የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 16
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሲባ የሜፊቦስቴን ስም አጠፋ (1-4)

      • ሺምአይ ዳዊትን ረገመው (5-14)

      • አቢሴሎም ኩሲን ተቀበለው (15-19)

      • የአኪጦፌል ምክር (20-23)

2 ሳሙኤል 16:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው በለስን ሲሆን ቴምርንም ሊጨምር ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 15:30
  • +2ሳሙ 9:2, 9
  • +2ሳሙ 9:6
  • +1ሳሙ 25:18

2 ሳሙኤል 16:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 17:27-29

2 ሳሙኤል 16:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የልጅ ልጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 9:3
  • +2ሳሙ 19:25-27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2002፣ ገጽ 14-15

2 ሳሙኤል 16:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 9:9, 10
  • +ምሳሌ 26:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2018፣ ገጽ 6

2 ሳሙኤል 16:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 19:16፤ 1ነገ 2:8, 44
  • +ዘፀ 22:28፤ መክ 10:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2018፣ ገጽ 6-7

2 ሳሙኤል 16:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 24:6, 7፤ 26:9, 11፤ መዝ 3:1, 2፤ 7:1፤ 71:10, 11

2 ሳሙኤል 16:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 2:15, 16
  • +1ሳሙ 24:14
  • +ዘፀ 22:28
  • +1ሳሙ 26:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/1999፣ ገጽ 32

2 ሳሙኤል 16:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 19:22፤ 1ነገ 2:5
  • +መዝ 37:8፤ 1ጴጥ 2:23
  • +2ሳሙ 12:10

2 ሳሙኤል 16:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 12:11፤ 15:14፤ 17:12
  • +2ሳሙ 19:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/1999፣ ገጽ 32

2 ሳሙኤል 16:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:32፤ ዘፀ 3:7፤ መዝ 25:18
  • +መዝ 109:28

2 ሳሙኤል 16:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 16:5

2 ሳሙኤል 16:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 15:12, 31

2 ሳሙኤል 16:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የዳዊት ሚስጥረኛ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 16:1, 2
  • +2ሳሙ 15:32, 37፤ 1ዜና 27:33
  • +1ነገ 1:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    3/2017፣ ገጽ 29

2 ሳሙኤል 16:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 15:34

2 ሳሙኤል 16:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 37:12

2 ሳሙኤል 16:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥቱን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 15:16
  • +ዘሌ 18:8፤ 20:11፤ 1ነገ 2:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2005፣ ገጽ 13

2 ሳሙኤል 16:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 11:2
  • +2ሳሙ 12:11, 12
  • +ዘዳ 22:30፤ 2ሳሙ 20:3

2 ሳሙኤል 16:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አንድ ሰው የእውነተኛውን አምላክ ቃል እንደጠየቀ ተደርጎ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 15:12፤ 17:14, 23

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 16:12ሳሙ 15:30
2 ሳሙ. 16:12ሳሙ 9:2, 9
2 ሳሙ. 16:12ሳሙ 9:6
2 ሳሙ. 16:11ሳሙ 25:18
2 ሳሙ. 16:22ሳሙ 17:27-29
2 ሳሙ. 16:32ሳሙ 9:3
2 ሳሙ. 16:32ሳሙ 19:25-27
2 ሳሙ. 16:42ሳሙ 9:9, 10
2 ሳሙ. 16:4ምሳሌ 26:22
2 ሳሙ. 16:52ሳሙ 19:16፤ 1ነገ 2:8, 44
2 ሳሙ. 16:5ዘፀ 22:28፤ መክ 10:20
2 ሳሙ. 16:81ሳሙ 24:6, 7፤ 26:9, 11፤ መዝ 3:1, 2፤ 7:1፤ 71:10, 11
2 ሳሙ. 16:91ዜና 2:15, 16
2 ሳሙ. 16:91ሳሙ 24:14
2 ሳሙ. 16:9ዘፀ 22:28
2 ሳሙ. 16:91ሳሙ 26:8
2 ሳሙ. 16:102ሳሙ 19:22፤ 1ነገ 2:5
2 ሳሙ. 16:10መዝ 37:8፤ 1ጴጥ 2:23
2 ሳሙ. 16:102ሳሙ 12:10
2 ሳሙ. 16:112ሳሙ 12:11፤ 15:14፤ 17:12
2 ሳሙ. 16:112ሳሙ 19:16
2 ሳሙ. 16:12ዘፍ 29:32፤ ዘፀ 3:7፤ መዝ 25:18
2 ሳሙ. 16:12መዝ 109:28
2 ሳሙ. 16:132ሳሙ 16:5
2 ሳሙ. 16:152ሳሙ 15:12, 31
2 ሳሙ. 16:16ኢያሱ 16:1, 2
2 ሳሙ. 16:162ሳሙ 15:32, 37፤ 1ዜና 27:33
2 ሳሙ. 16:161ነገ 1:25
2 ሳሙ. 16:192ሳሙ 15:34
2 ሳሙ. 16:20መዝ 37:12
2 ሳሙ. 16:212ሳሙ 15:16
2 ሳሙ. 16:21ዘሌ 18:8፤ 20:11፤ 1ነገ 2:22
2 ሳሙ. 16:222ሳሙ 11:2
2 ሳሙ. 16:222ሳሙ 12:11, 12
2 ሳሙ. 16:22ዘዳ 22:30፤ 2ሳሙ 20:3
2 ሳሙ. 16:232ሳሙ 15:12፤ 17:14, 23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 16:1-23

ሁለተኛ ሳሙኤል

16 ዳዊት የተራራውን ጫፍ+ አልፎ ጥቂት እንደሄደ ሲባ+ የተባለው የሜፊቦስቴ+ አገልጋይ 200 ዳቦዎች፣ 100 የዘቢብ ቂጣዎች፣ ከበጋ ፍሬ* የተዘጋጁ 100 ቂጣዎችና አንድ እንስራ የወይን ጠጅ የተጫነባቸው ሁለት አህዮች እየነዳ ሊያገኘው መጣ።+ 2 ንጉሡም ሲባን “እነዚህን ነገሮች ያመጣኸው ለምንድን ነው?” አለው። ሲባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተሰብ እንዲቀመጥባቸው፣ ዳቦውንና የበጋ ፍሬውን ደግሞ ወጣቶቹ እንዲበሏቸው፣ የወይን ጠጁንም በምድረ በዳ የደከሙ ሰዎች እንዲጠጡት ነው” ሲል መለሰ።+ 3 ንጉሡም “የጌታህ ልጅ* የት አለ?” አለው።+ በዚህ ጊዜ ሲባ ንጉሡን “‘ዛሬ የእስራኤል ቤት የአባቴን ንጉሣዊ ሥልጣን ይመልስልኛል’ ብሎ ስላሰበ ኢየሩሳሌም ቀርቷል” አለው።+ 4 ንጉሡም ሲባን “እንግዲህ የሜፊቦስቴ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው” አለው።+ ሲባም “በፊትህ እሰግዳለሁ። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በአንተ ዘንድ ሞገስ ላግኝ” ሲል መለሰ።+

5 ንጉሥ ዳዊትም ባሁሪም ሲደርስ ከሳኦል ቤት የሆነ ሺምአይ+ የተባለ ሰው ከዚያ ወጥቶ እየተራገመ+ ወደ እነሱ ቀረበ፤ እሱም የጌራ ልጅ ነበር። 6 ሺምአይ በንጉሥ ዳዊትና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ እንዲሁም በንጉሡ ግራና ቀኝ በነበረው ሕዝብ ሁሉና በኃያላኑ ላይ ድንጋይ ይወረውር ነበር። 7 ሺምአይም እንዲህ እያለ ይራገም ነበር፦ “ውጣ፣ ከዚህ ውጣ፣ አንተ የደም ሰው! አንተ የማትረባ ሰው! 8 ንግሥናውን በወሰድክበት በሳኦል ቤት የተነሳ ያለብህን የደም ዕዳ በሙሉ ይሖዋ በአንተ ላይ እያመጣብህ ነው፤ ይሖዋም መንግሥትህን ለልጅህ ለአቢሴሎም አሳልፎ ይሰጠዋል። የደም ሰው ስለሆንክ ይኸው መከራህን እያየህ ነው!”+

9 ከዚያም የጽሩያ+ ልጅ አቢሳ ንጉሡን “ይህ የሞተ ውሻ+ ጌታዬን ንጉሡን የሚራገመው ለምንድን ነው?+ እባክህ ልሂድና ራሱን ልቁረጠው”+ አለው። 10 ንጉሡ ግን “እናንተ የጽሩያ ልጆች፣ ከእናንተ ጋር ምን የሚያገናኘኝ ጉዳይ አለ?+ ተዉት ይርገመኝ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ‘ዳዊትን እርገመው!’ ብሎታል።+ ታዲያ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ማን ሊለው ይችላል?” አለው። 11 ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን በሙሉ እንዲህ አላቸው፦ “ከአብራኬ የወጣው የገዛ ልጄ እንኳ ይኸው ሕይወቴን* እየፈለገ አይደል?+ ታዲያ አንድ ቢንያማዊ+ እንዲህ ቢያደርግ ምን ያስደንቃል! ተዉት ይርገመኝ፤ ይሖዋ እርገመው ብሎት ነው! 12 ምናልባትም ይሖዋ መከራዬን ያይልኝና+ በዛሬው እርግማን ፋንታ ይሖዋ መልካም ነገር ያደርግልኝ ይሆናል።”+ 13 ከዚያም ዳዊትና ሰዎቹ መንገዱን ይዘው ቁልቁል ወረዱ፤ ሺምአይም በተራራው ጥግ ከዳዊት ጎን ጎን እየሄደ ይራገም፣+ ድንጋይ ይወረውርና አቧራ ይበትን ነበር።

14 በኋላም ንጉሡና አብሮት የነበረው ሕዝብ በሙሉ ወዳሰቡበት ቦታ ደረሱ፤ እነሱም በጣም ደክሟቸው ነበር፤ በዚያም አረፉ።

15 ይህ በእንዲህ እንዳለ አቢሴሎምና የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ኢየሩሳሌም ደረሱ፤ አኪጦፌልም+ አብሮት ነበር። 16 የዳዊት ወዳጅ* አርካዊው+ ኩሲም+ ልክ ወደ አቢሴሎም እንደገባ አቢሴሎምን “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!+ ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” አለው። 17 በዚህ ጊዜ አቢሴሎም ኩሲን “ለወዳጅህ ታማኝ ፍቅር የምታሳየው በዚህ መንገድ ነው? ከወዳጅህ ጋር አብረህ ያልሄድከው ለምንድን ነው?” አለው። 18 ኩሲም አቢሴሎምን እንዲህ አለው፦ “በጭራሽ፣ እንዲህማ አላደርግም፤ ይሖዋ፣ ይህ ሕዝብና የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ከመረጡት ሰው ጎን እቆማለሁ። ከእሱም ጋር እቀመጣለሁ። 19 ደግሜ ይህን እናገራለሁ፣ ማገልገል ያለብኝ ማንን ነው? ልጁን አይደለም? አባትህን እንዳገለገልኩ ሁሉ አንተንም አገለግላለሁ።”+

20 ከዚያም አቢሴሎም አኪጦፌልን “እስቲ ምክር ስጡኝ።+ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለው። 21 አኪጦፌልም አቢሴሎምን “አባትህ፣ ቤቱን* እንዲጠብቁ ከተዋቸው+ ቁባቶቹ ጋር ግንኙነት ፈጽም።+ ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ ራስህን በአባትህ ዘንድ እንደ ጥንብ እንዳስቆጠርክ ይሰማሉ፤ አንተንም የሚደግፉ ብርታት ያገኛሉ” አለው። 22 በመሆኑም ለአቢሴሎም በጣሪያው ላይ ድንኳን ተከሉለት፤+ አቢሴሎምም እስራኤላውያን ሁሉ እያዩት+ ከአባቱ ቁባቶች ጋር ግንኙነት ፈጸመ።+

23 በዚያ ዘመን አኪጦፌል+ የሚሰጠው ምክር እንደ እውነተኛው አምላክ ቃል ተደርጎ* ይቆጠር ነበር። ዳዊትም ሆነ አቢሴሎም የአኪጦፌልን ምክር ሁሉ የሚያዩት እንደዚያ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ