የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ነህምያ 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ነህምያ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቡ ሕጉን ለመጠበቅ ተስማማ (1-39)

        • “የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም” (39)

ነህምያ 10:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቲርሻታው።” ለአንድ የአውራጃ ገዢ የሚሰጥ የፋርሳውያን የማዕረግ ስም ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:38

ነህምያ 10:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 2:1, 39

ነህምያ 10:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 8:1, 2

ነህምያ 10:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 3:9፤ ነህ 12:8

ነህምያ 10:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 12:24

ነህምያ 10:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 7:6, 11

ነህምያ 10:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ናታኒሞቹ።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎች።”

  • *

    “ለማስተዋል የሚያስችል ዕድሜ ላይ የደረሰ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 8:1፤ 9:2

ነህምያ 10:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:15, 16፤ ዘዳ 7:3, 4

ነህምያ 10:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:10
  • +ዘፀ 12:16፤ ዘኁ 29:1, 12
  • +ዘፀ 23:10, 11፤ ዘሌ 25:4, 5
  • +ዘዳ 15:1-3

ነህምያ 10:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደስ።”

  • *

    አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:13

ነህምያ 10:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ገጸ ኅብስቱን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 28:9
  • +ዘኁ 28:11-13፤ 1ዜና 23:31
  • +ዘሌ 24:5-7
  • +ዘፀ 29:40, 41
  • +ዘዳ 16:16
  • +ዘሌ 16:15

ነህምያ 10:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:7፤ 6:12, 13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2006፣ ገጽ 11

ነህምያ 10:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:19፤ ዘኁ 18:8, 13፤ ዘዳ 26:2

ነህምያ 10:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:2፤ ዘኁ 18:15
  • +ዘኁ 18:8, 11፤ 1ቆሮ 9:13

ነህምያ 10:37

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መመገቢያ አዳራሾች።”

  • *

    ወይም “አሥራቱን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 15:20
  • +ዘሌ 27:30
  • +ዘኁ 18:8, 12፤ ዘዳ 18:1, 4
  • +2ዜና 31:11
  • +ዘኁ 18:21

ነህምያ 10:38

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መመገቢያ አዳራሾች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:26

ነህምያ 10:39

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መመገቢያ አዳራሾቹ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:23
  • +ዘዳ 12:5, 6
  • +ነህ 13:10, 11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1998፣ ገጽ 21-22

ተዛማጅ ሐሳብ

ነህ. 10:1ነህ 9:38
ነህ. 10:5ዕዝራ 2:1, 39
ነህ. 10:6ዕዝራ 8:1, 2
ነህ. 10:9ዕዝራ 3:9፤ ነህ 12:8
ነህ. 10:12ነህ 12:24
ነህ. 10:14ነህ 7:6, 11
ነህ. 10:28ነህ 8:1፤ 9:2
ነህ. 10:30ዘፀ 34:15, 16፤ ዘዳ 7:3, 4
ነህ. 10:31ዘፀ 20:10
ነህ. 10:31ዘፀ 12:16፤ ዘኁ 29:1, 12
ነህ. 10:31ዘፀ 23:10, 11፤ ዘሌ 25:4, 5
ነህ. 10:31ዘዳ 15:1-3
ነህ. 10:32ዘፀ 30:13
ነህ. 10:33ዘኁ 28:9
ነህ. 10:33ዘኁ 28:11-13፤ 1ዜና 23:31
ነህ. 10:33ዘሌ 24:5-7
ነህ. 10:33ዘፀ 29:40, 41
ነህ. 10:33ዘዳ 16:16
ነህ. 10:33ዘሌ 16:15
ነህ. 10:34ዘሌ 1:7፤ 6:12, 13
ነህ. 10:35ዘፀ 23:19፤ ዘኁ 18:8, 13፤ ዘዳ 26:2
ነህ. 10:36ዘፀ 13:2፤ ዘኁ 18:15
ነህ. 10:36ዘኁ 18:8, 11፤ 1ቆሮ 9:13
ነህ. 10:37ዘኁ 15:20
ነህ. 10:37ዘሌ 27:30
ነህ. 10:37ዘኁ 18:8, 12፤ ዘዳ 18:1, 4
ነህ. 10:372ዜና 31:11
ነህ. 10:37ዘኁ 18:21
ነህ. 10:38ዘኁ 18:26
ነህ. 10:39ዘዳ 14:23
ነህ. 10:39ዘዳ 12:5, 6
ነህ. 10:39ነህ 13:10, 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ነህምያ 10:1-39

ነህምያ

10 በስምምነቱ ላይ ማኅተማቸውን በማተም ያጸደቁት+ እነዚህ ናቸው፦

የሃካልያህ ልጅ የሆነው ገዢው* ነህምያ፣

ሴዴቅያስ፣ 2 ሰራያህ፣ አዛርያስ፣ ኤርምያስ፣ 3 ጳስኮር፣ አማርያህ፣ ማልኪያህ፣ 4 ሃጡሽ፣ ሸባንያህ፣ ማሉክ፣ 5 ሃሪም፣+ መሬሞት፣ አብድዩ፣ 6 ዳንኤል፣+ ጊነቶን፣ ባሮክ፣ 7 መሹላም፣ አቢያህ፣ ሚያሚን፣ 8 ማአዝያህ፣ ቢልጋይ እና ሸማያህ፤ ካህናቱ እነዚህ ናቸው።

9 ሌዋውያኑ ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የአዛንያህ ልጅ የሹዋ፣ ከሄናዳድ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው ቢኑይ፣ ቃድሚኤል፣+ 10 እንዲሁም ወንድሞቻቸው የሆኑት ሸባንያህ፣ ሆዲያህ፣ ቀሊጣ፣ ፐላያህ፣ ሃናን፣ 11 ሚካ፣ ሬሆብ፣ ሃሻብያህ፣ 12 ዛኩር፣ ሸረበያህ፣+ ሸባንያህ፣ 13 ሆዲያህ፣ ባኒ እና ቤኒኑ።

14 የሕዝቡ መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ፓሮሽ፣ ፓሃትሞአብ፣+ ኤላም፣ ዛቱ፣ ባኒ፣ 15 ቡኒ፣ አዝጋድ፣ ቤባይ፣ 16 አዶንያስ፣ ቢግዋይ፣ አዲን፣ 17 አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ አዙር፣ 18 ሆዲያህ፣ ሃሹም፣ ቤጻይ፣ 19 ሃሪፍ፣ አናቶት፣ ነባይ፣ 20 ማግፒአሽ፣ መሹላም፣ ሄዚር፣ 21 መሺዛቤል፣ ሳዶቅ፣ ያዱአ፣ 22 ጰላጥያህ፣ ሃናን፣ አናያ፣ 23 ሆሺአ፣ ሃናንያህ፣ ሃሹብ፣ 24 ሃሎሔሽ፣ ፒልሃ፣ ሾቤቅ፣ 25 ረሁም፣ ሃሻብናህ፣ ማአሴያህ፣ 26 አኪያህ፣ ሃናን፣ አናን፣ 27 ማሉክ፣ ሃሪም እና ባአናህ።

28 የቀረው ሕዝብ ማለትም ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ ዘማሪዎቹ፣ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ* እንዲሁም የእውነተኛውን አምላክ ሕግ ለመጠበቅ በምድሪቱ ካሉት ሕዝቦች ራሳቸውን የለዩ ሁሉ+ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ጨምሮ እውቀትና ማስተዋል ያለው* ማንኛውም ሰው 29 ከወንድሞቻቸውና ታዋቂ ከሆኑት ሰዎቻቸው ጋር በመሆን የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ በሆነው በሙሴ እጅ በተሰጠው የእውነተኛው አምላክ ሕግ መሠረት ለመሄድ እንዲሁም የጌታችንን የይሖዋን ትእዛዛት፣ ፍርዶችና ሥርዓቶች ሁሉ በጥንቃቄ ለመጠበቅ በእርግማንና በመሐላ ራሳቸውን ግዴታ ውስጥ አስገቡ። 30 ሴቶች ልጆቻችንን በምድሪቱ ለሚኖሩ ሰዎች አንሰጥም፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም።+

31 በምድሪቱ የሚኖሩት ሕዝቦች በሰንበት ቀን ሸቀጣ ሸቀጦቻቸውንና የተለያዩ ጥራጥሬዎችን ለመሸጥ ቢያመጡ በሰንበት+ ወይም ቅዱስ በሆነ ቀን+ ከእነሱ ላይ ምንም ነገር አንገዛም። በተጨማሪም በሰባተኛው ዓመት+ ምርት ከማምረት እንቆጠባለን፤ ያልተከፈለን ዕዳም ሁሉ እንሰርዛለን።+

32 በተጨማሪም እያንዳንዳችን በአምላካችን ቤት* ለሚከናወነው አገልግሎት በየዓመቱ አንድ ሦስተኛ ሰቅል* ለመስጠት ራሳችንን ግዴታ ውስጥ እናስገባለን፤+ 33 ይህም በሰንበት ቀናትና+ በአዲስ ጨረቃ ወቅት+ ለሚቀርበው የሚነባበር ዳቦ*+ እንዲሁም በእነዚህ ጊዜያት ዘወትር ለሚቀርበው የእህል መባና+ የሚቃጠል መባ፣ በተጨማሪም በተወሰኑ ጊዜያት ለሚከበሩት በዓላት፣+ ቅዱስ ለሆኑት ነገሮች፣ እስራኤልን ለማስተሰረይ ለሚቀርቡት የኃጢአት መባዎችና+ በአምላካችን ቤት ለሚከናወኑ ሥራዎች ሁሉ ይውላል።

34 ከዚህም ሌላ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና ሕዝቡ በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት በየዓመቱ በተወሰነው ጊዜ በአምላካችን በይሖዋ መሠዊያ ላይ እንዲቃጠል በየአባቶቻችን ቤት በየተራ ወደ አምላካችን ቤት ሊያመጡ የሚገባውን እንጨት በተመለከተ ዕጣ ጣልን።+ 35 እንዲሁም መሬታችን የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬና ማንኛውም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፍ የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ ሁሉ በየዓመቱ ወደ ይሖዋ ቤት እናመጣለን፤+ 36 በተጨማሪም በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት ከወንዶች ልጆቻችንና ከእንስሶቻችን በኩሩን+ እንዲሁም ከከብቶቻችንና ከመንጎቻችን በኩሩን እናመጣለን። ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት እናመጣለን።+ 37 ከዚህም በተጨማሪ የተፈጨውን የእህላችንን በኩር፣+ መዋጮዎቻችንን፣ ማንኛውም ዛፍ የሚያፈራውን ፍሬ፣+ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት+ ወደ አምላካችን ቤት ግምጃ ቤቶች*+ ወደ ካህናቱ እናመጣለን፤ እንዲሁም ከእርሻ ከተሞቻችን ሁሉ አንድ አሥረኛውን* የሚቀበሉት ሌዋውያኑ ስለሆኑ የመሬታችንን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ እናመጣለን።+

38 ሌዋውያኑ አንድ አሥረኛውን በሚቀበሉበት ጊዜ ካህኑ የአሮን ልጅ ከሌዋውያኑ ጋር አብሮ መሆን አለበት፤ ሌዋውያኑም የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ወደሚገኙት ክፍሎች* መውሰድ ይኖርባቸዋል።+ 39 ምክንያቱም እስራኤላውያንም ሆኑ የሌዋውያኑ ልጆች የእህሉን፣ የአዲሱን ወይን ጠጅና የዘይቱን+ መዋጮ ማምጣት ያለባቸው ወደ ግምጃ ቤቶቹ* ነው፤+ ደግሞም የመቅደሱ ዕቃዎች የሚቀመጡትም ሆነ የሚያገለግሉት ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና ዘማሪዎቹ የሚገኙት በዚያ ነው። እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ