የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 33
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • ለፈጣሪ የቀረበ ውዳሴ

        • “አዲስ መዝሙር ዘምሩለት” (3)

        • ይሖዋ በቃሉና በመንፈሱ የፈጠራቸው ነገሮች (6)

        • የይሖዋ ሕዝብ ደስተኛ ነው (12)

        • የይሖዋ ዓይኖች በትኩረት ይመለከታሉ (18)

መዝሙር 33:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ፊልጵ 4:4

መዝሙር 33:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 40:3፤ 98:1፤ 149:1፤ ኢሳ 42:10፤ ራእይ 5:9

መዝሙር 33:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 12:6

መዝሙር 33:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 37:23፤ መዝ 11:7፤ 45:7
  • +መዝ 145:16፤ ሥራ 14:17

መዝሙር 33:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እስትንፋስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 11:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 7

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2006፣ ገጽ 20

መዝሙር 33:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:9፤ ኢዮብ 38:8-11፤ ምሳሌ 8:29፤ ኤር 5:22

መዝሙር 33:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት ያሳዩት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 14:7

መዝሙር 33:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 148:4, 5
  • +መዝ 119:90

መዝሙር 33:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምክር።”

  • *

    ወይም “ሐሳብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 8:10፤ 19:3
  • +መዝ 21:8, 11

መዝሙር 33:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምክር ለዘላለም ይጸናል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 19:21፤ ኢሳ 46:10

መዝሙር 33:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 33:29፤ መዝ 65:4፤ 135:4፤ 1ጴጥ 2:9

መዝሙር 33:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 11:4፤ 14:2፤ ምሳሌ 15:3፤ ዕብ 4:13

መዝሙር 33:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 28:9፤ ኢዮብ 34:21፤ ምሳሌ 24:12

መዝሙር 33:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 11:6
  • +2ዜና 32:21፤ መዝ 44:4, 5

መዝሙር 33:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ድል ያጎናጽፈኛል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 7:6, 7፤ መዝ 20:7፤ ምሳሌ 21:31፤ ኢሳ 31:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2006፣ ገጽ 20

    6/1/1991፣ ገጽ 15

መዝሙር 33:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 36:7፤ መዝ 34:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2006፣ ገጽ 20

መዝሙር 33:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳቸውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 33:15, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2006፣ ገጽ 20

መዝሙር 33:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳችን ይሖዋን በተስፋ ትጠባበቃለች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 33:29

መዝሙር 33:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 28:7፤ ምሳሌ 18:10

መዝሙር 33:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 7:7
  • +መዝ 32:10

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 33:1ፊልጵ 4:4
መዝ. 33:3መዝ 40:3፤ 98:1፤ 149:1፤ ኢሳ 42:10፤ ራእይ 5:9
መዝ. 33:4መዝ 12:6
መዝ. 33:5ኢዮብ 37:23፤ መዝ 11:7፤ 45:7
መዝ. 33:5መዝ 145:16፤ ሥራ 14:17
መዝ. 33:6ዕብ 11:3
መዝ. 33:7ዘፍ 1:9፤ ኢዮብ 38:8-11፤ ምሳሌ 8:29፤ ኤር 5:22
መዝ. 33:8ራእይ 14:7
መዝ. 33:9መዝ 148:4, 5
መዝ. 33:9መዝ 119:90
መዝ. 33:10ኢሳ 8:10፤ 19:3
መዝ. 33:10መዝ 21:8, 11
መዝ. 33:11ምሳሌ 19:21፤ ኢሳ 46:10
መዝ. 33:12ዘዳ 33:29፤ መዝ 65:4፤ 135:4፤ 1ጴጥ 2:9
መዝ. 33:13መዝ 11:4፤ 14:2፤ ምሳሌ 15:3፤ ዕብ 4:13
መዝ. 33:151ዜና 28:9፤ ኢዮብ 34:21፤ ምሳሌ 24:12
መዝ. 33:16ኢያሱ 11:6
መዝ. 33:162ዜና 32:21፤ መዝ 44:4, 5
መዝ. 33:172ነገ 7:6, 7፤ መዝ 20:7፤ ምሳሌ 21:31፤ ኢሳ 31:1
መዝ. 33:18ኢዮብ 36:7፤ መዝ 34:15
መዝ. 33:19ኢሳ 33:15, 16
መዝ. 33:20ዘዳ 33:29
መዝ. 33:21መዝ 28:7፤ ምሳሌ 18:10
መዝ. 33:22ሚክ 7:7
መዝ. 33:22መዝ 32:10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 33:1-22

መዝሙር

33 እናንተ ጻድቃን ሆይ፣ ይሖዋ ባደረጋቸው ነገሮች የተነሳ እልል በሉ።+

ቅኖች እሱን ማወደሳቸው የተገባ ነው።

 2 ይሖዋን በበገና አመስግኑት፤

አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩለት።

 3 አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤+

በባለ አውታር መሣሪያ ጥሩ አድርጋችሁ ተጫወቱ፤ እልልም በሉ።

 4 የይሖዋ ቃል ትክክል ነውና፤+

ሥራውም ሁሉ እምነት የሚጣልበት ነው።

 5 ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል።+

ምድር በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ተሞልታለች።+

 6 ሰማያት በይሖዋ ቃል፣

በውስጣቸው ያሉትም ሁሉ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ* ተሠሩ።+

 7 የባሕርን ውኃዎች እንደ ግድብ ያከማቻል፤+

የሚናወጠውንም ውኃ በማከማቻ ቦታ ይሰበስባል።

 8 መላዋ ምድር ይሖዋን ትፍራ።+

የምድር ነዋሪዎች እሱን ይፍሩ።*

 9 እሱ ተናግሯልና፣ ሆኗል፤+

እሱ አዟል፤ ደግሞም ተፈጽሟል።+

10 ይሖዋ የብሔራትን ሴራ* አክሽፏል፤+

የሕዝቦችን ዕቅድ* አጨናግፏል።+

11 ይሁንና የይሖዋ ውሳኔዎች ለዘላለም ይጸናሉ፤*+

የልቡ ሐሳብ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።

12 ይሖዋ አምላኩ የሆነ ብሔር፣

የራሱ ንብረት አድርጎ የመረጠው ሕዝብ ደስተኛ ነው።+

13 ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤

የሰው ልጆችን ሁሉ ያያል።+

14 ከመኖሪያ ቦታው ሆኖ

በምድር የሚኖሩትን በትኩረት ይመለከታል።

15 የሁሉንም ልብ የሚሠራው እሱ ነው፤

ሥራቸውን ሁሉ ይመረምራል።+

16 በሠራዊት ብዛት የዳነ ንጉሥ የለም፤+

ኃያል ሰው በታላቅ ኃይሉ አይድንም።+

17 ፈረስ ያድነኛል* ብሎ መታመን ከንቱ ተስፋ ነው፤+

ታላቅ ኃይሉ ለመዳን ዋስትና አይሆንም።

18 እነሆ፣ የይሖዋ ዓይን የሚፈሩትን፣

ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን የሚጠባበቁትን በትኩረት ይመለከታል፤+

19 ይህም እነሱን* ከሞት ለመታደግ፣

በረሃብ ወቅትም እነሱን በሕይወት ለማኖር ነው።+

20 ይሖዋን በተስፋ እንጠባበቃለን።*

እሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው።+

21 ልባችን በእሱ ሐሴት ያደርጋል፤

በቅዱስ ስሙ እንታመናለንና።+

22 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን ስንጠባበቅ፣+

ታማኝ ፍቅርህ በእኛ ላይ ይሁን።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ