የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 21
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሥራ የመጽሐፉ ይዘት

      • ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዙ (1-14)

      • ኢየሩሳሌም ደረሱ (15-19)

      • ጳውሎስ ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ተግባራዊ አደረገ (20-26)

      • በቤተ መቅደሱ ረብሻ ተቀሰቀሰ፤ ጳውሎስ ተያዘ (27-36)

      • ጳውሎስ ለሕዝቡ ንግግር እንዲያቀርብ ተፈቀደለት (37-40)

የሐዋርያት ሥራ 21:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 173-174

የሐዋርያት ሥራ 21:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 173-174

የሐዋርያት ሥራ 21:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 173-174

የሐዋርያት ሥራ 21:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 21:10-12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 175

የሐዋርያት ሥራ 21:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 176

የሐዋርያት ሥራ 21:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 6:3, 5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 176-177

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/1999፣ ገጽ 25

የሐዋርያት ሥራ 21:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ድንግል የሆኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዩ 2:28፤ ሥራ 2:17፤ 1ቆሮ 11:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 176-177

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/1999፣ ገጽ 25

የሐዋርያት ሥራ 21:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 11:27, 28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 177

የሐዋርያት ሥራ 21:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 20:22, 23፤ 21:33
  • +ሥራ 9:15, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 177-178, 189

የሐዋርያት ሥራ 21:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 177-178

የሐዋርያት ሥራ 21:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 20:24፤ 2ቆሮ 4:10, 11፤ 2ጢሞ 4:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 177-178

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2008፣ ገጽ 32

የሐዋርያት ሥራ 21:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

  • *

    ወይም “መቃወማችንን አቆምን።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 178

የሐዋርያት ሥራ 21:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 12:17፤ 15:13፤ ገላ 1:19፤ 2:9፤ ያዕ 1:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 112, 181

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/1997፣ ገጽ 16-17

የሐዋርያት ሥራ 21:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 181-182

የሐዋርያት ሥራ 21:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 15:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 182-183

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2003፣ ገጽ 23-24

    10/15/2002፣ ገጽ 30

የሐዋርያት ሥራ 21:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 2:28, 29፤ 1ቆሮ 7:18-20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 182, 183-185

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2016፣ ገጽ 15

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2003፣ ገጽ 23-24

የሐዋርያት ሥራ 21:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 184-185

የሐዋርያት ሥራ 21:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 9:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    10/2023፣ ገጽ 10

    መመሥከር፣ ገጽ 184-185

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    10/2018፣ ገጽ 24-25

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2016፣ ገጽ 15

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2003፣ ገጽ 23-24

    6/15/2000፣ ገጽ 14

የሐዋርያት ሥራ 21:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደሙ ሳይፈስ ከተገደለ።”

  • *

    ግሪክኛ፣ ፖርኒያ። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:2፤ ዘፀ 34:15
  • +ዘፍ 9:4፤ ዘሌ 3:17፤ 17:10፤ 1ሳሙ 14:32, 33
  • +ዘሌ 17:13፤ ዘዳ 12:23, 24
  • +ሥራ 15:28, 29፤ 1ቆሮ 6:9፤ ቆላ 3:5፤ 1ተሰ 4:3፤ 1ጴጥ 4:3

የሐዋርያት ሥራ 21:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 9:20

የሐዋርያት ሥራ 21:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 24:5, 6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2001፣ ገጽ 22-23

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 17፣ ገጽ 13

የሐዋርያት ሥራ 21:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 20:4፤ 2ጢሞ 4:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2001፣ ገጽ 22-23

የሐዋርያት ሥራ 21:30

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    3/2020፣ ገጽ 31

የሐዋርያት ሥራ 21:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 20:22, 23፤ 21:10, 11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2001፣ ገጽ 21

የሐዋርያት ሥራ 21:37

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2011፣ ገጽ 5

የሐዋርያት ሥራ 21:38

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/2010፣ ገጽ 15

የሐዋርያት ሥራ 21:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 22:3
  • +ፊልጵ 3:4, 5

የሐዋርያት ሥራ 21:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 26:14

ተዛማጅ ሐሳብ

ሥራ 21:4ሥራ 21:10-12
ሥራ 21:8ሥራ 6:3, 5
ሥራ 21:9ኢዩ 2:28፤ ሥራ 2:17፤ 1ቆሮ 11:5
ሥራ 21:10ሥራ 11:27, 28
ሥራ 21:11ሥራ 20:22, 23፤ 21:33
ሥራ 21:11ሥራ 9:15, 16
ሥራ 21:13ሥራ 20:24፤ 2ቆሮ 4:10, 11፤ 2ጢሞ 4:6
ሥራ 21:18ሥራ 12:17፤ 15:13፤ ገላ 1:19፤ 2:9፤ ያዕ 1:1
ሥራ 21:20ሥራ 15:1
ሥራ 21:21ሮም 2:28, 29፤ 1ቆሮ 7:18-20
ሥራ 21:241ቆሮ 9:20
ሥራ 21:25ዘፍ 35:2፤ ዘፀ 34:15
ሥራ 21:25ዘፍ 9:4፤ ዘሌ 3:17፤ 17:10፤ 1ሳሙ 14:32, 33
ሥራ 21:25ዘሌ 17:13፤ ዘዳ 12:23, 24
ሥራ 21:25ሥራ 15:28, 29፤ 1ቆሮ 6:9፤ ቆላ 3:5፤ 1ተሰ 4:3፤ 1ጴጥ 4:3
ሥራ 21:261ቆሮ 9:20
ሥራ 21:28ሥራ 24:5, 6
ሥራ 21:29ሥራ 20:4፤ 2ጢሞ 4:20
ሥራ 21:33ሥራ 20:22, 23፤ 21:10, 11
ሥራ 21:39ሥራ 22:3
ሥራ 21:39ፊልጵ 3:4, 5
ሥራ 21:40ሥራ 26:14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የሐዋርያት ሥራ 21:1-40

የሐዋርያት ሥራ

21 ከእነሱ በግድ ከተለያየን በኋላ በመርከብ ተሳፍረን በቀጥታ በመጓዝ ቆስ ደረስን፤ በማግስቱ ደግሞ ወደ ሮድስ አመራን፤ ከዚያም ወደ ጳጥራ ሄድን። 2 ወደ ፊንቄ የሚሻገር መርከብ ባገኘን ጊዜ ተሳፍረን ጉዟችንን ቀጠልን። 3 የቆጵሮስ ደሴት በታየችን ጊዜ በስተ ግራ ትተናት ወደ ሶርያ አመራን፤ መርከቡ ጭነቱን በጢሮስ ማራገፍ ስለነበረበት እኛም እዚያ ወረድን። 4 ደቀ መዛሙርቱን ፈልገን ካገኘን በኋላ በዚያ ሰባት ቀን ቆየን። እነሱም በመንፈስ ተመርተው ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ደጋግመው ነገሩት።+ 5 የቆይታ ጊዜያችን ባለቀ ጊዜ ከዚያ ተነስተን ጉዟችንን ጀመርን፤ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ከከተማዋ እስክንወጣ ድረስ ሸኙን። ከዚያም በባሕሩ ዳርቻ ተንበርክከን ጸለይን፤ 6 በኋላም ተሰነባበትን። ከዚያም እኛ ወደ መርከቡ ገባን፤ እነሱ ደግሞ ወደ ቤታቸው ተመለሱ።

7 ከጢሮስ ተነስተን በመርከብ በመጓዝ ጴጤሌማይስ ደረስን፤ እዚያም ለወንድሞች ሰላምታ ካቀረብን በኋላ አብረናቸው አንድ ቀን ቆየን። 8 በማግስቱ ከዚያ ተነስተን ቂሳርያ ደረስን፤ በዚያም ከሰባቱ ወንዶች አንዱ ወደሆነው ወደ ወንጌላዊው ፊልጶስ+ ቤት ገብተን እሱ ጋ አረፍን። 9 ይህ ሰው ትንቢት የሚናገሩ አራት ያላገቡ* ሴቶች ልጆች ነበሩት።+ 10 ለብዙ ቀናት እዚያ ከተቀመጥን በኋላ አጋቦስ+ የሚባል አንድ ነቢይ ከይሁዳ ወረደ። 11 ወደ እኛም መጥቶ የጳውሎስን ቀበቶ በመውሰድ የራሱን እግርና እጅ ካሰረ በኋላ እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ‘አይሁዳውያን የዚህን ቀበቶ ባለቤት በኢየሩሳሌም እንዲህ አድርገው ያስሩታል፤+ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።’”+ 12 ይህን ስንሰማ እኛም ሆንን በዚያ የነበሩት ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ እንለምነው ጀመር። 13 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “እያለቀሳችሁ ልቤን ለምን ታባባላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም እንኳ ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ።+ 14 እሱን ለማሳመን ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ “እንግዲህ የይሖዋ* ፈቃድ ይሁን” ብለን ዝም አልን።*

15 ከዚህ በኋላ ለጉዞው ተዘጋጅተን ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ ጀመርን። 16 በቂሳርያ ከሚኖሩት ደቀ መዛሙርት አንዳንዶቹ ወደምናርፍበት ሰው ቤት እኛን ለመውሰድ አብረውን ሄዱ፤ ይህ ሰው ምናሶን የተባለ የቆጵሮስ ሰው ሲሆን ከቀድሞዎቹ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበር። 17 ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን። 18 በማግስቱም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ሄደ፤+ ሽማግሌዎቹም ሁሉ በዚያ ነበሩ። 19 ሰላምታ ካቀረበላቸውም በኋላ፣ እሱ ባከናወነው አገልግሎት አማካኝነት አምላክ በአሕዛብ መካከል የፈጸማቸውን ነገሮች በዝርዝር ይተርክላቸው ጀመር።

20 እነሱም ይህን ከሰሙ በኋላ አምላክን አመሰገኑ፤ እሱን ግን እንዲህ አሉት፦ “ወንድም፣ ከአይሁዳውያን መካከል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማኞች እንዳሉ ታውቃለህ፤ ደግሞም ሁሉም ለሕጉ ቀናተኞች ናቸው።+ 21 እነሱም አንተ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁዳውያን ሁሉ ልጆቻቸውን እንዳይገርዙም ሆነ የቆየውን ልማድ እንዳይከተሉ በመንገር የሙሴን ሕግ እንዲተዉ ስታስተምር እንደቆየህ ስለ አንተ የሚወራውን ወሬ ሰምተዋል።+ 22 እንግዲህ ምን ማድረግ ይሻላል? መምጣትህን እንደሆነ መስማታቸው አይቀርም። 23 ስለዚህ አሁን የምንነግርህን ነገር አድርግ፦ ስእለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ። 24 እነዚህን ሰዎች ይዘህ በመሄድ ከእነሱ ጋር የመንጻት ሥርዓት ፈጽም፤ ራሳቸውንም እንዲላጩ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ክፈልላቸው። ይህን ካደረግክ በአንተ ላይ የተወራው ሁሉ ከንቱ መሆኑንና አንተም ሕጉን እያከበርክ በሥርዓት እንደምትኖር ሁሉም ሰው ያውቃል።+ 25 ከአሕዛብ የመጡትን አማኞች በተመለከተ ግን ለጣዖት ከተሠዋ፣+ ከደም፣+ ታንቆ ከሞተ* እንስሳ ሥጋና+ ከፆታ ብልግና* እንዲርቁ+ ወስነን ደብዳቤ ጽፈንላቸዋል።”

26 ከዚያም ጳውሎስ በማግስቱ ሰዎቹን ይዞ በመሄድ አብሯቸው የመንጻት ሥርዓቱን ፈጸመ፤+ የመንጻት ሥርዓቱ የሚያበቃበትን ቀንና ለእያንዳንዳቸው መባ የሚቀርብበትን ጊዜ ለማሳወቅም ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ።

27 ሰባቱ ቀናት ሊጠናቀቁ በተቃረቡበት ጊዜ ከእስያ የመጡ አይሁዳውያን ጳውሎስን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያዩት ሕዝቡን ሁሉ ለሁከት በማነሳሳት ያዙት፤ 28 እንዲህ እያሉም ጮኹ፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እርዱን! በሄደበት ቦታ ሁሉ ለሚያገኛቸው ሰዎች ሕዝባችንን፣ ሕጋችንንና ይህን ስፍራ የሚቃወም ትምህርት የሚያስተምረው ይህ ሰው ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የግሪክ ሰዎችን ወደ ቤተ መቅደሱ ይዞ በመምጣት ይህን ቅዱስ ስፍራ አርክሷል።”+ 29 ይህን ያሉት ቀደም ሲል የኤፌሶኑን ሰው ጢሮፊሞስን+ ከእሱ ጋር ከተማው ውስጥ አይተውት ስለነበር ነው፤ ደግሞም ጳውሎስ ይህን ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ ይዞት የገባ መስሏቸው ነበር። 30 በመሆኑም ከተማዋ በሙሉ ታወከች፤ ሕዝቡም ግር ብለው እየሮጡ በመምጣት ጳውሎስን ያዙት፤ እየጎተቱም ከቤተ መቅደሱ አወጡት፤ በሮቹም ወዲያው ተዘጉ። 31 ሊገድሉትም እየሞከሩ ሳለ መላዋ ኢየሩሳሌም እንደታወከች የሚገልጽ ወሬ ለሠራዊቱ ሻለቃ ደረሰው፤ 32 እሱም ወዲያውኑ ወታደሮችንና የጦር መኮንኖችን ይዞ እየሮጠ ወደ እነሱ ወረደ። እነሱም ሻለቃውንና ወታደሮቹን ሲያዩ ጳውሎስን መደብደባቸውን ተዉ።

33 በዚህ ጊዜ የሠራዊቱ ሻለቃ ቀርቦ በቁጥጥር ሥር አዋለውና በሁለት ሰንሰለት እንዲታሰር አዘዘ፤+ ከዚያም ማን እንደሆነና ምን እንዳደረገ ጠየቀ። 34 ከሕዝቡም መካከል አንዳንዶች አንድ ነገር ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ነገር ይናገሩ ነበር። ስለዚህ ሻለቃው ከጫጫታው የተነሳ ምንም የተጨበጠ ነገር ማግኘት ስላልቻለ ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲወሰድ አዘዘ። 35 ሆኖም ጳውሎስ ወደ ደረጃው በደረሰ ጊዜ ከሕዝቡ ዓመፅ የተነሳ ወታደሮቹ ተሸክመውት ለመሄድ ተገደዱ፤ 36 ብዙ ሕዝብም እየተከተለ “ግደለው!” እያለ ይጮኽ ነበር።

37 ጳውሎስ ወደ ጦር ሰፈሩ ሊያስገቡት በተቃረቡ ጊዜ ሻለቃውን “አንዴ ላናግርህ?” አለው። ሻለቃውም እንዲህ አለው፦ “ግሪክኛ መናገር ትችላለህ እንዴ? 38 አንተ ከዚህ ቀደም ዓመፅ አነሳስተህ 4,000 ነፍሰ ገዳዮችን ወደ ምድረ በዳ ያሸፈትከው ግብፃዊ አይደለህም?” 39 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “እኔ እንኳ በኪልቅያ የምትገኘው የታወቀችው የጠርሴስ+ ከተማ ነዋሪ የሆንኩ አይሁዳዊ ነኝ።+ ስለዚህ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ” አለ። 40 ከፈቀደለት በኋላ ጳውሎስ ደረጃው ላይ ቆሞ ለሕዝቡ በእጁ ምልክት ሰጠ። ታላቅ ጸጥታ በሰፈነ ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ+ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፦

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ