የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቡ የይሖዋን ተግሣጽ አልሰማም (1-13)

      • ጥፋት ቢደርስባቸውም ሙሉ በሙሉ አልጠፉም (14-19)

      • ይሖዋ ሕዝቡን ተጠያቂ አደረገ (20-31)

ኤርምያስ 5:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 22:29፤ ሚክ 7:2

ኤርምያስ 5:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 48:1

ኤርምያስ 5:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እነሱ ግን አልደከሙም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 16:9
  • +2ዜና 28:20-22፤ ኤር 2:30
  • +ዘካ 7:11
  • +መዝ 50:17፤ ኢሳ 42:24, 25፤ ሕዝ 3:7፤ ሶፎ 3:2

ኤርምያስ 5:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 3:1

ኤርምያስ 5:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 9:6፤ ኢሳ 59:12፤ ሕዝ 23:19

ኤርምያስ 5:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 23:6, 7፤ ኤር 2:11፤ 12:16፤ ሶፎ 1:4, 5

ኤርምያስ 5:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 22:11

ኤርምያስ 5:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:25፤ ኤር 9:9፤ 44:22፤ ናሆም 1:2

ኤርምያስ 5:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:44፤ ኤር 46:28

ኤርምያስ 5:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 48:8፤ ኤር 3:20፤ ሆሴዕ 5:7፤ 6:7

ኤርምያስ 5:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “እሱ የለም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:15, 16፤ ኢሳ 28:15
  • +ኤር 23:17

ኤርምያስ 5:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የአምላክን ቃል ያመለክታል።

ኤርምያስ 5:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:9
  • +ኤር 23:29

ኤርምያስ 5:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:15፤ 4:16፤ 25:9፤ ሕዝ 7:24፤ ዕን 1:6
  • +ዘዳ 28:49, 50

ኤርምያስ 5:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:16

ኤርምያስ 5:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:27

ኤርምያስ 5:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:27፤ 28:48፤ 29:24, 25፤ 2ዜና 7:21, 22

ኤርምያስ 5:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ልብ የሚጎድላችሁ ሞኞች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:22
  • +ኢሳ 59:10
  • +ኢሳ 6:9፤ ሕዝ 12:2፤ ማቴ 13:13

ኤርምያስ 5:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 38:8, 11፤ መዝ 33:7፤ ምሳሌ 8:29

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2004፣ ገጽ 8

ኤርምያስ 5:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 95:10፤ ኤር 11:8

ኤርምያስ 5:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 11:14

ኤርምያስ 5:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:23, 24፤ ኤር 3:3

ኤርምያስ 5:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አሞጽ 8:5፤ ሚክ 6:11, 12

ኤርምያስ 5:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:23
  • +መዝ 82:2

ኤርምያስ 5:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”

ኤርምያስ 5:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 14:14፤ ሰቆ 2:14፤ ሕዝ 13:6
  • +ኢሳ 30:10፤ ዮሐ 3:19

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 5:1ሕዝ 22:29፤ ሚክ 7:2
ኤር. 5:2ኢሳ 48:1
ኤር. 5:32ዜና 16:9
ኤር. 5:32ዜና 28:20-22፤ ኤር 2:30
ኤር. 5:3ዘካ 7:11
ኤር. 5:3መዝ 50:17፤ ኢሳ 42:24, 25፤ ሕዝ 3:7፤ ሶፎ 3:2
ኤር. 5:5ሚክ 3:1
ኤር. 5:6ዕዝራ 9:6፤ ኢሳ 59:12፤ ሕዝ 23:19
ኤር. 5:7ኢያሱ 23:6, 7፤ ኤር 2:11፤ 12:16፤ ሶፎ 1:4, 5
ኤር. 5:8ሕዝ 22:11
ኤር. 5:9ዘሌ 26:25፤ ኤር 9:9፤ 44:22፤ ናሆም 1:2
ኤር. 5:10ዘሌ 26:44፤ ኤር 46:28
ኤር. 5:11ኢሳ 48:8፤ ኤር 3:20፤ ሆሴዕ 5:7፤ 6:7
ኤር. 5:122ዜና 36:15, 16፤ ኢሳ 28:15
ኤር. 5:12ኤር 23:17
ኤር. 5:14ኤር 1:9
ኤር. 5:14ኤር 23:29
ኤር. 5:15ኤር 1:15፤ 4:16፤ 25:9፤ ሕዝ 7:24፤ ዕን 1:6
ኤር. 5:15ዘዳ 28:49, 50
ኤር. 5:17ዘሌ 26:16
ኤር. 5:18ኤር 4:27
ኤር. 5:19ዘዳ 4:27፤ 28:48፤ 29:24, 25፤ 2ዜና 7:21, 22
ኤር. 5:21ኤር 4:22
ኤር. 5:21ኢሳ 59:10
ኤር. 5:21ኢሳ 6:9፤ ሕዝ 12:2፤ ማቴ 13:13
ኤር. 5:22ኢዮብ 38:8, 11፤ መዝ 33:7፤ ምሳሌ 8:29
ኤር. 5:23መዝ 95:10፤ ኤር 11:8
ኤር. 5:24ዘዳ 11:14
ኤር. 5:25ዘዳ 28:23, 24፤ ኤር 3:3
ኤር. 5:27አሞጽ 8:5፤ ሚክ 6:11, 12
ኤር. 5:28ኢሳ 1:23
ኤር. 5:28መዝ 82:2
ኤር. 5:31ኤር 14:14፤ ሰቆ 2:14፤ ሕዝ 13:6
ኤር. 5:31ኢሳ 30:10፤ ዮሐ 3:19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 5:1-31

ኤርምያስ

5 በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ወዲያና ወዲህ ተመላለሱ።

ዙሪያውን ተመልከቱ፤ ልብ በሉ።

ፍትሕን የሚያደርግ፣+

ታማኝ መሆን የሚሻ ሰውም ታገኙ እንደሆነ

በአደባባዮቿ ፈልጉ፤

እኔም ይቅር እላታለሁ።

 2 “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!” ቢሉም

የሚምሉት ሐሰት ለሆነ ነገር ነው።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖችህ የሚመለከቱት ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት አይደለም?+

አንተ መተሃቸዋል፤ በእነሱ ላይ ግን ያመጣው ለውጥ የለም።*

አንተ አድቅቀሃቸዋል፤ እነሱ ግን አልታረሙም።+

ፊታቸውን ከዓለት ይልቅ አጠነከሩ፤+

ለመመለስም አሻፈረን አሉ።+

 4 እኔ ግን ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ እነዚህ ምስኪኖች ናቸው።

የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ ባለማወቃቸው

የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ።

 5 ታዋቂ ወደሆኑት ሰዎች ሄጄ አነጋግራቸዋለሁ፤

እነሱ የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ

አስተውለው መሆን አለበትና።+

ነገር ግን ሁሉም ቀንበሩን ሰብረዋል፤

ማሰሪያውንም በጥሰዋል።”

 6 ስለዚህ ከጫካ የወጣ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፤

የበረሃ ተኩላም ይቦጫጭቃቸዋል፤

ነብር በከተሞቻቸው አቅራቢያ አድብቶ ይጠብቃል።

ከዚያ የሚወጣውንም ሁሉ ይዘነጣጥላል።

በደላቸው በዝቷልና፤

የክህደት ሥራቸው ተበራክቷል።+

 7 ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ይቅር እልሻለሁ?

ወንዶች ልጆችሽ ትተውኛል፤

አምላክ ባልሆነውም ይምላሉ።+

እኔም የሚያስፈልጋቸውን ነገር አሟላሁላቸው፤

እነሱ ግን ምንዝር መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤

ወደ ዝሙት አዳሪ ቤትም እየተንጋጉ ሄዱ።

 8 እንደሚቅበጠበጡ፣ ብርቱ ፈረሶች ናቸው፤

እያንዳንዱ የሌላውን ሰው ሚስት ተከትሎ ያሽካካል።+

 9 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።

“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?”+

10 “የወይን እርሻዋን እርከኖች ሄዳችሁ አበላሹ፤

ሆኖም ሙሉ በሙሉ አታጥፉት።+

የተንሰራፉ ቅርንጫፎቿን አስወግዱ፤

የይሖዋ አይደሉምና።

11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት

በእኔ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽመዋልና” ይላል ይሖዋ።+

12 “እነሱ ይሖዋን ክደዋል፤

‘እሱ ምንም ነገር አያደርግም።*+

በእኛ ላይ ምንም ጥፋት አይመጣም፤

ሰይፍም ሆነ ረሃብ አናይም’ ይላሉ።+

13 ነቢያቱ በነፋስ የተሞሉ ናቸው፤

ቃሉም* በውስጣቸው የለም።

ይህ በእነሱ ላይ ይድረስ!”

14 ስለዚህ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እነዚህ ሰዎች እንዲህ ስለሚሉ፣

ቃሌን በአፋችሁ ውስጥ እሳት አደርጋለሁ፤+

እንጨቱ ደግሞ ይህ ሕዝብ ነው፤

እሳቱም ይበላቸዋል።”+

15 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሩቅ ቦታ ያለን ብሔር አመጣባችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።

“እሱም ለረጅም ጊዜ የኖረ ብሔር ነው።

ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ፣

ቋንቋውን የማታውቀውና

ንግግሩን የማትረዳው ብሔር ነው።+

16 የፍላጻ ኮሮጇቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፤

ሁሉም ተዋጊዎች ናቸው።

17 እነሱ አዝመራህንና ምግብህን ይበላሉ።+

ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይበላሉ።

መንጎችህንና ከብቶችህን ይበላሉ።

የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ይበላሉ።

የምትታመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችህን በሰይፍ ያወድማሉ።”

18 “ይሁንና በእነዚያ ቀናት እንኳ” ይላል ይሖዋ፣ “ሙሉ በሙሉ አላጠፋችሁም።+ 19 ‘አምላካችን ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገብን ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቁ ደግሞ ‘በምድራችሁ ላይ ባዕድ አምላክን ለማገልገል ስትሉ እኔን እንደተዋችሁኝ ሁሉ የራሳችሁ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።”+

20 ይህን በያዕቆብ ቤት ተናገሩ፤

በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦

21 “እናንተ ሞኞችና የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ ሰዎች* ይህን ስሙ፦+

ዓይን አላቸው ግን አያዩም፤+

ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም።+

22 ‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤

‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም?

ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌ

አሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ።

ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤

ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም።+

23 ነገር ግን ይህ ሕዝብ ልቡ ግትርና ዓመፀኛ ነው፤

ጀርባቸውን ሰጥተው በራሳቸው መንገድ ሄደዋል።+

24 እነሱም በልባቸው

“እንግዲያው፣ ዝናቡን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ

በወቅቱ የሚሰጠንን፣

የተወሰኑትን የአዝመራ ሳምንታት የሚጠብቅልንን

አምላካችንን ይሖዋን እንፍራ” አላሉም።+

25 የገዛ ራሳችሁ በደል እነዚህ ነገሮች እንዲቀሩ አድርጓል፤

የገዛ ኃጢአታችሁ መልካም የሆነ ነገር አሳጥቷችኋል።+

26 በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና።

አድብተው እንደሚጠብቁ ወፍ አዳኞች፣ በዓይነ ቁራኛ ይመለከታሉ።

ገዳይ ወጥመድ ይዘረጋሉ።

ሰዎችን ያጠምዳሉ።

27 በወፎች እንደተሞላ የወፍ ጎጆ፣

ቤቶቻቸው በማታለያ የተሞሉ ናቸው።+

ኃያላንና ሀብታም የሆኑት ለዚህ ነው።

28 ወፍረዋል፤ ቆዳቸውም ለስልሷል፤

በክፋት ተሞልተዋል።

ለራሳቸው ስኬት ሲያስቡ

አባት ለሌለው ልጅ አይሟገቱም፤+

ድሆችንም ፍትሕ ይነፍጋሉ።’”+

29 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።

“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?

30 በምድሪቱ ላይ የሚያስደነግጥና የሚያሰቅቅ ነገር ተከስቷል፦

31 ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤+

ካህናቱም በራሳቸው ሥልጣን በኃይል ይገዛሉ።

የገዛ ሕዝቤም ይህን ወዶታል።+

ይሁንና መጨረሻው ሲመጣ ምን ታደርጉ ይሆን?”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ