መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
64 አምላክ ሆይ፣ የማቀርበውን ልመና ስማ።+
ጠላት ከሚሰነዝርብኝ አስፈሪ ጥቃት ሕይወቴን ታደግ።
2 ከክፉ ሰዎች ስውር ሴራ፣
ከክፉ አድራጊዎች ሸንጎ ጠብቀኝ፤+
3 እነሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤
መርዘኛ ቃላቸውን እንደ ቀስት ያነጣጥራሉ፤
4 ይህን የሚያደርጉት ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ንጹሑን ሰው ለመምታት ነው፤
ያላንዳች ፍርሃት በድንገት ይመቱታል።
5 ክፉ ዓላማቸውን ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፤*
በስውር እንዴት ወጥመድ እንደሚዘረጉ ይነጋገራሉ።
“ማን ያየዋል?” ይላሉ።+
7 ሆኖም አምላክ ይመታቸዋል፤+
እነሱም በድንገት በቀስት ይቆስላሉ።
8 የገዛ ምላሳቸው ለውድቀት ይዳርጋቸዋል፤+
ይህን የሚመለከቱ ሁሉ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።