የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 69
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • ጥበቃ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

        • “ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት በልቶኛል” (9)

        • “በፍጥነት መልስልኝ” (17)

        • “ኮምጣጤ እንድጠጣ ሰጡኝ” (21)

መዝሙር 69:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን ሊያሰምጣት ስለደረሰ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 144:7፤ ሰቆ 3:54፤ ዮናስ 2:5

መዝሙር 69:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 40:2
  • +መዝ 32:6፤ ዮናስ 2:3

መዝሙር 69:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:2
  • +መዝ 119:82, 123፤ ኢሳ 38:14

መዝሙር 69:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 23:22፤ ዮሐ 15:24, 25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 146

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2011፣ ገጽ 11

    6/1/2006፣ ገጽ 11

መዝሙር 69:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:6፤ ኤር 15:15
  • +ኢሳ 50:6፤ ማቴ 26:67፤ 27:29

መዝሙር 69:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 19:13፤ መዝ 31:11፤ ዮሐ 1:11፤ 7:5

መዝሙር 69:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 19:10፤ መዝ 119:139፤ ማቴ 21:12, 13፤ ማር 11:15-17፤ ዮሐ 2:13-17
  • +ሮም 15:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 146

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2010፣ ገጽ 8-9

መዝሙር 69:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን።”

  • *

    “ባለቀስኩና በጾምኩ ጊዜ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

መዝሙር 69:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “መተረቻ።”

መዝሙር 69:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 49:8፤ ዕብ 5:7
  • +መዝ 68:20

መዝሙር 69:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 144:7

መዝሙር 69:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 69:2
  • +መዝ 16:10

መዝሙር 69:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 63:3፤ 109:21
  • +መዝ 25:16

መዝሙር 69:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 27:9፤ 102:2
  • +መዝ 31:9፤ 40:13

መዝሙር 69:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወደ ነፍሴ ቀርበህ ተቤዣት።”

መዝሙር 69:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:6

መዝሙር 69:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ተስፋዬም ተሟጠጠ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 142:4
  • +ኢዮብ 19:14

መዝሙር 69:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መርዛማ ተክል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 27:34፤ ማር 15:23
  • +ማቴ 27:48፤ ማር 15:36፤ ሉቃስ 23:36፤ ዮሐ 19:29

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 146

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2011፣ ገጽ 15

መዝሙር 69:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወጥመድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 11:9, 10

መዝሙር 69:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዳሌያቸውም።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2006፣ ገጽ 10

መዝሙር 69:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 21:9

መዝሙር 69:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በግንብ የታጠረው ሰፈራቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 1:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 16፣ ገጽ 15

መዝሙር 69:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከሕይወት መጽሐፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:33
  • +ፊልጵ 4:3፤ ራእይ 3:5፤ 13:8

መዝሙር 69:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 109:22

መዝሙር 69:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 50:13-15፤ ሆሴዕ 14:2

መዝሙር 69:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 10:17፤ 102:17፤ ኢሳ 66:2
  • +መዝ 146:7፤ ኢሳ 61:1፤ ሉቃስ 4:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2008፣ ገጽ 12

    4/15/1997፣ ገጽ 4-5

መዝሙር 69:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 96:11፤ ኢሳ 49:13

መዝሙር 69:35

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ ቃል ምድሪቱን እንደሚወርሱ ያሳያል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 51:18

መዝሙር 69:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 61:9፤ 66:22
  • +መዝ 91:14፤ ያዕ 1:12

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 69:1መዝ 144:7፤ ሰቆ 3:54፤ ዮናስ 2:5
መዝ. 69:2መዝ 40:2
መዝ. 69:2መዝ 32:6፤ ዮናስ 2:3
መዝ. 69:3መዝ 22:2
መዝ. 69:3መዝ 119:82, 123፤ ኢሳ 38:14
መዝ. 69:4ሉቃስ 23:22፤ ዮሐ 15:24, 25
መዝ. 69:7መዝ 22:6፤ ኤር 15:15
መዝ. 69:7ኢሳ 50:6፤ ማቴ 26:67፤ 27:29
መዝ. 69:8ኢዮብ 19:13፤ መዝ 31:11፤ ዮሐ 1:11፤ 7:5
መዝ. 69:91ነገ 19:10፤ መዝ 119:139፤ ማቴ 21:12, 13፤ ማር 11:15-17፤ ዮሐ 2:13-17
መዝ. 69:9ሮም 15:3
መዝ. 69:13ኢሳ 49:8፤ ዕብ 5:7
መዝ. 69:13መዝ 68:20
መዝ. 69:14መዝ 144:7
መዝ. 69:15መዝ 69:2
መዝ. 69:15መዝ 16:10
መዝ. 69:16መዝ 63:3፤ 109:21
መዝ. 69:16መዝ 25:16
መዝ. 69:17መዝ 27:9፤ 102:2
መዝ. 69:17መዝ 31:9፤ 40:13
መዝ. 69:19መዝ 22:6
መዝ. 69:20መዝ 142:4
መዝ. 69:20ኢዮብ 19:14
መዝ. 69:21ማቴ 27:34፤ ማር 15:23
መዝ. 69:21ማቴ 27:48፤ ማር 15:36፤ ሉቃስ 23:36፤ ዮሐ 19:29
መዝ. 69:22ሮም 11:9, 10
መዝ. 69:24መዝ 21:9
መዝ. 69:25ሥራ 1:20
መዝ. 69:28ዘፀ 32:33
መዝ. 69:28ፊልጵ 4:3፤ ራእይ 3:5፤ 13:8
መዝ. 69:29መዝ 109:22
መዝ. 69:31መዝ 50:13-15፤ ሆሴዕ 14:2
መዝ. 69:33መዝ 10:17፤ 102:17፤ ኢሳ 66:2
መዝ. 69:33መዝ 146:7፤ ኢሳ 61:1፤ ሉቃስ 4:18
መዝ. 69:34መዝ 96:11፤ ኢሳ 49:13
መዝ. 69:35መዝ 51:18
መዝ. 69:36ኢሳ 61:9፤ 66:22
መዝ. 69:36መዝ 91:14፤ ያዕ 1:12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 69:1-36

መዝሙር

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። የዳዊት መዝሙር።

69 አምላክ ሆይ፣ ውኃ ሕይወቴን አደጋ ላይ ስለጣላት* አድነኝ።+

 2 መቆሚያ ስፍራ በሌለበት ጥልቅ ማጥ ውስጥ ሰምጫለሁ።+

ጥልቅ ውኃዎች ውስጥ ገባሁ፤

ኃይለኛ ጅረትም ጠርጎ ወሰደኝ።+

 3 ከመጮኼ ብዛት የተነሳ ደከምኩ፤+

ድምፄም ጎረነነ።

አምላኬን በመጠባበቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ።+

 4 ያለምክንያት የሚጠሉኝ+

ከራሴ ፀጉር ይልቅ በዙ።

ሊያጠፉኝ የሚፈልጉ፣

ተንኮለኛ የሆኑ ጠላቶቼ እጅግ በዝተዋል።

ያልሰረቅኩትን ነገር እንድመልስ ተገደድኩ።

 5 አምላክ ሆይ፣ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤

ጥፋቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

 6 ሉዓላዊ ጌታ የሆንከው የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣

አንተን ተስፋ የሚያደርጉ በእኔ የተነሳ አይፈሩ።

የእስራኤል አምላክ ሆይ፣

አንተን የሚሹ በእኔ የተነሳ አይዋረዱ።

 7 በአንተ የተነሳ ነቀፋ ይደርስብኛል፤+

ኀፍረት ፊቴን ይሸፍነዋል።+

 8 ለወንድሞቼ እንደ እንግዳ፣

ለእናቴ ልጆች እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆንኩ።+

 9 ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት በልቶኛል፤+

ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋም በእኔ ላይ ደረሰ።+

10 በጾም ራሴን* ባዋረድኩ ጊዜ፣*

ነቀፋ ደረሰብኝ።

11 ማቅ በለበስኩ ጊዜ፣

መቀለጃ* አደረጉኝ።

12 በከተማዋ መግቢያ የሚቀመጡት የመወያያ ርዕስ አደረጉኝ፤

ሰካራሞችም ስለ እኔ ይዘፍናሉ።

13 ይሁንና ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴ ተሰሚነት ሊያገኝ በሚችልበት ጊዜ

ወደ አንተ ይድረስ።+

አምላክ ሆይ፣ በታማኝ ፍቅርህ ብዛት፣

አስተማማኝ በሆነው የማዳን ሥራህም መልስልኝ።+

14 ከማጡ አውጣኝ፤

እንድሰምጥ አትፍቀድ።

ከሚጠሉኝ ሰዎችና

ከጥልቁ ውኃ ታደገኝ።+

15 ደራሽ ውኃ ጠርጎ እንዲወስደኝ አትፍቀድ፤+

ጥልቁም አይዋጠኝ፤

የጉድጓዱም አፍ በእኔ ላይ አይዘጋ።+

16 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ መልስልኝ።+

እንደ ምሕረትህ ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፤+

17 ፊትህንም ከአገልጋይህ አትሰውር።+

ጭንቅ ውስጥ ነኝና በፍጥነት መልስልኝ።+

18 ወደ እኔ ቀርበህ ታደገኝ፤*

ከጠላቶቼ የተነሳ ዋጀኝ።

19 የደረሰብኝን ነቀፋ፣ ኀፍረትና ውርደት ታውቃለህ።+

ጠላቶቼን በሙሉ ታያለህ።

20 የተሰነዘረብኝ ነቀፋ ልቤን ሰብሮታል፤ ቁስሉም የሚድን ዓይነት አይደለም።*

የሚያዝንልኝ ሰው ለማግኘት ተመኝቼ ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አልነበረም፤+

የሚያጽናናኝ ሰውም ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አላገኘሁም።+

21 ይልቁንም መርዝ* እንድበላ ሰጡኝ፤+

በጠማኝ ጊዜም ኮምጣጤ እንድጠጣ ሰጡኝ።+

22 ማዕዳቸው ወጥመድ፣

ብልጽግናቸውም አሽክላ* ይሁንባቸው።+

23 ዓይኖቻቸው ማየት እንዳይችሉ ይጨልሙ፤

ሰውነታቸውም* ምንጊዜም እንዲንቀጠቀጥ አድርግ።

24 ቁጣህን አውርድባቸው፤

የሚነደው ቁጣህም ድንገት ይምጣባቸው።+

25 ሰፈራቸው* ወና ይሁን፤

በድንኳኖቻቸው የሚኖር ሰው አይገኝ።+

26 አንተ የመታኸውን አሳደዋልና፤

ደግሞም አንተ ያቆሰልካቸውን ሰዎች ሥቃይ ሁልጊዜ ያወራሉ።

27 በበደላቸው ላይ በደል ጨምርባቸው፤

ከአንተም ጽድቅ ምንም ድርሻ አይኑራቸው።

28 ከሕያዋን መጽሐፍ* ይደምሰሱ፤+

በጻድቃንም መካከል አይመዝገቡ።+

29 እኔ ግን በጭንቅና በሥቃይ ላይ ነኝ።+

አምላክ ሆይ፣ የማዳን ኃይልህ ይጠብቀኝ።

30 ለአምላክ ስም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤

እሱንም በምስጋና ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።

31 ይህ ከበሬ ይበልጥ ይሖዋን ያስደስተዋል፤

ቀንድና ሰኮና ካለው ወይፈን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል።+

32 የዋሆች ይህን ያያሉ፤ ሐሴትም ያደርጋሉ።

እናንተ አምላክን የምትፈልጉ፣ ልባችሁ ይነቃቃ።

33 ይሖዋ ድሆችን ይሰማልና፤+

በምርኮ ላይ ያለውን ሕዝቡንም አይንቅም።+

34 ሰማይና ምድር፣

ባሕርና በውስጡ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያወድሱት።+

35 አምላክ ጽዮንን ያድናታልና፤+

የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይገነባል፤

እነሱም በዚያ ይኖራሉ፤ ደግሞም ይወርሷታል።*

36 የአገልጋዮቹ ዘሮች ይወርሷታል፤+

ስሙን የሚወዱም+ በእሷ ላይ ይኖራሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ