የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 40
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • ተወዳዳሪ ለማይገኝለት አምላክ የቀረበ ምስጋና

        • የአምላክን ሥራዎች ዘርዝረን መጨረስ አንችልም (5)

        • “መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም” (6)

        • “ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል” (8)

መዝሙር 40:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይሖዋን በትዕግሥት ጠበቅኩት።”

  • *

    ወይም “ለመስማት አጎነበሰ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 34:15

መዝሙር 40:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በአክብሮታዊ ፍርሃት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 33:3፤ 98:1

መዝሙር 40:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ውሸታም።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2006፣ ገጽ 13-14

መዝሙር 40:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 15:3
  • +ዘፀ 15:11
  • +መዝ 139:17, 18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 47

መዝሙር 40:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በመሥዋዕትና በመባ ደስ አልተሰኘህም።”

  • *

    አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ጥንታዊ ጽሑፎች “መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤ ከዚህ ይልቅ አካል አዘጋጀህልኝ” ይላሉ። ከዕብ 10:5 ጋር አወዳድር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 15:22፤ መዝ 51:16, 17፤ ሆሴዕ 6:6
  • +ኢሳ 50:5
  • +ዕብ 10:5-9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/1996፣ ገጽ 14

መዝሙር 40:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 24:44

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/1996፣ ገጽ 14

መዝሙር 40:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እሻለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 4:34
  • +መዝ 37:31፤ ሮም 7:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    11/2017፣ ገጽ 13

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2012፣ ገጽ 6-7

    7/1/1996፣ ገጽ 14

    3/1/1994፣ ገጽ 30

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 14፣ ገጽ 18

መዝሙር 40:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:22
  • +ዕብ 13:15

መዝሙር 40:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 2:12

መዝሙር 40:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 61:6, 7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2005፣ ገጽ 9, 11

መዝሙር 40:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 71:20
  • +መዝ 38:4

መዝሙር 40:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 25:17
  • +መዝ 38:22፤ 70:1-5

መዝሙር 40:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን።”

መዝሙር 40:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:29
  • +መዝ 13:5
  • +መዝ 35:27

መዝሙር 40:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 54:4፤ ኢሳ 50:7፤ ዕብ 13:6
  • +መዝ 143:7

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 40:1መዝ 34:15
መዝ. 40:3መዝ 33:3፤ 98:1
መዝ. 40:5ራእይ 15:3
መዝ. 40:5ዘፀ 15:11
መዝ. 40:5መዝ 139:17, 18
መዝ. 40:61ሳሙ 15:22፤ መዝ 51:16, 17፤ ሆሴዕ 6:6
መዝ. 40:6ኢሳ 50:5
መዝ. 40:6ዕብ 10:5-9
መዝ. 40:7ሉቃስ 24:44
መዝ. 40:8ዮሐ 4:34
መዝ. 40:8መዝ 37:31፤ ሮም 7:22
መዝ. 40:9መዝ 22:22
መዝ. 40:9ዕብ 13:15
መዝ. 40:10ዕብ 2:12
መዝ. 40:11መዝ 61:6, 7
መዝ. 40:12መዝ 71:20
መዝ. 40:12መዝ 38:4
መዝ. 40:13መዝ 25:17
መዝ. 40:13መዝ 38:22፤ 70:1-5
መዝ. 40:16ዘዳ 4:29
መዝ. 40:16መዝ 13:5
መዝ. 40:16መዝ 35:27
መዝ. 40:17መዝ 54:4፤ ኢሳ 50:7፤ ዕብ 13:6
መዝ. 40:17መዝ 143:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 40:1-17

መዝሙር

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።

40 ተስፋዬን ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ ጣልኩ፤*

እሱም ጆሮውን ወደ እኔ አዘነበለ፤* ለእርዳታ ያሰማሁትንም ጩኸት ሰማ።+

 2 የሚያስገመግም ድምፅ ካለበት ጉድጓድ፣

ከሚያዘቅጥ ማጥም አወጣኝ።

እግሮቼንም በዓለት ላይ አቆመ፤

አረማመዴንም አጸና።

 3 ከዚያም በአፌ ላይ አዲስ መዝሙር፣+

ለአምላካችን የሚቀርብ ውዳሴ አኖረ።

ብዙዎች በፍርሃት* ተውጠው ይመለከታሉ፤

በይሖዋም ይታመናሉ።

 4 በይሖዋ የሚታመን፣ እንቢተኛ ወደሆኑት ወይም

ሐሰት* ወደሆኑት ፊቱን ያላዞረ ሰው ደስተኛ ነው።

 5 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣

ያደረግካቸው ድንቅ ሥራዎች፣

ለእኛ ያሰብካቸው ነገሮችም ብዙ ናቸው።+

ከአንተ ጋር ሊወዳደር የሚችል ማንም የለም፤+

ስለ እነዚህ ነገሮች ላውራ፣ ልናገር ብል፣

ዘርዝሬ ልጨርሳቸው አልችልም!+

 6 መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤*+

ከዚህ ይልቅ እንድሰማ ጆሮዎቼን ከፈትክልኝ።*+

የሚቃጠል መባና የኃጢአት መባ እንዲቀርብልህ አልጠየቅክም።+

 7 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ መጥቻለሁ።

ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል ተጽፏል።+

 8 አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል፤*+

ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።+

 9 በታላቅ ጉባኤ መካከል የጽድቅን ምሥራች አውጃለሁ።+

ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው፣

እነሆ፣ ከንፈሮቼን አልከለክልም።+

10 ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሸሽግም።

ታማኝነትህንና ማዳንህን አውጃለሁ።

በታላቅ ጉባኤ መካከል ታማኝ ፍቅርህንና እውነትህን አልደብቅም።”+

11 ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህን አትንፈገኝ።

ታማኝ ፍቅርህና እውነትህ ምንጊዜም ይጠብቁኝ።+

12 ለመቁጠር እንኳ የሚያታክት መከራ ከቦኛል።+

የፈጸምኳቸው በርካታ ስህተቶች ስለዋጡኝ መንገዴን ማየት ተስኖኛል፤+

በራሴ ላይ ካሉት ፀጉሮች እጅግ ይበዛሉ፤

ደግሞም ተስፋ ቆረጥኩ።

13 ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለማዳን እባክህ ፈቃደኛ ሁን።+

ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+

14 ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚሹ ሁሉ፣

ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።

በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙ

አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።

15 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉኝ

በሚደርስባቸው ኀፍረት የተነሳ ክው ይበሉ።

16 አንተን የሚፈልጉ+ ግን

በአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+

የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣

ምንጊዜም “ይሖዋ ታላቅ ይሁን” ይበሉ።+

17 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤

ይሖዋ ትኩረት ይስጠኝ።

አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+

አምላኬ ሆይ፣ አትዘግይ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ