አንደኛ ሳሙኤል
31 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ ነበር።+ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦአ+ ተራራ ላይ ተገደሉ። 2 ፍልስጤማውያንም ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን እግር በእግር ተከታተሏቸው፤ ፍልስጤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንን፣+ አቢናዳብንና ሜልኪሳን መትተው ገደሏቸው።+ 3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታ፤ ቀስተኞቹም አገኙት፤ እነሱም ክፉኛ አቆሰሉት።+ 4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ ያልተገረዙ+ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝና በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ* ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም። በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ።+ 5 ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ+ እሱም በራሱ ሰይፍ ላይ ወድቆ ከእሱ ጋር ሞተ። 6 ስለዚህ ሳኦል፣ ሦስቱ ወንዶች ልጆቹ፣ ጋሻ ጃግሬውና የእሱ ሰዎች በሙሉ በዚያ ቀን አብረው ሞቱ።+ 7 በሸለቆውና* በዮርዳኖስ አካባቢ የነበሩት እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን እንዲሁም ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቹን ጥለው ሸሹ፤+ ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው ከተሞቹን ያዙ።
8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ሦስቱን ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ+ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው። 9 ስለሆነም የሳኦልን ራስ ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከገፈፉ በኋላ ወሬው በጣዖቶቻቸው+ ቤቶችና* በሕዝቡ ሁሉ መካከል እንዲሰራጭ+ ለማድረግ በመላው የፍልስጤም ምድር መልእክት ላኩ። 10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአስታሮት ምስሎች ቤት አስቀመጡት፣ አስከሬኑን ደግሞ በቤትሻን+ ግንብ ላይ ቸነከሩት። 11 የኢያቢስጊልያድ+ ነዋሪዎችም ፍልስጤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን ሲሰሙ 12 ተዋጊዎቹ ሁሉ ተነስተው ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዙ አደሩ፤ ከዚያም የሳኦልንና የልጆቹን አስከሬን ከቤትሻን ግንብ ላይ አወረዱ። ወደ ኢያቢስ ተመልሰውም በዚያ አቃጠሏቸው። 13 ከዚያም አፅማቸውን+ ወስደው በኢያቢስ+ በሚገኝ የታማሪስክ ዛፍ ሥር ቀበሩት፤ ለሰባት ቀንም ጾሙ።