የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ቆሮንቶስ 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የመተንበይና በልሳን የመናገር ስጦታ (1-25)

      • ሥርዓታማ የሆኑ ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች (26-40)

        • ሴቶች በጉባኤ ውስጥ ያላቸው ቦታ (34, 35)

1 ቆሮንቶስ 14:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቅንዓት የተሞላበት ጥረት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 5:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1993፣ ገጽ 31

1 ቆሮንቶስ 14:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 13:2
  • +1ቆሮ 14:5

1 ቆሮንቶስ 14:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2010፣ ገጽ 24-25

1 ቆሮንቶስ 14:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 12:30
  • +ኢዩ 2:28፤ ሥራ 2:17፤ 21:8, 9

1 ቆሮንቶስ 14:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ገላ 1:11, 12፤ 2:2
  • +1ቆሮ 12:8

1 ቆሮንቶስ 14:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2015፣ ገጽ 21

1 ቆሮንቶስ 14:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2015፣ ገጽ 21

1 ቆሮንቶስ 14:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 12:7፤ 14:4, 26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2007፣ ገጽ 23-24

1 ቆሮንቶስ 14:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 12:8, 10፤ 14:5

1 ቆሮንቶስ 14:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቃል ማስተማር።”

  • *

    ወይም “በማስተዋል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 14:4

1 ቆሮንቶስ 14:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 4:14
  • +ሮም 16:19
  • +ዕብ 5:13, 14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2007፣ ገጽ 11

    7/15/1993፣ ገጽ 20

1 ቆሮንቶስ 14:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 28:11, 12

1 ቆሮንቶስ 14:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 2:4, 13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 150

1 ቆሮንቶስ 14:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 45:14፤ ዘካ 8:23

1 ቆሮንቶስ 14:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 12:8, 10

1 ቆሮንቶስ 14:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 14:5

1 ቆሮንቶስ 14:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 13:1

1 ቆሮንቶስ 14:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 10:24, 25

1 ቆሮንቶስ 14:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 14:40፤ ቆላ 2:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 20

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 120

1 ቆሮንቶስ 14:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 2:11, 12
  • +1ቆሮ 11:3፤ ኤፌ 5:22፤ ቆላ 3:18፤ ቲቶ 2:5፤ 1ጴጥ 3:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2012፣ ገጽ 9

    3/1/2006፣ ገጽ 28-29

    ማመራመር፣ ገጽ 433

1 ቆሮንቶስ 14:36

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2011፣ ገጽ 14

1 ቆሮንቶስ 14:37

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1993፣ ገጽ 31

1 ቆሮንቶስ 14:38

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ይህን የማያውቅ ካለ ያለእውቀት ይኖራል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

1 ቆሮንቶስ 14:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 5:20
  • +1ቆሮ 14:27

1 ቆሮንቶስ 14:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 14:33፤ ቆላ 2:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 54

    ንቁ!፣

    ቁጥር 1 2020፣ ገጽ 10

    ከአምላክ ፍቅር፣ ገጽ 49

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/1997፣ ገጽ 9

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ቆሮ. 14:11ተሰ 5:20
1 ቆሮ. 14:21ቆሮ 13:2
1 ቆሮ. 14:21ቆሮ 14:5
1 ቆሮ. 14:51ቆሮ 12:30
1 ቆሮ. 14:5ኢዩ 2:28፤ ሥራ 2:17፤ 21:8, 9
1 ቆሮ. 14:6ገላ 1:11, 12፤ 2:2
1 ቆሮ. 14:61ቆሮ 12:8
1 ቆሮ. 14:121ቆሮ 12:7፤ 14:4, 26
1 ቆሮ. 14:131ቆሮ 12:8, 10፤ 14:5
1 ቆሮ. 14:191ቆሮ 14:4
1 ቆሮ. 14:20ኤፌ 4:14
1 ቆሮ. 14:20ሮም 16:19
1 ቆሮ. 14:20ዕብ 5:13, 14
1 ቆሮ. 14:21ኢሳ 28:11, 12
1 ቆሮ. 14:22ሥራ 2:4, 13
1 ቆሮ. 14:25ኢሳ 45:14፤ ዘካ 8:23
1 ቆሮ. 14:261ቆሮ 12:8, 10
1 ቆሮ. 14:271ቆሮ 14:5
1 ቆሮ. 14:29ሥራ 13:1
1 ቆሮ. 14:31ዕብ 10:24, 25
1 ቆሮ. 14:331ቆሮ 14:40፤ ቆላ 2:5
1 ቆሮ. 14:341ጢሞ 2:11, 12
1 ቆሮ. 14:341ቆሮ 11:3፤ ኤፌ 5:22፤ ቆላ 3:18፤ ቲቶ 2:5፤ 1ጴጥ 3:1
1 ቆሮ. 14:391ተሰ 5:20
1 ቆሮ. 14:391ቆሮ 14:27
1 ቆሮ. 14:401ቆሮ 14:33፤ ቆላ 2:5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ቆሮንቶስ 14:1-40

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

14 ፍቅርን ተከታተሉ፤ ሆኖም መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይልቁንም ትንቢት የመናገር ስጦታን ለማግኘት ጥረት* አድርጉ።+ 2 በልሳን የሚናገር ለአምላክ እንጂ ለሰው አይናገርምና፤ በመንፈስ አማካኝነት ቅዱስ ሚስጥሮችን ቢናገርም+ እንኳ ማንም አይሰማውም።+ 3 ይሁን እንጂ ትንቢት የሚናገር በንግግሩ ሰዎችን ያንጻል፣ ያበረታታል እንዲሁም ያጽናናል። 4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢት የሚናገር ግን ጉባኤን ያንጻል። 5 ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወድ ነበር፤+ ሆኖም ትንቢት ብትናገሩ እመርጣለሁ።+ ደግሞም ትንቢት የሚናገር በልሳን ከሚናገር ይበልጣል። ምክንያቱም በልሳን የሚናገር የተናገረውን ካልተረጎመው ጉባኤው ሊታነጽ አይችልም። 6 አሁን ግን ወንድሞች፣ ወደ እናንተ መጥቼ ራእይን በመግለጥ+ ወይም በእውቀት+ ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኳችሁ በስተቀር በልሳን ብነግራችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ?

7 እንደ ዋሽንትና በገና ካሉ ድምፅ የሚያወጡ ግዑዝ ነገሮች ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። የሚያወጡት የድምፅ ቃና ግልጽ የሆነ ልዩነት ከሌለው ከዋሽንቱም ሆነ ከበገናው የሚወጣው ዜማ እንዴት ይለያል? 8 ደግሞም መለከት ለመለየት የሚያስቸግር ድምፅ ቢያሰማ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል? 9 ልክ እንደዚሁም ከአንደበታችሁ የሚወጣው ቃል በቀላሉ የሚገባ ካልሆነ ስለ ምን እየተናገራችሁ እንዳለ ማን ሊያውቅ ይችላል? እንዲህ ከሆነ ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ። 10 በዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎች አሉ፤ ሆኖም ትርጉም የሌለው ቋንቋ የለም። 11 አንድ ሰው የሚናገረውን ቋንቋ ትርጉም ካላወቅኩ እኔ ለሚናገረው ሰው የባዕድ አገር ሰው እሆንበታለሁ፤ እሱም ለእኔ የባዕድ አገር ሰው ይሆንብኛል። 12 ስለዚህ እናንተም የመንፈስን ስጦታዎች እጅግ ስለምትፈልጉ ጉባኤውን የሚያንጹ ስጦታዎች በብዛት ለማግኘት ጥረት አድርጉ።+

13 ስለሆነም በልሳን የሚናገር ሰው የሚናገረውን መተርጎም እንዲችል ይጸልይ።+ 14 ምክንያቱም በልሳን የምጸልይ ከሆነ፣ የሚጸልየው የተቀበልኩት የመንፈስ ስጦታ ነው፤ አእምሮዬ ግን ምንም የሚያከናውነው ነገር የለም። 15 ታዲያ ምን ማድረግ ይሻላል? በመንፈስ ስጦታ እጸልያለሁ፤ ሆኖም የምጸልየው ትርጉሙ ገብቶኝ ነው። በመንፈስ ስጦታ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤ ሆኖም የምዘምረው ትርጉሙ ገብቶኝ ነው። 16 እንዲህ ካልሆነ በመንፈስ ስጦታ ውዳሴ ብታቀርብ በመካከልህ ያለው ምንም የማያውቅ ሰው ምን እየተናገርክ እንዳለህ ስለማይገባው ላቀረብከው ምስጋና እንዴት “አሜን” ሊል ይችላል? 17 እርግጥ አንተ ግሩም በሆነ መንገድ ምስጋና ታቀርብ ይሆናል፤ ሌላው ሰው ግን እየታነጸበት አይደለም። 18 ከሁላችሁ የበለጠ በብዙ ልሳኖች ስለምናገር አምላክን አመሰግናለሁ። 19 ይሁንና በጉባኤ ውስጥ አሥር ሺህ ቃላት በልሳን ከምናገር ሌሎችንም ማስተማር* እችል ዘንድ አምስት ቃላት በአእምሮዬ* ብናገር እመርጣለሁ።+

20 ወንድሞች፣ በማስተዋል ችሎታችሁ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤+ ለክፋት ግን ሕፃናት ሁኑ፤+ በማስተዋል ችሎታችሁም የጎለመሳችሁ ሁኑ።+ 21 በሕጉ ላይ “‘በባዕዳን አንደበትና እንግዳ በሆኑ ሰዎች ቋንቋዎች ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ እነሱ ግን በዚያን ጊዜም እንኳ አይሰሙኝም’ ይላል ይሖዋ”* ተብሎ ተጽፏል።+ 22 በመሆኑም ልሳን ለአማኞች ሳይሆን አማኝ ላልሆኑት ምልክት ነው፤+ ትንቢት ግን አማኝ ላልሆኑት ሳይሆን ለአማኞች ነው። 23 ስለዚህ ጉባኤው በሙሉ አንድ ላይ ተሰብስቦ ባለበት ወቅት ሁሉም በልሳኖች ቢናገሩና በዚህ መሃል ምንም የማያውቁ ሰዎች ወይም አማኞች ያልሆኑ ቢገቡ እነዚህ ሰዎች ‘አእምሯችሁን ስታችኋል’ አይሏችሁም? 24 ሆኖም ሁላችሁም ትንቢት እየተናገራችሁ ሳለ አማኝ ያልሆነ ወይም ምንም የማያውቅ ሰው ቢገባ ሁላችሁም የምትናገሩት ቃል እንደ ወቀሳ የሚያገለግለው ከመሆኑም በላይ ራሱን በሚገባ እንዲመረምር ያነሳሳዋል። 25 በዚህ ጊዜ በልቡ የተሰወረው ነገር ይገለጣል፤ በመሆኑም “አምላክ በእርግጥ በመካከላችሁ ነው” እያለ በግንባሩ ተደፍቶ ለአምላክ ይሰግዳል።+

26 እንግዲህ ወንድሞች፣ ምን ማድረግ ይሻላል? አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ አንዱ ይዘምራል፣ ሌላው ያስተምራል፣ ሌላው ራእይን ይገልጣል፣ ሌላው በልሳን ይናገራል፣ ሌላው ደግሞ ይተረጉማል።+ ሁሉም ነገር ለማነጽ ይሁን። 27 በልሳን የሚናገሩ ካሉ ከሁለት ወይም ከሦስት አይብለጡ፤ በየተራም ይናገሩ፤ የሚናገሩትንም ሌላ ሰው ይተርጉም።+ 28 የሚተረጉም ሰው ከሌለ ግን በጉባኤ መካከል ዝም ይበሉና ለራሳቸውና ለአምላክ ይናገሩ። 29 ሁለት ወይም ሦስት ነቢያት+ ይናገሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ ትርጉሙን ለመረዳት ይጣሩ። 30 ሆኖም አንድ ሰው እዚያ ተቀምጦ ሳለ ራእይ ቢገለጥለት የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። 31 ሁሉም እንዲማሩና ሁሉም እንዲበረታቱ ሁላችሁም በየተራ ትንቢት መናገር ትችላላችሁ።+ 32 ነቢያት የመንፈስ ስጦታዎችን በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው ይገባል። 33 አምላክ የሰላም እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና።+

በቅዱሳን ጉባኤዎች ሁሉ እንደሚደረገው 34 ሴቶች በጉባኤ ውስጥ እንዲናገሩ ስላልተፈቀደላቸው ዝም ይበሉ።+ ከዚህ ይልቅ ሕጉም እንደሚለው ይገዙ።+ 35 ያልገባቸው ነገር ካለ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።

36 የአምላክ ቃል የመጣው ከእናንተ ነው? ወይስ የአምላክ ቃል የደረሰው ወደ እናንተ ብቻ ነው?

37 ነቢይ እንደሆነ ወይም የመንፈስ ስጦታ እንዳለው የሚያስብ ሰው ካለ እነዚህ የጻፍኩላችሁ ነገሮች የጌታ ትእዛዛት መሆናቸውን አምኖ ይቀበል። 38 ሆኖም ይህን ችላ የሚል ካለ እሱም ችላ ይባላል።* 39 ስለዚህ ወንድሞቼ፣ ትንቢት ለመናገር ጥረት አድርጉ፤+ ይሁንና በልሳኖች መናገርንም አትከልክሉ።+ 40 ሆኖም ሁሉም ነገር በአግባብና በሥርዓት ይሁን።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ