ኢሳይያስ
እነሆ፣ ይሖዋ በፈጣን ደመና እየጋለበ ወደ ግብፅ እየመጣ ነው።
የግብፅ ከንቱ አማልክት በእሱ ፊት ይንቀጠቀጣሉ፤+
የግብፅም ልብ በውስጧ ይቀልጣል።
2 “ግብፃውያንን በግብፃውያን ላይ አስነሳለሁ፤
እርስ በርሳቸውም ይጨራረሳሉ፤
እያንዳንዱ ወንድሙን፣ እያንዳንዱም ባልንጀራውን፣
ከተማም ከተማን፣ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።
እነሱም እርዳታ ለማግኘት ከንቱ ወደሆኑት አማልክት፣
ወደ ድግምተኞች፣ ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች ይዞራሉ።+
5 የባሕሩ ውኃ ይደርቃል፤
ወንዙም ይተናል፤ ጨርሶም ይደርቃል።+
6 ወንዞቹም ይገማሉ፤
በግብፅ የሚገኙት የአባይ የመስኖ ቦዮች ይጎድላሉ፤ ይደርቃሉም።
ቄጠማውና እንግጫው ይበሰብሳል።+
በነፋስ ተጠርጎ ይወሰዳል፤ ደብዛውም ይጠፋል።
8 ዓሣ አጥማጆቹም ያዝናሉ፤
ወደ አባይ ወንዝ የዓሣ መንጠቆ የሚወረውሩም ሁሉ ያለቅሳሉ፤
በውኃው ላይ የዓሣ ማጥመጃ መረቦችን የሚጥሉም ይመናመናሉ።
9 በተነደፈ የተልባ እግር+ የሚሠሩም ሆኑ
ነጭ ሸማ የሚሠሩ ሸማኔዎች ለኀፍረት ይዳረጋሉ።
10 የሽመና ባለሙያዎቿ ይደቆሳሉ፤
ቅጥር ሠራተኞቹ ሁሉ ያዝናሉ።*
ጥበበኞች የሆኑ የፈርዖን አማካሪዎች የሚሰጡት ምክር ማስተዋል የጎደለው ነው።+
ፈርዖንን “እኔ የጥበበኞች ልጅ፣
የጥንት ነገሥታትም ዘር ነኝ”
እንዴት ትሉታላችሁ?
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ግብፅ የወሰነውን የሚያውቁ ከሆነ ይንገሩህ።
16 በዚያ ቀን ግብፃውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በእነሱ ላይ እጁን በዛቻ ስለሚያወዛውዝ ይንቀጠቀጣሉ፤ ይሸበራሉም።+ 17 የይሁዳም ምድር ግብፅን ታሸብራለች። ስለ ምድሪቱ ሲወራ የሚሰሙ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በግብፃውያን ላይ ከወሰነው ውሳኔ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ።+
18 በዚያ ቀን በግብፅ ምድር የከነአንን ቋንቋ የሚናገሩና+ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ታማኝ እንደሚሆኑ በመሐላ የሚያረጋግጡ አምስት ከተሞች ይኖራሉ። ከእነዚህም መካከል አንዷ ‘የማፍረስ ከተማ’ ተብላ ትጠራለች።
19 በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል ለይሖዋ መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ላይ ለይሖዋ ዓምድ ይቆማል። 20 ይህም በግብፅ ምድር ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ምልክትና ምሥክር ይሆናል፤ እነሱ ከጨቋኞቻቸው የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻሉና፤ እሱም የሚታደጋቸው አዳኝ፣ አዎ ታላቅ አዳኝ ይልክላቸዋል። 21 ይሖዋም በግብፃውያን ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ በዚያም ቀን ግብፃውያን ይሖዋን ያውቁታል፤ መሥዋዕትና ስጦታ ያቀርባሉ፤ ለይሖዋም ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽማሉ። 22 ይሖዋ ግብፅን ይመታታል፤+ መትቶ ይፈውሳታል፤ እነሱም ወደ ይሖዋ ይመለሳሉ፤ እሱም ልመናቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል።
23 በዚያ ቀን ከግብፅ ወደ አሦር የሚወስድ አውራ ጎዳና ይኖራል።+ ከዚያም አሦር ወደ ግብፅ፣ ግብፅም ወደ አሦር ይመጣል፤ ግብፅና አሦርም በአንድነት አምላክን ያገለግላሉ። 24 በዚያ ቀን እስራኤል ሦስተኛ ወገን ሆና ከግብፅና ከአሦር ጋር ትተባበራለች፤+ በምድርም መካከል በረከት ትሆናለች፤ 25 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ “ሕዝቤ ግብፅ፣ የእጄም ሥራ አሦር፣ ርስቴም እስራኤል የተባረኩ ይሁኑ”+ ብሎ ይባርካቸዋልና።