የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • ሐዘንን ለመግለጽ ተብለው የሚደረጉ ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች (1, 2)

      • ንጹሕ የሆነና ንጹሕ ያልሆነ ምግብ (3-21)

      • አንድ አሥረኛውን ለይሖዋ መስጠት (22-29)

ዘዳግም 14:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በዓይኖቻችሁ መካከል ያለውን ቦታ።” ግንባርን ሊጨምር ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:28
  • +ዘሌ 21:1, 5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2021፣ ገጽ 3

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2004፣ ገጽ 27

ዘዳግም 14:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ውድ ሀብቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:2፤ 20:26፤ ዘዳ 28:9፤ 1ጴጥ 1:15
  • +ዘፀ 19:5, 6፤ ዘዳ 7:6

ዘዳግም 14:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:43፤ 20:25፤ ሥራ 10:14

ዘዳግም 14:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:2, 3

ዘዳግም 14:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:4-8

ዘዳግም 14:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:9, 10

ዘዳግም 14:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:13-20

ዘዳግም 14:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳት።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2021፣ ገጽ 2-3

ዘዳግም 14:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በደጆችህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:31፤ ዘሌ 17:15
  • +ዘፀ 23:19፤ 34:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/2005፣ ገጽ 27

    9/15/2004፣ ገጽ 26

ዘዳግም 14:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አሥራት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:11፤ 26:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 2

ዘዳግም 14:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 111:10
  • +ዘዳ 12:5, 17፤ 15:19, 20

ዘዳግም 14:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:5, 6

ዘዳግም 14:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህ የምትሻውን።”

  • *

    ወይም “ነፍስህ የምትጠይቅህን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:7፤ 26:11፤ መዝ 100:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2010፣ ገጽ 23

ዘዳግም 14:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:21፤ 2ዜና 31:4፤ 1ቆሮ 9:13
  • +ዘኁ 18:20፤ ዘዳ 10:9

ዘዳግም 14:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 26:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 2

ዘዳግም 14:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወላጅ አልባ የሆኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:10፤ መዝ 41:1፤ ምሳሌ 11:24፤ 19:17፤ ሚል 3:10፤ ሉቃስ 6:35
  • +ዘፀ 22:21፤ ዘዳ 10:18፤ ያዕ 1:27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 2

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 14:1ዘሌ 19:28
ዘዳ. 14:1ዘሌ 21:1, 5
ዘዳ. 14:2ዘሌ 19:2፤ 20:26፤ ዘዳ 28:9፤ 1ጴጥ 1:15
ዘዳ. 14:2ዘፀ 19:5, 6፤ ዘዳ 7:6
ዘዳ. 14:3ዘሌ 11:43፤ 20:25፤ ሥራ 10:14
ዘዳ. 14:4ዘሌ 11:2, 3
ዘዳ. 14:7ዘሌ 11:4-8
ዘዳ. 14:9ዘሌ 11:9, 10
ዘዳ. 14:12ዘሌ 11:13-20
ዘዳ. 14:21ዘፀ 22:31፤ ዘሌ 17:15
ዘዳ. 14:21ዘፀ 23:19፤ 34:26
ዘዳ. 14:22ዘዳ 12:11፤ 26:12
ዘዳ. 14:23መዝ 111:10
ዘዳ. 14:23ዘዳ 12:5, 17፤ 15:19, 20
ዘዳ. 14:24ዘዳ 12:5, 6
ዘዳ. 14:26ዘዳ 12:7፤ 26:11፤ መዝ 100:2
ዘዳ. 14:27ዘኁ 18:21፤ 2ዜና 31:4፤ 1ቆሮ 9:13
ዘዳ. 14:27ዘኁ 18:20፤ ዘዳ 10:9
ዘዳ. 14:28ዘዳ 26:12
ዘዳ. 14:29ዘዳ 15:10፤ መዝ 41:1፤ ምሳሌ 11:24፤ 19:17፤ ሚል 3:10፤ ሉቃስ 6:35
ዘዳ. 14:29ዘፀ 22:21፤ ዘዳ 10:18፤ ያዕ 1:27
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 14:1-29

ዘዳግም

14 “እናንተ የአምላካችሁ የይሖዋ ልጆች ናችሁ። ለሞተ ሰው ብላችሁ ሰውነታችሁን አትተልትሉ፤+ ቅንድባችሁንም* አትላጩ።+ 2 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤+ ይሖዋም በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+

3 “ማንኛውንም አስጸያፊ ነገር አትብላ።+ 4 የምትበሏቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው፦+ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ 5 ርኤም፣ የሜዳ ፍየል፣ ድኩላ፣ የዱር ፍየል፣ አጋዘን፣ የዱር በግ እና የተራራ በግ። 6 ለሁለት የተከፈለ የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውን እንዲሁም የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ። 7 ሆኖም ከሚያመሰኩት ወይም የተሰነጠቀ ሰኮና ካላቸው እንስሳት መካከል እነዚህን አትብሉ፦ ግመል፣ ጥንቸልና ሽኮኮ፤ ምክንያቱም እነዚህ እንስሳት ቢያመሰኩም ሰኮናቸው ስንጥቅ አይደለም። እነሱ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+ 8 አሳማም እንደዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ሰኮናው ስንጥቅ ቢሆንም አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። ሥጋቸውን መብላትም ሆነ በድናቸውን መንካት የለባችሁም።

9 “በውኃ ውስጥ ከሚኖሩ መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ መብላት ትችላላችሁ።+ 10 ሆኖም ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ማንኛውንም ነገር አትብሉ። ለእናንተ ርኩስ ነው።

11 “ንጹሕ የሆነውን ወፍ ሁሉ መብላት ትችላላችሁ። 12 እነዚህን ግን አትብሉ፦ ንስር፣ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣+ 13 ቀይ ጭልፊትም ሆነ ጥቁር ጭልፊት እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት ሌሎች ጭልፊቶች፣ 14 ማንኛውንም ዓይነት ቁራ፣ 15 ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ ወፍ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሲላ፣ 16 ትንሿ ጉጉት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ ዝይ፣ 17 ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ ለማሚት፣ 18 ራዛ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅላቴና የሌሊት ወፍ። 19 በተጨማሪም ክንፍ ያላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት* በሙሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። መበላት የለባቸውም። 20 ንጹሕ የሆነን ማንኛውንም የሚበር ፍጥረት መብላት ትችላላችሁ።

21 “ሞቶ የተገኘን ማንኛውንም እንስሳ አትብሉ።+ ከዚህ ይልቅ በከተሞችህ* ውስጥ ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ልትሰጠውና እሱ ሊበላው ይችላል፤ አሊያም ለባዕድ አገር ሰው ሊሸጥ ይችላል። ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ።

“የፍየልን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።+

22 “በየዓመቱ ከእርሻህ ላይ ከምታገኘው ምርት ሁሉ አንድ አሥረኛውን* መስጠት አለብህ።+ 23 ዘወትር አምላክህን ይሖዋን መፍራትን+ እንድትማር የእህልህን፣ የአዲስ የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አንድ አሥረኛ እንዲሁም የከብትህንና የመንጋህን በኩራት በአምላክህ በይሖዋ ፊት ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ ብላ።+

24 “ሆኖም አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን የሚመርጠው ስፍራ+ አንተ ካለህበት ቦታ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ መንገዱ በጣም ቢረዝምብህና (አምላክህ ይሖዋ ስለባረከህ) እዚያ ድረስ ተሸክመኸው መሄድ ባትችል 25 ወደ ገንዘብ ልትቀይረው ትችላለህ፤ ገንዘቡንም ይዘህ አምላክህ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ። 26 ከዚያም በገንዘቡ የምትሻውን* ነገር ይኸውም ከብት፣ በግ፣ ፍየል፣ የወይን ጠጅ፣ ሌላ የሚያሰክር መጠጥና የሚያስደስትህን* ማንኛውንም ነገር መግዛት ትችላለህ፤ አንተና ቤተሰብህም በአምላክህ በይሖዋ ፊት በዚያ ብሉ፤ ተደሰቱም።+ 27 በከተሞችህ ውስጥ የሚኖረውን ሌዋዊ ችላ አትበለው፤+ ምክንያቱም እሱ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ አልተሰጠውም።+

28 “በየሦስት ዓመቱ መጨረሻ ላይ በዚያ ዓመት ያገኘኸውን ምርት አንድ አሥረኛ በሙሉ አምጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች።+ 29 አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ ያልተሰጠው ሌዋዊ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች፣ አባት የሌላቸው* ልጆችና መበለቶች መጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ይብሉ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ