የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት ለሜፊቦስቴ ታማኝ ፍቅር አሳየው (1-13)

2 ሳሙኤል 9:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 18:1, 3፤ 20:15, 42

2 ሳሙኤል 9:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 16:1፤ 19:17

2 ሳሙኤል 9:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 4:4፤ 9:13፤ 19:26

2 ሳሙኤል 9:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 17:27-29

2 ሳሙኤል 9:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 11:17
  • +2ሳሙ 19:28፤ ምሳሌ 11:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2002፣ ገጽ 19

2 ሳሙኤል 9:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 24:14

2 ሳሙኤል 9:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 9:1፤ 16:4፤ 19:29

2 ሳሙኤል 9:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 19:28
  • +2ሳሙ 19:17

2 ሳሙኤል 9:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ከእኔ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

2 ሳሙኤል 9:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 8:34፤ 9:40

2 ሳሙኤል 9:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 9:7፤ 19:28
  • +2ሳሙ 4:4

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 9:11ሳሙ 18:1, 3፤ 20:15, 42
2 ሳሙ. 9:22ሳሙ 16:1፤ 19:17
2 ሳሙ. 9:32ሳሙ 4:4፤ 9:13፤ 19:26
2 ሳሙ. 9:42ሳሙ 17:27-29
2 ሳሙ. 9:7ምሳሌ 11:17
2 ሳሙ. 9:72ሳሙ 19:28፤ ምሳሌ 11:25
2 ሳሙ. 9:81ሳሙ 24:14
2 ሳሙ. 9:92ሳሙ 9:1፤ 16:4፤ 19:29
2 ሳሙ. 9:102ሳሙ 19:28
2 ሳሙ. 9:102ሳሙ 19:17
2 ሳሙ. 9:121ዜና 8:34፤ 9:40
2 ሳሙ. 9:132ሳሙ 9:7፤ 19:28
2 ሳሙ. 9:132ሳሙ 4:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 9:1-13

ሁለተኛ ሳሙኤል

9 ከዚያም ዳዊት “ለመሆኑ ለዮናታን ስል ታማኝ ፍቅር ላሳየው የምችል ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው ይኖራል?” አለ።+ 2 በዚህ ጊዜ የሳኦል ቤት አገልጋይ የሆነ ሲባ+ የሚባል ሰው ነበር። እሱንም ወደ ዳዊት እንዲመጣ ጠሩት፤ ንጉሡም “ሲባ የምትባለው አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም “አዎ፣ እኔ አገልጋይህ ሲባ ነኝ” በማለት መለሰ። 3 ከዚያም ንጉሡ “እንደው የአምላክን ታማኝ ፍቅር ላሳየው የምችል ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው ይኖራል?” አለው። ሲባም ንጉሡን “ሁለቱም እግሮቹ ሽባ+ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” አለው። 4 ንጉሡም “ለመሆኑ የት ነው ያለው?” አለው። ሲባም ንጉሡን “ሎደባር ባለው በአሚዔል ልጅ በማኪር+ ቤት ይገኛል” አለው።

5 ንጉሥ ዳዊትም ወዲያውኑ መልእክተኞችን ልኮ ሎደባር ከሚገኘው ከአሚዔል ልጅ ከማኪር ቤት አስመጣው። 6 የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜፊቦስቴ ወደ ዳዊት ሲገባ ወዲያውኑ በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ። ከዚያም ዳዊት “ሜፊቦስቴ!” ብሎ ጠራው፤ እሱም “አቤት ጌታዬ” አለ። 7 ዳዊትም “ለአባትህ ለዮናታን ስል ታማኝ ፍቅር ስለማሳይህ አትፍራ፤+ የአያትህን የሳኦልንም መሬት በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ አንተም ዘወትር ከማዕዴ ትበላለህ”+ አለው።

8 እሱም ከሰገደ በኋላ “እንደ እኔ ላለ የሞተ ውሻ+ ሞገስ ታሳይ ዘንድ ለመሆኑ እኔ አገልጋይህ ማን ነኝ?” አለው። 9 ከዚያም ንጉሡ ለሳኦል አገልጋይ ለሲባ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “የሳኦልና የቤተሰቡ የሆነውን ነገር ሁሉ ለጌታህ የልጅ ልጅ ሰጥቼዋለሁ።+ 10 አንተ፣ ልጆችህና አገልጋዮችህ መሬቱን ታርሱለታላችሁ፤ ምርቱንም ታስገቡለታላችሁ፤ ይህም ለጌታህ የልጅ ልጅ ቤተሰቦች መብል ይሆናል። የጌታህ የልጅ ልጅ ሜፊቦስቴ ግን ዘወትር ከማዕዴ ይመገባል።”+

ሲባ 15 ልጆችና 20 አገልጋዮች ነበሩት።+ 11 ከዚያም ሲባ ንጉሡን “እኔ አገልጋይህ፣ ጌታዬ ንጉሡ ያዘዘኝን ሁሉ እፈጽማለሁ” አለው። ስለዚህ ሜፊቦስቴ ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት* ማዕድ በላ። 12 ሜፊቦስቴም ሚካ+ የሚባል ትንሽ ልጅ ነበረው፤ በሲባ ቤት የሚኖሩም ሁሉ የሜፊቦስቴ አገልጋዮች ሆኑ። 13 ሜፊቦስቴም ዘወትር ከንጉሡ ማዕድ ይበላ+ ስለነበር የሚኖረው በኢየሩሳሌም ነበር፤ ሁለቱም እግሮቹ ሽባ ነበሩ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ