መዝሙር
መዝሙር። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት።
48 ይሖዋ ታላቅ ነው፤
በአምላካችን ከተማ፣ በቅዱስ ተራራው እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።
3 አምላክ በማይደፈሩ ማማዎቿ ውስጥ
አስተማማኝ መጠጊያ መሆኑን አስመሥክሯል።+
4 እነሆ፣ ነገሥታት ተሰብስበዋልና፤*
አንድ ላይ ሆነው ገሰገሱ።
5 ከተማዋን ባዩአት ጊዜ ተገረሙ።
ደንግጠውም ፈረጠጡ።
6 በዚያም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤
እንደምትወልድ ሴት ጭንቅ ያዛቸው።
7 የተርሴስን መርከቦች በምሥራቅ ነፋስ ሰባበርክ።
8 የሰማነውን ነገር፣ በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ከተማ
ይኸውም በአምላካችን ከተማ አሁን በገዛ ዓይናችን አይተናል።
አምላክ ለዘላለም ያጸናታል።+ (ሴላ)
9 አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን
ስለ ታማኝ ፍቅርህ እናሰላስላለን።+
10 አምላክ ሆይ፣ እንደ ስምህ ሁሉ ውዳሴህም
እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል።+
ቀኝ እጅህ በጽድቅ ተሞልቷል።+
13 የመከላከያ ግንቦቿን*+ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።
ለመጪዎቹ ትውልዶች መናገር ትችሉ ዘንድ፣
የማይደፈሩ ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ።
14 ይህ አምላክ፣ ለዘላለም አምላካችን ነውና።+