8:20
  • +2ሳሙ 8:13፤ 1ዜና 18:12
  • +2ዜና 25:11, 12

2 ነገሥት 14:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፊት ለፊት እንገናኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 25:17-19

2 ነገሥት 14:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቤተ መንግሥትህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 14:7

2 ነገሥት 14:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 25:15, 16
  • +ኢያሱ 15:10, 12፤ 21:8, 16
  • +2ዜና 25:20-24

2 ነገሥት 14:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደየድንኳናቸው።”

2 ነገሥት 14:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወደ 178 ሜትር ገደማ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 8:16፤ 12:38, 39
  • +ኤር 31:38፤ ዘካ 14:10

2 ነገሥት 14:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

2 ነገሥት 14:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዳግማዊ ኢዮርብዓምን የሚያመለክት ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 10:35፤ 13:9
  • +ሆሴዕ 1:1፤ አሞጽ 1:1፤ 7:10

2 ነገሥት 14:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 13:10
  • +2ነገ 14:1
  • +2ዜና 25:25-28

2 ነገሥት 14:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 12:20

2 ነገሥት 14:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:10

2 ነገሥት 14:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ይሖዋ ረዳ” የሚል ትርጉም አለው። በ2ነገ 15:13፣ 2ዜና 26:1-23፣ ኢሳ 6:1 እና ዘካ 14:5 ላይ ዖዝያ ተብሎም ተጠርቷል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:1, 2
  • +ማቴ 1:8
  • +2ዜና 26:1

2 ነገሥት 14:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አባቱን አሜስያስን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 2:8፤ 1ነገ 9:26፤ 2ነገ 16:6
  • +2ዜና 26:2

2 ነገሥት 14:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 1:1፤ አሞጽ 1:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 18

2 ነገሥት 14:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28-30፤ 13:34፤ መዝ 106:20

2 ነገሥት 14:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከሃማት መግቢያ።”

  • *

    ጨው ባሕርን ወይም ሙት ባሕርን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:10, 13
  • +ዮናስ 1:1፤ ማቴ 12:39
  • +ዘኁ 13:21፤ 34:2, 7, 8
  • +ዘዳ 3:16, 17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 108-109

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2009፣ ገጽ 25

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 18

2 ነገሥት 14:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:7፤ መሳ 10:16፤ መዝ 106:43, 44

2 ነገሥት 14:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 31:20
  • +2ነገ 13:4, 5

2 ነገሥት 14:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 8:3
  • +2ሳሙ 8:6

2 ነገሥት 14:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:8

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 14:12ነገ 13:10
2 ነገ. 14:22ዜና 25:1-4
2 ነገ. 14:31ነገ 15:5
2 ነገ. 14:32ዜና 24:2
2 ነገ. 14:41ነገ 15:14
2 ነገ. 14:42ነገ 12:1, 3
2 ነገ. 14:52ነገ 12:20፤ 2ዜና 24:25
2 ነገ. 14:6ዘዳ 24:16
2 ነገ. 14:72ነገ 8:20
2 ነገ. 14:72ሳሙ 8:13፤ 1ዜና 18:12
2 ነገ. 14:72ዜና 25:11, 12
2 ነገ. 14:82ዜና 25:17-19
2 ነገ. 14:102ነገ 14:7
2 ነገ. 14:112ዜና 25:15, 16
2 ነገ. 14:11ኢያሱ 15:10, 12፤ 21:8, 16
2 ነገ. 14:112ዜና 25:20-24
2 ነገ. 14:13ነህ 8:16፤ 12:38, 39
2 ነገ. 14:13ኤር 31:38፤ ዘካ 14:10
2 ነገ. 14:162ነገ 10:35፤ 13:9
2 ነገ. 14:16ሆሴዕ 1:1፤ አሞጽ 1:1፤ 7:10
2 ነገ. 14:172ነገ 13:10
2 ነገ. 14:172ነገ 14:1
2 ነገ. 14:172ዜና 25:25-28
2 ነገ. 14:192ነገ 12:20
2 ነገ. 14:201ነገ 2:10
2 ነገ. 14:212ነገ 15:1, 2
2 ነገ. 14:21ማቴ 1:8
2 ነገ. 14:212ዜና 26:1
2 ነገ. 14:22ዘዳ 2:8፤ 1ነገ 9:26፤ 2ነገ 16:6
2 ነገ. 14:222ዜና 26:2
2 ነገ. 14:23ሆሴዕ 1:1፤ አሞጽ 1:1
2 ነገ. 14:241ነገ 12:28-30፤ 13:34፤ መዝ 106:20
2 ነገ. 14:25ኢያሱ 19:10, 13
2 ነገ. 14:25ዮናስ 1:1፤ ማቴ 12:39
2 ነገ. 14:25ዘኁ 13:21፤ 34:2, 7, 8
2 ነገ. 14:25ዘዳ 3:16, 17
2 ነገ. 14:26ዘፀ 3:7፤ መሳ 10:16፤ መዝ 106:43, 44
2 ነገ. 14:27ኤር 31:20
2 ነገ. 14:272ነገ 13:4, 5
2 ነገ. 14:282ዜና 8:3
2 ነገ. 14:282ሳሙ 8:6
2 ነገ. 14:292ነገ 15:8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 14:1-29

ሁለተኛ ነገሥት

14 የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ+ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ ነገሠ። 2 አሜስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ የሆዓዲን የተባለች የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች።+ 3 እሱም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ባይሆንም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ፈጸመ።+ ሁሉንም ነገር አባቱ ኢዮዓስ እንዳደረገው አደረገ።+ 4 ሆኖም ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤+ ሕዝቡ አሁንም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ይሠዋ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።+ 5 እሱም መንግሥቱ በእጁ እንደጸናለት፣ ንጉሥ የነበረውን አባቱን የገደሉትን አገልጋዮቹን+ ገደላቸው። 6 ይሁንና “አባቶች በልጆቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም በአባቶቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ይልቁንም እያንዳንዱ ሰው በገዛ ኃጢአቱ ይገደል”+ በሚለው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ ላይ በተጻፈው የይሖዋ ትእዛዝ መሠረት የገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም። 7 እሱም 10,000 ኤዶማውያንን+ በጨው ሸለቆ+ መታ፤ ተዋግቶም ሴላን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፤+ እሷም እስከ ዛሬ ድረስ ዮቅተኤል ተብላ ትጠራለች።

8 ከዚያም አሜስያስ የእስራኤል ንጉሥ ወደሆነው ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮዓካዝ ልጅ ወደ ኢዮዓስ “ና፤ ውጊያ እንግጠም”* በማለት መልእክተኞች ላከ።+ 9 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ደግሞ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ይህን መልእክት ላከ፦ “በሊባኖስ የሚገኘው ኩርንችት በሊባኖስ ወደሚገኘው አርዘ ሊባኖስ ‘ሴት ልጅህን ለወንድ ልጄ ዳርለት’ የሚል መልእክት ላከ። ይሁን እንጂ በሊባኖስ የነበረ አንድ የዱር አውሬ በዚያ ሲያልፍ ያን ኩርንችት ረገጠው። 10 እርግጥ ኤዶምን መተሃል፤+ በመሆኑም ልብህ ታብዮአል። ክብርህን ጠብቀህ አርፈህ ቤትህ* ተቀመጥ። በራስህ ላይ ለምን ጥፋት ትጋብዛለህ? ደግሞስ ራስህንም ሆነ ይሁዳን ለምን ለውድቀት ትዳርጋለህ?” 11 አሜስያስ ግን አልሰማም።+

በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ወጣ፤ እሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ በምትገኘው በቤትሼሜሽ+ ተጋጠሙ።+ 12 ይሁዳ በእስራኤል ድል ተመታ፤ እያንዳንዳቸውም ወደየቤታቸው* ሸሹ። 13 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ የአካዝያስ ልጅ፣ የኢዮዓስ ልጅ የሆነውን የይሁዳን ንጉሥ አሜስያስን ቤትሼሜሽ ላይ ያዘው። ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ እሱም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ ከኤፍሬም በር+ አንስቶ እስከ ማዕዘን በር+ ድረስ አፈረሰ፤ ርዝመቱም 400 ክንድ* ያህል ነበር። 14 በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች የተገኘውን ወርቅ፣ ብርና ዕቃ ሁሉ እንዲሁም የታገቱትን ሰዎች ወሰደ። ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።

15 የቀረው የኢዮዓስ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮችና ኃያልነቱ እንዲሁም ከይሁዳ ንጉሥ ከአሜስያስ ጋር እንዴት እንደተዋጋ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? 16 በመጨረሻም ኢዮዓስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ከእስራኤልም ነገሥታት ጋር በሰማርያ ተቀበረ፤+ ልጁም ኢዮርብዓም*+ በእሱ ምትክ ነገሠ።

17 የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ+ ከሞተ በኋላ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ+ 15 ዓመት ኖረ።+ 18 የቀረው የአሜስያስ ታሪክ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? 19 ከጊዜ በኋላ ኢየሩሳሌም ውስጥ በእሱ ላይ ሴራ ተጠነሰሰ፤+ እሱም ወደ ለኪሶ ሸሸ፤ እነሱ ግን ተከታትለው እንዲይዙት ሰዎችን ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት። 20 ከዚያም በፈረሶች ላይ ጭነው አመጡት፤ እሱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር በኢየሩሳሌም ተቀበረ።+ 21 ከዚያም የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ በወቅቱ የ16 ዓመት+ ልጅ የነበረውን አዛርያስን*+ ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ምትክ አነገሡት።+ 22 እሱም፣ ንጉሡ* ከአባቶቹ ጋር ካንቀላፋ በኋላ ኤላትን+ መልሶ በመገንባት ወደ ይሁዳ መለሳት።+

23 የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ በነገሠ በ15ኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ ኢዮርብዓም+ በሰማርያ ነገሠ፤ እሱም 41 ዓመት ገዛ። 24 በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ካደረጋቸው ኃጢአት ሁሉ ዞር አላለም።+ 25 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ የጋትሔፌር+ ነቢይ በሆነው በአሚታይ ልጅ፣ በአገልጋዩ በዮናስ+ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት ከሌቦሃማት*+ አንስቶ እስከ አረባ ባሕር*+ ድረስ ያለውን የእስራኤልን ወሰን አስመለሰ። 26 ይሖዋ በእስራኤል ላይ እየደረሰ ያለውን ከባድ ሥቃይ ተመልክቶ ነበርና።+ በዚያም እስራኤልን ሌላው ቀርቶ ምስኪኑንና ደካማውን የሚረዳ አልነበረም። 27 ሆኖም ይሖዋ የእስራኤልን ስም ከሰማይ በታች ጠራርጎ እንደማያጠፋ ቃል ገብቶ ነበር።+ በመሆኑም በኢዮዓስ ልጅ በኢዮርብዓም አማካኝነት አዳናቸው።+

28 የቀረው የኢዮርብዓም ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉና ኃያልነቱ እንዲሁም እንዴት እንደተዋጋ ብሎም ደማስቆንና ሃማትን+ ለይሁዳና ለእስራኤል እንዴት እንዳስመለሰ+ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? 29 በመጨረሻም ኢዮርብዓም ከአባቶቹ ከእስራኤል ነገሥታት ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ዘካርያስ+ በእሱ ምትክ ነገሠ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ