የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሰቆቃወ ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢየሩሳሌም እንደ መበለት ተደርጋ ተገልጻለች

        • ከተማዋ ብቻዋን ቀረች (1)

        • ጽዮን የፈጸመችው ከባድ ኃጢአት (8, 9)

        • ጽዮን በአምላክ ፊት ተቀባይነት አጣች (12-15)

        • ጽዮንን የሚያጽናናት የለም (17)

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የመጀመሪያዎቹ አራት ምዕራፎች በዕብራይስጥ ፊደላት ቅደም ተከተል የተዘጋጁ ሙሾዎች ናቸው።

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 122:3, 4
  • +1ነገ 4:20
  • +ዘዳ 28:15, 48፤ 2ነገ 25:11, 12

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 1:16
  • +ኤር 4:30፤ ሕዝ 16:37
  • +ኤር 30:14

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 17:4
  • +ዘሌ 26:33፤ 2ነገ 24:14, 15፤ 25:21፤ ኤር 39:9፤ 52:27
  • +ዘዳ 28:64

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወጣት ሴቶቿ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አሞጽ 8:10
  • +ኢሳ 3:26

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ራሶቿ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 1:15
  • +2ዜና 36:15, 16፤ ነህ 9:33፤ ዳን 9:7, 16
  • +ኤር 39:9፤ 52:30

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 24:21

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፈነደቁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:27
  • +ኤር 52:4
  • +መዝ 137:7፤ ሰቆ 2:16

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:4፤ 59:2፤ ሕዝ 22:4
  • +ኤር 13:22፤ ሕዝ 23:29
  • +ኤር 4:31

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 8:7
  • +ኤር 50:29

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 52:17, 19፤ ዳን 1:1, 2
  • +2ዜና 36:17, 18፤ መዝ 74:7፤ ኤር 52:13

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስን ለመመለስ።”

  • *

    ኢየሩሳሌምን የሚያመለክት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 38:9፤ 52:6፤ ሰቆ 2:12፤ 4:4

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 21:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2007፣ ገጽ 8

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 102:3

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:37፤ ሕዝ 11:9

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:14, 15
  • +2ዜና 36:17
  • +ራእይ 14:19፤ 19:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2007፣ ገጽ 8-9

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 31:15

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:31
  • +ዘዳ 28:49፤ 2ነገ 24:1, 2፤ 25:1
  • +ሰቆ 1:8

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በአፉ ላይ ዓመፅ ፈጽሜአለሁ።”

  • *

    ወይም “ወጣት ሴቶቼና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:33፤ ዳን 9:7
  • +1ሳሙ 12:14, 15
  • +ዘዳ 28:32

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስን ለመመለስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 30:14
  • +2ነገ 25:3፤ ኤር 38:9

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 107:11፤ ኢሳ 1:2፤ 63:10
  • +ዘዳ 32:25፤ ኤር 15:2

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 25:6, 7፤ አብ 12
  • +ኢሳ 13:19፤ ኤር 25:12-14፤ ኢዩ 3:19
  • +መዝ 137:8, 9፤ ኢሳ 51:22, 23

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:35

ተዛማጅ ሐሳብ

ሰቆ. 1:1መዝ 122:3, 4
ሰቆ. 1:11ነገ 4:20
ሰቆ. 1:1ዘዳ 28:15, 48፤ 2ነገ 25:11, 12
ሰቆ. 1:2ሰቆ 1:16
ሰቆ. 1:2ኤር 4:30፤ ሕዝ 16:37
ሰቆ. 1:2ኤር 30:14
ሰቆ. 1:3ኤር 17:4
ሰቆ. 1:3ዘሌ 26:33፤ 2ነገ 24:14, 15፤ 25:21፤ ኤር 39:9፤ 52:27
ሰቆ. 1:3ዘዳ 28:64
ሰቆ. 1:4ኢሳ 3:26
ሰቆ. 1:4አሞጽ 8:10
ሰቆ. 1:5ዘካ 1:15
ሰቆ. 1:52ዜና 36:15, 16፤ ነህ 9:33፤ ዳን 9:7, 16
ሰቆ. 1:5ኤር 39:9፤ 52:30
ሰቆ. 1:6ሕዝ 24:21
ሰቆ. 1:71ነገ 10:27
ሰቆ. 1:7ኤር 52:4
ሰቆ. 1:7መዝ 137:7፤ ሰቆ 2:16
ሰቆ. 1:8ኢሳ 1:4፤ 59:2፤ ሕዝ 22:4
ሰቆ. 1:8ኤር 13:22፤ ሕዝ 23:29
ሰቆ. 1:8ኤር 4:31
ሰቆ. 1:9ኤር 8:7
ሰቆ. 1:9ኤር 50:29
ሰቆ. 1:10ኤር 52:17, 19፤ ዳን 1:1, 2
ሰቆ. 1:102ዜና 36:17, 18፤ መዝ 74:7፤ ኤር 52:13
ሰቆ. 1:11ኤር 38:9፤ 52:6፤ ሰቆ 2:12፤ 4:4
ሰቆ. 1:12ኤር 21:7
ሰቆ. 1:13መዝ 102:3
ሰቆ. 1:14ዘሌ 26:37፤ ሕዝ 11:9
ሰቆ. 1:152ነገ 24:14, 15
ሰቆ. 1:152ዜና 36:17
ሰቆ. 1:15ራእይ 14:19፤ 19:15
ሰቆ. 1:16ኤር 31:15
ሰቆ. 1:17ኤር 4:31
ሰቆ. 1:17ዘዳ 28:49፤ 2ነገ 24:1, 2፤ 25:1
ሰቆ. 1:17ሰቆ 1:8
ሰቆ. 1:18ነህ 9:33፤ ዳን 9:7
ሰቆ. 1:181ሳሙ 12:14, 15
ሰቆ. 1:18ዘዳ 28:32
ሰቆ. 1:19ኤር 30:14
ሰቆ. 1:192ነገ 25:3፤ ኤር 38:9
ሰቆ. 1:20መዝ 107:11፤ ኢሳ 1:2፤ 63:10
ሰቆ. 1:20ዘዳ 32:25፤ ኤር 15:2
ሰቆ. 1:21ሕዝ 25:6, 7፤ አብ 12
ሰቆ. 1:21ኢሳ 13:19፤ ኤር 25:12-14፤ ኢዩ 3:19
ሰቆ. 1:21መዝ 137:8, 9፤ ኢሳ 51:22, 23
ሰቆ. 1:22ኤር 51:35
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:1-22

ሰቆቃወ ኤርምያስ

א [አሌፍ]*

1 በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን እንዴት ብቻዋን ቀረች!+

ከሌሎች ብሔራት ይበልጥ ብዙ ሕዝብ የነበረባት ከተማ እንዴት እንደ መበለት ሆነች!+

በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው ከተማ እንዴት ለባርነት ተዳረገች!+

ב [ቤት]

 2 በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤+ እንባዋም በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል።

ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል አንድም የሚያጽናናት የለም።+

ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤+ ጠላት ሆነውባታል።

ג [ጊሜል]

 3 ይሁዳ ተጎሳቁላና ለአስከፊ ባርነት ተዳርጋ+ በግዞት ተወስዳለች።+

በብሔራት መካከል ትቀመጣለች፤+ ምንም ማረፊያ ስፍራ አታገኝም።

በተጨነቀች ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ ያዟት።

ד [ዳሌት]

 4 በዓል ለማክበር የሚመጣ ስለሌለ ወደ ጽዮን የሚወስዱት መንገዶች አዝነዋል።+

በሮቿ ሁሉ ወና ሆነዋል፤+ ካህናቷም ሲቃ ይዟቸዋል።

ደናግሏ* አዝነዋል፤ እሷም አስከፊ ሥቃይ ደርሶባታል።

ה [ሄ]

 5 ባላጋራዎቿ አሁን ጌቶቿ* ሆነዋል፤ ጠላቶቿ ጭንቀት የለባቸውም።+

ከበደሏ ብዛት የተነሳ ይሖዋ ሐዘን አምጥቶባታልና።+

ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው ተወስደዋል።+

ו [ዋው]

 6 የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተገፏል።+

መኳንንቷ መሰማሪያ ቦታ እንዳጡ አጋዘኖች ሆነዋል፤

በሚያሳድዳቸውም ፊት አቅም አጥተው ይጓዛሉ።

ז [ዛየን]

 7 ኢየሩሳሌም በምትጎሳቆልበትና መኖሪያ በምታጣበት ጊዜ፣

በጥንት ዘመን የነበሯትን ውድ ነገሮች ሁሉ ታስታውሳለች።+

ሕዝቧ በጠላት እጅ በወደቀበትና የሚረዳት ባልነበረበት ጊዜ+

ጠላቶቿ አዩአት፤ በደረሰባትም ውድቀት ሳቁ።*+

ח[ኼት]

 8 ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ፈጽማለች።+

አስጸያፊ ነገር የሆነችው ለዚህ ነው።

ያከብሯት የነበሩ ሁሉ አሁን ናቋት፤ እርቃኗን አይተዋልና።+

እሷ ራሷም ትቃትታለች፤+ በኀፍረትም ፊቷን ታዞራለች።

ט [ቴት]

 9 ርኩሰቷ ቀሚሷ ላይ አለ።

ወደፊት የሚገጥማትን ቆም ብላ አላሰበችም።+

ውድቀቷ አስደንጋጭ ነበር፤ የሚያጽናናትም የለም።

ይሖዋ ሆይ፣ ጉስቁልናዬን ተመልከት፤ ጠላት ራሱን ከፍ ከፍ አድርጓልና።+

י [ዮድ]

10 ጠላት በውድ ሀብቶቿ ሁሉ ላይ እጁን አሳርፏል።+

ወደ አንተ ጉባኤ እንዳይገቡ ያዘዝካቸው ብሔራት

ወደ መቅደሷ ሲገቡ አይታለችና።+

כ [ካፍ]

11 ነዋሪዎቿ ሁሉ ሲቃ ይዟቸዋል፤ የሚበላ ነገር ይፈልጋሉ።+

ምግብ ለማግኘትና በሕይወት ለመቆየት* ብቻ ሲሉ ያሏቸውን ውድ ነገሮች ሰጥተዋል።

ይሖዋ ሆይ፣ እይ ደግሞም ተመልከት፤ እንደማትረባ ሴት ሆኛለሁና።*

ל [ላሜድ]

12 በዚህ መንገድ የምታልፉ ሁሉ፣ ይህ ለእናንተ ከምንም የማይቆጠር ነገር ነው?

እዩ፤ ደግሞም ተመልከቱ!

ይሖዋ በሚነድ ቁጣው ቀን እንድሠቃይ ያደረገበትን፣

በእኔ ላይ የደረሰውን ሥቃይ የመሰለ ሥቃይ አለ?+

מ [ሜም]

13 ከከፍታ ቦታ ወደ አጥንቶቼ እሳት ላከ፤+ በእያንዳንዳቸውም ላይ አየለባቸው።

ለእግሬ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላ እንድመለስ አስገደደኝ።

የተጣለች ሴት አድርጎኛል።

ቀኑን ሙሉ ታምሜአለሁ።

נ [ኑን]

14 በደሎቼ እንደ ቀንበር ታስረዋል፤ በእጁም ተገምደዋል።

አንገቴ ላይ ተደርገዋል፤ ጉልበቴም ተዳክሟል።

ይሖዋ መቋቋም ለማልችላቸው ሰዎች አሳልፎ ሰጥቶኛል።+

ס [ሳሜኽ]

15 ይሖዋ በውስጤ ያሉትን ኃያላን በሙሉ አስወገደ።+

ወጣቶቼን ለማድቀቅ በእኔ ላይ ጉባኤ ጠርቷል።+

ይሖዋ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረግጧል።+

ע [አይን]

16 በእነዚህ ነገሮች የተነሳ አለቅሳለሁ፤+ ዓይኖቼ እንባ ያፈሳሉ።

ሊያጽናናኝ ወይም መንፈሴን* ሊያድስ የሚችል ሰው ከእኔ ርቋልና።

ወንዶች ልጆቼ ተጥለዋል፤ ጠላት አይሏልና።

פ [ፔ]

17 ጽዮን እጆቿን ዘረጋች፤+ የሚያጽናናትም የለም።

በያዕቆብ ዙሪያ ያሉት ሁሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ ይሖዋ ትእዛዝ አስተላልፏል።+

ኢየሩሳሌም ለእነሱ አስጸያፊ ነገር ሆናለች።+

צ [ጻዴ]

18 ይሖዋ ጻድቅ ነው፤+ ትእዛዙን ተላልፌአለሁና።*+

እናንተ ሰዎች ሁሉ፣ አዳምጡ፤ ሥቃዬንም ተመልከቱ።

ደናግሌና* ወጣት ወንዶቼ በግዞት ተወስደዋል።+

ק [ኮፍ]

19 ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነሱ ግን ከዱኝ።+

ካህናቴና ሽማግሌዎቼ በሕይወት ለመቆየት* ብለው

የሚበላ ነገር ሲፈልጉ በከተማዋ ውስጥ አለቁ።+

ר [ረሽ]

20 ይሖዋ ሆይ፣ ተመልከት፤ በከባድ ጭንቀት ተውጫለሁና።

አንጀቴም ተላወሰ።

ልቤ በውስጤ እጅግ ተረብሿል፤ የለየለት ዓመፀኛ ሆኛለሁና።+

በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤+ በቤት ውስጥ ደግሞ ሞት አለ።

ש [ሺን]

21 ሰዎች ሲቃዬን ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝም የለም።

ጠላቶቼ ሁሉ ስለደረሰብኝ ጥፋት ሰምተዋል።

ይህን ጥፋት ስላመጣህ ደስ ተሰኝተዋል።+

አንተ ግን የተናገርከውን ቀን በእነሱ ላይ ታመጣለህ፤+ በዚያን ጊዜ እነሱ እንደ እኔ ይሆናሉ።+

ת [ታው]

22 ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ በሠራኋቸው በደሎች ሁሉ የተነሳ

እኔን እንደቀጣኸኝ፣ እነሱንም ቅጣቸው።+

ለቅሶዬ በዝቷልና፤ ልቤም ታሟል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ