የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • እስራኤል የፈጸመችው ታላቅ ክህደት (1-5)

      • እስራኤልና ይሁዳ አመነዘሩ (6-11)

      • ንስሐ እንዲገቡ የቀረበ ጥሪ (12-25)

ኤርምያስ 3:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 24:5፤ ኤር 2:7
  • +ኤር 2:20፤ ሕዝ 16:28, 29

ኤርምያስ 3:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዓረብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 16:16፤ 20:28

ኤርምያስ 3:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዝሙት አዳሪ የሆነች ሚስት ያላት ዓይነት ግንባር አለሽ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:19፤ ኤር 14:4፤ አሞጽ 4:7
  • +ኤር 6:15

ኤርምያስ 3:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:2

ኤርምያስ 3:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 2:1፤ 7:3

ኤርምያስ 3:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 22:1
  • +ሕዝ 20:28፤ ሆሴዕ 4:13

ኤርምያስ 3:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:13፤ 2ዜና 30:6፤ ሆሴዕ 14:1
  • +ሕዝ 16:46፤ 23:2, 4

ኤርምያስ 3:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 23:4, 5, 9፤ ሆሴዕ 2:2፤ 9:15
  • +ዘዳ 24:1
  • +2ነገ 17:19፤ ሕዝ 23:4, 11

ኤርምያስ 3:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 57:5, 6፤ ኤር 2:27

ኤርምያስ 3:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሷን ጻድቅ አድርጋ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 16:51፤ 23:4, 11

ኤርምያስ 3:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፊቴን አልጥልም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:6፤ ኤር 23:8
  • +ኤር 4:1፤ ሕዝ 33:11፤ ሆሴዕ 14:1
  • +ሆሴዕ 11:8, 9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 9

ኤርምያስ 3:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከባዕድ አማልክት።”

  • *

    ቃል በቃል “መንገዶችሽን ለእንግዶች ዘረጋሽ።”

ኤርምያስ 3:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ባላችሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 23:3

ኤርምያስ 3:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 23:4፤ ሕዝ 34:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 103

ኤርምያስ 3:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 1:10

ኤርምያስ 3:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 87:3፤ ሕዝ 43:7
  • +ኢሳ 2:2, 3፤ 56:6, 7፤ 60:3፤ ሚክ 4:1, 2፤ ዘካ 2:11፤ 8:22, 23

ኤርምያስ 3:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 50:4፤ ሕዝ 37:19፤ ሆሴዕ 1:11
  • +2ዜና 36:23፤ ዕዝራ 1:3፤ አሞጽ 9:15

ኤርምያስ 3:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 20:6

ኤርምያስ 3:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አጋሯን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 48:8፤ ሆሴዕ 3:1፤ 5:7

ኤርምያስ 3:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 17:10፤ ሆሴዕ 8:14፤ 13:6

ኤርምያስ 3:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 14:1, 4
  • +ኤር 31:18፤ ሆሴዕ 3:5

ኤርምያስ 3:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 65:7
  • +ኢሳ 12:2

ኤርምያስ 3:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አሳፋሪው አምላክ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 9:10

ኤርምያስ 3:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 9:7፤ መዝ 106:7፤ ኤር 2:19

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 3:1ኢሳ 24:5፤ ኤር 2:7
ኤር. 3:1ኤር 2:20፤ ሕዝ 16:28, 29
ኤር. 3:2ሕዝ 16:16፤ 20:28
ኤር. 3:3ዘሌ 26:19፤ ኤር 14:4፤ አሞጽ 4:7
ኤር. 3:3ኤር 6:15
ኤር. 3:4ኤር 2:2
ኤር. 3:5ሚክ 2:1፤ 7:3
ኤር. 3:62ነገ 22:1
ኤር. 3:6ሕዝ 20:28፤ ሆሴዕ 4:13
ኤር. 3:72ነገ 17:13፤ 2ዜና 30:6፤ ሆሴዕ 14:1
ኤር. 3:7ሕዝ 16:46፤ 23:2, 4
ኤር. 3:8ሕዝ 23:4, 5, 9፤ ሆሴዕ 2:2፤ 9:15
ኤር. 3:8ዘዳ 24:1
ኤር. 3:82ነገ 17:19፤ ሕዝ 23:4, 11
ኤር. 3:9ኢሳ 57:5, 6፤ ኤር 2:27
ኤር. 3:11ሕዝ 16:51፤ 23:4, 11
ኤር. 3:12ኤር 4:1፤ ሕዝ 33:11፤ ሆሴዕ 14:1
ኤር. 3:12ሆሴዕ 11:8, 9
ኤር. 3:122ነገ 17:6፤ ኤር 23:8
ኤር. 3:14ኤር 23:3
ኤር. 3:15ኤር 23:4፤ ሕዝ 34:23
ኤር. 3:16ሆሴዕ 1:10
ኤር. 3:17መዝ 87:3፤ ሕዝ 43:7
ኤር. 3:17ኢሳ 2:2, 3፤ 56:6, 7፤ 60:3፤ ሚክ 4:1, 2፤ ዘካ 2:11፤ 8:22, 23
ኤር. 3:18ኤር 50:4፤ ሕዝ 37:19፤ ሆሴዕ 1:11
ኤር. 3:182ዜና 36:23፤ ዕዝራ 1:3፤ አሞጽ 9:15
ኤር. 3:19ሕዝ 20:6
ኤር. 3:20ኢሳ 48:8፤ ሆሴዕ 3:1፤ 5:7
ኤር. 3:21ኢሳ 17:10፤ ሆሴዕ 8:14፤ 13:6
ኤር. 3:22ሆሴዕ 14:1, 4
ኤር. 3:22ኤር 31:18፤ ሆሴዕ 3:5
ኤር. 3:23ኢሳ 65:7
ኤር. 3:23ኢሳ 12:2
ኤር. 3:24ሆሴዕ 9:10
ኤር. 3:25ዕዝራ 9:7፤ መዝ 106:7፤ ኤር 2:19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 3:1-25

ኤርምያስ

3 ሰዎች እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፦ “አንድ ሰው ሚስቱን ቢያሰናብታት፣ እሷም ተለይታው ብትሄድና የሌላ ሰው ሚስት ብትሆን፣ ዳግመኛ ወደ እሷ መመለስ ይኖርበታል?”

ይህች ምድር ጨርሶ ተበክላ የለም?+

“አንቺ ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመነዘርሽ፤+

ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ይገባሻል?” ይላል ይሖዋ።

 2 “ዓይንሽን አንስተሽ የተራቆቱትን ኮረብቶች ተመልከቺ።

አንቺ ያልተደፈርሽበት ቦታ ይገኛል?

በምድረ በዳ እንዳለ ዘላን*

አንቺም በመንገዶቹ ዳር ተቀምጠሽ ጠበቅሻቸው።

በዝሙትሽና በክፋትሽ

ምድሪቱን በከልሽ።+

 3 ስለዚህ ዝናብ እንዳይዘንብ ተከልክሏል፤+

የኋለኛው ዝናብም አልዘነበም።

አንቺ ዝሙት አዳሪ እንደሆነች ሚስት፣ ዓይን አውጣ ነሽ፤*

ኀፍረት የሚባል ነገር አታውቂም።+

 4 አሁን ግን ወደ እኔ ተጣርተሽ እንዲህ ትያለሽ፦

‘አባቴ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምሮ ወዳጄ ነህ!+

 5 ለዘላለም ቅር ትሰኛለህ?

ወይስ ቂም እንደያዝክ ትኖራለህ?’

አንቺ እንዲህ ትያለሽ፤

ይሁንና የቻልሽውን ያህል ክፉ ነገር መሥራትሽን ቀጥለሻል።”+

6 በንጉሥ ኢዮስያስ+ ዘመን ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል ያደረገችውን አይተሃል? ከፍ ባለው ተራራ ሁሉ ላይና ቅጠሉ ከተንዠረገገው ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ሄዳለች።+ 7 ይህን ሁሉ ነገር ካደረገች በኋላ እንኳ ወደ እኔ እንድትመለስ መወትወቴን ቀጠልኩ፤+ እሷ ግን አልተመለሰችም፤ ይሁዳም ከሃዲ የሆነችውን እህቷን ተመለከተች።+ 8 ይህን ባየሁ ጊዜ፣ በማመንዘሯ የተነሳ+ ታማኝነቷን ላጎደለችው ለእስራኤል የፍችዋን የምሥክር ወረቀት ሰጥቼ አሰናበትኳት።+ ያም ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ አልፈራችም፤ እሷም ሄዳ አመነዘረች።+ 9 አመንዝራነቷን አቅልላ ተመለከተችው፤ ምድሪቱን መበከሏን እንዲሁም ከድንጋዮችና ከዛፎች ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች።+ 10 ይህም ሁሉ ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ ለይስሙላ እንጂ በሙሉ ልቧ ወደ እኔ አልተመለሰችም’ ይላል ይሖዋ።”

11 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል፣ ከሃዲ ከሆነችው ይሁዳ ይልቅ ጻድቅ ሆና* ተገኝታለች።+ 12 ሂድና እነዚህን ቃላት ወደ ሰሜን+ አውጅ፦

“‘“ከዳተኛይቱ እስራኤል ሆይ፣ ተመለሽ” ይላል ይሖዋ።’+ ‘“እኔ ታማኝ ስለሆንኩ እናንተን በቁጣ አልመለከትም”*+ ይላል ይሖዋ።’ ‘“ለዘላለም ቅር አልሰኝም። 13 ብቻ የሠራሽውን በደል አምነሽ ተቀበይ፤ በአምላክሽ በይሖዋ ላይ ዓምፀሻልና። ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር ከእንግዶች* ጋር አመነዘርሽ፤* ቃሌንም አትታዘዢም” ይላል ይሖዋ።’”

14 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ” ይላል ይሖዋ። “እኔ እውነተኛ ጌታችሁ* ሆኛለሁና፤ ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድም ሁለት እያደረግኩ እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ።+ 15 እንደ ልቤ የሆኑ እረኞችም እሰጣችኋለሁ፤+ እነሱም በእውቀትና በጥልቅ ማስተዋል ይመግቧችኋል። 16 በዚያ ዘመን በምድሪቱ ላይ ትበዛላችሁ፤ ፍሬያማም ትሆናላችሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ከእንግዲህ ‘የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት!’ አይሉም፤ ስለ እሱ አያስቡም፤ ጨርሶ አያስታውሱትም ወይም እንዳጎደላቸው ሆኖ አይሰማቸውም፤ ታቦቱም ዳግመኛ አይሠራም። 17 በዚያን ጊዜ ኢየሩሳሌምን የይሖዋ ዙፋን ብለው ይጠሯታል፤+ ብሔራትም ሁሉ በአንድነት የይሖዋን ስም ለማወደስ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤+ ከዚያ በኋላ ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን አይከተሉም።”

18 “በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤+ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።+ 19 እኔም እንዲህ ብዬ አሰብኩ፦ ‘በወንዶች ልጆች መካከል ባስቀምጥሽ፣ የተወደደችውንም ምድር፣ በብሔራት መካከል የምትገኘውን እጅግ ያማረች ርስት ብሰጥሽ ምንኛ ደስ ባለኝ!’+ በተጨማሪም እናንተ ‘አባቴ!’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሱም ብዬ አስቤ ነበር። 20 ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ ግን ባሏን* ክዳ እንደምትሄድ ሚስት በእኔ ላይ ክህደት ፈጽማችኋል’+ ይላል ይሖዋ።”

21 በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ድምፅ ተሰምቷል፤

አዎ፣ የእስራኤል ልጆች ለቅሶና ልመና ተሰምቷል፤

እነሱ መንገዳቸውን አጣመዋልና፤

አምላካቸውን ይሖዋን ረስተዋል።+

22 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ።

ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።”+

“እነሆ፣ እኛ ወደ አንተ መጥተናል!

ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህና።+

23 ኮረብቶቹና በተራሮቹ ላይ የሚሰማው ሁካታ የሐሰት ናቸው።+

በእርግጥ የእስራኤል መዳን በአምላካችን በይሖዋ ነው።+

24 ይሁንና አሳፋሪው ነገር* ከልጅነታችን ጀምሮ አባቶቻችን የደከሙበትን ሁሉ፣+

መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣

ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በልቷል።

25 ኀፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤

ውርደታችንም ይሸፍነን፤

እኛና አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ እስካሁን ድረስ

በአምላካችን በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፤+

የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅም አልታዘዝንም።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ