ምሳሌ
1 የእስራኤል ንጉሥ፣+ የዳዊት ልጅ+ የሰለሞን ምሳሌዎች፦+
ጥበብ ያዘሉ አባባሎችን ለመረዳት፣
ለወጣቶች እውቀትንና የማመዛዘን ችሎታን ለመስጠት።+
5 ጥበበኛ ሰው ያዳምጣል፤ ደግሞም ተጨማሪ ትምህርት ይቀስማል፤+
ማስተዋል ያለው ሰውም ጥበብ ያለበትን መመሪያ ይቀበላል፤+
6 ይህም ምሳሌንና ስውር የሆነ አባባልን
እንዲሁም የጥበበኞችን ቃላትና የሚናገሩትን እንቆቅልሽ ይረዳ ዘንድ ነው።+
ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው።+
10 ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች ሊያግባቡህ ቢሞክሩ እሺ አትበላቸው።+
11 እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ና አብረን እንሂድ።
ደም ለማፍሰስ እናድባ።
ንጹሐን ሰዎችን ያለምክንያት ለማጥቃት እናደፍጣለን።
13 ውድ ሀብታቸውን ሁሉ እንውሰድባቸው፤
ቤቶቻችንን በዘረፍናቸው ነገሮች እንሞላለን።
15 ልጄ ሆይ፣ አትከተላቸው።
17 ወፎች ዓይናቸው እያየ እነሱን ለማጥመድ መረብ መዘርጋት ከንቱ ነው።
በአደባባይ ላይ ያለማቋረጥ ድምፅዋን ታሰማለች።+
21 ሰው በሚበዛባቸው ጎዳናዎች ማዕዘን* ላይ ሆና ትጣራለች።
በከተማው መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ ትላለች፦+
22 “እናንተ አላዋቂዎች እስከ መቼ አላዋቂነትን ትወዳላችሁ?
እናንተ ፌዘኞች እስከ መቼ በሌሎች ላይ በማፌዝ ትደሰታላችሁ?
እናንተ ሞኞች እስከ መቼ እውቀትን ትጠላላችሁ?+
እንዲህ ብታደርጉ መንፈሴን አፈስላችኋለሁ፤
ቃሌን አሳውቃችኋለሁ።+
24 በተጣራሁ ጊዜ በእንቢተኝነታችሁ ጸንታችኋል፤
እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ትኩረት አልሰጠም፤+
25 ምክሬን ሁሉ ችላ ብላችኋል፤
ወቀሳዬንም አልተቀበላችሁም፤
26 እኔም ጥፋት ሲደርስባችሁ እስቃለሁ፤
የፈራችሁት ነገር ሲደርስ አላግጥባችኋለሁ፤+
27 የፈራችሁት ነገር እንደ ማዕበል ሲደርስባችሁ፣
ጥፋታችሁም እንደ አውሎ ነፋስ ከተፍ ሲልባችሁ፣
ጭንቀትና መከራ ሲመጣባችሁ አፌዝባችኋለሁ።
28 በዚያን ጊዜ ደጋግመው ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤
አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ሆኖም አያገኙኝም፤+
29 ምክንያቱም እውቀትን ጠልተዋል፤+
ይሖዋን መፍራትንም አልወደዱም።+
30 ምክሬን አልተቀበሉም፤
ወቀሳዬን ሁሉ አቃለዋል።
32 ተሞክሮ የሌላቸውን ሰዎች ጋጠወጥነታቸው ይገድላቸዋልና፤
ሞኞችን ደግሞ ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል።
2 ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበልና
ትእዛዛቴን እንደ ውድ ሀብት ብታስቀምጥ፣+
2 ይህን ለማድረግ ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣+
ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ልብህን ብታዘነብል፣+
ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ድምፅህን ብታሰማ፣+
እንዲሁም እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣+
5 ያን ጊዜ ይሖዋን መፍራት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ፤+
ደግሞም ስለ አምላክ እውቀት ትቀስማለህ።+
8 የፍትሕን ጎዳና ይከታተላል፤
የታማኞቹንም መንገድ ይጠብቃል።+
11 የማመዛዘን ችሎታ ምንጊዜም ይጠብቅሃል፤+
ጥልቅ ግንዛቤም ይጋርድሃል፤
12 ይህም አንተን ከክፉ መንገድ ለማዳን
እንዲሁም ጠማማ ነገር ከሚናገር ሰው፣+
13 በጨለማ መንገድ ለመጓዝ
ቀናውን ጎዳና ከሚተዉ፣+
14 መጥፎ ድርጊት በመፈጸም ሐሴት ከሚያደርጉ፣
ጠማማ በሆኑ ክፉ ነገሮች ከሚደሰቱ፣
15 መንገዳቸው ጠማማ ከሆነና
አካሄዳቸው በተንኮል ከተሞላ ሰዎች አንተን ለመታደግ ነው።
ባለጌ* ሴት ከምትናገረው የሚያባብል* ቃል ያድንሃል፤+
17 ይህች ሴት በወጣትነቷ የነበራትን የቅርብ ወዳጇን*+ የምትተው
እንዲሁም ከአምላኳ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን የምትረሳ ናት፤
18 ቤቷ ሰውን ይዞ ወደ ሞት ይወርዳልና፤
ይሖዋን ፍራ፤ ከክፉም ራቅ።
11 ልጄ ሆይ፣ የይሖዋን ተግሣጽ ለመቀበል እንቢተኛ አትሁን፤+
ወቀሳውም አያስመርርህ፤+
12 አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚወቅስ ሁሉ
ይሖዋም የሚወዳቸውን ይወቅሳልና።+
16 በቀኟ ረጅም ዕድሜ አለ፤
በግራዋም ሀብትና ክብር ይገኛል።
17 መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤
ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም የሰፈነበት ነው።+
18 ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፤
አጥብቀው የሚይዟትም ደስተኞች ይባላሉ።+
በማስተዋል ሰማያትን አጸና።+
20 በእውቀቱ ጥልቅ ውኃዎች ተከፈሉ፤
ደመና ያዘሉ ሰማያትም ጠል አንጠባጠቡ።+
21 ልጄ ሆይ፣ እነዚህ ባሕርያት ከእይታህ አይራቁ።*
28 ለባልንጀራህ አሁኑኑ መስጠት እየቻልክ
“ሂድና በኋላ ተመልሰህ ና! ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው።
29 ከአንተ ጋር ተማምኖ እየኖረ ሳለ
ባልንጀራህን ለመጉዳት አታሲር።+
30 መጥፎ ነገር ካላደረገብህ
ከሰው ጋር ያለምክንያት አትጣላ።+
35 ጥበበኞች ክብርን ይወርሳሉ፤
ሞኞች ግን ለውርደት የሚዳርግን ነገር ከፍ አድርገው ይመለከታሉ።+
4 አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፦ “ልብህ ቃሌን አጥብቆ ይያዝ።+
ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ።+
የምናገረውን ነገር አትርሳ፤ ከእሱም ፈቀቅ አትበል።
6 ጥበብን አትተዋት፤ እሷም ትጠብቅሃለች።
ውደዳት፤ እሷም ትከልልሃለች።
8 ለጥበብ የላቀ ዋጋ ስጥ፤ እሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች።+
ብታቅፋት ታከብርሃለች።+
9 በራስህ ላይ የሚያምር የአበባ ጉንጉን ትደፋልሃለች፤
በውበት አክሊልም ታስጌጥሃለች።”
12 በምትጓዝበት ጊዜ እርምጃህ አይስተጓጎልም፤
ብትሮጥም አትሰናከልም።
ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።+
16 እነሱ ክፋት ካልሠሩ አይተኙምና።
ሰውን ለውድቀት ካልዳረጉ እንቅልፍ በዓይናቸው አይዞርም።
17 የክፋት ምግብ ይበላሉ፤
የዓመፅም ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
19 የክፉዎች መንገድ እንደ ጨለማ ነው፤
ምን እንደሚያሰናክላቸው አያውቁም።
20 ልጄ ሆይ፣ ቃሌን በትኩረት ተከታተል፤
ንግግሬን በጥሞና አዳምጥ።*
እግርህን ከክፉ ነገር መልስ።
5 ልጄ ሆይ፣ ጥበቤን ልብ በል።
5 እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ።
እርምጃዎቿ በቀጥታ ወደ መቃብር* ይመራሉ።
6 ስለ ሕይወት መንገድ ግድ የላትም።
በጎዳናዎቿ ላይ ትባዝናለች፤ ወዴት እንደሚወስዱም አታውቅም።
7 እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤
ከምናገረውም ቃል አትራቁ።
8 ከእሷ ራቅ፤
ወደ ቤቷም ደጃፍ አትቅረብ፤+
9 ይህም ክብርህን ለሌሎች አሳልፈህ እንዳትሰጥ ነው፤+
ቀሪ የሕይወት ዘመንህም በመከራ የተሞላ እንዳይሆን ነው፤+
10 ደግሞም እንግዳ የሆኑ ሰዎች ጥሪትህን* እንዳያሟጥጡ፣+
የለፋህበትንም ነገር የባዕድ አገር ሰው እንዳይወርሰው ነው።
ልቤስ ምነው ወቀሳን ናቀ!
13 የአስተማሪዎቼን ቃል አላዳመጥኩም፤
መምህሮቼንም በጥሞና አልሰማሁም።
17 ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤
ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ።+
ጡቶቿ ምንጊዜም ያርኩህ።*
ፍቅሯ ምንጊዜም ይማርክህ።+
22 ክፉ ሰው የገዛ ጥፋቱ ወጥመድ ይሆንበታል፤
ኃጢአቱም እንደ ገመድ ተብትቦ ይይዘዋል።+
23 ተግሣጽ ከማጣቱ የተነሳ ይሞታል፤
በጣም ሞኝ ከመሆኑም የተነሳ መንገድ ይስታል።
ሂድና ባልንጀራህን በትሕትና አጥብቀህ ለምነው።+
4 ይህን ሳታደርግ አትተኛ፤
በዓይንህም እንቅልፍ አይዙር።
5 እንደ ሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣
እንደ ወፍም ከወፍ አዳኝ እጅ ራስህን አድን።
9 አንተ ሰነፍ፣ የምትጋደመው እስከ መቼ ነው?
ከእንቅልፍህ የምትነሳውስ መቼ ነው?
10 ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣
እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣+
11 ድህነት እንደ ወንበዴ፣
እጦትም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።+
17 ትዕቢተኛ ዓይን፣+ ውሸታም ምላስ፣+ ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣+
18 ክፉ ሐሳብ የሚያውጠነጥን ልብና+ ወደ ክፋት በፍጥነት የሚሮጡ እግሮች፣
19 ባወራ ቁጥር ውሸት የሚናገር ሐሰተኛ ምሥክርና+
በወንድማማቾች መካከል ጠብ የሚዘራ ሰው።+
21 ምንጊዜም በልብህ አኑራቸው፤
በአንገትህም ዙሪያ እሰራቸው።
27 በጉያው እሳት ታቅፎ ልብሱ የማይቃጠልበት ሰው አለ?+
28 ወይስ በፍም ላይ ተራምዶ እግሮቹ የማይቃጠሉበት ሰው ይኖራል?
4 ጥበብን “እህቴ ነሽ” በላት፤
ማስተዋልንም “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፤
6 በቤቴ መስኮት በፍርግርጉ በኩል
አጮልቄ ወደ ታች ተመለከትኩ፤
ፈጽሞ ቤቷ አትቀመጥም።*
13 አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤
ያላንዳች ኀፍረትም እንዲህ አለችው፦
ዛሬ ስእለቴን ፈጽሜአለሁ።
15 አንተን ለማግኘት የወጣሁት ለዚህ ነው፤
አንተን ፍለጋ ወጣሁ፤ ደግሞም አገኘሁህ!
17 አልጋዬ ላይ ከርቤ፣ እሬትና* ቀረፋ አርከፍክፌአለሁ።+
20 በከረጢት ገንዘብ ይዟል፤
ደግሞም ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን ድረስ ወደ ቤት አይመለስም።”
በለሰለሰ አንደበቷ ታታልለዋለች።
22 ለእርድ እንደሚነዳ በሬ፣
ለቅጣትም በእግር ግንድ* እንደታሰረ ሞኝ ሰው በድንገት ይከተላታል፤+
23 ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ፣
በወጥመድ ለመያዝ እንደምትቸኩል ወፍ ተከትሏት ይሄዳል፤ ሕይወቱን* ሊያሳጣው እንደሚችል አላወቀም።+
24 እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤
የምናገረውንም ቃል በትኩረት ስሙ።
25 ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ።
8 ጥበብ እየተጣራች አይደለም?
ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እያሰማች አይደለም?+
6 የምናገረው ነገር በጣም አስፈላጊ ስለሆነ አዳምጡኝ፤
ከንፈሮቼ ትክክል የሆነውን ይናገራሉ፤
7 አንደበቴ በለሰለሰ ድምፅ እውነትን ይናገራልና፤
ከንፈሮቼም ክፋትን ይጸየፋሉ።
8 ከአፌ የሚወጡት ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው።
የተጣመመ ወይም የተወላገደ ነገር አይገኝባቸውም።
9 ጥልቅ ግንዛቤ ላለው፣ ሁሉም ቀና ናቸው፤
እውቀት ላላቸውም ትክክል ናቸው።
13 ይሖዋን መፍራት ማለት ክፉ ነገርን መጥላት ነው።+
ትዕቢትን፣ ኩራትን፣+ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።+
16 መኳንንት የሚገዙት በእኔ ነው፤
ታላላቅ ሰዎችም በጽድቅ የሚፈርዱት በእኔ ነው።
25 ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣
ከኮረብቶች በፊት ተወለድኩ፤
26 ምድርንም ሆነ ሜዳዎቹን እንዲሁም
የመጀመሪያዎቹን የአፈር ጓሎች ከመሥራቱ በፊት ተወለድኩ።
27 ሰማያትን ባዘጋጀ ጊዜ+ በዚያ ነበርኩ፤
በውኃዎች ላይ የአድማስን ምልክት* ባደረገ ጊዜ፣+
28 ደመናትን በላይ ባዘጋጀ* ጊዜ፣
የጥልቅ ውኃ ምንጮችን በመሠረተ ጊዜ፣
29 የባሕሩ ውኃ
ከትእዛዙ አልፎ እንዳይሄድ በደነገገ ጊዜ፣+
የምድርን መሠረቶች ባቆመ* ጊዜ፣
በየዕለቱ በእኔ የተነሳ ልዩ ደስታ ይሰማው ነበር፤+
እኔም በፊቱ ሁልጊዜ ሐሴት አደርግ ነበር፤+
31 እሱ በፈጠረው፣ ሰው በሚኖርበት ምድር ሐሴት አደረግኩ፤
በተለይ ደግሞ በሰው ልጆች እጅግ እደሰት ነበር።
32 እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤
አዎ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ደስተኞች ናቸው።
በበሬ መቃን አጠገብ ቆሞ በመጠባበቅ
የሚያዳምጠኝ ሰው ደስተኛ ነው፤
በይሖዋም ዘንድ ሞገስ ያገኛል።
9 እውነተኛ ጥበብ ቤቷን ሠራች፤
ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አዘጋጀች።
4 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።”
ማስተዋል* ለጎደለው እንዲህ ትላለች፦
5 “ኑ፣ ያዘጋጀሁትን ምግብ ብሉ፤
የደባለቅኩትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።
ጥበበኛን ሰው ውቀሰው፤ እሱም ይወድሃል።+
9 ጥበበኛን ሰው አስተምረው፤ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል።+
ጻድቅን ሰው አስተምረው፤ ተጨማሪ እውቀት ያገኛል።
12 ጥበበኛ ብትሆን፣ ጥበበኛነትህ የሚጠቅመው ራስህን ነው፤
ፌዘኛ ብትሆን ግን መዘዙን የምትቀበለው አንተው ነህ።
እሷ ጨርሶ ማመዛዘን አትችልም፤ ደግሞም አንዳች ነገር አታውቅም።
16 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።”
ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤+
ሞኝ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናል።
ድሆችን የሚያጠፋቸው ድህነታቸው ነው።+
31 የጻድቅ አፍ ጥበብን ያፈልቃል፤*
ጠማማ ምላስ ግን ትቆረጣለች።
32 የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ደስ የሚያሰኘው ነገር ምን እንደሆነ ያውቃሉ፤
የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነው።
19 ለጽድቅ ጽኑ አቋም ያለው ሰው ሕይወት የማግኘት ተስፋ አለው፤+
ክፋትን የሚያሳድድ ግን ለሞት መዳረጉ አይቀርም።
22 ማስተዋልን የምትንቅ ቆንጆ ሴት፣
በአሳማ አፍንጫ ላይ እንዳለ የወርቅ ቀለበት ናት።
23 የጻድቅ ምኞት መልካም ነገር ያስገኛል፤+
የክፉ ሰው ተስፋ ግን ወደ ቁጣ ይመራል።
26 እህል ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነውን ሕዝቡ ይረግመዋል፤
የሚሸጠውን ግን ይባርከዋል።
5 የጻድቃን ሐሳብ ፍትሐዊ ነው፤
የክፉዎች ምክር ግን አሳሳች ነው።
12 ክፉ ሰው፣ ሌሎች መጥፎ ሰዎች ባጠመዱት ነገር ይቀናል፤
የጻድቃን ሥር ግን ፍሬ ያፈራል።
22 ይሖዋ ውሸታም ከንፈሮችን ይጸየፋል፤+
በታማኝነት የሚመላለሱ ግን ደስ ያሰኙታል።
26 ጻድቅ የግጦሽ መሬቱን በሚገባ ይቃኛል፤
የክፉዎች መንገድ ግን እንዲባዝኑ ያደርጋቸዋል።
28 የጽድቅ ጎዳና ወደ ሕይወት ይመራል፤+
በጎዳናው ላይ ሞት የለም።
አፉን የሚከፍት ግን ይጠፋል።+
15 ጥልቅ ማስተዋል ሞገስ ያስገኛል፤
የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው።
3 በሞኝ ሰው አፍ የትዕቢት በትር አለ፤
የጥበበኞች ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።
4 ከብት በሌለበት ግርግሙ ንጹሕ ይሆናል፤
የበሬ ጉልበት ግን ብዙ ምርት ያስገኛል።
13 አንድ ሰው እየሳቀ እንኳ ልቡ ሊያዝን ይችላል፤
ደስታም በሐዘን ሊቋጭ ይችላል።
19 መጥፎ ሰዎች በጥሩ ሰዎች ፊት፣
ክፉዎችም በጻድቅ ደጃፍ ይሰግዳሉ።
22 ተንኮል የሚሸርቡ ሰዎች መንገድ ይስቱ የለም?
መልካም ነገር ለመሥራት የሚያስቡ ሰዎች ግን ታማኝ ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ።+
27 ይሖዋን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤
ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል።
11 መቃብርና* የጥፋት ቦታ* በይሖዋ ፊት ወለል ብለው ይታያሉ።+
የሰዎች ልብማ በፊቱ ምንኛ የተገለጠ ነው!+
ጥበበኞችን አያማክርም።+
እንዲህ ያለው ሰው ሳይቀጣ እንደማይቀር እርግጠኛ ሁን።
13 ነገሥታት የጽድቅ ንግግር ደስ ያሰኛቸዋል።
ሐቁን የሚናገር ሰው ይወዳሉ።+
16 ጥበብን ማግኘት ወርቅ ከማግኘት ምንኛ የተሻለ ነው!+
ማስተዋልን ማግኘትም ብር ከማግኘት ይመረጣል።+
17 ቅኖች ከክፋት ጎዳና ይርቃሉ።
22 ጥልቅ ማስተዋል ለባለቤቱ የሕይወት ምንጭ ነው፤
ሞኞች ግን በገዛ ሞኝነታቸው ይቀጣሉ።
29 ዓመፀኛ ሰው ባልንጀራውን ክፉ ነገር እንዲሠራ ያግባባዋል፤
ወደተሳሳተ መንገድም ይመራዋል።
30 በዓይኑ እየጠቀሰ ተንኮል ይሸርባል።
ከንፈሮቹን ነክሶ ሸር ይሠራል።
2 ጥልቅ ማስተዋል ያለው አገልጋይ አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤
ከወንድማማቾቹ እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።
4 ክፉ ሰው ጎጂ የሆነን ንግግር በትኩረት ያዳምጣል፤
አታላይ ሰውም ተንኮለኛ የሆነን አንደበት ያዳምጣል።+
ለገዢ* ደግሞ ሐሰተኛ ንግግር ጨርሶ አይሆነውም!+
11 ክፉ ሰው የሚሻው ዓመፅን ብቻ ነው፤
ሆኖም እሱን እንዲቀጣ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።+
12 የቂል ሥራ እየሠራ ካለ ሞኝ ሰው ጋር ከመገናኘት ይልቅ
ግልገሎቿን ካጣች ድብ ጋር መገናኘት ይሻላል።+
13 ማንኛውም ሰው ለመልካም ነገር ክፉ የሚመልስ ከሆነ
ክፉ ነገር ከቤቱ አይጠፋም።+
15 ክፉውን ነፃ የሚያደርግ፣ በጻድቁም ላይ የሚፈርድ፣+
ሁለቱም በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።
በሩን ወደ ላይ አስረዝሞ የሚሠራ ጥፋትን ይጋብዛል።+
21 የሞኝ ልጅ አባት ሐዘን ላይ ይወድቃል፤
የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ልጅ የወለደም ደስታ አይኖረውም።+
25 ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤
እናቱም እንድትመረር ያደርጋል።+
26 ጻድቁን መቅጣት* መልካም አይደለም።
የተከበሩ ሰዎችንም መግረፍ ትክክል አይደለም።
28 ሞኝ ሰው እንኳ ዝም ሲል እንደ ጥበበኛ ይቆጠራል፤
ከንፈሮቹንም የሚዘጋ ማስተዋል እንዳለው ተደርጎ ይታያል።
2 ሞኝ ሰው ማስተዋል አያስደስተውም፤
ይልቁንም በልቡ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል።+
3 ክፉ ሰው ሲመጣ ንቀትም ይመጣል፤
ከውርደትም ጋር ኀፍረት ይመጣል።+
4 ከሰው አፍ የሚወጣ ቃል ጥልቅ ውኃ ነው።+
የጥበብ ምንጭ የሚንዶለዶል ጅረት ነው።
16 ስጦታ ለሰጪው መንገዱን ይከፍትለታል፤+
በታላላቅ ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል።
18 ዕጣ መጣል ጭቅጭቅ እንዲያበቃ ያደርጋል፤+
ኃይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።
20 ሰው በአፉ ፍሬ ሆዱ ይሞላል፤+
ከንፈሩም በሚያስገኘው ምርት ይረካል።
23 ድሃ እየተለማመጠ ይናገራል፤
ሀብታም ግን በኃይለ ቃል ይመልሳል።
3 የሰውን መንገድ የሚያጣምምበት የገዛ ሞኝነቱ ነው፤
ልቡም በይሖዋ ላይ ይቆጣል።
4 ሀብት ብዙ ወዳጆችን ይስባል፤
ድሃን ግን ጓደኛው እንኳ ይተወዋል።+
6 ብዙዎች በተከበረ ሰው* ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ይጥራሉ፤
ስጦታ ከሚሰጥ ሰው ጋር ደግሞ ሁሉም ይወዳጃል።
እየተከታተለ ሊለማመጣቸው ይሞክራል፤ ምላሽ የሚሰጠው ግን የለም።
8 ማስተዋል* የሚያገኝ ሰው ሁሉ ራሱን* ይወዳል።+
ጥልቅ ግንዛቤን እንደ ውድ ሀብት አድርጎ የሚመለከት ሁሉ ይሳካለታል።*+
9 ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤
ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ይጠፋል።+
10 ሞኝ ሰው ተንደላቆ መኖር አይገባውም፤
አገልጋይ መኳንንትን ቢገዛማ ምንኛ የከፋ ነው!+
14 ቤትና ሀብት ከአባቶች ይወረሳል፤
ልባም ሚስት ግን የምትገኘው ከይሖዋ ነው።+
19 ግልፍተኛ ሰው ይቀጣል፤
ልታድነው ብትሞክር እንኳ በተደጋጋሚ እንዲህ ለማድረግ ትገደዳለህ።+
22 የሰው ተወዳጅ ባሕርይ ታማኝ ፍቅሩ ነው፤+
ውሸታም ከመሆን ድሃ መሆን ይሻላል።
24 ሰነፍ እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፤
ሆኖም ወደ አፉ እንኳ መመለስ ይሳነዋል።+
26 አባቱን የሚበድልና እናቱን የሚያባርር ልጅ
ኀፍረትና ውርደት ያመጣል።+
27 ልጄ ሆይ፣ ተግሣጽን መስማት ከተውክ
እውቀት ከሚገኝበት ቃል ትርቃለህ።
6 ብዙ ሰዎች ስለ ራሳቸው ታማኝ ፍቅር ያወራሉ፤
ይሁንና ታማኝ የሆነን ሰው ማን ሊያገኘው ይችላል?
ከእሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቹ ደስተኞች ናቸው።+
12 የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፣
ሁለቱንም የሠራው ይሖዋ ነው።+
13 እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድሃ ትሆናለህ።+
ዓይንህን ግለጥ፤ የተትረፈረፈ ምግብም ታገኛለህ።+
14 ዕቃ የሚገዛ ሰው “የማይረባ ነው፣ የማይረባ ነው!” ይላል፤
ከሄደ በኋላ ግን በራሱ ይኩራራል።+
17 ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ያስደስተዋል፤
በኋላ ግን አፉን ኮረት ይሞላዋል።+
20 አባቱንና እናቱን የሚረግም ሁሉ
ጨለማ ሲሆን መብራቱ ይጠፋበታል።+
21 በመጀመሪያ በስግብግብነት የተገኘ ውርስ፣
የኋላ ኋላ በረከት አይሆንም።+
23 አባይ ሚዛን* በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤
ለማጭበርበር የሚያገለግሉ መለኪያዎችንም መጠቀም ጥሩ አይደለም።
25 ሰው ቸኩሎ “የተቀደሰ ነው!”+ ቢልና
ከተሳለ በኋላ ስእለቱን መልሶ ማጤን ቢጀምር ወጥመድ ይሆንበታል።+
27 የሰው እስትንፋስ የይሖዋ መብራት ነው፤
ውስጣዊ ማንነቱን በሚገባ ይመረምራል።
21 የንጉሥ ልብ በይሖዋ እጅ እንዳለ ጅረት ነው።+
እሱ ደስ ወዳሰኘው አቅጣጫ ሁሉ ይመራዋል።+
3 መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅ
ትክክልና ፍትሐዊ የሆነ ነገር ማድረግ ይሖዋን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል።+
4 ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብ
የክፉዎች መብራት ናቸው፤ ደግሞም ኃጢአት ናቸው።+
7 ክፉዎች ፍትሕን ማስፈን ስለማይፈልጉ
የሚፈጽሙት ግፍ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።+
8 የበደለኛ ሰው መንገድ ጠማማ ነው፤
የንጹሕ ሰው ሥራ ግን ቀና ነው።+
12 ጻድቅ የሆነው አምላክ፣ የክፉውን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤
ክፉዎችንም ይጠፉ ዘንድ ይገለብጣቸዋል።+
15 ጻድቅ ፍትሐዊ ነገር ማድረግ ያስደስተዋል፤+
ክፉ ድርጊት ለሚፈጽሙ ግን አስከፊ ነገር ነው።
16 ከማስተዋል መንገድ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣
በሞት ከተረቱት ጋር ያርፋል።+
18 ክፉ ሰው ለጻድቅ ቤዛ ነው፤
ከዳተኛ የሆነ ሰውም በቅን ሰው ፋንታ ይወሰዳል።+
24 በእብሪት የመሰለውን የሚያደርግ ሰው
እብሪተኛና ጉረኛ ይባላል።+
25 ሰነፍ ሰው ምኞቱ ይገድለዋል፤
እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።+
26 ቀኑን ሙሉ በስግብግብነት ሲመኝ ይውላል፤
ጻድቅ ግን ምንም ሳይሰስት ይሰጣል።+
27 የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው።+
በክፉ ዓላማ ተነሳስቶ* ሲያቀርብማ ምንኛ የከፋ ይሆናል!
30 ይሖዋን የሚጻረር ጥበብ፣ ማስተዋልም ሆነ ምክር ከንቱ ነው።+
2 ሀብታምንና ድሃን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፦*
ሁለቱንም የፈጠረው ይሖዋ ነው።+
4 ትሕትናና ይሖዋን መፍራት
ሀብት፣ ክብርና ሕይወት ያስገኛል።+
12 የይሖዋ ዓይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፤
የከዳተኛን ቃል ግን ይሽራል።+
13 ሰነፍ “ውጭ አንበሳ አለ!
አደባባይ ላይ እገደላለሁ!” ይላል።+
ይሖዋ ያወገዘው ሰው እዚያ ውስጥ ይወድቃል።
19 በይሖዋ እንድትተማመን፣
ዛሬ እውቀት እሰጥሃለሁ።
20 ከዚህ ቀደም ምክርና
እውቀት የያዙ ሐሳቦች አልጻፍኩልህም?
21 ይህን ያደረግኩት ለላከህ ትክክለኛ ወሬ ይዘህ እንድትመለስ፣
እውነት የሆነውንና እምነት የሚጣልበትን ቃል ላስተምርህ አይደለም?
22 ድሃውን ድሃ ስለሆነ ብቻ አትዝረፈው፤+
ችግረኛውንም በከተማው በር ላይ ግፍ አትፈጽምበት፤+
23 ይሖዋ ራሱ ይሟገትላቸዋልና፤+
የሚያጭበረብሯቸውንም ሰዎች ሕይወት ያጠፋል።*
27 የምትከፍለው ካጣህ
የተኛህበት አልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል!
29 በሥራው የተካነን ሰው አይተሃል?
በነገሥታት ፊት ይቆማል፤+
ተራ በሆኑ ሰዎች ፊት አይቆምም።
3 የእሱ ጣፋጭ ምግብ አያስጎምጅህ፤
ምግቡ አታላይ ነውና።
ይህን ትተህ በማስተዋል ተመላለስ።*
“ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ የሚናገረው ግን ከልቡ አይደለም።*
8 የበላሃትን ቁራሽ ምግብ ታስመልሳለህ፤
የተናገርካቸው የምስጋና ቃላትም ከንቱ ይሆናሉ።
10 የጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ፤+
ደግሞም አባት የሌላቸውን ልጆች መሬት አትያዝ።
12 ልብህን ለተግሣጽ፣
ጆሮህንም ለእውቀት ቃል ስጥ።
በበትር ብትመታው አይሞትም።
17 ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤+
ከዚህ ይልቅ ቀኑን ሙሉ ይሖዋን በመፍራት ተመላለስ፤+
18 እንዲህ ብታደርግ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤+
ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።
19 ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ ጥበበኛም ሁን፤
ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ምራ።
24 የጻድቅ አባት ደስ ይለዋል፤
ጥበበኛ ልጅ የወለደ ሁሉ በልጁ ሐሴት ያደርጋል።
25 አባትህና እናትህ ሐሴት ያደርጋሉ፤
አንተን የወለደችም ደስ ይላታል።
26 ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፤
ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።+
28 እንደ ዘራፊ ታደባለች፤+
ታማኝ ያልሆኑ ወንዶችን ቁጥር ታበዛለች።
29 ዋይታ የማን ነው? ጭንቀት የማን ነው?
ጠብ የማን ነው? እሮሮ የማን ነው?
ያለምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን ቅላት* የማን ነው?
31 በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣
እየጣፈጠም ሲወርድ በወይን ጠጅ ቅላት ዓይንህ አይማረክ፤
32 በመጨረሻ እንደ እባብ ይናደፋልና፤
እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል።
34 በባሕር መካከል እንደተኛ፣
በመርከብ ምሰሶም ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ።
35 እንዲህ ትላለህ፦ “መቱኝ፤ ሆኖም አልተሰማኝም።*
ደበደቡኝ፤ ሆኖም አልታወቀኝም።
ተጨማሪ መጠጥ እጠጣ ዘንድ*
የምነቃው መቼ ነው?”+
5 ጥበበኛ ሰው ኃያል ነው፤+
ሰውም በእውቀት ኃይሉን ይጨምራል።
7 ለሞኝ ሰው እውነተኛ ጥበብ ሊገኝ የማይችል ነገር ነው፤+
በከተማው በር ላይ አንዳች የሚናገረው ነገር የለውም።
8 መጥፎ ነገር ለማድረግ የሚያሴር ሁሉ
ሴራ በመጠንሰስ የተካነ ተብሎ ይጠራል።+
11 ወደ ሞት እየተወሰዱ ያሉትን ታደግ፤
ለእርድ እየተውተረተሩ የሚሄዱትንም አስጥል።+
12 “እኛ ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም አናውቅም” ብትል፣
13 ልጄ ሆይ፣ መልካም ስለሆነ ማር ብላ፤
ከማር እንጀራ የሚገኝ ማር ጣፋጭ ጣዕም አለው።
14 በተመሳሳይም ጥበብ ለአንተ መልካም* እንደሆነ እወቅ።+
ጥበብን ብታገኝ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤
ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።+
15 በጻድቁ ቤት ላይ በክፋት አትሸምቅ፤
ማረፊያ ቦታውንም አታፍርስበት።
21 ልጄ ሆይ፣ ይሖዋንና ንጉሥን ፍራ።+
ሁለቱም* በእነሱ ላይ የሚያመጡትን ጥፋት ማን ያውቃል?+
23 እነዚህም አባባሎች የጥበበኞች ናቸው፦
በፍርድ ማዳላት ጥሩ አይደለም።+
24 ክፉውን “አንተ ጻድቅ ነህ”+ የሚለውን ሰው ሁሉ
ሕዝቦች ይረግሙታል፤ ብሔራትም ያወግዙታል።
26 ሰዎች በሐቀኝነት መልስ የሚሰጥን ሰው ከንፈር ይስማሉ።*+
28 ምንም መሠረት ሳይኖርህ በባልንጀራህ ላይ አትመሥክር።+
በከንፈሮችህ ሌሎችን አታታል።+
32 ይህን ተመልክቼ በጥሞና አሰብኩበት፤
ካየሁትም ነገር ይህን ትምህርት አገኘሁ፦*
33 ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣
እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣
34 ድህነት እንደ ወንበዴ፣
ችጋርም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።+
25 እነዚህም የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ+ ሰዎች የጻፏቸው* የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፦+
3 ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉ
የንጉሥም ልብ አይመረመርም።
4 የብርን ቆሻሻ አስወግድ፤
ሙሉ በሙሉም የጠራ ይሆናል።+
5 ክፉን ሰው ከንጉሥ ፊት አስወግድ፤
ዙፋኑም በጽድቅ ይጸናል።+
እሱ ራሱ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና።+
8 ክስ ለመመሥረት አትቸኩል፤
የኋላ ኋላ ባልንጀራህ ቢያዋርድህ ምን ይውጥሃል?+
9 ከባልንጀራህ ጋር ስለ ራስህ ጉዳይ ተሟገት፤+
ሆኖም በሚስጥር የተነገረህን ጉዳይ* አትግለጥ፤+
10 አለዚያ የሚሰማህ ሰው ያዋርድሃል፤
ያናፈስከውንም መጥፎ ወሬ* መመለስ አትችልም።
16 ማር ካገኘህ የሚበቃህን ያህል ብቻ ብላ፤
ከልክ በላይ ከበላህ ሊያስመልስህ ይችላልና።+
17 እንዳይሰለችህና እንዳይጠላህ
ወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ።
18 በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሠክር
እንደ ቆመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ሹል ፍላጻ ነው።+
19 በችግር ወቅት እምነት በማይጣልበት* ሰው መተማመን፣
እንደተሰበረ ጥርስና እንደሰለለ እግር ነው።
23 የሰሜን ነፋስ ኃይለኛ ዝናብ ያመጣል፤
ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቆጣል።+
26 ለክፉ ሰው የሚንበረከክ* ጻድቅ፣
እንደጨቀየ ምንጭና እንደተበከለ የውኃ ጉድጓድ ነው።
26 በረዶ በበጋ፣ ዝናብም በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ
ክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም።+
2 ወፍ ቱር የምትልበት፣ ወንጭፊትም የምትበርበት ምክንያት እንዳላት ሁሉ
እርግማንም ያለበቂ ምክንያት አይመጣም።*
4 ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ አትመልስለት፤
አለዚያ አንተም የእሱ ቢጤ ትሆናለህ።*
5 ጥበበኛ የሆነ እንዳይመስለው
ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት።+
6 አንድን ጉዳይ ለሞኝ በአደራ የሚሰጥ
እግሩን ከሚያሽመደምድና ራሱን ከሚጎዳ* ሰው ተለይቶ አይታይም።
8 ለሞኝ ክብር መስጠት፣
በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።+
9 በሞኞች አፍ የሚነገር ምሳሌ
በሰካራም እጅ እንዳለ እሾህ ነው።
10 ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር፣
በነሲብ ያገኘውን ሁሉ* እንደሚያቆስል ቀስተኛ ነው።
11 ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ፣
ሞኝ ሰውም ሞኝነቱን ይደጋግማል።+
12 ጥበበኛ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው አይተህ ታውቃለህ?+
ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው።
13 ሰነፍ “በመንገድ ላይ ደቦል አንበሳ፣
በአደባባይም አንበሳ አለ!” ይላል።+
16 ሰነፍ ሰው በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ሰባት ሰዎች ይበልጥ
ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል።
18 የሚንበለበሉ ተወንጫፊ መሣሪያዎችን፣ ፍላጻዎችንና ሞትን* እንደሚወረውር እብድ፣
19 ባልንጀራውን አታሎ ሲያበቃ “ቀልዴን እኮ ነው!” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው።+
20 እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤
ስም አጥፊ ከሌለ ደግሞ ጭቅጭቅ ይበርዳል።+
21 ከሰል ፍምን፣ እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል
ጨቅጫቃ ሰውም ጠብ ይጭራል።+
24 ሌሎችን የሚጠላ ሰው ጥላቻውን በከንፈሩ ይደብቃል፤
በውስጡ ግን ተንኮል ይቋጥራል።
25 አነጋገሩን ቢያሳምርም እንኳ አትመነው፤
በልቡ ውስጥ ሰባት አስጸያፊ ነገሮች አሉና።*
26 ጥላቻው በተንኮል ቢሸፈንም
ክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል።
27 ጉድጓድ የሚቆፍር እሱ ራሱ እዚያ ውስጥ ይወድቃል፤
ድንጋይ የሚያንከባልልም ወደ እሱ ተመልሶ ይመጣበታል።+
28 ውሸታም ምላስ የጎዳቻቸውን ሰዎች ትጠላለች፤
የሚሸነግል አንደበትም ጥፋት ያስከትላል።+
3 ድንጋይ ከባድ ነው፤ አሸዋም ሸክም ነው፤
የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።+
4 ንዴት ጨካኝ ነው፤ ቁጣም ጎርፍ ነው፤
ይሁንና ቅናትን ማን ሊቋቋም ይችላል?+
5 ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ወቀሳ ይሻላል።+
8 ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን* ሰው
ከጎጆዋ ወጥታ እንደምትባዝን ወፍ ነው።
14 ሰው በማለዳ ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን ቢባርክ
እንደ እርግማን ይቆጠርበታል።
15 ጨቅጫቃ* ሚስት በዝናባማ ቀን ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት።+
16 እሷን መግታት የሚችል ሁሉ ነፋስን መግታት፣
ዘይትንም በቀኝ እጁ መጨበጥ ይችላል።
19 ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያንጸባርቅ ሁሉ፣
የሰውም ልብ የሌላ ሰው ልብ ነጸብራቅ ነው።
22 ሞኝን ሙቀጫ ውስጥ ከተህ በዘነዘና ብትወቅጠውና
እንደ እህል ብታደቀው እንኳ
ሞኝነቱ ከእሱ አይወገድም።
23 የመንጋህን ሁኔታ በሚገባ እወቅ።
25 ሣሩ በቦታው የለም፤ አዲስ ሣርም በቅሏል፤
በተራሮች ላይ ያለው ተክልም ተሰብስቧል።
26 የበግ ጠቦቶች ለልብስ፣
አውራ ፍየሎችም ለመሬት መግዣ ይሆኑልሃል።
27 ደግሞም አንተንና ቤተሰብህን ለመመገብ፣
ልጃገረዶችህንም በሕይወት ለማኖር የሚያስችል በቂ የፍየል ወተት ይኖርሃል።
2 በአንድ አገር ውስጥ ሕግ ተላላፊነት* ሲነግሥ ብዙ ገዢዎች ይፈራረቁበታል፤+
ይሁንና ጥልቅ ግንዛቤና እውቀት ያለው ሰው በሚያበረክተው እርዳታ ገዢ* ለረጅም ዘመን ይቆያል።+
3 ችግረኞችን የሚበዘብዝ ድሃ፣+
እህሉን ሁሉ ጠራርጎ እንደሚወስድ ዝናብ ነው።
4 ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያወድሳሉ፤
ሕግን የሚጠብቁ ሰዎች ግን በእነሱ ላይ ይቆጣሉ።+
7 አስተዋይ ልጅ ሕግን ይጠብቃል፤
ከሆዳሞች ጋር የሚወዳጅ ግን አባቱን ያዋርዳል።+
12 ጻድቃን ድል ሲያደርጉ ታላቅ ክብር ይሆናል፤
ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሰዎች ይሸሸጋሉ።+
15 ምስኪን በሆነ ሕዝብ ላይ የተሾመ ክፉ ገዢ፣
እንደሚያገሳ አንበሳና ተንደርድሮ እንደሚመጣ ድብ ነው።+
17 የሰው ሕይወት በማጥፋቱ የደም* ባለ ዕዳ የሆነ ሰው መቃብር* እስኪገባ ድረስ ሲሸሽ ይኖራል።+
እንዲህ ያለውን ሰው ማንም አይርዳው።
19 መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤
ከንቱ የሆኑ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን እጅግ ይደኸያል።+
21 አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤+
ሆኖም ሰው ለቁራሽ ዳቦ ብሎ ስህተት ሊፈጽም ይችላል።
24 አባቱንና እናቱን እየዘረፈ “ምንም ጥፋት የለበትም” የሚል ሁሉ+
የአጥፊ ተባባሪ ነው።+
27 ለድሃ የሚሰጥ ሁሉ አይቸገርም፤+
እነሱን ላለማየት ዓይኖቹን የሚከድን ግን ብዙ እርግማን ይደርስበታል።
28 ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ሰው ራሱን ይሸሽጋል፤
ክፉዎች ሲጠፉ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።+
2 ጻድቃን ሲበዙ ሕዝብ ሐሴት ያደርጋል፤
ክፉ ሰው ሲገዛ ግን ሕዝብ ይቃትታል።+
4 ንጉሥ ፍትሕ በማስፈን አገርን ያረጋጋል፤+
ጉቦ የሚፈልግ ሰው ግን ያወድማታል።
5 ባልንጀራውን የሚሸነግል ሰው፣
ለእግሩ ወጥመድ ይዘረጋበታል።+
9 ጥበበኛ ሰው ከሞኝ ጋር ቢሟገት፣
ሁከትና ፌዝ ይነግሣል፤ ደስታ ግን አይኖርም።+
12 ገዢ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣
አገልጋዮቹ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።+
13 ድሃንና ጨቋኝን የሚያመሳስላቸው* ነገር አለ፦
ይሖዋ ለሁለቱም የዓይን ብርሃን ይሰጣል።*
16 ክፉዎች ሲበዙ ክፋት ይበዛል፤
ጻድቃን ግን የእነሱን ውድቀት ያያሉ።+
19 አገልጋይ በቃል ብቻ ለመታረም ፈቃደኛ አይሆንም፤
የሚነገረውን ነገር ቢረዳውም እንኳ እሺ ብሎ አይታዘዝምና።+
20 ለመናገር የሚቸኩል ሰው አይተህ ታውቃለህ?+
ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው።+
21 አገልጋይ ከልጅነቱ ጀምሮ ከተሞላቀቀ፣
የኋላ ኋላ ምስጋና ቢስ ይሆናል።
24 የሌባ ግብረ አበር ራሱን* ይጠላል።
እንዲመሠክር የቀረበለትን ጥሪ* ቢሰማም ምንም አይናገርም።+
30 የያቄ ልጅ አጉር ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለዑካል የተናገራቸው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘሉ ቃላት።
2 እኔ ከማንም የባሰ አላዋቂ ነኝ፤+
ሰው ሊኖረው የሚገባው ማስተዋልም የለኝም።
3 ጥበብን አልተማርኩም፤
እጅግ ቅዱስ የሆነው አምላክ እውቀትም የለኝም።
4 ወደ ሰማይ የወጣ፣ ከዚያም የወረደ ማን ነው?+
ነፋስን በእፍኙ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው?
ውኃን በልብሱ የጠቀለለ ማን ነው?+
ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው? ታውቅ እንደሆነ ንገረኝ።
5 የአምላክ ቃል ሁሉ የነጠረ ነው።+
እሱ፣ መጠጊያቸው ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው።+
7 ሁለት ነገር እንድታደርግልኝ እለምንሃለሁ።
እነሱንም ከመሞቴ በፊት አትንፈገኝ።
ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ።
ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ* አትፍቀድ።
10 እንዳይረግምህና በደለኛ ሆነህ እንዳትገኝ
በጌታው ፊት የአገልጋዩን ስም አታጥፋ።+
11 አባቱን የሚረግም፣
እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ።+
13 እጅግ ትዕቢተኛ ዓይን ያለው ትውልድ አለ፤
ዓይኖቹም በታላቅ እብሪት ይመለከታሉ!+
15 አልቅቶች “ስጡን! ስጡን!” እያሉ የሚጮኹ ሁለት ሴቶች ልጆች አሏቸው።
ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤
ደግሞም “በቃኝ!” የማያውቁ አራት ነገሮች አሉ።
18 ከመረዳት አቅሜ በላይ የሆኑ* ሦስት ነገሮች አሉ፤
የማልገነዘባቸውም አራት ነገሮች አሉ፦
19 ንስር በሰማያት የሚበርበት መንገድ፣
እባብ በዓለት ላይ የሚሄድበት መንገድ፣
መርከብ በባሕር ላይ የሚጓዝበት መንገድ፣
ሰውም ከሴት ልጅ ጋር የሚሄድበት መንገድ ናቸው።
20 የአመንዝራ ሴት መንገድ ይህ ነው፦
በልታ አፏን ከጠራረገች በኋላ
“ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም” ትላለች።+
21 ምድርን የሚያናውጡ ሦስት ነገሮች አሉ፤
መታገሥ የማትችላቸውም አራት ነገሮች አሉ፦
29 ግርማ የተላበሰ አረማመድ ያላቸው ሦስት ፍጥረታት አሉ፤
አዎ፣ እየተጎማለሉ የሚሄዱ አራት ፍጥረታት አሉ፦
31 የንጉሥ ልሙኤል ቃል፤ እናቱ እሱን ለማስተማር የተናገረችው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘለ መልእክት፦+
5 አለዚያ ጠጥተው የተደነገገውን ሕግ ይረሳሉ፤
የችግረኞችንም መብት ይጥሳሉ።
7 ጠጥተው ድህነታቸውን ይርሱ፤
ችግራቸውንም ዳግመኛ አያስታውሱ።
8 ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት አንተ ተናገርላቸው፤
ሊጠፉ ለተቃረቡት ሰዎች ሁሉ መብት ተሟገት።+
א [አሌፍ]
ዋጋዋ ከዛጎል* እጅግ ይበልጣል።
ב [ቤት]
11 ባሏ ከልቡ ይታመንባታል፤
አንዳችም ጠቃሚ ነገር አይጎድልበትም።
ג [ጊሜል]
12 በሕይወቷ ዘመን ሁሉ
መልካም ነገር ታደርግለታለች እንጂ ክፉ ነገር አታደርግበትም።
ד [ዳሌት]
13 ሱፍና በፍታ ታመጣለች፤
በእጆቿ መሥራት ያስደስታታል።+
ה [ሄ]
ו [ዋው]
ז [ዛየን]
ח [ኼት]
ט [ቴት]
18 ንግዷ ትርፋማ እንደሆነ ታስተውላለች፤
መብራቷ በሌሊት አይጠፋም።
י [ዮድ]
כ [ካፍ]
20 እጆቿን ለተቸገረ ሰው ትዘረጋለች፤
ለድሃውም እጇን ትከፍታለች።+
ל [ላሜድ]
21 ቤተሰቦቿ ሁሉ የሚያሞቅ* ልብስ ስለሚለብሱ
በበረዶ ወቅት እንኳ አትሰጋም።
מ [ሜም]
22 ለራሷ የአልጋ ልብስ ትሠራለች።
ልብሷ ከበፍታና ከሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው።
נ [ኑን]
ס [ሳሜኽ]
24 የበፍታ ልብሶች እየሠራች* ትሸጣለች፤
ለነጋዴዎችም ቀበቶ ታስረክባለች።
ע [አይን]
25 ብርታትንና ግርማን ትጎናጸፋለች፤
የወደፊቱንም ጊዜ በልበ ሙሉነት ትጠባበቃለች።*
פ [ፔ]
צ [ጻዴ]
ק [ኮፍ]
28 ልጆቿ ተነስተው ደስተኛ ይሏታል፤
ባሏ ተነስቶ ያወድሳታል።
ר [ረሽ]
ש [ሺን]
ת [ታው]
ቃል በቃል “ለማወቅ።”
ወይም “ፍትሕና።”
ወይም “ሚዛናዊነት።”
ወይም “በጥልቅ ማክበር።”
ወይም “ሕግ፤ ትምህርት።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል።”
ወይም “አንድ የጋራ ከረጢት (ቦርሳ) ይኖረናል።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “ራስ።”
ወይም “ስወቅሳችሁ ተመለሱ።”
ቃል በቃል “የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ።”
ወይም “ውጥን፤ ዕቅድ።”
ወይም “ማስተዋል የታከለበት ጥበብን።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል የሥነ ምግባር ንጽሕናን፣ ሁለት ልብ አለመሆንንና እንከን የለሽ መሆንን ያመለክታል።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “እንግዳ።” ከምትከተለው የሥነ ምግባር አቋም የተነሳ ከአምላክ ጋር የተቆራረጠችን ሴት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ባዕድ።” ከምትከተለው የሥነ ምግባር አቋም የተነሳ ከአምላክ የራቀችን ሴት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “የሚያማልል።”
ወይም “ባሏን።”
ቃል በቃል “መንገዷም።”
ቃል በቃል “ወደ እሷ የሚገቡ።”
ወይም “ንጹሕ አቋማቸውን የሚጠብቁ።”
ወይም “ሕጌን።”
ወይም “እውነት።”
ቃል በቃል “በገዛ ራስህ ማስተዋል አትደገፍ።”
ቃል በቃል “ለእምብርትህ።”
ወይም “ከገቢህ።”
ወይም “ምርጥ በሆነው ነገር።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ከላይ በሚገኙት ቁጥሮች ላይ የተጠቀሱትን የአምላክ ባሕርያት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “ማስተዋል የታከለበትን ጥበብና።”
ወይም “ለነፍስህ ሕይወት ያስገኙላታል።”
ወይም “ከምንም ነገር ጋር አይጋጭም።”
ወይም “ማድረግ እስከቻልክ ድረስ።”
ወይም “ሕጌን።”
ወይም “ዓይነተኛ።”
ቃል በቃል “ጆሮህን ወደ ንግግሬ አዘንብል።”
ቃል በቃል “ለሥጋቸውም ሁሉ።”
ወይም “ብሩህ ዓይኖችህ ፊት ለፊት ይመልከቱ።”
“ልብ ብለህ አጢን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ወደ ማስተዋሌ ጆሮህን አዘንብል።”
ቃል በቃል “የእንግዳ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ኃይልህን።”
ቃል በቃል “በማኅበርና በጉባኤ መካከል።”
ወይም “የምንጭህን ንጹሕ ውኃ ጠጣ።”
ወይም “ዋልያ።”
ወይም “ያስክሩህ።”
ቃል በቃል “እንግዳ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ባዕድ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ተያዥ።”
ወይም “ብትጨብጥ።” ቃል መግባትን ያመለክታል።
ወይም “ነፍሱ የምትጸየፋቸው።”
ወይም “ሕግ፤ ትምህርት።”
ወይም “ያስተምርሃል።”
ቃል በቃል “ከባዕድ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ቃል በቃል “አንድ ሰው ያለውን ሁሉ አጥቶ አንድ ዳቦ ብቻ ይቀረዋል።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “ነፍሱን።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “በነፍሱ።”
ወይም “ቤዛ።”
ወይም “ሕጌን፤ ትምህርቴን።”
ቃል በቃል “እንግዳና።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ባዕድ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ወይም “የሚያማልል።”
ወይም “ተሞክሮ የሌላቸውን።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “የዝሙት አዳሪ ልብስ።”
ቃል በቃል “እግሮቿ ቤት አይቀመጡም።”
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሽቶ ለመሥራት የሚያገለግል ጥሩ መዓዛ ያለው ንጥረ ነገር የሚገኝበትን ዛፍ ያመለክታል።
ወይም “በእግር ብረት።”
ወይም “ነፍሱን።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ወደ ሞት ውስጠኛ ክፍሎችም።”
ቃል በቃል “ለሰው ወንዶች ልጆች።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “በውርስ የተገኙ ውድ ነገሮችና።”
ወይም “በውል ከማይታወቁ ዘመናት በፊት።”
ወይም “በምጥ ተወለድኩ።”
ቃል በቃል “ክበብን።”
ቃል በቃል “ባጸና።”
ወይም “በደነገገ።”
ወይም “በየዕለቱ በራፌ ላይ ነቅቶ በመጠበቅ።”
ወይም “ነፍሱን።”
ቃል በቃል “እርዷን አረደች።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “ተሞክሮ ከሌላቸው ሰዎች ራቁ።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “የጻድቁ ነፍስ እንድትራብ።”
ወይም “ጻድቅ ሰው ያተረፈው ስም።”
ቃል በቃል “ይበሰብሳል።”
ቃል በቃል “ትእዛዛትን።”
ምሳሌ 2:7 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “ውድ ንብረት።”
“ወደ ሕይወት በሚወስድ መንገድ ላይ ነው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “አሉባልታ።”
ወይም “ይመራሉ።”
ወይም “ሐዘንን፤ መከራን።”
ወይም “ለአሠሪው።”
ወይም “የጥበብን ፍሬ ያፈራል።”
ወይም “የማታለያ።”
ወይም “የተሟላ የድንጋይ መለኪያ።”
ምሳሌ 2:7 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ውድ ነገሮች ፋይዳ አይኖራቸውም።”
ወይም “አምላክ የለሽ ሰው።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “ባልንጀራውን ያቃልላል።”
ቃል በቃል “በመንፈሱ የታመነ ሰው።”
ቃል በቃል “ነገርን ይሰውራል።”
ወይም “መዳን።”
ወይም “ተያዥ የሚሆን።”
ወይም “በመጨበጥ።”
ቃል በቃል “(ቃል መግባት) የሚጠላ።”
ወይም “የምትወደድ።”
ወይም “ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ ሰው ነፍሱን ይጠቅማል።”
ወይም “ውርደት።”
ቃል በቃል “አንዱ ይበትናል።”
ወይም “ለጋስ ነፍስ።”
ቃል በቃል “ይሰባል።”
ቃል በቃል “እንደ ልብ የሚያጠጣም።”
ወይም “ውርደት።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ማስተዋል።”
ወይም “አሳፋሪ ድርጊት የምትፈጽም።”
ቃል በቃል “ደም ለማፍሰስ ያደባል።”
ቃል በቃል “ዳቦ።”
ወይም “የቤት እንስሳቱን ነፍስ።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “በዚያው ቀን።”
ቃል በቃል “ይሸፍናል።”
ቃል በቃል “ጽድቅ የሆነውን።”
ቃል በቃል “የሰላም አማካሪ የሆኑ።”
ወይም “የመንፈስ ጭንቀት ያስከትልበታል።”
ወይም “እርማትን።”
ወይም “የከዳተኞች ነፍስ።”
ወይም “ተጠንቅቆ የሚናገር ነፍሱን ይጠብቃል።”
ወይም “ነፍሱ ምንም አታገኝም።”
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “ትሰባለች።”
ወይም “ለነፍሱ።”
ቃል በቃል “ሐሴት ያደርጋል።”
ወይም “እርስ በርስ በሚመካከሩ።”
ወይም “ከምንም ተነስቶ የተገኘ ሀብት።”
ቃል በቃል “በእጁ የሚሰበስብ።”
ወይም “ቃልን የሚንቅ።”
ወይም “ሕግ።”
ወይም “ወቀሳን የሚቀበል።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “እሱ ይጠፋል።”
ወይም “ልጁን ከመገሠጽ፤ ልጁን ከመቅጣት።”
“ወዲያው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሱንም።”
ወይም “ጠማማ።”
“ሞኞች ግን ሌሎችን ያታልላሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በበደል ካሳ።”
ወይም “በቅኖች መካከል ግን በጎ ፈቃድ አለ።”
ወይም “የነፍሱን።”
ወይም “ተሞክሮ የሌለው።”
ወይም “ይቆጣል።”
ወይም “የማመዛዘን ችሎታ ያለው ሰው።”
ወይም “ተሞክሮ የሌላቸው።”
ወይም “ነፍስን።”
ወይም “ጤና።”
ምሳሌ 2:7 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ደግነት የተሞላበት።”
ወይም “የሚያቆስል።”
ወይም “ፈዋሽ ምላስ።”
ቃል በቃል “መንፈስን ያደቃል።”
ወይም “ገቢ።”
ወይም “ከባድ።”
ወይም “ሲኦልና።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “አባዶን።”
ወይም “የሚወቅሰውን።”
ወይም “ይከታተላል።”
ወይም “ጥሩ።”
ወይም “ከሽብር።”
ቃል በቃል “በግርግም የተቀለበ።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “ልብ ለልብ መነጋገር።”
ቃል በቃል “በአፉ መልስ።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ውርደት።”
ወይም “ምን ብሎ እንደሚመልስ በጥሞና ያስባል፤ ከመናገሩ በፊት ያስባል።”
ወይም “በፈገግታ የተሞላ ፊት።”
ቃል በቃል “ያሰባል።”
ወይም “ነፍሱን።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ቃል በቃል “ልብን ማዘጋጀት የሰው ድርሻ ነው።”
ወይም “ትክክለኛው መልስ።” ቃል በቃል “የምላስ መልስ።”
ቃል በቃል “ንጹሕ።”
ቃል በቃል “መንፈስን።”
ቃል በቃል “ሥራህን ለይሖዋ አስተላልፍ።”
ወይም “መለኮታዊ ውሳኔ።”
ወይም “ያስወግደዋል።”
ወይም “ነፍሱን ይጠብቃል።”
ቃል በቃል “የተዋረደ መንፈስ።”
ቃል በቃል “ጥሩ ነገር ያገኛል።”
ወይም “በሚማርክ መንገድ የሚናገርም።” ቃል በቃል “ከንፈሩ ጣፋጭ የሆነም።”
ወይም “ለአፍ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሱ።”
ቃል በቃል “አፉ።”
ወይም “ሴረኛ።”
ወይም “የክብር።”
ቃል በቃል “መንፈሱን የሚገዛም።”
ቃል በቃል “መሥዋዕቶች ከሞሉበት።”
ወይም “ጸጥታ።”
ቃል በቃል “ወንዶች የልጅ ልጆች።”
ወይም “ወላጆችም።”
ወይም “ለልጆቻቸው።”
ወይም “መልካም።”
ወይም “ለተከበረ ሰው።”
ወይም “ሞገስ የሚያስገኝ ድንጋይ።”
ቃል በቃል “የሚሸፍን።”
ቃል በቃል “ውኃን ከመልቀቅ።”
ወይም “ማስተዋል።”
ወይም “ተያዥ።”
ቃል በቃል “መልካም ነገር አያገኝም።”
ወይም “ፈውስ ያስገኛል።”
ወይም “አጥንትን ያደርቃል።”
ቃል በቃል “ከሰው ጉያ።”
ወይም “መቀጫ ማስከፈል።”
ቃል በቃል “መንፈሱ ቀዝቃዛ ነው።”
ወይም “ማስተዋል የታከለበትንም ጥበብ።”
ወይም “ይንቃል።”
ወይም “ለነፍሱ።”
ወይም “ተስገብግበው እንደሚውጡት ነገር ነው።”
ቃል በቃል “ከፍ ይላል።” ግለሰቡ እንደማይደረስበትና ከአደጋ እንደሚጠበቅ ያመለክታል።
ወይም “ከባድ የተስፋ መቁረጥ ስሜትን።”
ወይም “በጎ ፈቃድ።”
ምሳሌ 2:7 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “በእግሩ የሚጣደፍ።”
ወይም “ለጋስ በሆነ ሰው።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “ነፍሱን።”
ቃል በቃል “መልካም ነገር ያገኛል።”
ቃል በቃል “በደልንም ማለፉ።”
ወይም “ደቦል አንበሳ።”
ወይም “ነዝናዛ ሚስትም።”
ወይም “ታካች ነፍስም ትራባለች።”
ወይም “ነፍሱን።”
ወይም “ወሮታ።”
ወይም “የእሱንም ሞት አትመኝ።” ቃል በቃል “ለእሱ ሞት ነፍስህን አታንሳ።”
ወይም “ዓላማ።”
ወይም “የንጉሥ አስፈሪነት።”
ወይም “ደቦል አንበሳ።”
“በመከር ወራት ይፈልጋል፤ ግን አያገኝም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ዕቅድ።” ቃል በቃል “ምክር።”
ምሳሌ 2:7 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ሁለት ዓይነት የድንጋይ ሚዛንና ሁለት ዓይነት መስፈሪያ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ለባዕድ።”
ወይም “ምክር።”
ወይም “ይጸናል።”
ወይም “በከንፈሮቹ ከሚያባብል ሰው።”
ወይም “ሁለት ዓይነት የድንጋይ ሚዛን።”
ወይም “የሚሄድበትን መንገድ።”
ተሽከርካሪ እግር።
ወይም “ያነጻል።”
ወይም “ውስጣዊ ዓላማን ይመረምራል።”
ወይም “ጥቅም ያስገኝለታል።”
“ሞትን ለሚሹ ወዲያው እንደሚጠፋ ጉም ነው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ከነዝናዛ።”
ወይም “የክፉ ሰው ነፍስ።”
ወይም “ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል።”
ቃል በቃል “በጉያ የተሸጎጠ ጉቦም።”
ወይም “ደስታ።”
ወይም “ነዝናዛና።”
ቃል በቃል “ያለውን ይውጣል።”
ወይም “ከተማን ድል ያደርጋል።”
ወይም “ነፍሱን ከችግር ይጠብቃል።”
ወይም “አሳፋሪ ምግባር እያለው።”
ቃል በቃል “ለዘላለም ይናገራል።”
ወይም “ቅን ሰው ግን መንገዱን አስተማማኝ ያደርጋል።”
ወይም “ዝና።” ቃል በቃል “ስም።”
ቃል በቃል “ሞገስ።”
ቃል በቃል “ተገናኙ።”
ወይም “ቅጣቱንም።”
ወይም “ለነፍሱ።”
ወይም “ሕፃንን፤ ወጣትን።”
ቃል በቃል “ጥሩ ዓይን ያለው ሰው።”
ወይም “ክስና።”
ቃል በቃል “የእንግዳ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ወይም “በሕፃን፤ በወጣት።”
ወይም “ነፍስ ይቀማል።”
ወይም “ለነፍስህም።”
ወይም “እንደሚጨብጡ።”
ወይም “በምኞት የተሞላች ነፍስ ብትኖርህ።”
ወይም “ራስህን ተቆጣጠር።”
“በገዛ ራስህ ማስተዋል አትመራ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ክፉ ዓይን ያለው ሰው የሚያቀርበውን።”
ወይም “በነፍሱ እንደሚያሰላ።”
ቃል በቃል “ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።”
ቃል በቃል “የሚዋጃቸው።”
ወይም “ሕፃንን፤ ወጣትን።”
ወይም “ከሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሱን ከመቃብር ታድናት ዘንድ።”
ቃል በቃል “ኩላሊቶቼ ደስ ይላቸዋል።”
ወይም “ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡ፣ ሥጋም ያለልክ ከሚሰለቅጡ ሰዎች ጋር አትወዳጅ።”
ወይም “አግኝ።”
ቃል በቃል “ባዕድ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ወይም “መፍዘዝ።”
ወይም “ለመቀማመስ በሚሰባሰቡ።”
ወይም “አላመመኝም።”
ወይም “መጠጡን ደግሜ እሻዋለሁ።”
ወይም “ቤተሰብ በጥበብ ይገነባል።”
ወይም “ስኬት፤ መዳን።”
ወይም “የሞኝ ሴራ።”
ወይም “በችግር ጊዜ።”
ወይም “ውስጣዊ ዓላማን።”
ወይም “ነፍስህን።”
ወይም “ለነፍስህ ጣፋጭ።”
ጠላትን ያመለክታል።
ወይም “ለውጥ ለማካሄድ ከተነሱ ሰዎች።”
ይሖዋንና ንጉሡን ያመለክታል።
“በቀጥታ መልስ መስጠት እንደ መሳም ይቆጠራል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ቤተሰብህን ገንባ።”
ወይም “አጸፋውን እመልሳለሁ።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ቃል በቃል “ተግሣጽ ተቀበልኩ፦”
ወይም “የገለበጧቸውና ያጠናቀሯቸው።”
ወይም “የሌሎችን ሚስጥር።”
ወይም “ተንኮል ያዘለ አሉባልታ።”
ወይም “በብር መደብ ላይ።”
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “የውሸት ስጦታ።”
ወይም “የለዘበም አንደበት።”
“በከዳተኛ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “የሚጠላህ ሰው።”
የሰውየውን ልብ ለማለስለስና ግትር አቋሙን ለማለዘብ የሚደረግን ጥረት ያመለክታል።
ወይም “ከነዝናዛ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “በክፉ ሰው ፊት አቋሙን የሚያላላ።” ቃል በቃል “በክፉ ሰው ፊት የሚንገዳገድ።”
ወይም “መንፈሱን የማይገታ ሰው።”
“ተገቢ ያልሆነ እርግማንም በሰው ላይ አይደርስም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “አለዚያ አንተም እኩያው ትሆናለህ።”
ቃል በቃል “ዓመፅን ከሚጋት።”
ወይም “እንደ ሽባ ሰው የተንጠለጠለ እግር።”
ወይም “ሰውን ሁሉ።”
ወይም “በመሽከርከሪያው።”
“ጣልቃ የሚገባ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ገዳይ ፍላጻዎችን።”
ወይም “ተስገብግበው እንደሚውጡት ነገር ነው።”
ቃል በቃል “ኃይለኛ ስሜትን የሚገልጽ ከንፈር።”
ወይም “ልቡ ሙሉ በሙሉ አስጸያፊ ነውና።”
ቃል በቃል “የሚወልደውን።”
ቃል በቃል “እንግዳ ያመስግንህ።”
ቃል በቃል “የባዕድ አገር ሰዎች።”
“የውሸት፤ የግድ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “ይረግጣል።”
ወይም “የተራበች ነፍስ።”
ወይም “የሚሰደድ።”
ወይም “በነፍስ ምክር ላይ።”
ወይም “ይቀጣልም።”
ወይም “ለባዕድ።”
ወይም “ነዝናዛ።”
ቃል በቃል “የጓደኛውን ፊት ይስላል።”
ወይም “ሲኦልና አባዶን።”
ወይም “ሰውም በሚያገኘው ውዳሴ መሠረት ነው።”
ወይም “ልብህን በበጎችህ ላይ አኑር፤ ለበጎችህ ትኩረት ስጥ።”
ወይም “ዘውድም።”
ወይም “ዓመፅ።”
ቃል በቃል “እሱ።”
ምሳሌ 2:7 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ፍርሃት ተለይቶት የማያውቅ።”
ወይም “የነፍስ ደም።”
ወይም “ጉድጓድ።”
ወይም “ስግብግብ።”
“እብሪተኛ ነፍስ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ይሰባል።”
ወይም “ግትር የሆነ።”
ወይም “ነቀፋ የሌለበትን።”
ወይም “ነፍስ።”
“ቅን የሆነ ሰው ግን ሕይወቱን ለመጠበቅ ይሻል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “መንፈሱን።”
ቃል በቃል “የሚያገናኛቸው።”
ሕይወት እንደሚሰጣቸው ያመለክታል።
ወይም “ተግሣጽና፤ ቅጣትና።”
ወይም “ነፍስህን እጅግ ደስ ያሰኛታል።”
ወይም “ትንቢታዊ ራእይ።”
ወይም “የገዛ ነፍሱን።”
ወይም “እርግማን የሚያስከትለውን መሐላ።”
ወይም “በሰው ፊት መንቀጥቀጥ።”
“የገዢን ሞገስ ማግኘት” ማለትም ሊሆን ይችላል። ቃል በቃል “የገዢን ፊት።”
ቃል በቃል “ያቆመ።”
ወይም “እንዳስነቅፍ።”
ቃል በቃል “ከእዳሪው።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “የደረቅ ወንዝ።”
ወይም “እጅግ የሚያስደንቁኝ።”
ወይም “የማትወደድ።”
ወይም “ስትቀማ።”
ወይም “እጅግ ጥበበኞች።”
ቃል በቃል “ጥንካሬ የሌለው ሕዝብ።”
ቃል በቃል “ሕዝብ።”
ወይም “በቡድን ተከፋፍለው።”
ጌኮ የተባለችውን እንሽላሊት ያመለክታል።
ወይም “በነፍሳቸው ለተመረሩትም።”
ወይም “ጉዳይ ተሟገት።”
ወይም “እጅግ ጥሩ የሆነችን ሚስት።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “በምታገኘው ገቢ።” ቃል በቃል “ከእጆቿ ፍሬ።”
ቃል በቃል “ዳሌዋን በኃይል ትታጠቃለች።”
የአመልማሎ ዘንግና እንዝርት፣ ድርና ማግ ለማጠንጠን ወይም ለመሥራት የሚያገለግሉ ቀጫጭን እንጨቶች ናቸው።
ቃል በቃል “ድርብ።”
ወይም “የውስጥ ልብሶች እየሠራች።”
ወይም “በመጪው ጊዜ ላይ ትስቃለች።”
ወይም “ፍቅራዊ መመሪያም፤ የታማኝ ፍቅር ሕግም።”
ወይም “እጅግ ጥሩ።”
ወይም “ከንቱ።”
ቃል በቃል “ከእጆቿ ፍሬ ስጧት።”