የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ኤልሳዕ ንዕማንን ከሥጋ ደዌ ፈወሰው (1-19)

      • ስግብግብ የሆነው ግያዝ በሥጋ ደዌ ተመታ (20-27)

2 ነገሥት 5:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መዳን ያስገኘው።”

  • *

    ወይም “የቆዳ በሽታ የያዘው።”

2 ነገሥት 5:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 19:16
  • +ማቴ 8:2፤ 11:5፤ ሉቃስ 4:27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2008፣ ገጽ 9-10

    8/1/2005፣ ገጽ 10

2 ነገሥት 5:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ንዕማንን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

2 ነገሥት 5:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

2 ነገሥት 5:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:39

2 ነገሥት 5:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 17:24፤ 19:16፤ 2ነገ 3:11, 12፤ 8:4

2 ነገሥት 5:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 14:7፤ ዘኁ 19:4
  • +ዮሐ 9:6, 7

2 ነገሥት 5:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 7:8

2 ነገሥት 5:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 5:10
  • +ኢዮብ 33:25
  • +ሉቃስ 4:27፤ 5:13

2 ነገሥት 5:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በረከት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 17:15, 16
  • +መዝ 96:4, 5፤ ኢሳ 43:10

2 ነገሥት 5:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፊቱ በምቆመውና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2005፣ ገጽ 9

2 ነገሥት 5:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደስ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2005፣ ገጽ 9

2 ነገሥት 5:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 17:24
  • +2ነገ 4:12፤ 8:4
  • +2ነገ 5:1፤ ሉቃስ 4:27

2 ነገሥት 5:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 5:5

2 ነገሥት 5:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 5:16

2 ነገሥት 5:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በሰማርያ የሚገኝ ቦታ ሲሆን ኮረብታ ወይም ምሽግ ሊሆን ይችላል።

2 ነገሥት 5:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 5:8, 9

2 ነገሥት 5:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:8፤ ሉቃስ 12:15፤ ሥራ 20:33፤ 1ጢሞ 6:10

2 ነገሥት 5:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 5:1
  • +ዘፀ 4:6፤ ዘኁ 12:10

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 5:31ነገ 19:16
2 ነገ. 5:3ማቴ 8:2፤ 11:5፤ ሉቃስ 4:27
2 ነገ. 5:7ዘዳ 32:39
2 ነገ. 5:81ነገ 17:24፤ 19:16፤ 2ነገ 3:11, 12፤ 8:4
2 ነገ. 5:10ዘሌ 14:7፤ ዘኁ 19:4
2 ነገ. 5:10ዮሐ 9:6, 7
2 ነገ. 5:12ኢሳ 7:8
2 ነገ. 5:142ነገ 5:10
2 ነገ. 5:14ኢዮብ 33:25
2 ነገ. 5:14ሉቃስ 4:27፤ 5:13
2 ነገ. 5:15ሉቃስ 17:15, 16
2 ነገ. 5:15መዝ 96:4, 5፤ ኢሳ 43:10
2 ነገ. 5:16ማቴ 10:8
2 ነገ. 5:201ነገ 17:24
2 ነገ. 5:202ነገ 4:12፤ 8:4
2 ነገ. 5:202ነገ 5:1፤ ሉቃስ 4:27
2 ነገ. 5:222ነገ 5:5
2 ነገ. 5:232ነገ 5:16
2 ነገ. 5:25ሥራ 5:8, 9
2 ነገ. 5:26ማቴ 10:8፤ ሉቃስ 12:15፤ ሥራ 20:33፤ 1ጢሞ 6:10
2 ነገ. 5:272ነገ 5:1
2 ነገ. 5:27ዘፀ 4:6፤ ዘኁ 12:10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 5:1-27

ሁለተኛ ነገሥት

5 የሶርያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃ የሆነው ንዕማን በጌታው ፊት የተከበረና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሰው ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ ለሶርያ ድል ያጎናጸፈው* በእሱ አማካኝነት ነበር። ይህ ሰው የሥጋ ደዌ በሽተኛ* ቢሆንም ኃያል ተዋጊ ነበር። 2 ሶርያውያን በአንድ ወቅት ወረራ ሲያካሂዱ ከእስራኤል ምድር አንዲት ትንሽ ልጅ ማርከው ወስደው ነበር፤ እሷም የንዕማን ሚስት አገልጋይ ሆነች። 3 ይህች ልጅ እመቤቷን “ጌታዬ በሰማርያ ወዳለው ነቢይ+ ቢሄድ እኮ ጥሩ ነው! ከሥጋ ደዌው ይፈውሰው ነበር”+ አለቻት። 4 እሱም* ወደ ጌታው ሄዶ ከእስራኤል ምድር የመጣችው ልጅ ያለችውን ነገረው።

5 የሶርያም ንጉሥ “እንግዲያው ሂድ! እኔም ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልክለታለሁ” አለ። እሱም አሥር ታላንት* ብር፣ 6,000 ሰቅል ወርቅና አሥር ቅያሪ ልብሶች ይዞ ሄደ። 6 ለእስራኤልም ንጉሥ “አገልጋዬን ንዕማንን ከሥጋ ደዌው እንድትፈውሰው ከዚህ ደብዳቤ ጋር ወደ አንተ ልኬዋለሁ” የሚለውን ደብዳቤ ሰጠው። 7 የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን እንዳነበበ ልብሱን ቀደደ፤ ከዚያም “ይህን ሰው ከሥጋ ደዌው እንድፈውስ ወደ እኔ የሚልከው እኔ መግደልና ማዳን የምችል አምላክ ሆኜ ነው?+ እንግዲህ ነገር ሲፈልገኝ እዩ” አለ።

8 ይሁንና የእውነተኛው አምላክ ሰው ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን እንደቀደደ ሲሰማ ወዲያውኑ “ልብስህን የቀደድከው ለምንድን ነው? በእስራኤል ነቢይ መኖሩን እንዲያውቅ እባክህ ወደ እኔ ላከው”+ የሚል መልእክት ወደ ንጉሡ ላከ። 9 በመሆኑም ንዕማን ፈረሶቹንና የጦር ሠረገሎቹን ይዞ መጣ፤ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ላይ ቆመ። 10 ሆኖም ኤልሳዕ “ሄደህ ዮርዳኖስ ውስጥ ሰባት ጊዜ+ ታጠብ፤+ ሥጋህም ይፈወሳል፤ ንጹሕም ትሆናለህ” ብሎ እንዲነግረው መልእክተኛ ላከ። 11 በዚህ ጊዜ ንዕማን ተቆጥቶ ለመሄድ ተነሳ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ እኮ ‘ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የይሖዋን ስም እየጠራ ቁስሉ ያለበትን ቦታ በመዳሰስ ከያዘኝ የሥጋ ደዌ ይፈውሰኛል’ ብዬ አስቤ ነበር። 12 ለዚህ ለዚህማ የደማስቆ+ ወንዞች አባና እና ፋርፋር በእስራኤል ከሚገኙ ውኃዎች ሁሉ የተሻሉ አይደሉም? እነሱ ውስጥ ታጥቤ መንጻት አልችልም ነበር?” ከዚያም በቁጣ ተመልሶ ሄደ።

13 አገልጋዮቹም ቀርበው “አባቴ ሆይ፣ ነቢዩ ያልተለመደ ነገር እንድታደርግ ቢነግርህ ኖሮ አታደርገውም ነበር? ታዲያ ‘ታጠብና ንጻ’ ቢልህ ምኑ ከበደህ?” አሉት። 14 በዚህ ጊዜ ንዕማን የእውነተኛው አምላክ ሰው በነገረው መሠረት ወርዶ ዮርዳኖስ ውስጥ ሰባት ጊዜ ጠለቀ።+ ከዚያም ሥጋው እንደ ትንሽ ልጅ ሥጋ ሆነ፤+ ደግሞም ነጻ።+

15 ከዚያ በኋላ አጃቢዎቹን አስከትሎ ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው ተመለሰ፤+ በፊቱም ቆሞ “በእስራኤል እንጂ በምድር ላይ በሌላ በየትኛውም ቦታ አምላክ እንደሌለ አሁን አውቄአለሁ።+ እባክህ ከአገልጋይህ ስጦታ* ተቀበል” አለው። 16 እሱ ግን “በማገለግለውና* ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ ምንም ነገር አልቀበልም”+ አለው። ንዕማን እንዲቀበለው ቢወተውተውም ፈቃደኛ አልሆነም። 17 በመጨረሻም ንዕማን እንዲህ አለው፦ “እንግዲያው የማትቀበለኝ ከሆነ፣ አገልጋይህ ከአሁን በኋላ ለይሖዋ እንጂ ለሌሎች አማልክት የሚቃጠል መባም ሆነ መሥዋዕት ስለማያቀርብ እባክህ ለአገልጋይህ ከዚህ ቦታ የሁለት በቅሎ ጭነት አፈር ይሰጠው። 18 ይሁንና ይሖዋ ስለ አንድ ነገር ብቻ አገልጋይህን ይቅር ይበለው፤ ይኸውም ጌታዬ ለመስገድ ወደ ሪሞን ቤት* በሚገባበት ጊዜ ክንዴን ይደገፋል፤ እኔም በሪሞን ቤት መስገዴ አይቀርም። በሪሞን ቤት በምሰግድበት ጊዜ ይሖዋ ይህን ነገር አገልጋይህን ይቅር ይበለው።” 19 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ “በሰላም ሂድ” አለው። ከእሱ ተለይቶ የተወሰነ ርቀት እንደተጓዘ 20 የእውነተኛው አምላክ ሰው+ የኤልሳዕ አገልጋይ የሆነው ግያዝ+ ‘ጌታዬ ሶርያዊው ንዕማን+ ያመጣውን ነገር ሳይቀበለው እንዲሁ አሰናበተው። ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ ተከትዬው ሮጬ የሆነ ነገር እቀበለዋለሁ’ ብሎ አሰበ። 21 ስለዚህ ግያዝ ንዕማንን ተከተለው። ንዕማንም አንድ ሰው በሩጫ እየተከተለው እንዳለ ሲያይ ሰውየውን ለማግኘት ከሠረገላው ላይ ወርዶ “በደህና ነው?” አለው። 22 በዚህ ጊዜ ግያዝ እንዲህ አለው፦ “አዎ፣ በደህና ነው። ጌታዬ ‘ከነቢያት ልጆች መካከል ሁለት ወጣቶች ከተራራማው ከኤፍሬም አካባቢ አሁን ድንገት ወደ እኔ መጡ። ስለሆነም እባክህ አንድ ታላንት ብርና ሁለት ቅያሪ ልብስ ስጣቸው’+ ብዬ እንድነግርህ ልኮኝ ነው።” 23 ንዕማንም “እባክህ፣ ሁለት ታላንት ውሰድ” አለው። አጥብቆም ለመነው፤+ ከዚያም ሁለት ታላንት ብር በሁለት ከረጢት ጠቅልሎ እንዲሁም ሁለት ቅያሪ ልብስ ጨምሮ ለሁለቱ አገልጋዮቹ ሰጣቸው፤ እነሱም ተሸክመው ከፊት ከፊቱ ሄዱ።

24 እሱም ኦፌል* በደረሰ ጊዜ ዕቃዎቹን ከእጃቸው ላይ ወስዶ ቤት ውስጥ ካስቀመጠ በኋላ ሰዎቹን አሰናበታቸው። እነሱም ከሄዱ በኋላ 25 ገብቶ ጌታው አጠገብ ቆመ። ኤልሳዕም “ግያዝ፣ ከየት ነው የመጣኸው?” አለው። እሱ ግን “ኧረ አገልጋይህ የትም አልሄደም” አለ።+ 26 ኤልሳዕም እንዲህ አለው፦ “ሰውየው አንተን ለማግኘት ከሠረገላው ላይ ሲወርድ ልቤ በዚያ ከአንተ ጋር አልነበረም? ለመሆኑ ጊዜው ብር ወይም ልብስ፣ የወይራ ወይም የወይን እርሻ፣ በግ ወይም ከብት አሊያም ደግሞ ወንድ ወይም ሴት አገልጋዮች የሚቀበሉበት ነው?+ 27 ስለሆነም የንዕማን የሥጋ ደዌ+ በአንተና በዘርህ ላይ ለዘላለም ይጣበቃል።” ግያዝም በሥጋ ደዌ የተነሳ እንደ በረዶ ነጭ ሆኖ ወዲያውኑ ከፊቱ ወጣ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ