የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 27
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ፍልስጤማውያን ጺቅላግን ለዳዊት ሰጡት (1-12)

1 ሳሙኤል 27:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 19:18፤ 22:1, 5
  • +1ሳሙ 18:29፤ 23:23

1 ሳሙኤል 27:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 25:13፤ 30:9
  • +1ሳሙ 21:10, 14፤ 27:12

1 ሳሙኤል 27:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 25:43
  • +1ሳሙ 25:39, 42

1 ሳሙኤል 27:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 23:14፤ 26:25

1 ሳሙኤል 27:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:1, 5፤ 1ሳሙ 30:1፤ 2ሳሙ 1:1፤ 1ዜና 12:1, 20

1 ሳሙኤል 27:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የቀናት ቁጥር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 29:3

1 ሳሙኤል 27:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 13:1, 2
  • +ዘፍ 36:12፤ ዘፀ 17:8, 14፤ ዘኁ 13:29፤ 1ሳሙ 15:2፤ 2ሳሙ 1:1
  • +ዘፍ 25:17, 18፤ ዘፀ 15:22፤ 1ሳሙ 15:7

1 ሳሙኤል 27:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 25:19፤ 1ሳሙ 15:3

1 ሳሙኤል 27:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኔጌብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:1, 2
  • +1ዜና 2:9
  • +ዘኁ 24:21፤ 1ሳሙ 15:6

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ሳሙ. 27:11ሳሙ 19:18፤ 22:1, 5
1 ሳሙ. 27:11ሳሙ 18:29፤ 23:23
1 ሳሙ. 27:21ሳሙ 25:13፤ 30:9
1 ሳሙ. 27:21ሳሙ 21:10, 14፤ 27:12
1 ሳሙ. 27:31ሳሙ 25:43
1 ሳሙ. 27:31ሳሙ 25:39, 42
1 ሳሙ. 27:41ሳሙ 23:14፤ 26:25
1 ሳሙ. 27:6ኢያሱ 19:1, 5፤ 1ሳሙ 30:1፤ 2ሳሙ 1:1፤ 1ዜና 12:1, 20
1 ሳሙ. 27:71ሳሙ 29:3
1 ሳሙ. 27:8ኢያሱ 13:1, 2
1 ሳሙ. 27:8ዘፍ 36:12፤ ዘፀ 17:8, 14፤ ዘኁ 13:29፤ 1ሳሙ 15:2፤ 2ሳሙ 1:1
1 ሳሙ. 27:8ዘፍ 25:17, 18፤ ዘፀ 15:22፤ 1ሳሙ 15:7
1 ሳሙ. 27:9ዘዳ 25:19፤ 1ሳሙ 15:3
1 ሳሙ. 27:10ኢያሱ 15:1, 2
1 ሳሙ. 27:101ዜና 2:9
1 ሳሙ. 27:10ዘኁ 24:21፤ 1ሳሙ 15:6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ሳሙኤል 27:1-12

አንደኛ ሳሙኤል

27 ሆኖም ዳዊት በልቡ እንዲህ አለ፦ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ መጥፋቴ አይቀርም። የሚያዋጣኝ ወደ ፍልስጤማውያን ምድር መሸሽ ነው፤+ ሳኦልም ተስፋ ቆርጦ በእስራኤል ግዛት ሁሉ እኔን መፈለጉን ያቆማል፤+ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ።” 2 በመሆኑም ዳዊት አብረውት ከነበሩት 600 ሰዎች+ ጋር ተነስቶ የጌት ንጉሥ ወደሆነው ወደ ማኦክ ልጅ ወደ አንኩስ+ ተሻገረ። 3 ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰባቸው ጌት ውስጥ አንኩስ ዘንድ ተቀመጡ። ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ማለትም ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪኖዓም+ እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢጋኤል+ ጋር ነበር። 4 ሳኦልም ዳዊት ወደ ጌት መሸሹ ሲነገረው እሱን መፈለጉን ተወ።+

5 ከዚያም ዳዊት አንኩስን “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ በገጠር ካሉ ከተሞች በአንዱ እንድኖር ቦታ እንዲሰጡኝ አድርግ። አገልጋይህ ለምን በንጉሥ ከተማ ከአንተ ጋር ይኖራል?” አለው። 6 በመሆኑም አንኩስ በዚያ ቀን ጺቅላግን+ ሰጠው። ጺቅላግ እስካሁንም ድረስ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ የሆነችው በዚህ ምክንያት ነው።

7 ዳዊት በፍልስጤማውያን ገጠራማ አካባቢ የኖረበት ጊዜ* አንድ ዓመት ከአራት ወር ነበር።+ 8 ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር በመሆን ገሹራውያንን፣+ ጊዝራውያንን እና አማሌቃውያንን+ ለመውረር ይወጣ ነበር፤ ምክንያቱም እነዚህ ሕዝቦች ከቴላም አንስቶ እስከ ሹር+ እና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ ነበር። 9 ዳዊት በምድሪቱ ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ጊዜ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር፤+ ሆኖም መንጎችን፣ ከብቶችን፣ አህዮችን፣ ግመሎችንና ልብሶችን ወስዶ ወደ አንኩስ ይመለስ ነበር። 10 አንኩስም “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ይለው ነበር። ዳዊትም “በይሁዳ ደቡባዊ ክፍል*+ ላይ ዘምተን ነበር” ወይም “በየራህምኤላውያን+ ምድር ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር” አሊያም “በቄናውያን+ ምድር ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር” በማለት ይመልስለት ነበር። 11 ዳዊት “‘እሱ እንዲህ አደረገ’ በማለት ስለ እኛ ሊነግሯቸው ይችላሉ” ብሎ ስላሰበ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስተርፎ ወደ ጌት አያመጣም ነበር። (ዳዊት በፍልስጤም ገጠራማ አካባቢ በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ የማድረግ ልማድ ነበረው።) 12 ስለዚህ አንኩስ ‘በእርግጥም ይህ ሰው በገዛ ሕዝቦቹ በእስራኤላውያን ዘንድ እንደ ጥንብ ተቆጥሯል፤ ስለሆነም ዕድሜ ልኩን አገልጋዬ ይሆናል’ ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ