የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መሳፍንት 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መሳፍንት የመጽሐፉ ይዘት

      • ይሁዳና ስምዖን ድል አድርገው የያዟቸው ግዛቶች (1-20)

      • ኢያቡሳውያን በኢየሩሳሌም መኖራቸውን ቀጠሉ (21)

      • ዮሴፍ ቤቴልን ያዘ (22-26)

      • ከነአናውያን ሙሉ በሙሉ ከምድሪቱ አልተባረሩም (27-36)

መሳፍንት 1:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የእስራኤል ወንዶች ልጆች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 24:29
  • +ዘኁ 27:18, 21፤ መሳ 20:18

መሳፍንት 1:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰጥቼዋለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:8፤ ዘዳ 33:7፤ 1ዜና 5:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2005፣ ገጽ 24

መሳፍንት 1:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ዕጣዬ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:1፤ 19:1, 9

መሳፍንት 1:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 9:3

መሳፍንት 1:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:6፤ ዘዳ 20:17
  • +ዘፍ 15:18-21፤ ዘፀ 3:8፤ መሳ 3:5፤ 1ነገ 9:20, 21

መሳፍንት 1:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2005፣ ገጽ 24

መሳፍንት 1:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:8, 12

መሳፍንት 1:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:63፤ መሳ 1:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 95-96

መሳፍንት 1:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 11:16፤ 15:20, 33

መሳፍንት 1:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 11:21፤ 15:13, 14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 9/2021፣ ገጽ 8-9

መሳፍንት 1:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 10:38
  • +ኢያሱ 15:15

መሳፍንት 1:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:3, 6፤ 14:24፤ ዘዳ 1:35, 36፤ ኢያሱ 14:13
  • +ኢያሱ 15:16-19

መሳፍንት 1:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 4:13
  • +መሳ 3:9

መሳፍንት 1:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በአህያዋ ላይ እያለች አጨበጨበች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

መሳፍንት 1:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በኔጌብ።”

  • *

    “የውኃ ምንጮች” የሚል ትርጉም አለው።

መሳፍንት 1:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 24:21፤ መሳ 4:11
  • +ዘፀ 3:1፤ 4:18፤ 18:1፤ ዘኁ 10:29
  • +ዘዳ 34:3፤ መሳ 3:13
  • +ዘኁ 21:1
  • +ዘኁ 10:29-32

መሳፍንት 1:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ለጥፋት መዳረግ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:29፤ ዘዳ 20:16
  • +ኢያሱ 19:1, 4

መሳፍንት 1:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:19፤ ኢያሱ 11:22
  • +መሳ 14:19
  • +ኢያሱ 13:1-3፤ 15:20, 45

መሳፍንት 1:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በረባዳማው ሜዳ።”

  • *

    ቃል በቃል “የብረት ሠረገሎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 20:1፤ ኢያሱ 17:16

መሳፍንት 1:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:24፤ ኢያሱ 14:9
  • +ዘኁ 13:22

መሳፍንት 1:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:63፤ 2ሳሙ 5:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 95-96

መሳፍንት 1:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 14:4
  • +ዘፍ 49:22, 24፤ ኢያሱ 16:1፤ መዝ 44:3

መሳፍንት 1:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:6

መሳፍንት 1:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ታማኝ ፍቅር እናሳይሃለን።”

መሳፍንት 1:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 6:25፤ 1ሳሙ 15:6

መሳፍንት 1:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በዙሪያዋ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 21:8, 25፤ መሳ 5:19
  • +ኢያሱ 17:11, 12

መሳፍንት 1:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:25፤ 1ነገ 9:20, 21
  • +ዘኁ 33:55፤ ዘዳ 7:2፤ 20:16፤ ኢያሱ 17:13

መሳፍንት 1:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 16:10፤ 1ነገ 9:16

መሳፍንት 1:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:15, 16
  • +ዘዳ 20:17፤ መሳ 2:2

መሳፍንት 1:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 11:8፤ 19:28, 31
  • +ኢያሱ 19:29, 31
  • +ኢያሱ 19:30, 31
  • +ኢያሱ 21:8, 31

መሳፍንት 1:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:38, 39
  • +ዘዳ 7:2

መሳፍንት 1:34

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ረባዳማው ሜዳ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:47፤ መሳ 18:1

መሳፍንት 1:35

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጁ።”

  • *

    ቃል በቃል “እየከበደ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 10:12
  • +ኢያሱ 19:42, 48

መሳፍንት 1:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 34:2, 4፤ ኢያሱ 15:3, 12

ተዛማጅ ሐሳብ

መሳ. 1:1ኢያሱ 24:29
መሳ. 1:1ዘኁ 27:18, 21፤ መሳ 20:18
መሳ. 1:2ዘፍ 49:8፤ ዘዳ 33:7፤ 1ዜና 5:2
መሳ. 1:3ኢያሱ 15:1፤ 19:1, 9
መሳ. 1:4ዘዳ 9:3
መሳ. 1:5ዘፍ 10:6፤ ዘዳ 20:17
መሳ. 1:5ዘፍ 15:18-21፤ ዘፀ 3:8፤ መሳ 3:5፤ 1ነገ 9:20, 21
መሳ. 1:7ኢያሱ 15:8, 12
መሳ. 1:8ኢያሱ 15:63፤ መሳ 1:21
መሳ. 1:9ኢያሱ 11:16፤ 15:20, 33
መሳ. 1:10ኢያሱ 11:21፤ 15:13, 14
መሳ. 1:11ኢያሱ 10:38
መሳ. 1:11ኢያሱ 15:15
መሳ. 1:12ዘኁ 13:3, 6፤ 14:24፤ ዘዳ 1:35, 36፤ ኢያሱ 14:13
መሳ. 1:12ኢያሱ 15:16-19
መሳ. 1:131ዜና 4:13
መሳ. 1:13መሳ 3:9
መሳ. 1:16ዘኁ 24:21፤ መሳ 4:11
መሳ. 1:16ዘፀ 3:1፤ 4:18፤ 18:1፤ ዘኁ 10:29
መሳ. 1:16ዘዳ 34:3፤ መሳ 3:13
መሳ. 1:16ዘኁ 21:1
መሳ. 1:16ዘኁ 10:29-32
መሳ. 1:17ዘሌ 27:29፤ ዘዳ 20:16
መሳ. 1:17ኢያሱ 19:1, 4
መሳ. 1:18ዘፍ 10:19፤ ኢያሱ 11:22
መሳ. 1:18መሳ 14:19
መሳ. 1:18ኢያሱ 13:1-3፤ 15:20, 45
መሳ. 1:19ዘዳ 20:1፤ ኢያሱ 17:16
መሳ. 1:20ዘኁ 14:24፤ ኢያሱ 14:9
መሳ. 1:20ዘኁ 13:22
መሳ. 1:21ኢያሱ 15:63፤ 2ሳሙ 5:6
መሳ. 1:22ኢያሱ 14:4
መሳ. 1:22ዘፍ 49:22, 24፤ ኢያሱ 16:1፤ መዝ 44:3
መሳ. 1:23ዘፍ 35:6
መሳ. 1:25ኢያሱ 6:25፤ 1ሳሙ 15:6
መሳ. 1:27ኢያሱ 21:8, 25፤ መሳ 5:19
መሳ. 1:27ኢያሱ 17:11, 12
መሳ. 1:28ዘፍ 9:25፤ 1ነገ 9:20, 21
መሳ. 1:28ዘኁ 33:55፤ ዘዳ 7:2፤ 20:16፤ ኢያሱ 17:13
መሳ. 1:29ኢያሱ 16:10፤ 1ነገ 9:16
መሳ. 1:30ኢያሱ 19:15, 16
መሳ. 1:30ዘዳ 20:17፤ መሳ 2:2
መሳ. 1:31ኢያሱ 11:8፤ 19:28, 31
መሳ. 1:31ኢያሱ 19:29, 31
መሳ. 1:31ኢያሱ 19:30, 31
መሳ. 1:31ኢያሱ 21:8, 31
መሳ. 1:33ኢያሱ 19:38, 39
መሳ. 1:33ዘዳ 7:2
መሳ. 1:34ኢያሱ 19:47፤ መሳ 18:1
መሳ. 1:35ኢያሱ 10:12
መሳ. 1:35ኢያሱ 19:42, 48
መሳ. 1:36ዘኁ 34:2, 4፤ ኢያሱ 15:3, 12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መሳፍንት 1:1-36

መሳፍንት

1 ኢያሱ+ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን* “ከከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” በማለት ይሖዋን ጠየቁ።+ 2 ይሖዋም “ይሁዳ ይውጣ።+ እኔም ምድሪቱን በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ”* አለ። 3 ከዚያም ይሁዳ ወንድሙን ስምዖንን “ከከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ወደተመደበልኝ ርስት* + አብረኸኝ ውጣ። እኔም ደግሞ በዕጣ ወደደረሰህ ርስት አብሬህ እሄዳለሁ” አለው። ስለዚህ ስምዖን አብሮት ሄደ።

4 ይሁዳም በወጣ ጊዜ ይሖዋ ከነአናውያንንና ፈሪዛውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤+ በመሆኑም ቤዜቅ ላይ 10,000 ሰዎችን ድል አደረጉ። 5 አዶኒቤዜቅን ቤዜቅ ላይ ባገኙት ጊዜ በዚያ ከእሱ ጋር ተዋጉ፤ ከነአናውያንንና+ ፈሪዛውያንንም+ ድል አደረጉ። 6 አዶኒቤዜቅም በሸሸ ጊዜ አሳደው ያዙት፤ ከዚያም የእጆቹንና የእግሮቹን አውራ ጣቶች ቆረጡ። 7 አዶኒቤዜቅም እንዲህ አለ፦ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቆረጡባቸው ከገበታዬ ሥር ሆነው ፍርፋሪ የሚለቃቅሙ 70 ነገሥታት ነበሩ። አምላክም ልክ እኔ እንዳደረግኩት አደረገብኝ።” ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤+ እሱም በዚያ ሞተ።

8 በተጨማሪም የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው በቁጥጥር ሥር አዋሏት፤+ ከተማዋንም በሰይፍ መትተው በእሳት አቃጠሏት። 9 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች በተራራማው አካባቢ፣ በኔጌብና በሸፌላ+ ከሚኖሩት ከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ወረዱ። 10 በመሆኑም ይሁዳ በኬብሮን ይኖሩ በነበሩት ከነአናውያን ላይ ዘመተ (ኬብሮን ቀደም ሲል ቂርያትአርባ ተብላ ትጠራ ነበር)፤ እነሱም ሸሻይን፣ አሂማንን እና ታልማይን መቱ።+

11 ከዚያም ተነስተው በደቢር ነዋሪዎች ላይ ዘመቱ።+ (ደቢር ቀደም ሲል ቂርያትሰፈር ትባል ነበር።)+ 12 ካሌብም+ “ቂርያትሰፈርን መትቶ በቁጥጥር ሥር ላደረጋት ሰው ሴት ልጄን አክሳን እድርለታለሁ” አለ።+ 13 የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነው የቀናዝ+ ልጅ ኦትኒኤልም+ ከተማዋን በቁጥጥር ሥር አደረጋት። ስለሆነም ካሌብ ሴት ልጁን አክሳን ዳረለት። 14 እሷም ወደ ባሏ ቤት እየሄደች ሳለ ባሏን ከአባቷ መሬት እንዲጠይቅ ወተወተችው። ከዚያም ከአህያዋ ላይ ወረደች።* በዚህ ጊዜ ካሌብ “ምን ፈለግሽ?” ሲል ጠየቃት። 15 እሷም “የሰጠኸኝ በስተ ደቡብ* ያለ ቁራሽ መሬት ስለሆነ እባክህ ባርከኝ፤ ጉሎትማይምንም* ስጠኝ” አለችው። በመሆኑም ካሌብ ላይኛውን ጉሎት እና ታችኛውን ጉሎት ሰጣት።

16 የቄናዊው+ የሙሴ አማት+ ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባ ዛፎች ከተማ+ ወጥተው ከአራድ+ በስተ ደቡብ ወደሚገኘው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ አቀኑ። እነሱም ወደዚያ ሄደው ከሕዝቡ ጋር መኖር ጀመሩ።+ 17 ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር በመዝመት በጸፋት በሚኖሩት ከነአናውያን ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ ከተማዋንም ሙሉ በሙሉ ደመሰሱ።+ በመሆኑም ከተማዋን ሆርማ* + ብለው ሰየሟት። 18 ከዚያም ይሁዳ ጋዛንና+ ግዛቶቿን፣ አስቀሎንንና+ ግዛቶቿን እንዲሁም ኤቅሮንንና+ ግዛቶቿን ተቆጣጠረ። 19 ይሖዋ ከይሁዳ ጋር ስለነበር ይሁዳ ተራራማውን አካባቢ ወረሰ፤ በሜዳው* ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ግን ማባረር አልቻሉም፤ ምክንያቱም እነሱ የብረት ማጭድ የተገጠመላቸው የጦር ሠረገሎች* ነበሯቸው።+ 20 ሙሴ ቃል በገባው መሠረት ኬብሮንን ለካሌብ ሰጡት፤+ እሱም ሦስቱን የኤናቅ ልጆች ከዚያ አባረራቸው።+

21 ቢንያማውያን ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከዚያ አላስወጧቸውም ነበር፤ በመሆኑም ኢያቡሳውያኑ ከቢንያማውያን ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም አብረው ይኖራሉ።+

22 በዚህ ጊዜ የዮሴፍ ቤት+ ቤቴልን ለመውጋት ወጣ፤ ይሖዋም ከእነሱ ጋር ነበር።+ 23 የዮሴፍ ቤት ቤቴልን እየሰለለ ነበር (ቤቴል ቀደም ሲል ሎዛ ተብላ ትጠራ ነበር)፤+ 24 ሰላዮቹም አንድ ሰው ከከተማዋ ሲወጣ አዩ። በመሆኑም “እባክህ ወደ ከተማዋ የሚያስገባውን መንገድ አሳየን፤ እኛም ደግነት እናደርግልሃለን”* አሉት። 25 በመሆኑም ሰውየው ወደ ከተማዋ የሚያስገባውን መንገድ አሳያቸው፤ እነሱም የከተማዋን ነዋሪዎች በሰይፍ መቱ፤ ይሁንና ሰውየውንና ቤተሰቡን በሙሉ ነፃ ለቀቋቸው።+ 26 ሰውየውም ወደ ሂታውያን ምድር ሄዶ ከተማ ገነባ፤ ከተማዋንም ሎዛ ብሎ ጠራት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ስሟ ይኸው ነው።

27 ምናሴ ቤትሼንንና በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ ታአናክንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች፣ የዶርን ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉትን ከተሞች፣ የይብለአምን ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም የመጊዶን ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉትን ከተሞች አልወረሰም ነበር።+ ከነአናውያን ይህን ምድር ላለመልቀቅ ቆርጠው ነበር። 28 እስራኤላውያንም እያየሉ በሄዱ ጊዜ ከነአናውያንን የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው+ እንጂ ሙሉ በሙሉ አላባረሯቸውም።+

29 ኤፍሬምም ቢሆን በጌዜር ይኖሩ የነበሩትን ከነአናውያን አላባረራቸውም። ከነአናውያን በጌዜር አብረዋቸው ይኖሩ ነበር።+

30 ዛብሎንም የቂትሮንን ነዋሪዎችና የናሃሎልን+ ነዋሪዎች አላባረራቸውም። ከነአናውያን አብረዋቸው ይኖሩ የነበረ ሲሆን የግዳጅ ሥራም እንዲሠሩ ተገደው ነበር።+

31 አሴር የአኮን ነዋሪዎች እንዲሁም የሲዶናን፣+ የአህላብን፣ የአክዚብን፣+ የሄልባን፣ የአፊቅን+ እና የሬሆብን+ ነዋሪዎች አላባረራቸውም። 32 በመሆኑም አሴራውያን በምድሩ ይኖሩ ከነበሩት ከነአናውያን ጋር አብረው መኖራቸውን ቀጠሉ፤ ምክንያቱም አላባረሯቸውም ነበር።

33 ንፍታሌም የቤትሼሜሽን ነዋሪዎችና የቤትአናትን ነዋሪዎች+ አላባረራቸውም፤ ከዚህ ይልቅ በምድሩ ይኖሩ ከነበሩት ከነአናውያን ጋር አብረው ኖሩ።+ የቤትሼሜሽ ነዋሪዎችና የቤትአናት ነዋሪዎች የግዳጅ ሥራ ይሠሩላቸው ነበር።

34 ዳናውያን ወደ ሜዳው* እንዲወርዱ አሞራውያን ስላልፈቀዱላቸው በተራራማው አካባቢ ተወስነው ለመኖር ተገደዱ።+ 35 አሞራውያን የሃሬስ ተራራን፣ አይሎንን+ እና ሻአልቢምን+ አንለቅም በማለት በዚያ መኖራቸውን ቀጠሉ። ይሁንና የዮሴፍ ቤት ኃይሉ* እየጨመረ* በመጣ ጊዜ የጉልበት ሥራ ለመሥራት ተገደዱ። 36 የአሞራውያን ክልል ከአቅራቢም አቀበትና+ ከሴላ አንስቶ ወደ ላይ ያለው ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ