የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 15
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ይሖዋ ፍርዱን አይለውጥም (1-9)

      • የኤርምያስ ስሞታ (10)

      • ይሖዋ የሰጠው መልስ (11-14)

      • ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (15-18)

        • የአምላክን ቃል መብላት የሚያስገኘው ደስታ (16)

      • ይሖዋ ኤርምያስን አበረታታው (19-21)

ኤርምያስ 15:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ ወደዚህ ሕዝብ አታዘነብልም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:11፤ 1ሳሙ 7:9፤ መዝ 99:6፤ 106:23

ኤርምያስ 15:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 5:2
  • +ሕዝ 12:11

ኤርምያስ 15:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “አራት ዓይነት ፍርድ” ማለትም ሊሆን ይችላል። ቃል በቃል “አራት ወገኖች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 14:21
  • +ዘዳ 28:26፤ ኤር 7:33

ኤርምያስ 15:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 21:11፤ 23:26፤ 24:3, 4
  • +ዘዳ 28:15, 25፤ ኤር 24:9፤ ሕዝ 23:46

ኤርምያስ 15:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ወደ ኋላ ማፈግፈግሽን ቀጥለሻል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

  • *

    ወይም “መጸጸት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:13
  • +ኢሳ 1:4
  • +ሶፎ 1:4

ኤርምያስ 15:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:15, 18፤ ኤር 9:21፤ ሕዝ 24:21
  • +ኤር 5:3

ኤርምያስ 15:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሷ ትንፋሽ አጥሯት።”

  • *

    “ኀፍረት ተከናንባለች፤ ተዋርዳለችም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 44:27፤ ሕዝ 5:12

ኤርምያስ 15:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 20:14

ኤርምያስ 15:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 20:5

ኤርምያስ 15:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:38፤ ኤር 16:13
  • +ዘዳ 32:22፤ ኢሳ 42:24, 25፤ ኤር 17:4

ኤርምያስ 15:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አትውሰደኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 11:20፤ 12:3፤ 17:18፤ 37:15
  • +መዝ 69:7

ኤርምያስ 15:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 3:1-3፤ ራእይ 10:9, 10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 47

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    5/2017፣ ገጽ 20

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2011፣ ገጽ 30

    3/15/2007፣ ገጽ 10

ኤርምያስ 15:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በውግዘት መልእክት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 1:1
  • +ኤር 20:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 10

    5/1/2004፣ ገጽ 12

ኤርምያስ 15:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 9

    3/1/1998፣ ገጽ 28

ኤርምያስ 15:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የእኔ ቃል አቀባይ።”

ኤርምያስ 15:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አያሸንፉህም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:18፤ ሕዝ 3:9
  • +ኤር 20:11

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 15:1ዘፀ 32:11፤ 1ሳሙ 7:9፤ መዝ 99:6፤ 106:23
ኤር. 15:2ሕዝ 5:2
ኤር. 15:2ሕዝ 12:11
ኤር. 15:3ሕዝ 14:21
ኤር. 15:3ዘዳ 28:26፤ ኤር 7:33
ኤር. 15:42ነገ 21:11፤ 23:26፤ 24:3, 4
ኤር. 15:4ዘዳ 28:15, 25፤ ኤር 24:9፤ ሕዝ 23:46
ኤር. 15:6ኤር 2:13
ኤር. 15:6ኢሳ 1:4
ኤር. 15:6ሶፎ 1:4
ኤር. 15:7ዘዳ 28:15, 18፤ ኤር 9:21፤ ሕዝ 24:21
ኤር. 15:7ኤር 5:3
ኤር. 15:9ኤር 44:27፤ ሕዝ 5:12
ኤር. 15:10ኤር 20:14
ኤር. 15:13ኤር 20:5
ኤር. 15:14ዘሌ 26:38፤ ኤር 16:13
ኤር. 15:14ዘዳ 32:22፤ ኢሳ 42:24, 25፤ ኤር 17:4
ኤር. 15:15ኤር 11:20፤ 12:3፤ 17:18፤ 37:15
ኤር. 15:15መዝ 69:7
ኤር. 15:16ሕዝ 3:1-3፤ ራእይ 10:9, 10
ኤር. 15:17መዝ 1:1
ኤር. 15:17ኤር 20:8
ኤር. 15:20ኤር 1:18፤ ሕዝ 3:9
ኤር. 15:20ኤር 20:11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 15:1-21

ኤርምያስ

15 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙ እንኳ+ ለዚህ ሕዝብ አልራራም።* ከፊቴ አስወጣቸው። ይሂዱ። 2 እነሱም ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ በመቅሰፍት እንዲሞት ይሂድ፤

ሰይፍ የሚገባው ሁሉ በሰይፍ ይሙት፤+

ረሃብ የሚገባው ሁሉ በረሃብ ይሙት፤

በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ደግሞ ተማርኮ ይወሰድ!”’+

3 “‘እኔም አራት ዓይነት ጥፋት* አዝባቸዋለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱም፦ ለመግደል ሰይፍ፣ ጎትቶ ለመውሰድ ውሾች እንዲሁም ለመሰልቀጥና ለማጥፋት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ናቸው።+ 4 የይሁዳ ንጉሥ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ከፈጸመው ድርጊት የተነሳ+ ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።+

 5 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ማን ይራራልሻል?

ማንስ ያዝንልሻል?

ደህንነትሽንስ ማን ጎራ ብሎ ይጠይቃል?’

 6 ‘ትተሽኛል’ ይላል ይሖዋ።+

‘አሁንም ጀርባሽን ሰጥተሽኛል።*+

ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጠፋሻለሁ።+

ለአንቺ አዘኔታ ማሳየት* ታክቶኛል።

 7 በምድሪቱ በሮች፣ በመንሽ እበትናቸዋለሁ።

የወላድ መሃን አደርጋቸዋለሁ።+

ሕዝቤን አጠፋዋለሁ፤

ከመንገዱ ለመመለስ አሻፈረኝ ብሏልና።+

 8 መበለቶቻቸው በፊቴ ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይበዛሉ።

በእነሱ ይኸውም በእናቶችና በወጣት ወንዶች ላይ በቀትር አጥፊ አመጣለሁ።

ከባድ ጭንቀትና ሽብር በድንገት አመጣባቸዋለሁ።

 9 ሰባት ልጆች የወለደችው ሴት ተዝለፍልፋለች፤

ትንፋሽ አጥሯት* ታጣጥራለች።

ገና ቀን ሳለ ፀሐይዋ ጠልቃለች፤

ይህም ኀፍረትና ውርደት አስከትሎባታል።’*

‘ከእነሱ መካከል የተረፉትንም ጥቂት ሰዎች

በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።”+

10 እናቴ ሆይ፣ ወዮልኝ!

በምድሪቱ ሁሉ ላይ የጠብና የጭቅጭቅ መንስኤ የሆንኩትን እኔን ወልደሻልና።+

እኔ ለማንም አላበደርኩም፤ ከማንም አልተበደርኩም፤

ይሁንና ሁሉም ይረግሙኛል።

11 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “እኔ በእርግጥ ለአንተ መልካም ነገር አደርግልሃለሁ፤

በጥፋትና በጭንቀት ጊዜ

በአንተና በጠላት መካከል ጣልቃ ገብቼ እረዳሃለሁ።

12 ሰው ብረትን ይኸውም ከሰሜን የመጣን ብረትና

መዳብን መሰባበር ይችላል?

13 በመላው ክልልህ ከፈጸምከው ኃጢአት ሁሉ የተነሳ

ንብረትህንና ውድ ሀብትህን፣ ያለዋጋ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።+

14 እነዚህን ነገሮች ጠላቶችህ ወደማታውቀው አገር እንዲወስዷቸው

አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+

ቁጣዬ እሳት አስነስቷልና፤

በእናንተም ላይ እየነደደ ነው።”+

15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ታውቃለህ፤

አስበኝ፤ ትኩረትህንም ወደ እኔ አዙር።

አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ።+

ቁጣህን በማዘግየት እንድጠፋ አታድርግ።*

ይህን ነቀፋ የተሸከምኩት ለአንተ ስል እንደሆነ እወቅ።+

16 ቃልህ ተገኝቷል፤ እኔም በልቼዋለሁ፤+

የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ በስምህ ተጠርቻለሁና፣

ቃልህ ሐሴት፣ ለልቤም ደስታ ሆነልኝ።

17 ፈንጠዝያ ከሚወዱ ሰዎች ጋር አልተቀመጥኩም፤ ከእነሱም ጋር ሐሴት አላደረግኩም።+

እጅህ በእኔ ላይ ስለሆነ ብቻዬን እቀመጣለሁ፤

በቁጣ* ሞልተኸኛልና።+

18 ሕመሜ ሥር የሰደደው፣ ቁስሌም የማይፈወስ የሆነው ለምንድን ነው?

ጨርሶ አልድን ብሏል።

እምነት ሊጣልበት እንደማይችል

የሚያታልል የውኃ ምንጭ ትሆንብኛለህ?

19 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ብትመለስ፣ እኔም ወደ ቀድሞው ሁኔታህ እመልስሃለሁ፤

በፊቴም ትቆማለህ።

ውድ የሆነውን ነገር ከማይረባው ነገር ብትለይ፣

እንደ አፌ* ትሆናለህ።

እነሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ

አንተ ወደ እነሱ አትመለስም።”

20 “ለዚህ ሕዝብ ጠንካራ የመዳብ ቅጥር አደርግሃለሁ።+

እነሱ በእርግጥ ይዋጉሃል፤

ሆኖም በአንተ ላይ አያይሉም፤*+

እኔ አንተን ለማዳንና ለመታደግ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ።

21 “ከክፉዎች እጅ እታደግሃለሁ፤

ከጨካኞችም መዳፍ እቤዥሃለሁ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ