የሉቃስ ወንጌል
1 ብዙዎች እኛ ሙሉ እምነት የጣልንባቸውን መረጃዎች ለማጠናቀር የተቻላቸውን ጥረት አድርገዋል፤+ 2 ደግሞም ከመጀመሪያው አንስቶ የዓይን ምሥክሮች የነበሩ ሰዎችና+ መልእክቱን የሚያውጁ አገልጋዮች+ እነዚህን መረጃዎች ለእኛ አስተላልፈዋል። 3 ክቡር ቴዎፍሎስ ሆይ፣+ እኔም በበኩሌ ሁሉንም ነገር ከመጀመሪያው አንስቶ በጥንቃቄ ስለመረመርኩ ታሪኩን በቅደም ተከተል ልጽፍልህ ወሰንኩ። 4 ይህን ያደረግኩት በቃል የተማርካቸው ነገሮች እርግጠኛ መሆናቸውን በሚገባ እንድታውቅ ነው።+
5 በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ* ዘመን፣+ በአቢያህ+ የክህነት ምድብ ውስጥ የሚያገለግል ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበር። ሚስቱ የአሮን ዘር ስትሆን ስሟም ኤልሳቤጥ ነበር። 6 ሁለቱም በአምላክ ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ የይሖዋን* ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ እየጠበቁ ያለነቀፋ ይኖሩ ነበር። 7 ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መሃን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፤ እንዲሁም ሁለቱም በዕድሜ የገፉ ነበሩ።
8 አንድ ቀን ዘካርያስ እሱ ያለበት ምድብ+ ተራው ደርሶ በአምላክ ፊት በክህነት እያገለገለ ሳለ 9 በክህነት ሥርዓቱ* መሠረት ወደ ይሖዋ* ቤተ መቅደስ+ ገብቶ ዕጣን+ የሚያጥንበት ተራ ደረሰው። 10 ዕጣን በሚቀርብበትም ሰዓት ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ሆነው ይጸልዩ ነበር። 11 የይሖዋም* መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተ ቀኝ ቆሞ ታየው። 12 ዘካርያስም መልአኩን ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሃትም ተዋጠ። 13 መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ፣ አትፍራ፤ ምክንያቱም አምላክ ያቀረብከውን ምልጃ ሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።+ 14 አንተም ደስ ይልሃል፤ ሐሴትም ታደርጋለህ፤ ብዙዎችም በእሱ መወለድ ደስ ይላቸዋል፤+ 15 በይሖዋ* ፊት ታላቅ ይሆናልና።+ ይሁንና የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ፈጽሞ መጠጣት የለበትም፤+ ከመወለዱ በፊት እንኳ* በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፤+ 16 ከእስራኤል ልጆች መካከልም ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ* ይመልሳል።+ 17 በተጨማሪም ሰዎችን ለይሖዋ * ያዘጋጅ ዘንድ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ ለማድረግ፣*+ የማይታዘዙትንም ሰዎች ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ በኤልያስ መንፈስና ኃይል+ በአምላክ ፊት ይሄዳል።”+
18 ዘካርያስ መልአኩን “ይህ እንደሚሆን እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ? እኔ እንደሆነ አርጅቻለሁ፤ ሚስቴም ዕድሜዋ ገፍቷል” አለው። 19 መልአኩም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እኔ በአምላክ አጠገብ በፊቱ የምቆመው+ ገብርኤል+ ነኝ፤ አንተን እንዳነጋግርህና ይህን ምሥራች እንዳበስርህ ተልኬአለሁ። 20 ሆኖም የተወሰነለትን ጊዜ ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንክ ይህ ነገር እስኪፈጸም ድረስ ዱዳ ትሆናለህ! መናገርም አትችልም።” 21 ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕዝቡ ዘካርያስን በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፤ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ብዙ በመቆየቱም ግራ ተጋቡ። 22 በወጣ ጊዜም ሊያናግራቸው አልቻለም፤ እነሱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ አንድ ራእይ እንዳየ ተገነዘቡ። ከዚያ በኋላ ዱዳ ስለሆነ በምልክት ብቻ ያናግራቸው ነበር። 23 በቤተ መቅደሱ ውስጥ ቅዱስ አገልግሎት* የሚያቀርብባቸው ቀናት ሲያበቁ ወደ ቤቱ ሄደ።
24 ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፤ ለአምስት ወርም ከቤት ሳትወጣ ቆየች፤ እንዲህም አለች፦ 25 “ይሖዋ* በዚህ ወቅት ይህን አደረገልኝ። በሰዎች መካከል ይደርስብኝ የነበረውን ነቀፋ ለማስወገድ ፊቱን ወደ እኔ መለሰ።”+
26 ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድስተኛ ወሯ አምላክ መልአኩ ገብርኤልን+ በገሊላ ወደምትገኝ ናዝሬት ወደተባለች ከተማ ላከው፤ 27 የተላከውም ከዳዊት ቤት ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች አንዲት ድንግል+ ሲሆን የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር።+ 28 መልአኩም ገብቶ “እጅግ የተባረክሽ ሆይ፣ ሰላም ለአንቺ ይሁን፤ ይሖዋ* ከአንቺ ጋር ነው” አላት። 29 እሷ ግን በንግግሩ በጣም ደንግጣ ይህ ሰላምታ ምን ትርጉም እንዳለው ለመረዳት በውስጧ ታስብ ጀመር። 30 ስለዚህ መልአኩ እንዲህ አላት፦ “ማርያም ሆይ፣ በአምላክ ፊት ሞገስ ስላገኘሽ አትፍሪ። 31 እነሆም፣ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤+ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።+ 32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+
34 ማርያም ግን መልአኩን “እኔ ከወንድ ጋር ግንኙነት ፈጽሜ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለችው።+ 35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤+ የልዑሉም ኃይል በአንቺ ላይ ያርፋል። ስለሆነም የሚወለደው ልጅ ቅዱስና+ የአምላክ ልጅ+ ይባላል። 36 እነሆ፣ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መሃን ትባል የነበረ ቢሆንም ይኸው ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ 37 አምላክ የተናገረው ቃል ሳይፈጸም አይቀርምና።”*+ 38 በዚህ ጊዜ ማርያም “እነሆ፣ እኔ የይሖዋ* ባሪያ ነኝ! እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” አለች። ከዚያም መልአኩ ተለይቷት ሄደ።
39 ማርያምም በዚያው ሰሞን ተነስታ በተራራማው አገር ወደምትገኝ አንዲት የይሁዳ ከተማ በፍጥነት ሄደች፤ 40 ወደ ዘካርያስ ቤት ገብታም ኤልሳቤጥን ሰላም አለቻት። 41 ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማህፀኗ ውስጥ ያለው ፅንስ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤ 42 ድምፅዋንም ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፦ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማህፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው! 43 የጌታዬ እናት ወደ እኔ መምጣቷ ለእኔ እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው! 44 እነሆ፣ የሰላምታሽን ድምፅ እንደሰማሁ በማህፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘሏልና። 45 ይሖዋ* የነገራት ነገር ሙሉ በሙሉ የሚፈጸም በመሆኑ ይህን ያመነች ደስተኛ ነች።”
46 ማርያምም እንዲህ አለች፦ “ነፍሴ ይሖዋን* ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤*+ 47 መንፈሴም አዳኜ በሆነው አምላክ እጅግ ደስ ይሰኛል፤+ 48 ምክንያቱም የባሪያውን መዋረድ* ተመልክቷል።+ እነሆ፣ ከአሁን ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ደስተኛ ይሉኛል፤+ 49 ምክንያቱም ኃያል የሆነው አምላክ ታላላቅ ነገሮች አድርጎልኛል፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤+ 50 ምሕረቱም በሚፈሩት ሁሉ ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።+ 51 በክንዱም ታላላቅ ሥራዎች አከናውኗል፤ በልባቸው ሐሳብ ትዕቢተኛ የሆኑትንም በትኗቸዋል።+ 52 ኃያላን ሰዎችን ከዙፋናቸው አውርዷል፤+ ዝቅ ያሉትንም ከፍ አድርጓል፤+ 53 የተራቡትን በመልካም ነገሮች አጥግቧል፤+ ሀብታሞችንም ባዶ እጃቸውን ሰዷቸዋል። 54 ምሕረቱን በማስታወስ አገልጋዩን እስራኤልን ረድቷል፤+ 55 ይህን ያደረገው ለአባቶቻችን በገባው ቃል መሠረት ለአብርሃምና ለዘሩ+ ለዘላለም ምሕረት ለማሳየት ነው።” 56 ማርያምም ከኤልሳቤጥ ጋር ሦስት ወር ያህል ከቆየች በኋላ ወደ ቤቷ ተመለሰች።
57 ኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰና ወንድ ልጅ ወለደች። 58 ጎረቤቶቿና ዘመዶቿም ይሖዋ* ታላቅ ምሕረት እንዳደረገላት ሰምተው የደስታዋ ተካፋዮች ሆኑ።+ 59 በስምንተኛው ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤+ በአባቱም ስም ዘካርያስ ብለው ሊጠሩት ፈልገው ነበር። 60 እናትየው ግን መልሳ “አይሆንም! ዮሐንስ ይባል” አለች። 61 በዚህ ጊዜ “ከዘመዶችሽ መካከል በዚህ ስም የተጠራ ማንም የለም” አሏት። 62 ከዚያም አባቱን ማን ተብሎ እንዲጠራ እንደሚፈልግ በምልክት ጠየቁት። 63 እሱም የእንጨት ጽላት እንዲያመጡለት ጠየቀና “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ።+ በዚህ ጊዜ ሁሉም ተደነቁ። 64 ወዲያውም አፉ ተከፈተ፤ ምላሱም ተፈቶ መናገር ጀመረ፤+ አምላክንም አወደሰ። 65 ጎረቤቶቻቸውም ሁሉ በፍርሃት ተዋጡ፤ የሆነውም ነገር ሁሉ በተራራማው የይሁዳ አገር በሙሉ ይወራ ጀመር። 66 ይህን የሰሙም ሁሉ “የዚህ ሕፃን መጨረሻ ምን ይሆን?” በማለት ነገሩን በልባቸው ያዙ። የይሖዋ* እጅ ከእሱ ጋር እንደሆነ በግልጽ ይታይ ነበርና።
67 ከዚያም አባቱ ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፦ 68 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ* ፊቱን ወደ ሕዝቡ ስለመለሰና ሕዝቡን ስላዳነ+ ውዳሴ ይድረሰው።+ 69 ደግሞም በአገልጋዩ በዳዊት ቤት+ የመዳን ቀንድ* አስነስቶልናል፤+ 70 ይህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ በነበሩት ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ በተናገረው መሠረት ነው።+ 71 ከባላጋራዎቻችንና ከሚጠሉን ሰዎች ሁሉ እጅ እንደሚያድነን ቃል ገብቷል።+ 72 ለአባቶቻችን በሰጠው ተስፋ መሠረት ምሕረት ያሳየናል፤ ቅዱስ ቃል ኪዳኑንም ያስታውሳል።+ 73 ይህም ቃል ኪዳን ለአባታችን ለአብርሃም የማለው መሐላ ነው፤+ 74 በመሐላው መሠረትም ከጠላቶቻችን እጅ ነፃ ካወጣን በኋላ ለእሱ ያለፍርሃት ቅዱስ አገልግሎት የማቅረብ መብት ይሰጠናል፤ 75 ይህም ታማኝ እንድንሆንና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ጽድቅ የሆነውን ነገር እንድናደርግ ነው። 76 ደግሞም አንተ ሕፃን፣ መንገዱን ለማዘጋጀት ቀድመህ በይሖዋ* ፊት ስለምትሄድ የልዑሉ ነቢይ ትባላለህ፤+ 77 ለሕዝቡም ኃጢአታቸው ይቅር ተብሎላቸው መዳን እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን እውቀት ትሰጣቸዋለህ፤+ 78 ይህም የሆነው አምላካችን ከአንጀት ስለራራልን ነው። ከዚህ ርኅራኄም የተነሳ እንደ ንጋት ፀሐይ የሚያበራ ብርሃን ከላይ ይወጣልናል፤ 79 ይኸውም በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ+ ለተቀመጡት ብርሃን ለመስጠት እንዲሁም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ለመምራት ነው።”
80 ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤልም በይፋ እስከታየበት ቀን ድረስ በበረሃ ኖረ።
2 በዚያ ዘመን፣ አውግስጦስ ቄሳር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲመዘገብ አዋጅ አወጣ። 2 (ይህ የመጀመሪያ ምዝገባ የተካሄደው ቄሬኔዎስ የሶርያ አገረ ገዢ በነበረበት ጊዜ ነው።) 3 ሁሉም ሰው ለመመዝገብ ወደየራሱ ከተማ ሄደ። 4 ዮሴፍም+ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለነበር በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነስቶ በይሁዳ ወዳለች ቤተልሔም+ ተብላ ወደምትጠራ የዳዊት ከተማ ወጣ። 5 ለመመዝገብ የሄደውም በታጨችለት መሠረት+ ካገባትና የመውለጃ ጊዜዋ ከተቃረበው+ ከማርያም ጋር ነበር። 6 በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ። 7 የበኩር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅም ወለደች፤+ በእንግዶች ማረፊያም፣ ቦታ ስላላገኙ ልጁን በጨርቅ ጠቅልላ በግርግም ውስጥ አስተኛችው።+
8 በዚያው ክልል፣ ሌሊት* ሜዳ ላይ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። 9 በድንገት የይሖዋ* መልአክ መጥቶ በፊታቸው ቆመ፤ የይሖዋም* ክብር በዙሪያቸው አንጸባረቀ፤ እነሱም በታላቅ ፍርሃት ተዋጡ። 10 መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፤ እነሆ፣ ለሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚያስገኝ ምሥራች እነግራችኋለሁ፤ 11 በዛሬው ዕለት በዳዊት ከተማ+ አዳኝ+ ተወልዶላችኋልና፤ እሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።+ 12 ይህም ምልክት ይሁናችሁ፦ አንድ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ።” 13 በድንገት ብዙ የሰማይ ሠራዊት+ ከመልአኩ ጋር ታዩ፤ አምላክንም እያመሰገኑ እንዲህ አሉ፦ 14 “በሰማያት ለአምላክ ክብር ይሁን፤ በምድርም አምላክ ሞገስ ለሚያሳያቸው ሰዎች ሰላም ይሁን።”
15 መላእክቱም ከእነሱ ተለይተው ወደ ሰማይ ከሄዱ በኋላ እረኞቹ እርስ በርሳቸው “አሁኑኑ ወደ ቤተልሔም ሄደን ይሖዋ* በገለጠልን መሠረት በዚያ የተፈጸመውን ነገር ማየት አለብን” ተባባሉ። 16 በፍጥነትም ሄደው ማርያምንና ዮሴፍን አገኟቸው፤ ሕፃኑም በግርግም ተኝቶ ነበር። 17 ይህን ባዩ ጊዜ ስለ ሕፃኑ የተነገራቸውን መልእክት አወሩ። 18 ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር ተደነቁ፤ 19 ማርያም ግን የሰማቻቸውን ነገሮች በውስጧ ይዛ በልቧ ታሰላስል ነበር።+ 20 እረኞቹም የሰሙትና ያዩት ነገር ሁሉ ልክ እንደተነገራቸው ሆኖ ስላገኙት አምላክን እያከበሩና እያወደሱ ተመለሱ።
21 ከስምንት ቀን በኋላ፣ ሕፃኑ የሚገረዝበት ጊዜ ሲደርስ+ ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ባወጣለት ስም ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።+
22 በተጨማሪም በሙሴ ሕግ መሠረት+ የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ ሕፃኑን በይሖዋ* ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት መጡ፤ 23 ይህን ያደረጉት “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* ለይሖዋ* የተቀደሰ መሆን አለበት”+ ተብሎ በይሖዋ* ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ነው። 24 ደግሞም የይሖዋ* ሕግ በሚያዘው መሠረት “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች”+ መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።
25 እነሆም፣ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እሱም አምላክ እስራኤልን የሚያጽናናበትን+ ጊዜ የሚጠባበቅ ጻድቅና ለአምላክ ያደረ ሰው ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእሱ ላይ ነበር። 26 በተጨማሪም ይሖዋ* የቀባውን* ሳያይ እንደማይሞት አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ገልጦለት ነበር። 27 እሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መጣ፤ ሕጉ ለልጁ* እንዲደረግ በሚያዘው የተለመደ ሥርዓት መሠረት+ ወላጆቹ ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘውት በገቡ ጊዜ 28 ስምዖን ሕፃኑን ተቀብሎ አቀፈውና አምላክን አወደሰ፤ እንዲህም አለ፦ 29 “ሉዓላዊው ጌታ ሆይ፣ በተናገርከው ቃል መሠረት አሁን ባሪያህን በሰላም እንዲያርፍ ታደርገዋለህ፤+ 30 ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤+ 31 ይህም በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፤+ 32 ደግሞም ብሔራትን የጋረደውን መሸፈኛ+ የሚገልጥ ብርሃን+ እንዲሁም የሕዝብህ የእስራኤል ክብር ነው።” 33 አባቱና እናቱም ስለ ልጁ በሚነገሩት ነገሮች ይደነቁ ነበር። 34 ስምዖንም እነሱን ከባረካቸው በኋላ እናቱን ማርያምን እንዲህ አላት፦ “እነሆ፣ ይህ ልጅ በእስራኤል ለብዙዎች መውደቅም+ ሆነ መነሳት+ ምክንያት ይሆናል፤ እንዲሁም ብዙዎች የሚቃወሙት ምልክት ይሆናል፤+ 35 ይህም የሚሆነው በብዙዎች ልብ ውስጥ ያለው ሐሳብ ይገለጥ ዘንድ ነው፤ በአንቺም ውስጥ* ትልቅ ሰይፍ ያልፋል።”+
36 ከአሴር ነገድ፣ የፋኑኤል ልጅ የሆነች ሐና የምትባል ነቢዪት ነበረች። ይህች ሴት በዕድሜ የገፋች ነበረች፤ ካገባች በኋላ* ከባሏ ጋር የኖረችው ለሰባት ዓመት ብቻ ነበር፤ 37 በዚህ ጊዜ 84 ዓመት የሆናት መበለት ነበረች። ሌትና ቀንም በጾምና በምልጃ ቅዱስ አገልግሎት እያቀረበች ከቤተ መቅደስ ፈጽሞ አትጠፋም ነበር። 38 በዚያን ሰዓትም ቀርባ አምላክን ታመሰግን ጀመር፤ አምላክ ኢየሩሳሌምን ነፃ ያወጣል ብለው ለሚጠባበቁም ሁሉ ስለ ሕፃኑ መናገር ጀመረች።+
39 የይሖዋ* ሕግ በሚለው መሠረት+ ሁሉንም ነገር ከፈጸሙ በኋላ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ መኖሪያ ከተማቸው ወደ ናዝሬት+ ተመለሱ። 40 ሕፃኑም እያደገና እየጠነከረ እንዲሁም በጥበብ እየተሞላ ሄደ፤ የአምላክም ሞገስ በእሱ ላይ ነበር።+
41 ወላጆቹም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል* ወደ ኢየሩሳሌም የመሄድ ልማድ ነበራቸው።+ 42 ኢየሱስ የ12 ዓመት ልጅ ሳለ እንደተለመደው በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።+ 43 በዓሉ የሚከበርባቸው ቀናት ተጠናቀው መመለስ በጀመሩ ጊዜ ኢየሱስ እዚያው ኢየሩሳሌም ቀረ፤ ወላጆቹም ይህን አላስተዋሉም ነበር። 44 አብረዋቸው ከሚጓዙት ሰዎች ጋር ያለ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላም ዘመዶቻቸውና የሚያውቋቸው ሰዎች ጋ ይፈልጉት ጀመር። 45 ባጡት ጊዜ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እሱን ለማግኘትም ብዙ ደከሙ። 46 በመጨረሻም ከሦስት ቀን በኋላ ቤተ መቅደሱ ውስጥ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲያዳምጣቸውና ሲጠይቃቸው አገኙት። 47 በዚያ የነበሩት ሰዎችም ሁሉ በመረዳት ችሎታውና በመልሱ ተደንቀው ያዳምጡት ነበር።+ 48 ወላጆቹም ባዩት ጊዜ ተገረሙ፤ እናቱም “ልጄ፣ ምነው እንዲህ አደረግከን? እኔና አባትህ እኮ በጣም ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” አለችው። 49 እሱ ግን “ለምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት መሆን እንደሚገባኝ አታውቁም?” አላቸው።+ 50 እነሱ ግን ምን እያላቸው እንዳለ አልገባቸውም።
51 ከዚያም ኢየሱስ አብሯቸው ወደ ናዝሬት ተመለሰ፤ እንደ ወትሮውም ይገዛላቸው* ነበር።+ እናቱም የተባሉትን ነገሮች ሁሉ በልቧ ትይዝ ነበር።+ 52 ኢየሱስም በአካልና በጥበብ እያደገ እንዲሁም በአምላክና በሰው ፊት ይበልጥ ሞገስ እያገኘ ሄደ።
3 ጢባርዮስ ቄሳር በነገሠ በ15ኛው ዓመት፣ ጳንጥዮስ ጲላጦስ የይሁዳ አገረ ገዢ፣ ሄሮድስ*+ የገሊላ አውራጃ ገዢ፣* ወንድሙ ፊልጶስ ደግሞ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አውራጃ ገዢ፣ ሊሳኒዮስ የአቢላኒስ አውራጃ ገዢ በነበሩበት ጊዜ 2 እንዲሁም ቀያፋና የካህናት አለቃው ሐና በነበሩበት ዘመን+ የአምላክ ቃል በምድረ በዳ+ ወደነበረው ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ+ መጣ።
3 ዮሐንስም ለኃጢአት ይቅርታ፣ የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለው አገር ሁሉ ሄደ፤+ 4 ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት ነው፦ “አንድ ሰው በምድረ በዳ ‘የይሖዋን* መንገድ አዘጋጁ! ጎዳናዎቹንም አቅኑ’ በማለት ይጮኻል።+ 5 ‘ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤ ተራራውና ኮረብታው ሁሉ ይደልደል፤ ጠማማው መንገድ ቀጥ ያለ፣ ጎርበጥባጣውም መንገድ ለጥ ያለ ይሁን፤ 6 ሥጋም* ሁሉ የአምላክን ማዳን* ያያል።’”+
7 በመሆኑም ዮሐንስ በእሱ እጅ ለመጠመቅ የሚመጡትን ሰዎች እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ያስጠነቀቃችሁ ማን ነው?+ 8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ። ‘እኛ እኮ አባታችን አብርሃም ነው’ እያላችሁ ራሳችሁን አታጽናኑ። አምላክ ለአብርሃም ከእነዚህ ድንጋዮች ልጆች ማስነሳት እንደማይሳነው ልነግራችሁ እወዳለሁ። 9 እንዲያውም መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።”+
10 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ “ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” ብለው ይጠይቁት ነበር። 11 እሱም መልሶ “ሁለት ልብስ* ያለው አንዱን ምንም ለሌለው ይስጥ፤ ምግብ ያለውም እንዲሁ ያድርግ” አላቸው።+ 12 ቀረጥ ሰብሳቢዎች እንኳ ሳይቀሩ ለመጠመቅ+ ወደ እሱ መጥተው “መምህር፣ ምን እናድርግ?” አሉት። 13 እሱም “ከተተመነው ቀረጥ በላይ አትጠይቁ”* አላቸው።+ 14 ወታደሮች ደግሞ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እሱም “በማንም ላይ ግፍ አትሥሩ* ወይም ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፤+ ከዚህ ይልቅ ባላችሁ መተዳደሪያ* ረክታችሁ ኑሩ” አላቸው።
15 ሕዝቡ ክርስቶስን ይጠባበቁ ስለነበር “ይህ ሰው ክርስቶስ ይሆን?” እያሉ ሁሉም በልባቸው ስለ ዮሐንስ ያስቡ ነበር።+ 16 ዮሐንስ ለሁሉም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ሆኖም ከእኔ የሚበረታ የሚመጣ ሲሆን እኔ የጫማውን ማሰሪያ እንኳ ለመፍታት አልበቃም።+ እሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።+ 17 አውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን ወደ ጎተራ ለማስገባት ላይዳውን* በእጁ ይዟል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”
18 በተጨማሪም ዮሐንስ በተለያዩ መንገዶች ምክር በመስጠት ለሕዝቡ ምሥራች ማብሰሩን ቀጠለ። 19 ሆኖም የአውራጃ ገዢ የሆነው ሄሮድስ የወንድሙ ሚስት በሆነችው በሄሮድያዳ ምክንያትና በሠራቸው ሌሎች ክፉ ድርጊቶች የተነሳ ዮሐንስ ስለወቀሰው 20 በክፋት ላይ ክፋት በመጨመር ዮሐንስን ወህኒ ቤት አስገባው።+
21 ሕዝቡም ሁሉ እየተጠመቁ በነበረ ጊዜ ኢየሱስም ተጠመቀ።+ እየጸለየም ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤+ 22 መንፈስ ቅዱስም አካላዊ ቅርጽ ይዞ በርግብ መልክ በእሱ ላይ ወረደ፤ ከዚያም “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።+
23 ኢየሱስ+ ሥራውን ሲጀምር 30 ዓመት ገደማ ሆኖት ነበር፤+ ሕዝቡም የዮሴፍ ልጅ+ እንደሆነ አድርገው ያስቡ ነበር፤
ዮሴፍ የሄሊ ልጅ፣
24 ሄሊ የማታት ልጅ፣
ማታት የሌዊ ልጅ፣
ሌዊ የሚልኪ ልጅ፣
ሚልኪ የያና ልጅ፣
ያና የዮሴፍ ልጅ፣
25 ዮሴፍ የማታትዩ ልጅ፣
ማታትዩ የአሞጽ ልጅ፣
አሞጽ የናሆም ልጅ፣
ናሆም የኤስሊ ልጅ፣
ኤስሊ የናጌ ልጅ፣
26 ናጌ የማአት ልጅ፣
ማአት የማታትዩ ልጅ፣
ማታትዩ የሴሜይ ልጅ፣
ሴሜይ የዮሴክ ልጅ፣
ዮሴክ የዮዳ ልጅ፣
27 ዮዳ የዮናን ልጅ፣
ዮናን የሬስ ልጅ፣
ሬስ የዘሩባቤል ልጅ፣+
ዘሩባቤል የሰላትያል ልጅ፣+
ሰላትያል የኔሪ ልጅ፣
28 ኔሪ የሚልኪ ልጅ፣
ሚልኪ የሐዲ ልጅ፣
ሐዲ የቆሳም ልጅ፣
ቆሳም የኤልሞዳም ልጅ፣
ኤልሞዳም የኤር ልጅ፣
ኢየሱስ የኤሊዔዘር ልጅ፣
ኤሊዔዘር የዮሪም ልጅ፣
ዮሪም የማታት ልጅ፣
ማታት የሌዊ ልጅ፣
30 ሌዊ የሲምዖን ልጅ፣
ሲምዖን የይሁዳ ልጅ፣
ይሁዳ የዮሴፍ ልጅ፣
ዮሴፍ የዮናም ልጅ፣
ዮናም የኤልያቄም ልጅ፣
31 ኤልያቄም የሜልያ ልጅ፣
ሜልያ የሜና ልጅ፣
ሜና የማጣታ ልጅ፣
ማጣታ የናታን ልጅ፣+
ናታን የዳዊት ልጅ፣+
እሴይ የኢዮቤድ ልጅ፣+
ኢዮቤድ የቦዔዝ ልጅ፣+
ቦዔዝ የሰልሞን ልጅ፣+
ሰልሞን የነአሶን ልጅ፣+
33 ነአሶን የአሚናዳብ ልጅ፣
አሚናዳብ የአርናይ ልጅ፣
አርናይ የኤስሮን ልጅ፣
ኤስሮን የፋሬስ ልጅ፣+
ፋሬስ የይሁዳ ልጅ፣+
ያዕቆብ የይስሐቅ ልጅ፣+
ይስሐቅ የአብርሃም ልጅ፣+
አብርሃም የታራ ልጅ፣+
ታራ የናኮር ልጅ፣+
ሴሮህ የረኡ ልጅ፣+
ረኡ የፋሌቅ ልጅ፣+
ፋሌቅ የኤቤር ልጅ፣+
ኤቤር የሴሎም ልጅ፣+
36 ሴሎም የቃይናን ልጅ፣
ቃይናን የአርፋክስድ ልጅ፣+
አርፋክስድ የሴም ልጅ፣+
ሴም የኖኅ ልጅ፣+
ኖኅ የላሜህ ልጅ፣+
ማቱሳላ የሄኖክ ልጅ፣
ሄኖክ የያሬድ ልጅ፣+
ያሬድ የመላልኤል ልጅ፣+
መላልኤል የቃይናን ልጅ፣+
ሄኖስ የሴት ልጅ፣+
ሴት የአዳም ልጅ፣+
አዳም የአምላክ ልጅ።
4 ከዚያም ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ተመለሰ፤ በምድረ በዳም ሳለ መንፈስ ይመራው ነበር፤+ 2 በዚያም 40 ቀን ቆየ፤ ዲያብሎስም ፈተነው።+ በእነዚህም ቀናት ምንም ስላልበላ መጨረሻ ላይ ተራበ። 3 በዚህ ጊዜ ዲያብሎስ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ይህ ድንጋይ ዳቦ እንዲሆን እዘዝ” አለው። 4 ኢየሱስ ግን “‘ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰለት።+
5 ዲያብሎስም ወደ አንድ ከፍ ያለ ቦታ አወጣውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።+ 6 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ይህ ሁሉ ሥልጣንና የእነዚህ መንግሥታት ክብር ተሰጥቶኛል፤+ እኔ ደግሞ ለፈለግኩት መስጠት ስለምችል ለአንተ እሰጥሃለሁ። 7 ስለዚህ አንድ ጊዜ በፊቴ ተደፍተህ ብታመልከኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።” 8 ኢየሱስም መልሶ “‘ይሖዋ* አምላክህን ብቻ አምልክ፤ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው።+
9 ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት* ላይ አቁሞ እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤+ 10 እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘አንተን እንዲጠብቁ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ 11 እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’”+ 12 ኢየሱስም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* አትፈታተነው’ ተብሏል” አለው።+ 13 ዲያብሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ትቶት ሄደ።+
14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ።+ ዝናውም በዙሪያው ባለ አገር ሁሉ ተሰራጨ። 15 በተጨማሪም በምኩራቦቻቸው ማስተማር ጀመረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ያከብረው ነበር።
16 ከዚያም ወዳደገበት ቦታ ወደ ናዝሬት መጣ፤+ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባ፤+ ሊያነብም ተነስቶ ቆመ። 17 የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልልም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም ተርትሮ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ፦ 18 “የይሖዋ* መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ምክንያቱም ለድሆች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል። ለተማረኩት ነፃነትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቆኑትን ነፃ እንዳወጣ+ 19 እንዲሁም የይሖዋን* ሞገስ ስለሚያገኙበት ዓመት+ እንድሰብክ ልኮኛል።” 20 ከዚያም ጥቅልሉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኩራቡ ውስጥ ያሉት ሰዎችም ሁሉ ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር። 21 እሱም “ይህ አሁን የሰማችሁት የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ዛሬ ተፈጸመ” አላቸው።+
22 ሁሉም ስለ እሱ መልካም ነገር ይናገሩ ጀመር፤ ከአፉ በሚወጡት የሚማርኩ ቃላትም+ በመደነቅ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ?” ይሉ ነበር።+ 23 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “‘አንተ ሐኪም፣ እስቲ ራስህን አድን’ የሚለውን አባባል እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም። ‘በቅፍርናሆም+ እንደተደረገ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ አገርም አድርግ’ ትሉኛላችሁ።” 24 እንዲህም አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ነቢይ በገዛ አገሩ ተቀባይነት አያገኝም።+ 25 እውነቱን ልንገራችሁ፦ ለምሳሌ በኤልያስ ዘመን ሰማይ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር በተዘጋና በምድሪቱ ሁሉ ላይ ጽኑ ረሃብ በተከሰተ ጊዜ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ።+ 26 ሆኖም ኤልያስ በሲዶና አገር በሰራፕታ ትኖር ወደነበረች አንዲት መበለት ተላከ እንጂ ከእነዚህ ሴቶች ወደ አንዷም አልተላከም።+ 27 በተጨማሪም በነቢዩ ኤልሳዕ ዘመን በእስራኤል ብዙ የሥጋ ደዌ በሽተኞች ነበሩ፤ ሆኖም ከሶርያዊው ከንዕማን በስተቀር ከእነሱ መካከል አንድም ሰው አልነጻም።”*+ 28 በምኩራቡ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ይህን ሲሰሙ እጅግ ተቆጡ፤+ 29 ተነስተውም እያጣደፉ ከከተማው አስወጡት፤ ቁልቁል ገፍትረው ሊጥሉትም ፈልገው ከተማቸው ወደምትገኝበት ተራራ አፋፍ ወሰዱት። 30 እሱ ግን በመካከላቸው ሰንጥቆ ሄደ።+
31 ከዚያም በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ወረደ። እዚያም በሰንበት ሕዝቡን ያስተምር ነበር፤+ 32 በሥልጣን ይናገር ስለነበረም ሕዝቡ በትምህርት አሰጣጡ እጅግ ተደነቁ።+ 33 በምኩራቡም ውስጥ ርኩስ መንፈስ ማለትም ጋኔን ያደረበት አንድ ሰው ነበር፤ ሰውየውም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፦+ 34 “እንዴ! የናዝሬቱ ኢየሱስ፣+ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን? የመጣኸው ልታጠፋን ነው? ማን እንደሆንክ በሚገባ አውቃለሁ፤ አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ ነህ።”+ 35 ሆኖም ኢየሱስ “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም ሰውየውን በሕዝቡ ፊት ከጣለው በኋላ ምንም ሳይጎዳው ለቆት ወጣ። 36 በዚህ ጊዜ ሁሉም በመገረም “እንዴ! ይህ ምን ዓይነት አነጋገር ነው? ርኩሳን መናፍስትን በሥልጣንና በኃይል ያዛል፤ እነሱም ታዘው ይወጣሉ!” ሲሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር። 37 ስለ ኢየሱስ የሚወራው ወሬም በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተዳረሰ።
38 ኢየሱስ ከምኩራቡ ከወጣ በኋላ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት ኃይለኛ ትኩሳት ይዟት እየተሠቃየች ነበር፤ እነሱም እንዲረዳት ለመኑት።+ 39 እሱም አጠገቧ ቆመና ጎንበስ ብሎ ትኩሳቱን ገሠጸው፤ ትኩሳቱም ለቀቃት። ወዲያውም ተነስታ ታገለግላቸው ጀመር።
40 ፀሐይ ስትጠልቅም ሰዎች በተለያየ በሽታ የተያዙ ሕመምተኞቻቸውን ወደ እሱ አመጡ። እሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው።+ 41 አጋንንትም “አንተ የአምላክ ልጅ ነህ” እያሉና እየጮኹ+ ከብዙ ሰዎች ወጡ። እሱ ግን ገሠጻቸው፤ ክርስቶስ መሆኑንም አውቀው ስለነበር+ እንዳይናገሩ ከለከላቸው።+
42 በነጋም ጊዜ ወጥቶ ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ።+ ሕዝቡ ግን ፈልገው ፈላልገው * ያለበት ቦታ ድረስ መጡ፤ እንዳይሄድባቸውም ለመኑት። 43 እሱ ግን “ለሌሎች ከተሞችም የአምላክን መንግሥት ምሥራች ማወጅ አለብኝ፤ ምክንያቱም የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው” አላቸው።+ 44 በመሆኑም በይሁዳ ምኩራቦች መስበኩን ቀጠለ።
5 አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሴሬጥ ሐይቅ*+ ዳርቻ ቆሞ የአምላክን ቃል ሲያስተምር ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ያዳምጡት ነበር፤ ከዚያም ሰዎቹ እየተገፋፉ ያጨናንቁት ጀመር። 2 በዚህ ጊዜ ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ዳርቻ ቆመው ተመለከተ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ላይ ወርደው መረቦቻቸውን እያጠቡ ነበር።+ 3 ኢየሱስም አንደኛዋ ጀልባ ላይ ወጣ፤ የጀልባዋ ባለቤት የሆነውን ስምዖንንም ከየብስ ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ጠየቀው። ከዚያም ጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር። 4 ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን “ጥልቅ ወደሆነው አካባቢ ፈቀቅ በልና መረቦቻችሁን ጥላችሁ አጥምዱ” አለው። 5 ሆኖም ስምዖን መልሶ “መምህር፣ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም፤+ አንተ ካልክ ግን መረቦቹን እጥላለሁ” አለው። 6 እንደተባሉት ባደረጉም ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ። እንዲያውም መረቦቻቸው መበጣጠስ ጀመሩ።+ 7 በመሆኑም በሌላኛው ጀልባ ላይ የነበሩትን የሥራ ባልደረቦቻቸውን መጥተው እንዲያግዟቸው በምልክት ጠሯቸው፤ እነሱም መጡ፤ ሁለቱንም ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፤ ከዚህም የተነሳ ጀልባዎቹ መስጠም ጀመሩ። 8 ስምዖን ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ እግር ሥር ተንበርክኮ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ስለሆንኩ ከእኔ ራቅ” አለው። 9 ይህን ያለው እሱና ከእሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ከያዙት ዓሣ ብዛት የተነሳ በጣም ስለተደነቁ ነው፤ 10 የስምዖን የሥራ ባልደረቦች የሆኑት የዘብዴዎስ ልጆች+ ያዕቆብና ዮሐንስም በጣም ተደንቀው ነበር። ኢየሱስ ግን ስምዖንን “አይዞህ አትፍራ፤ ከአሁን ጀምሮ ሰውን* የምታጠምድ ትሆናለህ” አለው።+ 11 ስለዚህ ጀልባዎቹን መልሰው ወደ የብስ ካስጠጉ በኋላ ሁሉን ነገር ትተው ተከተሉት።+
12 በሌላ ጊዜ ደግሞ በአንድ ከተማ ውስጥ በነበረበት ጊዜ መላ ሰውነቱን የሥጋ ደዌ የወረሰው ሰው በዚያ ነበር። ሰውየውም ኢየሱስን ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ “ጌታ ሆይ፣ ብትፈልግ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ሲል ለመነው።+ 13 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው። ወዲያውኑ የሥጋ ደዌው ለቀቀው።+ 14 ከዚያም ኢየሱስ ሰውየውን ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ባዘዘው መሠረት+ ስለ መንጻትህ መባ አቅርብ፤ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ” አለው።+ 15 ሆኖም ስለ እሱ የሚወራው ወሬ ይበልጥ እየተሰራጨ ሄደ፤ በጣም ብዙ ሰዎችም የሚናገረውን ለመስማትና ከበሽታቸው ለመፈወስ ይሰበሰቡ ነበር።+ 16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ጭር ወዳሉ ስፍራዎች በመሄድ ይጸልይ ነበር።
17 አንድ ቀን ኢየሱስ እያስተማረ ሳለ ከገሊላ፣ ከይሁዳ መንደሮች ሁሉ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕጉ መምህራን በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ ሰዎችንም ለመፈወስ የሚያስችለው የይሖዋ* ኃይል ከኢየሱስ ጋር ነበር።+ 18 በዚያን ጊዜም አንድ ሽባ ሰው በቃሬዛ የተሸከሙ ሰዎች መጡ፤ ሽባውን ወደ ውስጥ ለማስገባትና ኢየሱስ ፊት ለማስቀመጥ ጥረት አደረጉ።+ 19 ከሕዝቡም ብዛት የተነሳ መግቢያ ስላላገኙ ጣራው ላይ ወጥተው ጡቡን ካነሱ በኋላ የተኛበትን ቃሬዛ አሾልከው፣ ሽባውን ኢየሱስ ፊት በነበሩት ሰዎች መካከል አወረዱት። 20 ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት “አንተ ሰው፣ ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው።+ 21 በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን “አምላክን የሚዳፈረው ይሄ ማን ነው? ከአምላክ በቀር ኃጢአትን ማን ይቅር ሊል ይችላል?” ይባባሉ ጀመር።+ 22 ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ተረድቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በልባችሁ የምታስቡት ምንድን ነው? 23 ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሏል’ ከማለትና ‘ተነስተህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል? 24 ይሁንና የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ . . .” አላቸውና ሽባውን “ተነስ፣ ቃሬዛህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።+ 25 በዚህ ጊዜ ሰውየው በፊታቸው ተነስቶ ተኝቶበት የነበረውን ቃሬዛ ተሸከመና አምላክን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ። 26 ይህን ሲያዩ ሁሉም በአድናቆት ተውጠው አምላክን ማመስገን ጀመሩ፤ ታላቅ ፍርሃትም አድሮባቸው “ዛሬ የሚያስደንቅ ነገር አየን!” አሉ።
27 ይህ ከሆነም በኋላ ኢየሱስ ወጥቶ ሲሄድ ሌዊ የሚባል ቀረጥ ሰብሳቢ በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየና “ተከታዬ ሁን” አለው።+ 28 እሱም ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጎ በመተው ተነስቶ ይከተለው ጀመር። 29 ከዚያም ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ በግብዣውም ላይ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ሰዎች ከእነሱ ጋር ይበሉ ነበር።+ 30 ፈሪሳውያንና ከእነሱ ወገን የሆኑ ጸሐፍት ይህን ባዩ ጊዜ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” በማለት በደቀ መዛሙርቱ ላይ ማጉረምረም ጀመሩ።+ 31 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።+ 32 እኔ የመጣሁት ኃጢአተኞች ንስሐ እንዲገቡ ለመጥራት እንጂ ጻድቃንን ለመጥራት አይደለም።”+
33 እነሱም “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ እንዲሁም ምልጃ ያቀርባሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ፣ ይጠጣሉ” አሉት።+ 34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው ከእነሱ ጋር እያለ የሙሽራው ጓደኞች እንዲጾሙ ልታደርጓቸው ትችላላችሁ? 35 ሆኖም ሙሽራው+ ከእነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።”+
36 በተጨማሪም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “ከአዲስ ልብስ ላይ ቁራጭ ጨርቅ ወስዶ በአሮጌ ልብስ ላይ የሚጥፍ ሰው የለም። እንዲህ ቢያደርግ ግን አዲሱ ቁራጭ ጨርቅ ተቦጭቆ ይነሳል፤ ከአዲሱ ልብስ የተቆረጠው ጨርቅ ከአሮጌው ልብስ ጋር አይስማማም።+ 37 ደግሞም ባረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያስቀምጥ ሰው የለም። እንዲህ ቢያደርግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁ ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። 38 ስለዚህ አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ መቀመጥ አለበት። 39 አሮጌ የወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲሱን የሚፈልግ የለም፤ ምክንያቱም ‘አሮጌው ግሩም ነው’ ይላል።”
6 በአንድ የሰንበት ቀን ኢየሱስ በእህል እርሻ መካከል እያለፈ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ እሸት ቀጥፈው በእጃቸው እያሹ+ ይበሉ ነበር።+ 2 በዚህ ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን “በሰንበት ቀን በሕግ የተከለከለ ነገር የምታደርጉት ለምንድን ነው?” አሏቸው።+ 3 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ዳዊት እሱና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ነገር ፈጽሞ አላነበባችሁም?+ 4 ወደ አምላክ ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር ማንም እንዲበላው ያልተፈቀደውን በአምላክ ፊት የቀረበ ኅብስት ተቀብሎ እንደበላና ከእሱ ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው አላነበባችሁም?”+ 5 ከዚያም “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው” አላቸው።+
6 በሌላ የሰንበት ቀን+ ወደ ምኩራብ ገብቶ ያስተምር ጀመር። በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለ* አንድ ሰው ነበር።+ 7 ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም ኢየሱስን የሚከሱበት ምክንያት ማግኘት ይፈልጉ ስለነበር በሰንበት ይፈውስ እንደሆነ ለማየት በትኩረት ይከታተሉት ነበር። 8 እሱ ግን ሐሳባቸውን አውቆ+ ስለነበር እጁ የሰለለበትን* ሰው “ተነሳና መሃል ላይ ቁም” አለው። ሰውየውም ተነስቶ በዚያ ቆመ። 9 ከዚያም ኢየሱስ “እስቲ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ፤ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት* ማዳን ነው ወይስ ማጥፋት?” አላቸው።+ 10 በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ” አለው። ሰውየውም እንደተባለው አደረገ፤ እጁም ዳነለት። 11 እነሱ ግን እጅግ ተቆጡ፤ በኢየሱስ ላይ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉም እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር።
12 በዚያው ሰሞን ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤+ ሌሊቱንም ሙሉ ወደ አምላክ ሲጸልይ አደረ።+ 13 በነጋ ጊዜም ደቀ መዛሙርቱን ወደ እሱ ጠርቶ ከመካከላቸው 12 ሰዎች መረጠ፤ ሐዋርያት ብሎም ሰየማቸው፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦+ 14 ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፣ ወንድሙ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣+ በርቶሎሜዎስ፣ 15 ማቴዎስ፣ ቶማስ፣+ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ “ቀናተኛው” የሚባለው ስምዖን፣ 16 የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና በኋላ ከሃዲ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ።
17 ከእነሱም ጋር ከተራራው ወርዶ ደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ የሆኑ እጅግ ብዙ ሰዎችም በዚያ ነበሩ፤ በተጨማሪም እሱን ለመስማትና ከበሽታቸው ለመፈወስ ከይሁዳ ሁሉና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አካባቢ ከሚገኙት ከጢሮስና ከሲዶና የመጡ በጣም ብዙ ሰዎች ነበሩ። 18 በርኩሳን መናፍስት ይሠቃዩ የነበሩ ሰዎችም እንኳ ተፈወሱ። 19 ኃይል ከእሱ እየወጣ+ ሁሉንም ይፈውስ ስለነበር ሕዝቡ ሁሉ ሊነካው ይፈልግ ነበር።
20 ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ቀና ብሎ በመመልከት እንዲህ ይል ጀመር፦
“እናንተ ድሆች የሆናችሁ ደስተኞች ናችሁ፤ የአምላክ መንግሥት የእናንተ ነውና።+
21 “እናንተ አሁን የምትራቡ ደስተኞች ናችሁ፤ ኋላ ትጠግባላችሁና።+
“እናንተ አሁን የምታለቅሱ ደስተኞች ናችሁ፤ ኋላ ትስቃላችሁና።+
22 “ሰዎች፣ በሰው ልጅ ምክንያት በሚጠሏችሁ፣+ በሚያገሏችሁ፣+ በሚነቅፏችሁና ክፉ እንደሆናችሁ አድርገው ያለስማችሁ ስም በሚሰጧችሁ* ጊዜ ሁሉ ደስተኞች ናችሁ። 23 በሰማይ ታላቅ ሽልማት ስለሚጠብቃችሁ በዚያን ቀን ሐሴት አድርጉ፤ በደስታም ፈንጥዙ፤ አባቶቻቸው በነቢያት ላይ እንዲሁ ያደርጉ ነበርና።+
24 “ነገር ግን እናንተ ሀብታሞች ወዮላችሁ፤+ መጽናኛችሁን* በሙሉ አግኝታችኋልና።+
25 “እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፤ ኋላ ትራባላችሁና።
“እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፤ ኋላ ታዝናላችሁና፤ እንዲሁም ታለቅሳላችሁ።+
26 “ሰዎች ስለ እናንተ መልካም ነገር በሚናገሩበት ጊዜ ሁሉ ወዮላችሁ፤+ አባቶቻቸው ለሐሰተኛ ነቢያት እንዲህ ያለ ነገር አድርገው ነበርና።
27 “ለእናንተ ለምትሰሙ ግን እላችኋለሁ፦ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ፤+ 28 የሚረግሟችሁን መርቁ፤ እንዲሁም ለሚሰድቧችሁ ጸልዩ።+ 29 አንዱን ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ስጠው፤ መደረቢያህን ለሚወስድብህ እጀ ጠባብህንም አትከልክለው።+ 30 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤+ ንብረትህን የሚወስድብህንም ሰው እንዲመልስ አትጠይቀው።
31 “በተጨማሪም ልክ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ እንደምትፈልጉት ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።+
32 “የሚወዷችሁን ብቻ ብትወዱ ምን የሚያስመሰግን ነገር አለው? ኃጢአተኞችም እንኳ የሚወዷቸውን ይወዳሉና።+ 33 መልካም ለሚያደርጉላችሁ መልካም ብታደርጉስ ምን ዋጋ አለው? ኃጢአተኞችም እንኳ እንዲሁ ያደርጋሉ። 34 እንዲሁም ይመልስልኛል ብላችሁ ለምታስቡት ሰው ብታበድሩ* ምን ፋይዳ አለው?+ ኃጢአተኞችም እንኳ የሰጡትን ያህል መልሰው ለመቀበል ለኃጢአተኞች ያበድራሉ። 35 ከዚህ ይልቅ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ደግሞም በምላሹ ምንም ሳትጠብቁ አበድሩ፤+ ሽልማታችሁም ታላቅ ይሆናል፤ ደግሞም የልዑሉ አምላክ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ደግ ነውና።+ 36 አባታችሁ መሐሪ እንደሆነ ሁሉ እናንተም መሐሪዎች ሁኑ።+
37 “በተጨማሪም በሌሎች ላይ አትፍረዱ፤* በእናንተም ላይ ፈጽሞ አይፈረድባችሁም፤+ ሌሎችን አትኮንኑ፤ እናንተም ፈጽሞ አትኮነኑም። ምንጊዜም ሌሎችን ይቅር በሉ፤* እናንተም ይቅር ትባላላችሁ።*+ 38 ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል።+ ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና በተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው በእቅፋችሁ ይሰጧችኋል። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።”
39 ከዚያም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላል? ሁለቱም ተያይዘው ጉድጓድ ውስጥ አይወድቁም?+ 40 ተማሪ* ከአስተማሪው አይበልጥም፤ በሚገባ የተማረ ሁሉ ግን እንደ አስተማሪው ይሆናል። 41 ታዲያ በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለምን ታያለህ?+ 42 በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ ወንድምህን ‘ዓይንህ ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! መጀመሪያ በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ማየት ትችላለህ።
43 “መልካም ዛፍ ሆኖ ሳለ የበሰበሰ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም፤ እንዲሁም የበሰበሰ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም።+ 44 እያንዳንዱ ዛፍ በፍሬው ይታወቃል።+ ለምሳሌ ሰዎች ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፤ ወይም ከእሾሃማ ቁጥቋጦ ወይን አይቆርጡም። 45 ጥሩ ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር ጥሩ ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰው ግን ካከማቸው መጥፎ ነገር ክፉ ነገር ያወጣል፤ አንደበቱ የሚናገረው በልቡ ውስጥ የሞላውን ነውና።+
46 “ታዲያ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የምትሉኝ፣ የምለውን ግን የማታደርጉት ለምንድን ነው?+ 47 ወደ እኔ የሚመጣ፣ ቃሌን የሚሰማና የሚያደርግ ሁሉ ከማን ጋር እንደሚመሳሰል ልንገራችሁ፦+ 48 ቤት ለመሥራት በጥልቀት ቆፍሮ በዓለት ላይ መሠረቱን ከጣለ ሰው ጋር ይመሳሰላል። በኋላም ጎርፍ በመጣ ጊዜ ወንዙ ቤቱን በኃይል መታው፤ ሆኖም ቤቱ በደንብ ስለተገነባ ሊያነቃንቀው አልቻለም።+ 49 በሌላ በኩል ደግሞ ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ሰው+ ሁሉ መሠረት ሳይጥል፣ በአፈር ላይ ቤት ከሠራ ሰው ጋር ይመሳሰላል። ወንዙም ቤቱን በኃይል መታው፤ ወዲያውም ተደረመሰ፤ እንዳልነበረም ሆነ።”
7 ኢየሱስ ለሕዝቡ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ። 2 በዚያም አንድ የጦር መኮንን* ነበር፤ በጣም የሚወደው ባሪያውም በጠና ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር።+ 3 እሱም ስለ ኢየሱስ ሲሰማ መጥቶ ባሪያውን እንዲፈውስለት ይለምኑለት ዘንድ የተወሰኑ አይሁዳውያን ሽማግሌዎችን ላከ። 4 እነሱም ወደ ኢየሱስ መጥተው እንዲህ በማለት ተማጸኑት፦ “ይህን ሰው ልትረዳው ይገባል፤ 5 ምክንያቱም ሕዝባችንን ይወዳል፤ ምኩራባችንንም ያሠራልን እሱ ነው።” 6 ስለዚህ ኢየሱስ አብሯቸው ሄደ። ሆኖም ወደ ቤቱ በተቃረበ ጊዜ መኮንኑ ወዳጆቹን እንዲህ ሲል ወደ ኢየሱስ ላከ፦ “ጌታዬ፣ በቤቴ ጣሪያ ሥር ልትገባ የሚገባኝ ሰው ስላልሆንኩ አትድከም።+ 7 ከዚህም የተነሳ አንተ ፊት መቅረብ የሚገባኝ ሰው እንደሆንኩ አልተሰማኝም። ስለዚህ አንተ አንድ ቃል ተናገርና አገልጋዬ ይፈወስ። 8 እኔ ራሴ የምታዘዛቸው የበላይ አዛዦች አሉ፤ ለእኔም የሚታዘዙ የበታች ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።” 9 ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ በሰውየው በጣም ተደንቆ ይከተለው ወደነበረው ሕዝብ ዞር በማለት “እላችኋለሁ፣ በእስራኤል ውስጥ እንኳ እንዲህ ዓይነት ታላቅ እምነት አላገኘሁም” አለ።+ 10 የተላኩትም ሰዎች ወደ ቤት ሲመለሱ ባሪያው ድኖ አገኙት።+
11 ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ናይን ወደምትባል ከተማ ተጓዘ፤ ደቀ መዛሙርቱና ሌሎች ብዙ ሰዎችም አብረውት ይጓዙ ነበር። 12 ወደ ከተማዋ መግቢያ ሲቃረብ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው በመውጣት ላይ ነበሩ፤ ሟቹ ለእናቱ አንድ ልጇ ነበር።+ በተጨማሪም እናቱ መበለት ነበረች። ብዙ የከተማዋ ሕዝብም ከእሷ ጋር ነበር። 13 ጌታ ባያት ጊዜ በጣም አዘነላትና+ “በቃ፣ አታልቅሺ”+ አላት። 14 ከዚያም ቀረብ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙት ሰዎችም ባሉበት ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት፣ ተነስ እልሃለሁ!” አለ።+ 15 የሞተውም ሰው ቀና ብሎ ተቀመጠና መናገር ጀመረ፤ ኢየሱስም ለእናቱ ሰጣት።+ 16 በዚህ ጊዜ ሁሉም በፍርሃት ተውጠው “ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነስቷል፤”+ እንዲሁም “አምላክ ሕዝቡን አሰበ” እያሉ አምላክን ያወድሱ ጀመር።+ 17 ኢየሱስ ያከናወነውም ነገር በይሁዳ ሁሉና በአካባቢው ባለ አገር ሁሉ ተሰማ።
18 በዚህ ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ይህን ሁሉ አወሩለት።+ 19 ዮሐንስም ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ጠርቶ “ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ+ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው እንዲጠይቁት ወደ ጌታ ላካቸው። 20 ሰዎቹም ወደ ኢየሱስ መጥተው “መጥምቁ ዮሐንስ፣ ‘ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?’ ብለን እንድንጠይቅህ ወደ አንተ ልኮናል” አሉት። 21 ኢየሱስ በዚያኑ ሰዓት ብዙዎችን ከሕመምና ከከባድ በሽታ ፈወሳቸው፤+ እንዲሁም ያደሩባቸውን ክፉ መናፍስት አወጣ፤ የብዙ ዓይነ ስውራንንም ዓይን አበራ። 22 እሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፦ ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤+ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+ 23 በእኔ ምክንያት የማይሰናከል ደስተኛ ነው።”+
24 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ይናገር ጀመር፦ “ወደ ምድረ በዳ የሄዳችሁት ምን ለማየት ነበር? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆ?+ 25 ታዲያ ምን ለማየት ነበር የሄዳችሁት? ምርጥ ልብስ* የለበሰ ሰው ለማየት?+ የተንቆጠቆጠ ልብስ የሚለብሱና በቅንጦት የሚኖሩማ የሚገኙት በቤተ መንግሥት ነው። 26 ታዲያ ምን ለማየት ሄዳችሁ? ነቢይ? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጥ ነው።+ 27 ‘እነሆ፣ ከፊትህ እየሄደ መንገድህን እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ’ ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ነው።+ 28 እላችኋለሁ፣ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ የለም፤ ሆኖም በአምላክ መንግሥት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።”+ 29 (ሕዝቡ ሁሉ እንዲሁም ቀራጮች ይህን በሰሙ ጊዜ በዮሐንስ ጥምቀት ተጠምቀው ስለነበር አምላክ ጻድቅ መሆኑን አምነው ተቀበሉ።+ 30 ሆኖም ፈሪሳውያንና የሕጉ አዋቂዎች በዮሐንስ ባለመጠመቃቸው የአምላክን ምክር* አቃለሉ።)+
31 ኢየሱስ በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የዚህን ትውልድ ሰዎች ከማን ጋር ላነጻጽራቸው? ማንንስ ይመስላሉ?+ 32 በገበያ ስፍራ ተቀምጠው እርስ በርሳቸው እየተጠራሩ ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ እናንተ ግን አላለቀሳችሁም’ ከሚባባሉ ልጆች ጋር ይመሳሰላሉ። 33 በተመሳሳይም መጥምቁ ዮሐንስ እህል ሳይበላና ወይን ጠጅ ሳይጠጣ መጣ፤+ እናንተ ግን ‘ጋኔን አለበት’ አላችሁ። 34 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እናንተ ግን ‘እዩ፣ ይህን ሆዳምና ለወይን ጠጅ ያደረ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኃጢአተኞች ወዳጅ!’ አላችሁ።+ 35 የሆነ ሆኖ፣ ጥበብ ጻድቅ* መሆኗ በልጆቿ* ሁሉ ተረጋግጧል።”+
36 ከዚህ በኋላ ከፈሪሳውያን አንዱ አብሮት እንዲበላ ኢየሱስን ደጋግሞ ለመነው። ስለሆነም ኢየሱስ ወደ ፈሪሳዊው ቤት ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። 37 እነሆም፣ በከተማው ውስጥ በኃጢአተኝነቷ የምትታወቅ አንዲት ሴት ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት እየበላ መሆኑን በሰማች ጊዜ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች።+ 38 እሷም ከበስተ ኋላ እግሩ አጠገብ ሆና እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመር፤ ከዚያም በፀጉሯ አበሰችው። በተጨማሪም እግሩን እየሳመች ዘይቱን ቀባችው። 39 የጋበዘው ፈሪሳዊም ይህን ሲያይ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢይ ቢሆን ኖሮ የምትነካው ማን መሆኗንና ምን ዓይነት ሴት እንደሆነች ይኸውም ኃጢአተኛ መሆኗን ባወቀ ነበር” ብሎ በልቡ አሰበ።+ 40 ኢየሱስ ግን መልሶ “ስምዖን፣ አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። እሱም “መምህር፣ እሺ ንገረኝ” አለው።
41 “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንዱ 500 ሌላው ደግሞ 50 ዲናር* ተበድረው ነበር። 42 ሁለቱም የተበደሩትን መክፈል ባቃታቸው ጊዜ አበዳሪው ዕዳቸውን ሙሉ በሙሉ ተወላቸው። እንግዲህ ከሁለቱ ሰዎች አበዳሪውን አብልጦ የሚወደው የትኛው ነው?” 43 ስምዖንም መልሶ “ብዙ ዕዳ የተተወለት ይመስለኛል” አለው። እሱም “በትክክል ፈርደሃል” አለው። 44 ከዚያም ወደ ሴቲቱ ዞር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያታለህ? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ይሁንና አንተ ለእግሬ ውኃ አልሰጠኸኝም። ይህች ሴት ግን እግሬን በእንባዋ እያራሰች በፀጉሯ አበሰች። 45 አንተ አልሳምከኝም፤ ይህች ሴት ግን ከገባሁበት ሰዓት አንስቶ እግሬን መሳሟን አላቋረጠችም። 46 አንተ ራሴን ዘይት አልቀባህም፤ ይህች ሴት ግን እግሬን ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ቀባች። 47 ስለዚህ እልሃለሁ፣ ኃጢአቷ ብዙ* ቢሆንም ይቅር ተብሎላታል፤+ ምክንያቱም ታላቅ ፍቅር አሳይታለች። በትንሹ ይቅር የተባለ ግን የሚያሳየውም ፍቅር አነስተኛ ነው።” 48 ከዚያም ሴትየዋን “ኃጢአትሽ ይቅር ተብሎልሻል” አላት።+ 49 በማዕድ አብረውት የተቀመጡት በልባቸው “ኃጢአትን እንኳ ይቅር የሚል ይህ ሰው ማን ነው?” ይሉ ጀመር።+ 50 ኢየሱስ ግን ሴትየዋን “እምነትሽ አድኖሻል፤+ በሰላም ሂጂ” አላት።
8 ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የአምላክን መንግሥት ምሥራች እየሰበከና እያወጀ ከከተማ ወደ ከተማ እንዲሁም ከመንደር ወደ መንደር ተጓዘ።+ አሥራ ሁለቱም ከእሱ ጋር ነበሩ፤ 2 በተጨማሪም ከክፉ መናፍስትና ከበሽታ የተፈወሱ አንዳንድ ሴቶች አብረውት ነበሩ፦ ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የተባለችው ማርያም፣ 3 የሄሮድስ ቤት አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐና፣+ ሶስና እንዲሁም ሌሎች ብዙ ሴቶች የነበሩ ሲሆን በንብረታቸው ያገለግሏቸው ነበር።+
4 ኢየሱስም የየከተማው ሕዝብ ተከትሎት በመጣ ጊዜና እጅግ ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት ወቅት እንዲህ ሲል በምሳሌ ተናገረ፦+ 5 “አንድ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ። በሚዘራበት ጊዜ አንዳንዶቹ ዘሮች መንገድ ዳር ወድቀው ተረጋገጡ፤ የሰማይ ወፎችም መጥተው ለቀሟቸው።+ 6 አንዳንዶቹ ዓለት ላይ ወደቁ፤ ከበቀሉም በኋላ እርጥበት ስላላገኙ ደረቁ።+ 7 ሌሎቹ ደግሞ በእሾህ መካከል ወደቁ፤ አብሯቸው ያደገውም እሾህ አነቃቸው።+ 8 ሌሎቹ ግን ጥሩ አፈር ላይ ወደቁ፤ ከበቀሉም በኋላ 100 እጥፍ አፈሩ።”+ ይህን ከተናገረ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ “የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” አለ።+
9 ደቀ መዛሙርቱ ግን የዚህን ምሳሌ ትርጉም ጠየቁት።+ 10 እሱም እንዲህ አለ፦ “ለእናንተ የአምላክን መንግሥት ቅዱስ ሚስጥሮች የመረዳት ችሎታ ተሰጥቷችኋል፤ ለቀሩት ግን በምሳሌ እነግራቸዋለሁ፤+ ይኸውም እያዩ እንዳያስተውሉ እንዲሁም እየሰሙ ትርጉሙን እንዳይረዱ ነው።+ 11 እንግዲህ የምሳሌው ትርጉም ይህ ነው፦ ዘሩ የአምላክ ቃል ነው።+ 12 በመንገድ ዳር የወደቁት ቃሉን የሰሙ ናቸው፤ ከዚያ በኋላ ግን አምነው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል።+ 13 በዓለት ላይ የወደቁት ቃሉን ሲሰሙ በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ ነገር ግን ሥር የላቸውም። ለጊዜው አምነው ቢቀበሉም በፈተና ወቅት ይወድቃሉ።+ 14 በእሾህ መካከል የወደቁት ቃሉን የሰሙ ናቸው፤ ሆኖም በዚህ ዓለም የኑሮ ጭንቀት፣ ሀብትና+ ሥጋዊ ደስታ+ ትኩረታቸው ተከፋፍሎ ሙሉ በሙሉ ይታነቃሉ፤ ለፍሬም አይበቁም።+ 15 በጥሩ አፈር ላይ የወደቁት ደግሞ ቃሉን በመልካምና በጥሩ ልብ+ ሰምተው በውስጣቸው በማኖር በጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።+
16 “መብራት አብርቶ ዕቃ የሚከድንበት ወይም አልጋ ሥር የሚያስቀምጥ ሰው የለም፤ ከዚህ ይልቅ ወደ ቤት የሚገቡ ሁሉ ብርሃን እንዲያገኙ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል።+ 17 በመሆኑም ተሸሽጎ የማይገለጥ፣ በሚገባ ቢሰወርም የማይታወቅና ይፋ የማይወጣ ነገር የለም።+ 18 ስለዚህ እንዴት እንደምታዳምጡ በጥሞና አስቡ፤ ላለው ተጨማሪ ይሰጠዋልና፤+ የሌለው ግን እንዳለው አድርጎ የሚያስበው ነገር እንኳ ይወሰድበታል።”+
19 ከዚህ በኋላ እናቱና ወንድሞቹ+ እሱ ወዳለበት መጡ፤ ሆኖም ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ወደ እሱ ሊቀርቡ አልቻሉም።+ 20 ስለዚህ “እናትህና ወንድሞችህ ሊያገኙህ ፈልገው ውጭ ቆመዋል” ተብሎ ተነገረው። 21 እሱም መልሶ “እናቴና ወንድሞቼ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው” አላቸው።+
22 አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጀልባ ከተሳፈረ በኋላ “ወደ ሐይቁ ማዶ እንሻገር” አላቸው። በመሆኑም ጉዞ ጀመሩ።+ 23 እየተጓዙም ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደው። በዚህ ጊዜ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በሐይቁ ላይ ተነሳ፤ ጀልባቸውም በውኃ መሞላት ስለጀመረች አደጋ ላይ ወደቁ።+ 24 ስለዚህ ሄደው ቀሰቀሱትና “መምህር፣ መምህር ማለቃችን እኮ ነው!” አሉት። እሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ ነፋሱንና የሚናወጠውን ውኃ ገሠጸ፤ በዚህ ጊዜ ነፋሱ ቆመ፤ ጸጥታም ሰፈነ።+ 25 ከዚያም “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነሱ ግን በፍርሃት ተውጠውና በጣም ተደንቀው እርስ በርሳቸው “ለመሆኑ ይህ ማን ነው? ነፋስና ውኃ እንኳ ይታዘዙለታል” ተባባሉ።+
26 ከዚያም በገሊላ ማዶ ወደሚገኘው ጌርጌሴኖን+ ወደተባለው ክልል የባሕር ዳርቻ ደረሱ። 27 ኢየሱስ ከጀልባዋ ወደ የብስ በወረደ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት በአቅራቢያው በሚገኝ ከተማ የሚኖር አንድ ሰው አገኘው። ይህ ሰው ልብስ መልበስ ከተወ ብዙ ጊዜ ሆኖት ነበር፤ የሚኖረውም በቤት ውስጥ ሳይሆን በመቃብር ስፍራ ነበር።+ 28 ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እየጮኸ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም “የልዑል አምላክ ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለ።+ 29 (ይህን ያለውም ኢየሱስ ርኩሱ መንፈስ ከሰውየው እንዲወጣ እያዘዘው ስለነበረ ነው። ርኩሱ መንፈስ ሰውየውን ብዙ ጊዜ ይይዘው ነበር፤*+ ሰውየው በተደጋጋሚ በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም የታሰረበትን ሰንሰለት ይበጣጥስ ነበር፤ ጋኔኑም ጭር ወዳሉ ቦታዎች ይነዳው ነበር።) 30 ኢየሱስ “ስምህ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ስለነበር “ሌጌዎን” አለው። 31 አጋንንቱም ወደ ጥልቁ እንዲሄዱ እንዳያዛቸው ተማጸኑት።+ 32 በዚያም በተራራው ላይ ብዛት ያለው የአሳማ+ መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ ስለዚህ ወደ አሳማዎቹ ይገቡ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ተማጸኑት፤ እሱም ፈቀደላቸው።+ 33 በዚህ ጊዜ አጋንንቱ ከሰውየው ወጥተው አሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ የአሳማውም መንጋ ከገደሉ አፋፍ* እየተንደረደረ በመውረድ ሐይቁ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። 34 እረኞቹ ግን የሆነውን ነገር ሲያዩ ሸሽተው በመሄድ ወሬውን በከተማውና በገጠሩ አዳረሱ።
35 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ የሆነውን ነገር ለማየት ወጡ። ወደ ኢየሱስ ሲመጡም አጋንንት የወጡለት ሰው ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጦ አገኙት፤ በዚህ ጊዜ ፍርሃት አደረባቸው። 36 የተፈጸመውን ነገር ያዩ ሰዎች አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው እንዴት ጤናማ ሊሆን እንደቻለ አወሩላቸው። 37 በዚህ ጊዜ ከጌርጌሴኖን ክልል የመጡት ሰዎች በሙሉ ታላቅ ፍርሃት ስላደረባቸው ኢየሱስን ከዚያ እንዲሄድላቸው ለመኑት። እሱም ከዚያ ለመሄድ ጀልባዋ ላይ ተሳፈረ። 38 አጋንንት የወጡለት ሰው ግን አብሮት ይሆን ዘንድ ደጋግሞ ለመነው፤ ሆኖም ኢየሱስ ሰውየውን እንዲህ ሲል አሰናበተው፦+ 39 “ወደ ቤትህ ተመለስ፤ አምላክ ያደረገልህንም ነገር ተናገር።” ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ነገር በከተማው ሁሉ እያወጀ ሄደ።
40 ሕዝቡ እየጠበቁት ስለነበር ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ ሁሉም በደስታ ተቀበሉት።+ 41 በዚህ ጊዜ ኢያኢሮስ የሚባል አንድ የምኩራብ አለቃ መጣ። ኢየሱስ እግር ላይም ወድቆ ወደ ቤቱ እንዲገባ ይማጸነው ጀመር፤+ 42 ይህን ያደረገው 12 ዓመት ገደማ የሆናት አንዲት ልጁ ልትሞት ተቃርባ ስለነበር ነው።
ኢየሱስ እየተጓዘ ሳለ ሕዝቡ እየተጋፋ ያጨናንቀው ነበር። 43 በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈስሳት+ የኖረች አንዲት ሴት የነበረች ሲሆን ይህችን ሴት ሊፈውሳት የቻለ አንድም ሰው አልነበረም።+ 44 ከኋላም መጥታ የልብሱን ዘርፍ ነካች፤+ ይፈሳት የነበረውም ደም ወዲያውኑ ቆመ። 45 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፣ ጴጥሮስ “መምህር፣ ሕዝቡ ከቦህ እየተጋፋህ ነው የሚሄደው” አለው።+ 46 ኢየሱስ ግን “ኃይል+ ከእኔ እንደወጣ ስለታወቀኝ አንድ ሰው ነክቶኛል” አለ። 47 ሴትየዋም ሳይታወቅባት መሄድ እንዳልቻለች በተረዳች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ ከዚያም ለምን እንደነካችውና እንዴት ወዲያውኑ እንደተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት ተናገረች። 48 እሱ ግን “ልጄ ሆይ፣ እምነትሽ አድኖሻል። በሰላም ሂጂ” አላት።+
49 ገና እየተናገረ ሳለ ከምኩራብ አለቃው ቤት የተላከ አንድ ሰው መጥቶ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታስቸግረው” አለው።+ 50 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ “አትፍራ፤ ብቻ እመን፤ ልጅህ ትድናለች” አለው።+ 51 ወደ ኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቷ አባትና እናት በስተቀር ማንም አብሮት ወደ ውስጥ እንዲገባ አልፈቀደም። 52 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ ለልጅቷ እያለቀሱና በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ “በቃ አታልቅሱ፤+ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም”+ አላቸው። 53 ይህን ሲሰሙ ልጅቷ እንደሞተች ያውቁ ስለነበር በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። 54 እሱ ግን እጇን በመያዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” አለ።+ 55 የልጅቷም መንፈስ*+ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሳች፤+ የምትበላውም ነገር እንዲሰጧት አዘዘ። 56 ወላጆቿም የሚሆኑት ጠፋቸው፤ እሱ ግን የሆነውን ነገር ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።+
9 ከዚያም አሥራ ሁለቱን አንድ ላይ ጠርቶ አጋንንትን ሁሉ የማዘዝ+ እንዲሁም በሽታን የመፈወስ+ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው። 2 ደግሞም የአምላክን መንግሥት እንዲሰብኩና የታመሙትን እንዲፈውሱ ላካቸው፤ 3 እንዲህም አላቸው፦ “ለጉዟችሁ ምንም ነገር አትያዙ፤ በትርም ሆነ የምግብ ከረጢት፣ ዳቦም ሆነ ገንዘብ* እንዲሁም ሁለት ልብስ* አትያዙ።+ 4 ሆኖም ወደ አንድ ቤት ስትገቡ ከተማዋን ለቃችሁ እስክትሄዱ ድረስ እዚያው ቆዩ፤+ ከዚያም ተነስታችሁ ሂዱ። 5 በየትኛውም ከተማ የሚቀበላችሁ ሰው ካጣችሁ፣ ከዚያ ከተማ ስትወጡ ምሥክር እንዲሆንባቸው የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።”*+ 6 እነሱም ወጥተው በሄዱበት ሁሉ ምሥራቹን እየተናገሩና የታመሙትን እየፈወሱ ከመንደር ወደ መንደር በመሄድ ክልሉን አዳረሱ።+
7 በዚህ ጊዜ የአውራጃ* ገዢ የሆነው ሄሮድስ* የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ አንዳንዶች ዮሐንስ ከሞት ተነስቷል ይሉ ስለነበረም በጣም ግራ ተጋባ፤+ 8 ይሁንና ሌሎች ኤልያስ ተገልጧል፤ ሌሎች ደግሞ ከጥንት ነቢያት አንዱ ተነስቷል ይሉ ነበር።+ 9 ሄሮድስም “ዮሐንስን አንገቱን ቆርጬዋለሁ።+ ታዲያ እንዲህ ሲወራለት የምሰማው ይህ ሰው ማን ነው?” አለ። ስለሆነም ሊያየው ይፈልግ ነበር።+
10 ሐዋርያቱም በተመለሱ ጊዜ ያደረጉትን ነገር ሁሉ ለኢየሱስ ተረኩለት።+ እሱም ቤተሳይዳ ወደምትባል ከተማ ብቻቸውን ይዟቸው ሄደ።+ 11 ሆኖም ሕዝቡ ይህን ስላወቁ ተከተሉት። እሱም በደግነት ተቀብሎ ስለ አምላክ መንግሥት ይነግራቸው ጀመር፤ ፈውስ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው።+ 12 ቀኑም መምሸት ሲጀምር አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ወደ እሱ መጥተው “ያለንበት ስፍራ ገለል ያለ ስለሆነ ሕዝቡ በአካባቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት።+ 13 እሱ ግን “እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው።+ እነሱም “ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ምግብ ካልገዛን በስተቀር ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ ሌላ ምንም የለንም” አሉት። 14 በዚያም 5,000 ያህል ወንዶች ነበሩ። እሱ ግን ደቀ መዛሙርቱን “ሕዝቡን በሃምሳ በሃምሳ ከፋፍላችሁ አስቀምጧቸው” አላቸው። 15 እነሱም በታዘዙት መሠረት ሕዝቡ እንዲቀመጥ አደረጉ። 16 ከዚያም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ። ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። 17 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+
18 በኋላም ብቻውን ሆኖ እየጸለየ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ መጡ፤ እሱም “ሕዝቡ እኔን ማን ይሉኛል?” ሲል ጠየቃቸው።+ 19 እነሱም መልሰው “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ከጥንት ነቢያት አንዱ ተነስቷል ይላሉ” አሉት።+ 20 እሱም “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ “የአምላክ መሲሕ ነህ”* አለው።+ 21 ከዚያም ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አስጠነቀቃቸው፤+ 22 ቀጥሎም “የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበሉ፣ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ተቀባይነት ማጣቱ ብሎም መገደሉና+ በሦስተኛው ቀን መነሳቱ+ አይቀርም” አላቸው።
23 ከዚያም ለሁሉም እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤+ የራሱን የመከራ እንጨት* በየዕለቱ ይሸከም፤ ያለማቋረጥም ይከተለኝ።+ 24 ሕይወቱን* ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔ ሲል ሕይወቱን* የሚያጣ ሁሉ ግን ያድናታል።+ 25 ደግሞስ አንድ ሰው ዓለምን ሁሉ የራሱ ቢያደርግ፣ ነገር ግን ሕይወቱን ቢያጣ ወይም ለጉዳት ቢዳረግ ምን ይጠቅመዋል?+ 26 በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅም በክብሩ እንዲሁም በአብና በቅዱሳን መላእክት ክብር ሲመጣ ያፍርበታል።+ 27 እውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆሙት መካከል አንዳንዶች የአምላክን መንግሥት እስኪያዩ ድረስ ፈጽሞ ሞትን አይቀምሱም።”+
28 በመሆኑም ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ያህል በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ።+ 29 እየጸለየም ሳለ የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ነጭ ሆኖ አንጸባረቀ። 30 እነሆም ሁለት ሰዎች ይኸውም ሙሴና ኤልያስ ከእሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር። 31 እነሱም በክብር ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ስለሚፈጸመውና ከዚህ ዓለም ተለይቶ ስለሚሄድበት ሁኔታ ይነጋገሩ ጀመር።+ 32 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና አብረውት የነበሩት እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ነበር፤ ሙሉ በሙሉ ሲነቁ ግን የኢየሱስን ክብር እንዲሁም አብረውት የቆሙትን ሁለት ሰዎች አዩ።+ 33 ሰዎቹ ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ ጴጥሮስ ኢየሱስን “መምህር፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። ስለዚህ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴና አንድ ለኤልያስ ሦስት ድንኳኖች እንትከል” አለው፤ ምን እየተናገረ እንዳለ አላስተዋለም ነበር። 34 ይህን እየተናገረ ሳለ ግን ደመና መጥቶ ጋረዳቸው። ደመናው ሲሸፍናቸው ፍርሃት አደረባቸው። 35 ከዚያም ከደመናው “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ መጣ።+ 36 ድምፁም በተሰማ ጊዜ ኢየሱስን ብቻውን ሆኖ አዩት። እነሱም ዝም አሉ፤ ያዩትንም ነገር በዚያን ወቅት ለማንም አልተናገሩም።+
37 በማግስቱ ከተራራው ሲወርዱ እጅግ ብዙ ሕዝብ ከኢየሱስ ጋር ተገናኘ።+ 38 እነሆም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “መምህር፣ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ፤ ምክንያቱም ያለኝ ልጅ አንድ እሱ ብቻ ነው።+ 39 እነሆም፣ ርኩስ መንፈስ ይይዘውና በድንገት ይጮኻል፤ ጥሎም በአፉ አረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ጉዳት ካደረሰበትም በኋላ በስንት መከራ ይለቀዋል። 40 ደቀ መዛሙርትህ እንዲያስወጡት ለመንኳቸው፤ እነሱ ግን አልቻሉም።” 41 ኢየሱስም መልሶ “እምነት የለሽና ጠማማ ትውልድ ሆይ፣+ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር መቆየትና እናንተን መታገሥ ሊኖርብኝ ነው? እስቲ ልጅህን ወደዚህ አምጣው” አለ።+ 42 ሆኖም ወደ እሱ እየመጣ ሳለ ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ በኃይል አንፈራገጠው። ይሁንና ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ገሠጸውና ልጁን ፈወሰው፤ ከዚያም ለአባቱ መልሶ ሰጠው። 43 በዚህ ጊዜ ሁሉም በአምላክ ታላቅ ኃይል ተደነቁ።
ሰዎቹ ኢየሱስ ባደረገው ነገር ሁሉ እየተደነቁ ሳሉ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ 44 “ይህን የምነግራችሁን ቃል በጥሞና አዳምጡ፤ ደግሞም አስታውሱ፤ የሰውን ልጅ ለሰዎች አሳልፈው ይሰጡታልና።”+ 45 እነሱ ግን የነገራቸው ነገር አልገባቸውም። እንዲያውም እንዳያስተውሉት ነገሩ ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ጉዳይ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።
46 ከዚህ በኋላ ከመካከላቸው ማን እንደሚበልጥ እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ጀመር።+ 47 ኢየሱስ የልባቸውን ሐሳብ ስላወቀ አንድ ትንሽ ልጅ አምጥቶ አጠገቡ አቆመ፤ 48 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝንም ይቀበላል።+ ምክንያቱም ታላቅ የሚባለው ራሱን ከሁላችሁ እንደሚያንስ አድርጎ የሚቆጥር ነው።”+
49 ዮሐንስም “መምህር፣ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያስወጣ አየን፤ ይሁንና ከእኛ ጋር ሆኖ አንተን ስለማይከተል ልንከለክለው ሞከርን” አለው።+ 50 ኢየሱስ ግን “የማይቃወማችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ስለሆነ አትከልክሉት” አለው።
51 ኢየሱስ የሚያርግበት+ ጊዜ ሲቃረብ* ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቆርጦ ተነሳ። 52 ስለዚህ አስቀድሞ መልእክተኞች ላከ። እነሱም ሄደው ለእሱ የሚያስፈልገውን ነገር ለማዘጋጀት ወደ አንድ የሳምራውያን መንደር ገቡ። 53 ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቆርጦ እንደተነሳ* ስላወቁ አልተቀበሉትም።+ 54 ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ+ ይህን ባዩ ጊዜ “ጌታ ሆይ፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝ ትፈልጋለህ?” አሉት።+ 55 እሱ ግን ዞር ብሎ ገሠጻቸው። 56 ስለዚህ ወደ ሌላ መንደር ሄዱ።
57 በመንገድ እየተጓዙም ሳሉ አንድ ሰው “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው። 58 ኢየሱስ ግን “ቀበሮዎች ጉድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ቦታ የለውም” አለው።+ 59 ከዚያም ሌላውን “ተከታዬ ሁን” አለው። ሰውየውም “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው።+ 60 እሱ ግን “ሙታን+ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤ አንተ ግን ሄደህ የአምላክን መንግሥት በየቦታው አውጅ” አለው።+ 61 አንድ ሌላ ሰው ደግሞ “ጌታ ሆይ፣ እኔ እከተልሃለሁ፤ በመጀመሪያ ግን ቤተሰቤን እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለው። 62 ኢየሱስም “ዕርፍ ጨብጦ በኋላው ያሉትን ነገሮች የሚመለከት ሰው+ ለአምላክ መንግሥት የሚገባ አይደለም” አለው።+
10 ከዚህ በኋላ ጌታ ሌሎች 70* ሰዎችን ሾመ፤ እሱ ሊሄድበት ወዳሰበው ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱም ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው።+ 2 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “አዎ፣ አዝመራው ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂት ናቸው። ስለዚህ የመከሩ ሥራ ኃላፊ ወደ መከሩ፣ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።+ 3 እንግዲህ ሂዱ! እነሆ፣ በተኩላዎች መካከል እንዳሉ በጎች እልካችኋለሁ።+ 4 የገንዘብ ኮሮጆ ወይም የምግብ ከረጢት ወይም ትርፍ ጫማ አትያዙ፤+ በመንገድም ላይ ቆማችሁ ከማንም ጋር ሰላምታ አትለዋወጡ።* 5 ወደ ማንኛውም ቤት ስትገቡ በቅድሚያ ‘ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን’ በሉ።+ 6 በዚያም ሰላም ወዳድ ሰው ካለ ሰላማችሁ ያርፍበታል። ሰላም ወዳድ ሰው ከሌለ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል። 7 ለሠራተኛ ደሞዙ ስለሚገባው+ ያቀረቡላችሁን ነገር እየበላችሁና እየጠጣችሁ+ በዚያው ቤት ቆዩ።+ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ።
8 “በተጨማሪም ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ ሰዎቹ ከተቀበሏችሁ ያቀረቡላችሁን ብሉ፤ 9 እንዲሁም በዚያ ያሉትን በሽተኞች ፈውሱ፤ ደግሞም ‘የአምላክ መንግሥት ወደ እናንተ ቀርቧል’ በሏቸው።+ 10 ሆኖም ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ ሰዎቹ ካልተቀበሏችሁ ወደ አውራ ጎዳናዎች ወጥታችሁ እንዲህ በሉ፦ 11 ‘በእግራችን ላይ ያለውን የከተማችሁን አቧራ እንኳ ሳይቀር አራግፈንላችሁ እንሄዳለን።+ ይሁንና የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ እወቁ።’ 12 እላችኋለሁ፦ በዚያ ቀን* ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል።+
13 “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በጢሮስና በሲዶና* ተደርገው ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ማቅ ለብሰውና አመድ ላይ ተቀምጠው ንስሐ በገቡ ነበር።+ 14 ስለዚህ በፍርድ ወቅት ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። 15 አንቺም ቅፍርናሆም ወደ ሰማይ ከፍ የምትዪ ይመስልሻል? በፍጹም! ወደ መቃብር* ትወርጃለሽ!
16 “እናንተን የሚሰማ ሁሉ እኔንም ይሰማል።+ እናንተን የማይቀበል ሁሉ ደግሞ እኔንም አይቀበልም። ከዚህም በላይ እኔን የማይቀበል ሁሉ የላከኝንም አይቀበልም።”+
17 ከዚያም 70ዎቹ ደስ እያላቸው ተመልሰው “ጌታ ሆይ፣ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዙልን” አሉት።+ 18 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ።+ 19 እነሆ፣ እባቦችንና ጊንጦችን እንድትረግጡ እንዲሁም የጠላትን ኃይል ሁሉ እንድትቋቋሙ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፤+ የሚጎዳችሁም አንዳች ነገር አይኖርም። 20 ይሁን እንጂ መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፤ ከዚህ ይልቅ ስማችሁ በሰማያት ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”+ 21 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሴት አድርጎ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች+ ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ። አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ የአንተ ፈቃድ ነውና።+ 22 ሁሉንም ነገር አባቴ ሰጥቶኛል፤ ከአብ በስተቀር ወልድ ማን እንደሆነ የሚያውቅ የለም፤+ እንዲሁም ከወልድና ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በስተቀር አብ ማን እንደሆነ የሚያውቅ የለም።”+
23 ከዚያም ብቻቸውን በነበሩበት ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ አሁን የምታዩትን ነገር የሚያዩ ዓይኖች ደስተኞች ናቸው።+ 24 እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ አሁን የምታዩትን ነገር ለማየት ተመኝተው ነበር፤ ግን አላዩም፤+ አሁን የምትሰሙትን ነገር ለመስማት ተመኝተው ነበር፤ ግን አልሰሙም።”
25 እነሆም አንድ ሕግ አዋቂ ኢየሱስን ሊፈትነው ተነስቶ “መምህር፣ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ አለብኝ?” አለው።+ 26 ኢየሱስም “በሕጉ ላይ የተጻፈው ምንድን ነው? አንተስ ምን ትረዳለህ?” አለው። 27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው። 28 ኢየሱስም “በትክክል መልሰሃል፤ ዘወትር ይህን አድርግ፤ ሕይወትም ታገኛለህ” አለው።+
29 ሰውየው ግን ጻድቅ መሆኑን ለማሳየት ፈልጎ+ ኢየሱስን “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” አለው። 30 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በዘራፊዎች እጅ ወደቀ፤ እነሱም ከገፈፉትና ከደበደቡት በኋላ በሞትና በሕይወት መካከል ጥለውት ሄዱ። 31 እንደ አጋጣሚ አንድ ካህን በዚያ መንገድ ሲወርድ ሰውየውን አየውና ራቅ ብሎ አልፎት ሄደ። 32 በተመሳሳይም አንድ ሌዋዊ እዚያ ቦታ ሲደርስ አየውና ገለል ብሎ አልፎት ሄደ። 33 ሆኖም አንድ ሳምራዊ+ በዚያ መንገድ ሲጓዝ ሰውየው ወዳለበት ቦታ ደረሰ፤ ባየውም ጊዜ በጣም አዘነለት። 34 ስለሆነም ወደ ሰውየው ቀርቦ በቁስሎቹ ላይ ዘይትና የወይን ጠጅ አፍስሶ በጨርቅ አሰረለት። ከዚያም በራሱ አህያ ላይ ካስቀመጠው በኋላ ወደ አንድ የእንግዶች ማረፊያ በመውሰድ ተንከባከበው። 35 በማግስቱ ሁለት ዲናር* አውጥቶ ለእንግዶች ማረፊያ ቤቱ ባለቤት ሰጠውና ‘ይህን ሰው አስታመው፤ ከዚህ በላይ የምታወጣውን ተጨማሪ ወጪ ሁሉ ስመለስ እከፍልሃለሁ’ አለው። 36 ታዲያ ከእነዚህ ሦስት ሰዎች መካከል በዘራፊዎች እጅ ለወደቀው ሰው ባልንጀራ+ ሆኖ የተገኘው የትኛው ይመስልሃል?” 37 እሱም “ምሕረት በማሳየት የረዳው ነው” አለ።+ ከዚያም ኢየሱስ “አንተም ሂድና እንዲሁ አድርግ” አለው።+
38 እየተጓዙም ሳሉ ወደ አንድ መንደር ገባ። በዚያም ማርታ+ የምትባል አንዲት ሴት በቤቷ በእንግድነት ተቀበለችው። 39 እሷም ማርያም የምትባል እህት ነበረቻት፤ ማርያምም በጌታ እግር ሥር ተቀምጣ የሚናገረውን* ታዳምጥ ነበር። 40 ማርታ ግን በብዙ ሥራ ተጠምዳ ትባክን ነበር። በመሆኑም ወደ እሱ መጥታ “ጌታ ሆይ፣ እህቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ጥላ ስትቀመጥ ምንም ግድ አይሰጥህም? መጥታ እንድታግዘኝ ንገራት እንጂ” አለችው። 41 ጌታም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ማርታ፣ ማርታ፣ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ደግሞም ትጠበቢያለሽ። 42 ይሁንና የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር ብቻ ነው። ማርያም በበኩሏ ጥሩ የሆነውን ድርሻ* መርጣለች፤+ ይህም ከእሷ አይወሰድም።”
11 አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ እየጸለየ ነበር፤ ጸሎቱንም ሲጨርስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ “ጌታ ሆይ፣ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው ሁሉ አንተም እንዴት እንደምንጸልይ አስተምረን” አለው።
2 በመሆኑም እንዲህ አላቸው፦ “በምትጸልዩበት ጊዜ ሁሉ እንዲህ በሉ፦ ‘አባት ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ።*+ መንግሥትህ ይምጣ።+ 3 የዕለቱን ምግባችንን* ለዕለቱ የሚያስፈልገንን ያህል ስጠን።+ 4 እኛ የበደሉንን* ሁሉ ይቅር ስለምንል+ ኃጢአታችንን ይቅር በለን፤+ ወደ ፈተናም አታግባን።’”+
5 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ መካከል አንዱ፣ አንድ ወዳጅ አለው እንበል፤ በእኩለ ሌሊትም ወደ እሱ ሄዶ እንዲህ አለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ፣ እባክህ ሦስት ዳቦ አበድረኝ፤ 6 አንድ ወዳጄ ከመንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ነገር አጣሁ።’ 7 ወዳጁ ግን ከውስጥ ሆኖ ‘ባክህ አታስቸግረኝ። በሩ ተቆልፏል፤ ልጆቼም አብረውኝ ተኝተዋል። አሁን ተነስቼ ምንም ነገር ልሰጥህ አልችልም’ ይለዋል። 8 እላችኋለሁ፣ ወዳጁ ስለሆነ ተነስቶ ባይሰጠው እንኳ ስለ ውትወታው ሲል+ ተነስቶ የፈለገውን ሁሉ ይሰጠዋል። 9 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ደጋግማችሁ ለምኑ፣+ ይሰጣችኋል፤ ሳታሰልሱ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ ደጋግማችሁ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።+ 10 ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋል፤+ የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል፤ የሚያንኳኳም ሁሉ ይከፈትለታል። 11 ደግሞስ ከመካከላችሁ ልጁ ዓሣ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ የሚሰጥ አባት ይኖራል?+ 12 ወይስ እንቁላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋል? 13 ታዲያ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባትማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸው!”+
14 ከጊዜ በኋላ፣ ኢየሱስ ዱዳ የሚያደርግ ጋኔን አስወጣ።+ ጋኔኑ ከወጣ በኋላ ዱዳው ሰው መናገር ጀመረ፤ ሕዝቡም ተደነቀ።+ 15 ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል* ነው” አሉ።+ 16 ሌሎች ደግሞ ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ይጠይቁት ጀመር።+ 17 ኢየሱስም ሐሳባቸውን አውቆ+ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ እንዲሁም እርስ በርሱ የሚከፋፈል ቤት ይወድቃል። 18 በተመሳሳይም ሰይጣን እርስ በርሱ ከተከፋፈለ መንግሥቱ እንዴት ይቆማል? እናንተ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል እንደሆነ ትናገራላችሁና። 19 እኔ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ የሚያስወጧቸው ታዲያ በማን ነው? ልጆቻችሁ ፈራጆች የሚሆኑባችሁ ለዚህ ነው። 20 ሆኖም አጋንንትን የማስወጣው በአምላክ ጣት+ ከሆነ የአምላክ መንግሥት ሳታስቡት ደርሶባችኋል ማለት ነው።+ 21 አንድ ብርቱ ሰው በደንብ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ ንብረቱ ምንም አይነካበትም። 22 ይሁን እንጂ ከእሱ ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው ካጠቃውና ካሸነፈው ተማምኖበት የነበረውን መሣሪያ ሁሉ ይነጥቀዋል፤ ከእሱ የወሰደውንም ለሌሎች ያካፍላል። 23 ከእኔ ጎን ያልቆመ ሁሉ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ሁሉ ይበትናል።+
24 “ርኩስ መንፈስ ከሰው ሲወጣ የሚያርፍበት ቦታ ፍለጋ ውኃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ የሚያርፍበት ቦታ ሲያጣ ግን ‘ወደለቀቅኩት ቤቴ እመለሳለሁ’ ይላል።+ 25 ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና አጊጦ ያገኘዋል። 26 ከዚያም ሄዶ ከእሱ የከፉ ሌሎች ሰባት መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውም ይኖሩበታል። በመሆኑም የዚያ ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከቀድሞው የከፋ ይሆንበታል።”
27 ይህን እየተናገረ ሳለ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “አንተን የተሸከመች ማህፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ደስተኞች ናቸው!” አለችው።+ 28 እሱ ግን “ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!” አለ።+
29 ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክትም ማየት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከዮናስ ምልክት በስተቀር ምንም ምልክት አይሰጠውም።+ 30 ምክንያቱም ዮናስ+ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። 31 የደቡብ ንግሥት+ የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለመጣች በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነስታ ትኮንናቸዋለች። ነገር ግን ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።+ 32 የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሐ ስለገቡ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይኮንኑታል።+ ነገር ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ። 33 አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ በሰዋራ ቦታ አያስቀምጠውም ወይም እንቅብ* አይደፋበትም፤+ ከዚህ ይልቅ ወደ ቤት የሚገቡ ሁሉ ብርሃን እንዲያገኙ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል። 34 የሰውነት መብራት ዓይን ነው። ዓይንህ በአንድ ነገር ላይ ሲያተኩር* መላ ሰውነትህም ብሩህ * ይሆናል፤ ዓይንህ ምቀኛ* ሲሆን ግን መላ ሰውነትህም ጨለማ ይሆናል።+ 35 ስለዚህ በውስጥህ ያለው ብርሃን፣ ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። 36 እንግዲህ መላ ሰውነትህ ምንም ጨለማ ሳይኖርበት ብሩህ ከሆነ፣ ልክ ብርሃን እንደሚፈነጥቅልህ መብራት ሁለንተናህ ብሩህ ይሆናል።”
37 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ አንድ ፈሪሳዊ አብሮት እንዲበላ ጋበዘው። እሱም ወደ ቤቱ ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። 38 ይሁን እንጂ ፈሪሳዊው ኢየሱስ ከምሳ በፊት እጁን እንዳልታጠበ* ባየ ጊዜ ተገረመ።+ 39 ጌታ ግን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ፈሪሳውያን ጽዋውንና ሳህኑን ከውጭ በኩል ታጸዳላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን በስግብግብነትና በክፋት የተሞላ ነው።+ 40 እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁ! የውስጡንስ የሠራው የውጭውን የሠራው አይደለም? 41 ስለዚህ በልባችሁ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ምጽዋት* አድርጋችሁ ስጡ፤ ያን ጊዜ በሁሉም ነገር ንጹሕ ትሆናላችሁ። 42 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ከኮሰረት፣ ከጤና አዳምና ከሌሎች አትክልቶች ሁሉ አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን የአምላክን ፍትሕና እሱን መውደድን ችላ ትላላችሁ። እርግጥ አሥራት የመስጠት ግዴታ አለባችሁ፤ ሆኖም ሌሎቹን ነገሮች ችላ ማለት አልነበረባችሁም።+ 43 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም በምኩራብ ከፊት መቀመጥ፣* በገበያ ቦታ ደግሞ ሰዎች እጅ እንዲነሷችሁ ትፈልጋላችሁ።+ 44 ሰዎች ሳያውቁ በላዩ ላይ የሚሄዱበትን የተሰወረ* መቃብር ስለምትመስሉ ወዮላችሁ!”+
45 ከሕጉ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ “መምህር፣ እንዲህ ስትል እኮ እኛንም መስደብህ ነው” አለው። 46 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለ፦ “እናንተ የሕጉ አዋቂዎችም ወዮላችሁ! ምክንያቱም ለመሸከም የሚከብድ ሸክም በሰው ላይ ትጭናላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ ግን ሸክሙን በጣታችሁ እንኳ አትነኩትም።+
47 “አባቶቻችሁ የገደሏቸውን ነቢያት መቃብሮች ስለምትሠሩ ወዮላችሁ!+ 48 እንግዲህ እናንተ ለአባቶቻችሁ ሥራ ምሥክሮች ናችሁ፤ ያም ሆኖ የእነሱን ሥራ ትደግፋላችሁ፤ ምክንያቱም እነሱ ነቢያትን ገደሉ፤+ እናንተ ደግሞ መቃብሮቻቸውን ትሠራላችሁ። 49 ስለዚህ የአምላክ ጥበብ እንዲህ አለች፦ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነሱ እልካለሁ፤ እነሱም አንዳንዶቹን ይገድላሉ በአንዳንዶቹም ላይ ስደት ያደርሳሉ፤ 50 በመሆኑም ይህ ትውልድ ዓለም ከተመሠረተበት* ጊዜ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ሁሉ ተጠያቂ ነው፤*+ 51 ከአቤል+ አንስቶ በመሠዊያውና በቤቱ* መካከል እስከተገደለው እስከ ዘካርያስ+ ድረስ ለፈሰሰው ደም ተጠያቂ ነው።’ አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል።*
52 “እናንተ የሕጉ አዋቂዎች ወዮላችሁ! ምክንያቱም የእውቀትን ቁልፍ ነጥቃችሁ ወስዳችኋል። እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁም፤ ለመግባት የሚሞክሩትንም ትከለክላላችሁ።”+
53 ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ሲሄድ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ከበው እያጨናነቁት ስለተለያዩ ነገሮች በመጠየቅ ያዋክቡት ጀመር፤ 54 በሚናገረውም ነገር ሊያጠምዱት ያደቡ ነበር።+
12 በዚያን ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ እርስ በርስ እየተጋፋ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ ኢየሱስ በቅድሚያ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ከፈሪሳውያን እርሾ ይኸውም ከግብዝነት ተጠንቀቁ።+ 2 ይሁንና የተሰወረ መገለጡ፣ ሚስጥር የሆነም መታወቁ አይቀርም።+ 3 ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በጓዳ የምታንሾካሹኩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። 4 በተጨማሪም ወዳጆቼ+ ሆይ፣ እላችኋለሁ፣ ሥጋን የሚገድሉትን ከዚያ በላይ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ።+ 5 ይልቁንስ ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ አሳያችኋለሁ፦ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም* የመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ።+ አዎ፣ እላችኋለሁ እሱን ፍሩ።+ 6 አምስት ድንቢጦች አነስተኛ ዋጋ ባላቸው ሁለት ሳንቲሞች* ይሸጡ የለም? ሆኖም አንዷም እንኳ በአምላክ ዘንድ አትረሳም።*+ 7 የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል።+ አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።+
8 “እላችኋለሁ፣ በሰዎች ፊት የሚመሠክርልኝን+ ሁሉ የሰው ልጅም በአምላክ መላእክት ፊት ይመሠክርለታል።+ 9 በሰዎች ፊት የሚክደኝ ሁሉ ግን በአምላክ መላእክት ፊት ይካዳል።+ 10 በሰው ልጅ ላይ ክፉ ቃል የሚናገር ሁሉ ይቅር ይባልለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን ይቅር አይባልም።+ 11 በሕዝባዊ ሸንጎዎች* እንዲሁም በመንግሥት ሹማምንትና ባለሥልጣናት ፊት ሲያቀርቧችሁ እንዴት ብለን ወይም ምን ብለን የመከላከያ መልስ እንሰጣለን ወይም ደግሞ ምን እንላለን ብላችሁ አትጨነቁ፤+ 12 ምን መናገር እንዳለባችሁ መንፈስ ቅዱስ በዚያኑ ሰዓት ያስተምራችኋልና።”+
13 ከዚያም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው “መምህር፣ ወንድሜ ውርሳችንን እንዲያካፍለኝ ንገረው” አለው። 14 ኢየሱስም “አንተ ሰው፣ በእናንተ መካከል ፈራጅና ዳኛ እንድሆን ማን ሾመኝ?” አለው። 15 ከዚያም “አንድ ሰው ሀብታም ቢሆንም እንኳ ንብረቱ ሕይወት ሊያስገኝለት አይችልም፤+ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም* ሁሉ ተጠበቁ”+ አላቸው። 16 ይህን ካለ በኋላ እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “አንድ ሀብታም ሰው መሬቱ ብዙ ምርት አስገኘለት። 17 በመሆኑም ‘ምርቴን የማከማችበት ቦታ ስለሌለኝ ምን ባደርግ ይሻላል?’ ብሎ በልቡ ማሰብ ጀመረ። 18 ከዚያም እንዲህ አለ፦ ‘እንዲህ አደርጋለሁ፦+ ያሉኝን ጎተራዎች አፈርስና ትላልቅ ጎተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም እህሌንና ንብረቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ 19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+ 21 ለራሱ ሀብት የሚያከማች በአምላክ ዘንድ ግን ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው።”+
22 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ሕይወታችሁ* ምን እንበላለን ወይም ደግሞ ስለ ሰውነታችሁ ምን እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ።*+ 23 ሕይወት* ከምግብ ሰውነትም ከልብስ የላቀ ዋጋ አለውና። 24 ቁራዎችን ተመልከቱ፦ አይዘሩም፣ አያጭዱም እንዲሁም የእህል ማከማቻ ወይም ጎተራ የላቸውም፤ ሆኖም አምላክ ይመግባቸዋል።+ ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ የላቀ ዋጋ የላችሁም?+ 25 ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ርዝማኔ ላይ አንድ ክንድ* መጨመር የሚችል ይኖራል? 26 ታዲያ እንዲህ ያለውን ትንሽ ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ ስለ ሌሎች ነገሮች ለምን ትጨነቃላችሁ?+ 27 እስቲ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ፦ አይለፉም ወይም አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ያን ያህል ክብር የነበረው ሰለሞን እንኳ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዷ አላጌጠም።+ 28 አምላክ ዛሬ ያለውንና ነገ ወደ ምድጃ የሚጣለውን በሜዳ ያለ ተክል እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁ! 29 ስለዚህ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት ነገር ከልክ በላይ አታስቡ፤ እንዲሁም አትጨነቁ፤*+ 30 እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዓለም ያሉ ሰዎች አጥብቀው የሚፈልጓቸው ናቸው፤ ይሁንና አባታችሁ እነዚህ ነገሮች እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል።+ 31 ይልቁንስ ዘወትር መንግሥቱን ፈልጉ፤ እነዚህም ነገሮች ይሰጧችኋል።+
32 “አንተ ትንሽ መንጋ+ አትፍራ፤ አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗልና።+ 33 ያላችሁን ንብረት ሸጣችሁ ምጽዋት* ስጡ።+ የማያረጁ የገንዘብ ኮሮጆዎች አዘጋጁ፤ አዎ፣ ሌባ በማይደርስበት፣ ብልም ሊበላው በማይችልበት በሰማያት ለራሳችሁ የማያልቅ ውድ ሀብት አከማቹ።+ 34 ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም በዚያ ይሆናልና።
35 “ወገባችሁን ታጠቁ፤*+ መብራታችሁንም አብሩ፤+ 36 ጌታቸው ከሠርግ+ እስኪመለስ እንደሚጠባበቁና+ መጥቶ በሩን ሲያንኳኳ ወዲያው ለመክፈት እንደተዘጋጁ ዓይነት ሰዎች ሁኑ። 37 ጌታቸው በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው ሲጠባበቁ የሚያገኛቸው ባሪያዎች ደስተኞች ናቸው! እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታቸው ለሥራ ካሸረጠና* በማዕድ እንዲቀመጡ ካደረገ በኋላ ቆሞ ያስተናግዳቸዋል። 38 በሁለተኛው ክፍለ ሌሊትም* ይምጣ በሦስተኛው፣* ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ካገኛቸው ደስተኞች ናቸው! 39 ነገር ግን ይህን እወቁ፤ አንድ ሰው ሌባ በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ ቤቱ እንዳይደፈር በተከላከለ ነበር።+ 40 እናንተም የሰው ልጅ ይመጣል ብላችሁ ባላሰባችሁት ሰዓት ስለሚመጣ ዝግጁ ሆናችሁ ጠብቁ።”+
41 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ምሳሌ እየተናገርክ ያለኸው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሁሉም?” አለው። 42 ጌታም እንዲህ አለ፦ “ጌታው ምንጊዜም የሚያስፈልጋቸውን ምግብ በተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው በአገልጋዮቹ* ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም* መጋቢ* በእርግጥ ማን ነው?+ 43 ጌታው ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ካገኘው ያ ባሪያ ደስተኛ ነው! 44 እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታው በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል። 45 ነገር ግን ያ ባሪያ በልቡ ‘ጌታዬ የሚመጣው ዘግይቶ ነው’ ብሎ ቢያስብና ወንድና ሴት አገልጋዮችን መደብደብ እንዲሁም መብላት፣ መጠጣትና መስከር ቢጀምር+ 46 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላሰበው ሰዓት ይመጣል፤ ከባድ ቅጣት ይቀጣዋል፤* ዕጣውንም ታማኝ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ያደርገዋል። 47 ደግሞም የጌታውን ፈቃድ እያወቀ ተዘጋጅቶ ያልጠበቀው ወይም ጌታው የጠየቀውን ነገር ያላደረገው * ያ ባሪያ ብዙ ግርፋት ይገረፋል።+ 48 ነገር ግን ሳያውቅ፣ ግርፋት የሚገባው ድርጊት የፈጸመ ጥቂት ይገረፋል። በእርግጥም ብዙ ከተሰጠው ሁሉ ብዙ ይጠበቅበታል፤ ብዙ ኃላፊነት የተሰጠውም ብዙ ይጠበቅበታል።+
49 “እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኮስ ነው፤ ታዲያ እሳቱ ከተቀጣጠለ ከዚህ በላይ ምን እፈልጋለሁ? 50 እርግጥ እኔ የምጠመቀው አንድ ጥምቀት አለኝ፤ ይህ እስኪጠናቀቅ ድረስ በጣም ተጨንቄአለሁ!+ 51 የመጣሁት በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን ይመስላችኋል? በፍጹም አይደለም፤ እላችኋለሁ፣ የመጣሁት ሰላም ለማስፈን ሳይሆን ለመከፋፈል ነው።+ 52 ከአሁን ጀምሮ በአንድ ቤት ውስጥ እርስ በርስ የተከፋፈሉ አምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሦስቱ በሁለቱ ላይ ሁለቱ ደግሞ በሦስቱ ላይ ይነሳሉ። 53 አባት በልጁ፣ ልጅ በአባቱ፣ እናት በልጇ፣ ልጅ በእናቷ፣ አማት በምራቷ፣ ምራት በአማቷ ላይ በመነሳት እርስ በርስ ይከፋፈላሉ።”+
54 ከዚያም ለሕዝቡ ደግሞ እንዲህ አለ፦ “ከምዕራብ በኩል ደመና ሲመጣ ስታዩ ወዲያውኑ ‘ዶፍ ዝናብ ሊጥል ነው’ ትላላችሁ፤ እንዳላችሁትም ይሆናል። 55 የደቡብ ነፋስ ሲነፍስ ስታዩ ደግሞ ‘ኃይለኛ ሙቀት ይሆናል’ ትላላችሁ፤ በእርግጥም ይሆናል። 56 እናንተ ግብዞች፣ የምድሩንና የሰማዩን መልክ አይታችሁ መረዳት ትችላላችሁ፤ ታዲያ ይህን የአሁኑን ዘመን መርምራችሁ መረዳት እንዴት ተሳናችሁ?+ 57 ደግሞስ ጽድቅ የሆነውን ነገር ለራሳችሁ ለምን አትፈርዱም? 58 ለምሳሌ ከከሳሽህ ጋር ወደ አንድ ባለሥልጣን እየሄድክ ሳለ፣ ከእሱ ጋር ያለህን ቅራኔ እዚያው በመንገድ ላይ ለመፍታት ጥረት አድርግ፤ አለዚያ ዳኛ ፊት ያቀርብሃል፤ ዳኛውም ለፍርድ ቤቱ መኮንን አሳልፎ ይሰጥሃል፤ መኮንኑ ደግሞ እስር ቤት ያስገባሃል።+ 59 እልሃለሁ፣ የመጨረሻዋን ትንሽ ሳንቲም* ከፍለህ እስክትጨርስ ድረስ ከዚያ ፈጽሞ አትወጣም።”
13 በወቅቱ፣ በዚያ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስለደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች ለኢየሱስ አወሩለት። 2 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለደረሰባቸው ከሌሎቹ የገሊላ ሰዎች ይበልጥ ኃጢአተኞች እንደሆኑ አድርጋችሁ ታስባላችሁ? 3 በፍጹም፤ ነገር ግን ንስሐ ካልገባችሁ ሁላችሁም እንደ እነሱ ትጠፋላችሁ።+ 4 ወይም ደግሞ የሰሊሆም ግንብ ተንዶባቸው የሞቱት 18 ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ይበልጥ በደለኞች የነበሩ ይመስላችኋል? 5 በፍጹም፤ ነገር ግን ንስሐ ካልገባችሁ ሁላችሁም ልክ እንደ እነሱ ትጠፋላችሁ።”
6 ከዚያም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ተናገረ፦ “አንድ ሰው በወይን እርሻው ውስጥ የተተከለች አንዲት የበለስ ዛፍ ነበረችው፤ እሱም ከዛፏ ፍሬ ሊለቅም መጣ፤ ሆኖም ምንም አላገኘባትም።+ 7 በዚህ ጊዜ የወይን አትክልት ሠራተኛውን ‘ከዚህች የበለስ ዛፍ ፍሬ ለማግኘት ሦስት ዓመት ሙሉ ተመላለስኩ፤ ሆኖም ምንም አላገኘሁባትም። ስለዚህ ቁረጣት! ለምን በከንቱ ቦታ ትይዛለች?’ አለው። 8 እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ ‘ጌታዬ፣ ዙሪያዋን ቆፍሬ ፍግ ላድርግባትና እስቲ ለአንድ ዓመት ደግሞ እንያት። 9 ወደፊት ፍሬ ካፈራች ጥሩ፤ ካልሆነ ግን ትቆርጣታለህ።’”+
10 ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድ ምኩራብ ውስጥ እያስተማረ ነበር። 11 በዚያም ባደረባት ክፉ መንፈስ የተነሳ ለ18 ዓመት በበሽታ ስትማቅቅ የኖረች* አንዲት ሴት ነበረች፤ በጣም ከመጉበጧም የተነሳ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር። 12 ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና “አንቺ ሴት፣ ከበሽታሽ ተገላግለሻል” አላት።+ 13 እጁንም ጫነባት፤ ወዲያውም ቀጥ አለች፤ አምላክንም ማመስገን ጀመረች። 14 የምኩራቡ አለቃ ግን ኢየሱስ በሰንበት ቀን በመፈወሱ ተቆጥቶ ሕዝቡን “ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤+ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አላቸው።+ 15 ይሁን እንጂ ጌታ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እናንተ ግብዞች፣+ እያንዳንዳችሁ በሰንበት ቀን በሬያችሁን ወይም አህያችሁን ከጋጣው ፈታችሁ ውኃ ለማጠጣት ትወስዱ የለም?+ 16 ታዲያ የአብርሃም ልጅ የሆነችውና 18 ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ የኖረችው ይህች ሴት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራቷ መፈታት አይገባትም?” 17 ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ሁሉ በኀፍረት ተሸማቀቁ፤ ሕዝቡ በሙሉ ግን እሱ ባደረጋቸው አስደናቂ ነገሮች+ ሁሉ ይደሰቱ ጀመር።
18 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የአምላክ መንግሥት ከምን ጋር ይመሳሰላል? ከምንስ ጋር ላነጻጽረው? 19 አንድ ሰው ወስዶ በአትክልት ቦታው ከዘራት የሰናፍጭ ዘር ጋር ይመሳሰላል፤ ይህች ዘር አድጋ ዛፍ ሆነች፤ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎቿ ላይ ሰፈሩ።”+
20 ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የአምላክን መንግሥት ከምን ጋር ላነጻጽረው? 21 አንዲት ሴት ወስዳ ሊጡ በሙሉ እስኪቦካ ድረስ ከሦስት ትላልቅ መስፈሪያ* ዱቄት ጋር ከደባለቀችው እርሾ ጋር ይመሳሰላል።”+
22 ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዘ ሳለ በየከተማውና በየመንደሩ እያስተማረ ያልፍ ነበር። 23 በዚህ ጊዜ አንድ ሰው “ጌታ ሆይ፣ የሚድኑት ጥቂቶች ናቸው?” ሲል ጠየቀው። እሱም እንዲህ አላቸው፦ 24 “በጠባቡ በር ለመግባት ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጉ፤+ እላችኋለሁ፦ ብዙዎች ለመግባት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን አይችሉም። 25 የቤቱ ባለቤት ተነስቶ አንዴ በሩን ከዘጋው በኋላ ውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ፣ ክፈትልን’+ እያላችሁ በሩን ብታንኳኩ ‘ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል። 26 በዚህ ጊዜ ‘አብረንህ እኮ በልተናል፤ ደግሞም ጠጥተናል፤ በአውራ ጎዳናዎቻችንም አስተምረሃል’ ማለት ትጀምራላችሁ።+ 27 እሱ ግን ‘ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም። እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፣ ከእኔ ራቁ!’ ይላችኋል። 28 አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብንና ነቢያትን ሁሉ በአምላክ መንግሥት ውስጥ ስታዩና እናንተ ግን በውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ በዚያ ታለቅሳላችሁ፤ ጥርሳችሁንም ታፋጫላችሁ።+ 29 በተጨማሪም ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ እንዲሁም ከሰሜንና ከደቡብ መጥተው በአምላክ መንግሥት በማዕድ ይቀመጣሉ። 30 ደግሞም ከኋለኞች መካከል ፊተኞች የሚሆኑ፣ ከፊተኞች መካከልም ኋለኞች የሚሆኑ አሉ።”+
31 በዚያን ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን መጥተው “ሄሮድስ ሊገድልህ ስለሚፈልግ ከዚህ ውጣና ሂድ” አሉት። 32 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሄዳችሁ ያንን ቀበሮ ‘ዛሬና ነገ አጋንንትን አስወጣለሁ እንዲሁም ሰዎችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ሥራዬን አጠናቅቃለሁ’ በሉት። 33 ይሁንና ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ሊገደል ስለማይችል* ዛሬና ነገ እንዲሁም ከነገ ወዲያ ጉዞዬን መቀጠል አለብኝ።+ 34 ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም፣ ነቢያትን የምትገድል፤ ወደ እሷ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግር፤+ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግኩ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።+ 35 እነሆ፣ ቤታችሁ* ለእናንተ የተተወ ይሆናል።+ እላችኋለሁ፣ ‘በይሖዋ* ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!’ እስክትሉ ድረስ ፈጽሞ አታዩኝም።”+
14 በሌላ ወቅት ኢየሱስ በአንድ የሰንበት ቀን ከፈሪሳውያን መሪዎች ወደ አንዱ ቤት ምግብ ሊበላ በገባ ጊዜ በቤቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች በትኩረት ይከታተሉት ነበር። 2 በዚያም ሰውነት የሚያሳብጥ በሽታ* የያዘው አንድ ሰው ከፊት ለፊቱ ነበር። 3 ኢየሱስም ሕግ አዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን “በሰንበት መፈወስ በሕግ ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?” ሲል ጠየቃቸው።+ 4 እነሱ ግን ዝም አሉ። በዚህ ጊዜ በሰውየው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሰውና አሰናበተው። 5 ከዚያም “ከእናንተ መካከል ልጁ ወይም በሬው በሰንበት ቀን የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ቢወድቅ ወዲያውኑ ጎትቶ የማያወጣው ማን ነው?” አላቸው።+ 6 እነሱም ለዚህ መልስ ሊሰጡ አልቻሉም።
7 ኢየሱስ የተጋበዙት ሰዎች ለራሳቸው የክብር ቦታ ሲመርጡ+ ተመልክቶ እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ 8 “አንድ ሰው ወደ ሠርግ ሲጠራህ በክብር ቦታ አትቀመጥ።+ ምናልባት ከአንተ የበለጠ የተከበረ ሰው ተጠርቶ ሊሆን ይችላል። 9 በመሆኑም ሁለታችሁንም የጋበዘው ሰው መጥቶ ‘ቦታውን ለዚህ ሰው ልቀቅለት’ ይልሃል። በዚህ ጊዜ እያፈርክ ወደ ዝቅተኛው ቦታ ትሄዳለህ። 10 አንተ ግን ስትጋበዝ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ የጋበዘህም ሰው ሲመጣ ‘ወዳጄ ሆይ፣ ወደ ላይ ከፍ በል’ ይልሃል። በዚህ ጊዜ አብረውህ በተጋበዙት ሰዎች ሁሉ ፊት ክብር ታገኛለህ።+ 11 ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይደረጋልና፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ደግሞ ከፍ ይደረጋል።”+
12 ቀጥሎ ደግሞ የጋበዘውን ሰው እንዲህ አለው፦ “የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ጓደኞችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ሀብታም ጎረቤቶችህን አትጥራ። አለዚያ እነሱም ሊጋብዙህና ብድር ሊመልሱልህ ይችላሉ። 13 ሆኖም ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውራንን ጥራ፤+ 14 ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ ደስተኛ ትሆናለህ። ምክንያቱም በጻድቃን ትንሣኤ+ ብድራት ይመለስልሃል።”
15 ከተጋበዙት መካከል አንዱ ይህን ሲሰማ “በአምላክ መንግሥት፣ ከማዕድ የሚበላ ደስተኛ ነው” አለው።
16 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “አንድ ሰው ትልቅ የራት ግብዣ አዘጋጅቶ+ ብዙ ሰዎች ጠራ። 17 የራት ግብዣው ሰዓት በደረሰ ጊዜ የተጋበዙትን ሰዎች ‘አሁን ሁሉም ነገር ስለተዘጋጀ ኑ’ ብሎ እንዲጠራቸው ባሪያውን ላከ። 18 ይሁን እንጂ ሁሉም ሰበብ ያቀርቡ ጀመር።+ የመጀመሪያው ‘እርሻ ስለገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ ስለዚህ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው። 19 ሌላውም ‘አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ፤ ልፈትናቸው ስለሆነ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለ።+ 20 ሌላኛው ደግሞ ‘ገና ማግባቴ ስለሆነ መምጣት አልችልም’ አለ። 21 ባሪያውም መጥቶ ለጌታው ይህን ነገረው። በዚህ ጊዜ የቤቱ ጌታ ተቆጣ፤ ከዚያም ባሪያውን ‘ፈጥነህ ወደ ከተማው አውራ ጎዳናዎችና ስላች መንገዶች ሄደህ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ ዓይነ ስውራንንና አንካሶችን ወደዚህ አምጣቸው’ አለው። 22 በኋላም ባሪያው ‘ጌታዬ፣ ያዘዝከው ተፈጽሟል፤ ያም ሆኖ አሁንም ቦታ አለ’ አለው። 23 በመሆኑም ጌታው ባሪያውን እንዲህ አለው፦ ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ጎዳናዎችና ወደ ስላች መንገዶች ሄደህ ያገኘሃቸውን ሰዎች በግድ አምጥተህ አስገባ።+ 24 እላችኋለሁ፣ ከእነዚያ ከተጋበዙት ሰዎች መካከል አንዳቸውም ያዘጋጀሁትን ራት አይቀምሱም።’”+
25 ከዚያም እጅግ ብዙ ሕዝብ አብሮት እየተጓዘ ሳለ ወደ እነሱ ዞሮ እንዲህ አላቸው፦ 26 “ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱን፣ እናቱን፣ ሚስቱን፣ ልጆቹን፣ ወንድሞቹንና እህቶቹን ሌላው ቀርቶ የገዛ ራሱን ሕይወት* እንኳ የማይጠላ*+ ከሆነ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።+ 27 የራሱን የመከራ እንጨት* ተሸክሞ የማይከተለኝ ሁሉ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።+ 28 ለምሳሌ ከእናንተ መካከል፣ ግንብ ለመገንባት ፈልጎ ለመጨረስ የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ በመጀመሪያ ተቀምጦ ወጪውን የማያሰላ ማን ነው? 29 እንዲህ ካላደረገ ግን መሠረቱን ከጣለ በኋላ ፍጻሜ ላይ ማድረስ ሊያቅተውና የሚያዩት ሰዎች ሁሉ ሊያፌዙበት ይችላሉ፤ 30 ‘ይህ ሰው መገንባት ጀምሮ ነበር፤ መጨረስ ግን አቃተው’ ይሉታል። 31 ወይም ደግሞ አንድ ንጉሥ ሌላን ንጉሥ ጦርነት ለመግጠም በሚነሳበት ጊዜ 20,000 ሠራዊት አሰልፎ የመጣበትን ንጉሥ በ10,000 ሠራዊት ሊቋቋመው ይችል እንደሆነ ለማወቅ በቅድሚያ ተቀምጦ አይማከርም? 32 መቋቋም የማይችል ከሆነ ሊገጥመው የሚመጣው ንጉሥ ገና ሩቅ ሳለ አምባሳደሮች* ልኮ እርቅ ለመፍጠር ይደራደራል። 33 እንደዚሁም ከእናንተ መካከል ያለውን ንብረት ሁሉ የማይሰናበት* ፈጽሞ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።+
34 “ጨው ጥሩ ነገር እንደሆነ የታወቀ ነው። ሆኖም ጨው ራሱ የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን በምን መመለስ ይቻላል?+ 35 እንዲህ ያለ ጨው ለአፈር የሚሰጠው ጥቅም የለም፤ ማዳበሪያም ሊሆን አይችልም። በመሆኑም ሰዎች ወደ ውጭ ይጥሉታል። ስለዚህ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”+
15 አንድ ቀን ቀራጮችና ኃጢአተኞች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት በዙሪያው ተሰበሰቡ።+ 2 ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም “ይህ ሰው ኃጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነሱም ጋር ይበላል” እያሉ አጉረመረሙ። 3 በዚህ ጊዜ የሚከተለውን ምሳሌ ነገራቸው፦ 4 “ከእናንተ መካከል 100 በጎች ያሉት ሰው አንዷ ብትጠፋበት 99ኙን በምድረ በዳ ትቶ የጠፋችውን እስኪያገኝ ድረስ አይፈልግም?+ 5 በሚያገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ላይ ይሸከማታል። 6 ቤት ሲደርስም ጓደኞቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋችውን በጌን ስላገኘኋት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ይላቸዋል።+ 7 እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ መግባት ከማያስፈልጋቸው 99 ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል።+
8 “ወይም ደግሞ አሥር ድራክማ ሳንቲሞች* ያሏት አንዲት ሴት አንዱ ድራክማ* ቢጠፋባት መብራት አብርታ ቤቷን በመጥረግ እስክታገኘው ድረስ በደንብ አትፈልገውም? 9 ሳንቲሙን ባገኘችው ጊዜም ጓደኞቿንና ጎረቤቶቿን* በአንድነት ጠርታ ‘የጠፋብኝን ድራክማ ሳንቲም* ስላገኘሁት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ትላቸዋለች። 10 እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በአምላክ መላእክት ዘንድ ደስታ ይሆናል።”+
11 ከዚያም እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። 12 ታናሽየውም ልጅ አባቱን ‘አባቴ ሆይ፣ ከንብረትህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው። በመሆኑም አባትየው ንብረቱን ለልጆቹ አካፈላቸው። 13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሽየው ልጅ ያለውን ነገር ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ተጓዘ፤ በዚያም ልቅ የሆነ* ሕይወት በመኖር ንብረቱን አባከነ። 14 ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ በዚያ አገር በሙሉ ከባድ ረሃብ ተከሰተ፤ በዚህ ጊዜ ችግር ላይ ወደቀ። 15 ከችግሩም የተነሳ ከዚያ አገር ሰዎች ወደ አንዱ ሄዶ የሙጥኝ አለ፤ ሰውየውም አሳማ+ እንዲጠብቅለት ወደ ሜዳ ላከው። 16 እሱም አሳማዎቹ የሚመገቡትን ምግብ በልቶ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ ነገር ግን የሚሰጠው አልነበረም።
17 “ወደ ልቦናው ሲመለስ ግን እንዲህ አለ፦ ‘ስንቶቹ የአባቴ ቅጥር ሠራተኞች ምግብ ተርፏቸው እኔ እዚህ በረሃብ ልሞት ነው! 18 ተነስቼ ወደ አባቴ በመሄድ እንዲህ እለዋለሁ፦ “አባቴ ሆይ፣ በአምላክና* በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ። 19 ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም። ከቅጥር ሠራተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ።”’ 20 ስለዚህ ተነስቶ ወደ አባቱ ሄደ። ገና ሩቅ ሳለም አባቱ አየው፤ በዚህ ጊዜ አንጀቱ ተላወሰ፤ እየሮጠ ሄዶም አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ሳመው። 21 ከዚያም ልጁ ‘አባቴ ሆይ፣ በአምላክና በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ።+ ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው። 22 አባትየው ግን ባሪያዎቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ቶሎ በሉ! ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጥታችሁ አልብሱት፤ ለእጁ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት። 23 የሰባውንም ጥጃ አምጥታችሁ እረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት። 24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል።+ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር።
25 “በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ በእርሻ ቦታ ነበር፤ ተመልሶ መጥቶ ወደ ቤት በተቃረበ ጊዜ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ። 26 ስለዚህ ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ ነገሩ ምን እንደሆነ ጠየቀው። 27 አገልጋዩም ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በደህና ስለመጣም አባትህ የሰባውን ጥጃ አርዶለታል’ አለው። 28 እሱ ግን ተቆጣ፤ ወደ ቤት ለመግባትም አሻፈረኝ አለ። ከዚያም አባቱ ወጥቶ ይለምነው ጀመር። 29 እሱም መልሶ አባቱን እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ እኔ ስንት ዓመት ሙሉ እንደ ባሪያ ሳገለግልህ ኖርኩ፤ መቼም ቢሆን ከትእዛዝህ ዝንፍ ብዬ አላውቅም፤ አንተ ግን ከጓደኞቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ጠቦት እንኳ ሰጥተኸኝ አታውቅም። 30 ሆኖም ሀብትህን ከዝሙት አዳሪዎች ጋር ያወደመው* ይህ ልጅህ ገና ከመምጣቱ የሰባውን ጥጃ አረድክለት።’ 31 በዚህ ጊዜ አባቱ እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ ደግሞም የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው። 32 ሆኖም ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል። ስለዚህ ልንደሰትና ሐሴት ልናደርግ ይገባል።’”
16 ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ሀብታም ሰው አንድ መጋቢ* ነበረው፤ ይህ ሰው፣ መጋቢው ንብረቱን እያባከነበት እንዳለ የሚገልጽ ክስ ደረሰው። 2 ስለዚህ መጋቢውን ጠራውና ‘ይህ ስለ አንተ የምሰማው ነገር ምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ቤቱን ማስተዳደር ስለማትችል በመጋቢነት ስትሠራበት የነበረውን የሒሳብ መዝገብ አስረክበኝ’ አለው። 3 በዚህ ጊዜ መጋቢው በልቡ እንዲህ አለ፦ ‘ጌታዬ የመጋቢነት ኃላፊነቴን ሊወስድብኝ ነው፤ ታዲያ ምን ባደርግ ይሻላል? እንዳልቆፍር አቅም የለኝም፤ እንዳልለምን ያሳፍረኛል። 4 ቆይ፣ ምን እንደማደርግ አውቃለሁ! ከመጋቢነት ኃላፊነቴ ስነሳ ሰዎች በቤታቸው እንዲቀበሉኝ አንድ ነገር አደርጋለሁ።’ 5 ከዚያም ከጌታው የተበደሩትን ሰዎች አንድ በአንድ በመጥራት የመጀመሪያውን ‘ከጌታዬ የተበደርከው ምን ያህል ነው?’ አለው። 6 እሱም ‘አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ* የወይራ ዘይት’ ሲል መለሰለት። መጋቢውም ‘የውል ሰነድህ ይኸውልህ፤ ቁጭ በልና ቶሎ ብለህ 50 ብለህ ጻፍ’ አለው። 7 ቀጥሎም ሌላውን ‘አንተስ፣ የተበደርከው ምን ያህል ነው?’ አለው። እሱም ‘አንድ መቶ የቆሮስ መስፈሪያ* ስንዴ’ አለው። መጋቢውም ‘የውል ሰነድህ ይኸውልህ፤ 80 ብለህ ጻፍ’ አለው። 8 ጌታውም መጋቢው ዓመፀኛ ቢሆንም እንኳ አርቆ በማሰብ* ባደረገው ነገር አደነቀው፤ ምክንያቱም የዚህ ሥርዓት* ልጆች በእነሱ ትውልድ ካሉት ሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ረገድ ከብርሃን ልጆች+ ይበልጥ ብልሆች ናቸው።
9 “ደግሞም እላችኋለሁ፦ በዓመፅ ሀብት ለራሳችሁ ወዳጆች አፍሩ፤+ እነሱም የዓመፅ ሀብት ሲያልቅ በዘላለማዊ መኖሪያ ይቀበሏችኋል።+ 10 በትንሽ ነገር ታማኝ የሆነ ሰው በብዙ ነገርም ታማኝ ነው፤ በትንሽ ነገር ታማኝ ያልሆነ ሰው ደግሞ በብዙ ነገርም ታማኝ አይሆንም። 11 ስለዚህ በዓመፅ ሀብት ታማኝ ሆናችሁ ካልተገኛችሁ እውነተኛውን ሀብት ማን በአደራ ይሰጣችኋል? 12 የሌላ ሰው በሆነው ነገር ታማኝ ሆናችሁ ካልተገኛችሁ ለእናንተ የታሰበውን ማን ይሰጣችኋል?+ 13 ለሁለት ጌቶች ባሪያ መሆን የሚችል አገልጋይ የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል ወይም አንዱን ደግፎ ሌላውን ይንቃል። ለአምላክም ለሀብትም በአንድ ጊዜ ባሪያ መሆን አትችሉም።”+
14 ገንዘብ ወዳድ የሆኑት ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሲናገር ሰምተው ያፌዙበት ጀመር።+ 15 በመሆኑም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ በሰዎች ፊት ጻድቅ መስላችሁ ትቀርባላችሁ፤+ አምላክ ግን ልባችሁን ያውቃል።+ በሰዎች ፊት ከፍ ተደርጎ የሚታየው ነገር በአምላክ ፊት አስጸያፊ ነውና።+
16 “ሕጉም ሆነ የነቢያት ቃል እስከ ዮሐንስ ድረስ ሲነገሩ ቆይተዋል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የአምላክ መንግሥት ምሥራች እየታወጀ ነው፤ የተለያዩ ዓይነት ሰዎችም ወደዚያ ለመግባት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ነው።+ 17 እንደ እውነቱ ከሆነ ከሕጉ የአንዷ ፊደል ጭረት ሳትፈጸም ከምትቀር ሰማይና ምድር ቢያልፉ ይቀላል።+
18 “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ባሏ የፈታትንም ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።+
19 “አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ሐምራዊ* ልብስና በፍታ ይለብስ የነበረ ከመሆኑም በላይ ዕለት ተዕለት በደስታና በቅንጦት ይኖር ነበር። 20 ይሁን እንጂ እዚህ ሰው ደጃፍ ላይ እያመጡ የሚያስቀምጡት መላ ሰውነቱን ቁስል የወረሰው አልዓዛር የሚባል አንድ ለማኝ ነበር፤ 21 እሱም ከሀብታሙ ማዕድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ በልቶ ለመጥገብ ይመኝ ነበር። ውሾችም* ሳይቀር እየመጡ ቁስሉን ይልሱ ነበር። 22 ከጊዜ በኋላ ለማኙ ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ* ወሰዱት።
“ሀብታሙም ሰው ሞተና ተቀበረ። 23 በመቃብርም* ሆኖ እየተሠቃየ ሳለ አሻቅቦ ሲመለከት ከሩቅ አብርሃምንና በእቅፉ ያለውን አልዓዛርን አየ። 24 በዚህ ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ‘አብርሃም አባት ሆይ፣ በዚህ የሚንቀለቀል እሳት እየተሠቃየሁ ስለሆነ እባክህ ራራልኝና አልዓዛር የጣቱን ጫፍ ውኃ ውስጥ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ ላከው’ አለ። 25 አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፣ አንተ በሕይወት ዘመንህ መልካም ነገሮችን ሁሉ እንደተቀበልክ፣ አልዓዛር ግን መጥፎ ነገሮች እንደደረሱበት አስታውስ። አሁን ግን እሱ እዚህ ሲጽናና አንተ ትሠቃያለህ። 26 ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ከእኛ ወደ እናንተ መሻገር የሚፈልጉ መሻገር እንዳይችሉ እንዲሁም ሰዎች ከእናንተ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል ተደርጓል።’ 27 በዚህ ጊዜ ሀብታሙ ሰው እንዲህ አለ፦ ‘አባት ሆይ፣ እንደዚያ ከሆነ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትልከው እለምንሃለሁ፤ 28 አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነሱም ወደዚህ የሥቃይ ስፍራ እንዳይገቡ በሚገባ ይመሥክርላቸው።’ 29 አብርሃም ግን ‘ሙሴና ነቢያት አሉላቸው፤ እነሱን ይስሙ’ አለው።+ 30 እሱም ‘አይ፣ እንደሱ አይደለም፤ አብርሃም አባት ሆይ፣ አንድ ሰው ከሞት ተነስቶ ወደ እነሱ ቢሄድ ንስሐ ይገባሉ’ አለ። 31 አብርሃም ግን ‘ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ+ አንድ ሰው ከሞት ቢነሳም አምነው አይቀበሉም’ አለው።”
17 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ሰዎችን የሚያሰናክሉ ነገሮች መከሰታቸው የማይቀር ነው። ሆኖም ለመሰናክሉ ምክንያት ለሚሆነው ለዚያ ሰው ወዮለት! 2 ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል።+ 3 ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤+ ከተጸጸተም ይቅር በለው።+ 4 በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህ እንኳ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ሰባት ጊዜ ወደ አንተ ከመጣ ይቅር ልትለው ይገባል።”+
5 በዚህ ጊዜ ሐዋርያቱ ጌታን “እምነት ጨምርልን” አሉት።+ 6 ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰናፍጭ ዘር የሚያህል እምነት ካላችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ ባሕሩ ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዛችኋል።+
7 “ከእናንተ መካከል አራሽ ወይም እረኛ የሆነ ባሪያ ያለው ሰው ቢኖር፣ ባሪያው ከእርሻ ሲመለስ ‘ቶሎ ናና ወደ ማዕድ ቅረብ’ ይለዋል? 8 ከዚህ ይልቅ ‘ራቴን አዘጋጅልኝ፤ በልቼና ጠጥቼ እስክጨርስም ድረስ አሸርጠህ አገልግለኝ፤ ከዚያ በኋላ መብላትና መጠጣት ትችላለህ’ አይለውም? 9 ባሪያው የተሰጠውን ሥራ በማከናወኑ ጌታው የሚያመሰግነው ይመስላችኋል? 10 በተመሳሳይ እናንተም የተሰጣችሁን ሥራ ሁሉ ባከናወናችሁ ጊዜ ‘ምንም የማንጠቅም ባሪያዎች ነን። ያደረግነው ልናደርገው የሚገባንን ነገር ነው’ በሉ።”+
11 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደ ሳለ በሰማርያና በገሊላ መካከል አለፈ። 12 ወደ አንድ መንደር እየገባም ሳለ የሥጋ ደዌ የያዛቸው አሥር ሰዎች አዩት፤ እነሱም በርቀት ቆሙ።+ 13 ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ “ኢየሱስ፣ መምህር፣ ምሕረት አድርግልን!” አሉ። 14 እሱም ባያቸው ጊዜ “ሄዳችሁ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ” አላቸው።+ ከዚያም እየሄዱ ሳሉ ነጹ።+ 15 ከእነሱ አንዱ እንደተፈወሰ ባየ ጊዜ አምላክን በታላቅ ድምፅ እያመሰገነ ተመለሰ። 16 ኢየሱስ እግር ላይ ተደፍቶም አመሰገነው። ሰውየውም ሳምራዊ+ ነበር። 17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “የነጹት አሥሩም አይደሉም እንዴ? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ? 18 ከዚህ ከባዕድ አገር ሰው በስተቀር አምላክን ለማመስገን የተመለሰ ሌላ አንድም ሰው የለም?” 19 ከዚያም ሰውየውን “ተነስና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።+
20 ፈሪሳውያን የአምላክ መንግሥት መቼ እንደሚመጣ ሲጠይቁት+ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የአምላክ መንግሥት በግልጽ በሚታይ ሁኔታ አይመጣም፤ 21 ሰዎችም ‘እነሆ እዚህ ነው!’ ወይም ‘እዚያ ነው!’ አይሉም። እነሆ፣ የአምላክ መንግሥት በመካከላችሁ ነውና።”+
22 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትመኙበት ጊዜ ይመጣል፤ ግን አታዩትም። 23 ሰዎችም ‘እዚያ ነው!’ ወይም ‘እዚህ ነው!’ ይሏችኋል። ነገር ግን አትሂዱ ወይም አትከተሏቸው።+ 24 ምክንያቱም መብረቅ ከአንዱ የሰማይ ክፍል እስከ ሌላኛው የሰማይ ክፍል እንደሚያበራ ሁሉ የሰው ልጅ+ በሚገለጥበትም ቀን እንዲሁ ይሆናል።+ 25 በመጀመሪያ ግን ብዙ መከራ መቀበሉና በዚህ ትውልድ ተቀባይነት ማጣቱ የግድ ነው።+ 26 በተጨማሪም በኖኅ ዘመን+ እንደተከሰተው ሁሉ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል፦+ 27 ኖኅ ወደ መርከቡ እስከገባበትና+ የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉንም እስካጠፋበት ቀን+ ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ወንዶች ያገቡ፣ ሴቶችም ይዳሩ ነበር። 28 በተመሳሳይም በሎጥ ዘመን እንደተከሰተው ሁሉ እንዲሁ ይሆናል፦+ ሰዎች ይበሉ፣ ይጠጡ፣ ይገዙ፣ ይሸጡ፣ ይተክሉና ቤቶችን ይገነቡ ነበር። 29 ሆኖም ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ከሰማይ እሳትና ድኝ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋቸው።+ 30 የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን+ እንዲሁ ይሆናል።
31 “በዚያን ቀን በጣሪያ* ላይ ያለ ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ ለመውሰድ አይውረድ፤ እርሻም ላይ ያለ ሰው በኋላው ያለውን ነገር ለመውሰድ አይመለስ። 32 የሎጥን ሚስት አስታውሱ።+ 33 ሕይወቱን* ጠብቆ ለማቆየት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ሕይወቱን የሚያጣት ሁሉ ግን በሕይወት ጠብቆ ያቆያታል።+ 34 እላችኋለሁ፣ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ላይ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላኛው ግን ይተዋል።+ 35 ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላኛዋ ግን ትተዋለች።” 36 *—— 37 እነሱም መልሰው “ጌታ ሆይ፣ የት?” አሉት። እሱም “በድን ባለበት ንስሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው።+
18 ከዚያም ምንጊዜም ተስፋ ሳይቆርጡ የመጸለይን+ አስፈላጊነት በተመለከተ ለደቀ መዛሙርቱ አንድ ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ 2 እንዲህም አላቸው፦ “በአንዲት ከተማ አምላክን የማይፈራና ሰውን የማያከብር አንድ ዳኛ ነበር። 3 በዚያች ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ በየጊዜው ወደ እሱ እየሄደች ‘ከባላጋራዬ ጋር ለምከራከርበት ጉዳይ ፍረድልኝ’ ትለው ነበር። 4 ይሁንና ዳኛው ለተወሰነ ጊዜ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ፤ በኋላ ግን በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፦ ‘ምንም እንኳ አምላክን የማልፈራ፣ ሰውንም የማላከብር ብሆን 5 ይህች መበለት ሁልጊዜ እየመጣች ስለምታስቸግረኝ ፍትሕ እንድታገኝ አደርጋለሁ፤ አለዚያ በየጊዜው እየመጣች ትነዘንዘኛለች።’”*+ 6 ከዚያም ጌታ እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ዳኛው ዓመፀኛ ቢሆንም ምን እንዳለ ልብ በሉ! 7 ታዲያ አምላክ በትዕግሥት የሚይዛቸውና+ ቀን ከሌት ወደ እሱ የሚጮኹት ምርጦቹ+ ፍትሕ እንዲያገኙ አያደርግም? 8 እላችኋለሁ፣ በቶሎ ፍትሕ እንዲያገኙ ያደርጋል። ሆኖም የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ በእርግጥ እምነት* ያገኝ ይሆን?”
9 በራሳቸው ጽድቅ ለሚታመኑና ሌሎችን በንቀት ዓይን ለሚመለከቱ ደግሞ የሚከተለውን ምሳሌ ተናገረ፦ 10 “ሁለት ሰዎች ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፤ አንደኛው ፈሪሳዊ፣ ሌላኛው ደግሞ ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር። 11 ፈሪሳዊው ቆሞ በልቡ እንዲህ ሲል ይጸልይ ጀመር፦ ‘አምላክ ሆይ፣ እንደ ሌላው ሰው ቀማኛ፣ ዓመፀኛ፣ አመንዝራ፣ በተለይ ደግሞ እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ። 12 በሳምንት ሁለቴ እጾማለሁ፤ ከማገኘውም ነገር ሁሉ አሥራት እሰጣለሁ።’+ 13 ቀረጥ ሰብሳቢው ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ለማየትም እንኳ አልደፈረም፤ እንዲያውም ‘አምላክ ሆይ፣ ኃጢአተኛ ለሆንኩት ለእኔ ቸርነት አድርግልኝ’* እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።+ 14 እላችኋለሁ፣ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይሄኛው ሰው ይበልጥ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ።+ ምክንያቱም ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ግን ከፍ ይደረጋል።”+
15 ሰዎችም ኢየሱስ እጁን እንዲጭንባቸው ሕፃናትን ወደ እሱ ያመጡ ጀመር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ይህን ሲያዩ ገሠጿቸው።+ 16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ሕፃናቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አለ፦ “ልጆቹ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ የአምላክ መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ነውና።+ 17 እውነት እላችኋለሁ፣ የአምላክን መንግሥት እንደ አንድ ትንሽ ልጅ ሆኖ የማይቀበል ሁሉ ፈጽሞ ወደዚህ መንግሥት አይገባም።”+
18 ከአይሁዳውያን አለቆችም አንዱ “ጥሩ መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” ሲል ጠየቀው።+ 19 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ለምን ጥሩ ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ጥሩ የለም።+ 20 ‘አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ በሐሰት አትመሥክር፣+ አባትህንና እናትህን አክብር’+ የሚሉትን ትእዛዛት ታውቃለህ።” 21 ሰውየውም “እነዚህን ሁሉ ከልጅነቴ ጀምሮ ስጠብቅ ኖሬአለሁ” አለ። 22 ኢየሱስ ይህን ከሰማ በኋላ “አሁንም አንድ የሚቀርህ ነገር አለ፤ ያለህን ነገር ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድሆች አከፋፍል፤ በሰማያትም ውድ ሀብት ታገኛለህ፤ ደግሞም መጥተህ ተከታዬ ሁን” አለው።+ 23 ሰውየው በጣም ሀብታም ስለነበረ ይህን ሲሰማ እጅግ አዘነ።+
24 ኢየሱስም ሰውየውን ተመልክቶ እንዲህ አለ፦ “ገንዘብ ላላቸው ሰዎች ወደ አምላክ መንግሥት መግባት ምንኛ አስቸጋሪ ነው!+ 25 እንዲያውም ሀብታም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።”+ 26 ይህን የሰሙ ሰዎች “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።+ 27 እሱም “በሰዎች ዘንድ የማይቻል፣ በአምላክ ዘንድ ይቻላል” አለ።+ 28 ጴጥሮስ ግን “እነሆ፣ እኛ ያለንን ነገር ትተን ተከትለንሃል” አለ።+ 29 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለአምላክ መንግሥት ሲል ቤትን ወይም ሚስትን ወይም ወንድሞችን ወይም ወላጆችን ወይም ልጆችን የተወ ሁሉ፣+ 30 አሁን በዚህ ዘመን ብዙ እጥፍ፣ በሚመጣው ሥርዓት* ደግሞ የዘላለም ሕይወት ያገኛል።”+
31 ከዚያም አሥራ ሁለቱን ገለል አድርጎ በመውሰድ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰውን ልጅ በተመለከተም በነቢያት የተጻፉት ነገሮች ሁሉ ይፈጸማሉ።+ 32 ለምሳሌ ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤+ ያፌዙበታል፤+ ያንገላቱታል እንዲሁም ይተፉበታል።+ 33 ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤+ በሦስተኛው ቀን ግን ይነሳል።”+ 34 ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ መካከል አንዱንም አልተረዱም፤ የተናገረው ቃል ተሰውሮባቸው ነበርና፤ የተባለውም ነገር አልገባቸውም።
35 ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ እየተቃረበ ሳለ አንድ ዓይነ ስውር መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።+ 36 ዓይነ ስውሩም ብዙ ሕዝብ በዚያ ሲያልፍ ሰምቶ ስለ ሁኔታው ይጠይቅ ጀመር። 37 ሰዎቹም “የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ እያለፈ ነው!” ብለው ነገሩት። 38 በዚህ ጊዜ “ኢየሱስ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” ሲል ጮኸ። 39 ከፊት ከፊት የሚሄዱትም ሰዎች ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” እያለ ይበልጥ መጮኹን ቀጠለ። 40 ኢየሱስም ቆመና ሰውየውን ወደ እሱ እንዲያመጡት አዘዘ። ሰውየው ወደ እሱ በቀረበ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ 41 “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” እሱም “ጌታ ሆይ፣ የዓይኔን ብርሃን መልስልኝ” አለው። 42 ስለዚህ ኢየሱስ “የዓይንህ ብርሃን ይመለስልህ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።+ 43 ወዲያውም የዓይኑ ብርሃን ተመለሰለት፤ አምላክን እያመሰገነም ይከተለው ጀመር።+ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ አምላክን አወደሱ።+
19 ከዚያም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ እያለፈ ነበር። 2 በዚያም ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሀብታም ሰው የነበረ ሲሆን ይህ ሰው የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ ነበር። 3 እሱም ኢየሱስ የሚባለው ማን እንደሆነ ለማየት ይፈልግ ነበር፤ ሆኖም አጭር በመሆኑ ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ማየት አልቻለም። 4 ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለነበር ዘኬዎስ ሮጦ ወደ ፊት በመሄድ እሱን ለማየት አንድ የሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። 5 ኢየሱስ እዚያ ቦታ በደረሰ ጊዜ ቀና ብሎ ተመለከተውና “ዘኬዎስ፣ ዛሬ ወደ አንተ ቤት ስለምመጣ ቶሎ ውረድ” አለው። 6 በዚህ ጊዜ በፍጥነት ወርዶ ደስ እያለው በእንግድነት ተቀበለው። 7 ሰዎቹ ይህን ባዩ ጊዜ “ኃጢአተኛ ሰው ቤት ሊስተናገድ ገባ” ብለው ሁሉም አጉተመተሙ።+ 8 ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን “ጌታ ሆይ፣ ካለኝ ሀብት ግማሹን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ከሰው የቀማሁትንም* ሁሉ አራት እጥፍ እመልሳለሁ” አለው።+ 9 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ይህም ሰው የአብርሃም ልጅ ስለሆነ ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን መጥቷል። 10 ምክንያቱም የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ለመፈለግና ለማዳን ነው።”+
11 እነሱም እነዚህን ነገሮች እየሰሙ ሳሉ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ ይህን የተናገረው ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የአምላክ መንግሥት ወዲያውኑ የሚገለጥ ስለመሰላቸው ነው።+ 12 ስለዚህ እንዲህ አለ፦ “አንድ መስፍን ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተረክቦ ለመመለስ ወደ ሩቅ አገር ሊሄድ ተነሳ።+ 13 ከባሪያዎቹ መካከል አሥሩን ጠርቶ አሥር ምናን* ሰጣቸውና ‘እስክመጣ ድረስ ነግዱበት’ አላቸው።+ 14 የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ስለነበር እሱ ከሄደ በኋላ ‘ይህ ሰው በእኛ ላይ እንዲነግሥ አንፈልግም’ ብለው እንዲነግሩላቸው መልእክተኞች ላኩ።
15 “ከጊዜ በኋላ ንጉሣዊ ሥልጣኑን* ተረክቦ ሲመጣ ገንዘብ* የሰጣቸው ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ለማወቅ አስጠራቸው።+ 16 በመሆኑም የመጀመሪያው ቀርቦ ‘ጌታዬ፣ ምናንህ አሥር ምናን ትርፍ አስገኝቷል’ አለው።+ 17 ጌታው ‘ጎበዝ፣ አንተ ጥሩ ባሪያ! በጣም አነስተኛ በሆነው ነገር ታማኝ ሆነህ ስለተገኘህ በአሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ተሰጥቶሃል’ አለው።+ 18 ሁለተኛው ደግሞ ቀርቦ ‘ጌታዬ፣ ምናንህ አምስት ምናን አስገኝቷል’ አለ።+ 19 ይሄኛውንም ‘አንተም በአምስት ከተሞች ላይ ተሹመሃል’ አለው። 20 ሆኖም ሌላኛው መጥቶ እንዲህ አለ፦ ‘ጌታዬ፣ በጨርቅ ጠቅልዬ የደበቅኩት ምናንህ ይኸውልህ። 21 ይህን ያደረግኩት ጨካኝ ሰው ስለሆንክ ፈርቼህ ነው፤ አንተ ያላስቀመጥከውን የምትወስድ፣ ያልዘራኸውንም የምታጭድ ሰው ነህ።’+ 22 ጌታውም እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፣ በራስህ ቃል እፈርድብሃለሁ። ያላስቀመጥኩትን የምወስድ፣ ያልዘራሁትንም የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደሆንኩ ታውቅ ኖሯል ማለት ነው?+ 23 ታዲያ ገንዘቤን* ለምን ለገንዘብ ለዋጮች* አልሰጠህም? እንደዚህ አድርገህ ቢሆን ኖሮ ስመጣ ከነወለዱ እወስደው ነበር።’
24 “ከዚያም በዚያ ቆመው የነበሩትን ሰዎች ‘ምናኑን ውሰዱበትና አሥር ምናን ላለው ስጡት’ አላቸው።+ 25 እነሱ ግን ‘ጌታ ሆይ፣ እሱ እኮ አሥር ምናን አለው’ አሉት። እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ 26 ‘እላችኋለሁ፣ ላለው ሁሉ ተጨማሪ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ሰው ላይ ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።+ 27 በተጨማሪም በእነሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡና በፊቴ ግደሏቸው።’”
28 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ጉዞውን በመቀጠል ወደ ኢየሩሳሌም አቀና። 29 ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ+ ወደሚገኙት ወደ ቤተፋጌ እና ወደ ቢታንያ በተቃረበ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ላካቸው፤+ 30 እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ ወደ መንደሩ ከገባችሁም በኋላ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ ውርንጭላ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደዚህ አምጡት። 31 ይሁን እንጂ ማንም ሰው ‘የምትፈቱት ለምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ ‘ጌታ ይፈልገዋል’ ብላችሁ ንገሩት።” 32 የተላኩትም ሄደው ልክ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት።+ 33 ውርንጭላውን እየፈቱ ሳሉ ግን ባለቤቶቹ “ውርንጭላውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። 34 እነሱም “ጌታ ይፈልገዋል” አሉ። 35 ከዚያም ውርንጭላውን ወደ ኢየሱስ ወሰዱት፤ መደረቢያቸውንም በውርንጭላው ላይ ጣል አድርገው ኢየሱስን በላዩ አስቀመጡት።+
36 እየተጓዘም ሳለ መደረቢያቸውን በመንገዱ ላይ ያነጥፉ ነበር።+ 37 ከደብረ ዘይት ተራራ ቁልቁል ወደሚወስደው መንገድ እንደተቃረበ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደቀ መዛሙርቱ ባዩአቸው ተአምራት መደሰትና አምላክን በታላቅ ድምፅ ማወደስ ጀመሩ፤ 38 እንዲህም ይሉ ነበር፦ “በይሖዋ* ስም ንጉሥ ሆኖ የሚመጣ የተባረከ ነው! በሰማይ ሰላም፣ በአርያም ላለውም ክብር ይሁን!”+ 39 በሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያን ግን “መምህር፣ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው እንጂ” አሉት።+ 40 እሱ ግን መልሶ “እላችኋለሁ፣ እነዚህ ዝም ቢሉ እንኳ ድንጋዮች ይጮኻሉ” አላቸው።
41 ወደ ኢየሩሳሌም በተቃረበ ጊዜም ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤+ 42 እንዲህም አለ፦ “አንቺ፣ አዎ አንቺ ራስሽ፣ ሰላም የሚያስገኙልሽን ነገሮች ምነው ዛሬ በተረዳሽ ኖሮ፤ አሁን ግን ከዓይኖችሽ ተሰውረዋል።+ 43 ምክንያቱም ጠላቶችሽ በሾለ እንጨት በዙሪያሽ ቅጥር ቀጥረው አንቺን የሚከቡበትና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል።+ 44 አንቺንና በውስጥሽ የሚኖሩትን ልጆችሽን ፈጥፍጠው ከአፈር ይደባልቃሉ፤+ በአንቺ ውስጥም ሳያፈርሱ እንደተነባበረ የሚተዉት ድንጋይ አይኖርም፤+ ምክንያቱም በአንቺ ላይ ምርመራ የተካሄደበትን ጊዜ አልተገነዘብሽም።”
45 ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ ገብቶ በዚያ የሚሸጡትን ያስወጣ ጀመር፤+ 46 እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’+ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት።”+
47 እሱም በየዕለቱ በቤተ መቅደሱ ማስተማሩን ቀጠለ። ሆኖም የካህናት አለቆችና ጸሐፍት እንዲሁም የሕዝቡ መሪዎች ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፤+ 48 ይሁንና ሕዝቡ ሁሉ እሱን ለመስማት ከአጠገቡ ስለማይለይ ምን እንደሚያደርጉ ግራ ገባቸው።+
20 አንድ ቀን ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሕዝቡን እያስተማረና ምሥራቹን እያወጀ ሳለ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር መጡ፤ 2 ከዚያም “እስቲ ንገረን፤ እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት።+ 3 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም መልሱልኝ፦ 4 ዮሐንስ የማጥመቅ ሥልጣን ያገኘው ከአምላክ* ነው ወይስ ከሰው?” 5 እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “‘ከአምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ 6 ‘ከሰው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ ነው ብለው ስለሚያምኑ+ በድንጋይ ይወግሩናል።” 7 ስለዚህ ‘ከየት እንደሆነ አናውቅም’ ብለው መለሱለት። 8 ኢየሱስም “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
9 ከዚያም ለሕዝቡ የሚከተለውን ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ+ አለማና ለገበሬዎች አከራየ፤ ወደ ሌላ አገር ሄዶም ረዘም ላለ ጊዜ ቆየ።+ 10 ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን እንዲልኩለት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ። ይሁንና ገበሬዎቹ ባሪያውን ከደበደቡት በኋላ ባዶ እጁን ሰደዱት።+ 11 እሱ ግን በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። ይሄኛውንም ደብድበውና አዋርደው* ባዶ እጁን ሰደዱት። 12 አሁንም ሦስተኛ ባሪያ ላከ፤ እሱንም ካቆሰሉት በኋላ አውጥተው ጣሉት። 13 በዚህ ጊዜ የወይን እርሻው ባለቤት ‘ምን ባደርግ ይሻላል? የምወደውን ልጄን+ እልካለሁ። መቼም እሱን ያከብሩታል’ አለ። 14 ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው። ርስቱ የእኛ እንዲሆን እንግደለው’ ተባባሉ። 15 ከዚያም ከወይን እርሻው ጎትተው በማውጣት ገደሉት።+ ታዲያ የወይኑ እርሻ ባለቤት ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል? 16 ይመጣና እነዚህን ገበሬዎች ይገድላል፤ የወይን እርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል።”
ሕዝቡም ይህን ሲሰሙ “ይህስ ከቶ አይሁን!” አሉ። 17 ኢየሱስም እነሱን ትኩር ብሎ በመመልከት እንዲህ አለ፦ “ታዲያ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ’+ ተብሎ የተጻፈው ትርጉሙ ምንድን ነው? 18 በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል።+ ድንጋዩ የሚወድቅበት ሰው ሁሉ ደግሞ ይደቅቃል።”
19 በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ የተናገረው እነሱን አስቦ እንደሆነ ስለተረዱ በዚያኑ ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፤ ሆኖም ሕዝቡን ፈሩ።+ 20 በቅርብ ሲከታተሉት ከቆዩ በኋላ በንግግሩ እንዲያጠምዱት ጻድቅ መስለው የሚቀርቡ ሰዎችን በድብቅ ቀጥረው ላኩ፤+ ይህን ያደረጉት ለመንግሥትና ለአገረ ገዢው* አሳልፈው ለመስጠት ነው። 21 የተላኩትም ሰዎች እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ “መምህር፣ አንተ ትክክለኛውን ነገር እንደምትናገርና እንደምታስተምር እንዲሁም እንደማታዳላ፣ ከዚህ ይልቅ የአምላክን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፦ 22 ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባናል ወይስ አይገባንም?”* 23 እሱ ግን ተንኮላቸው ገብቶት እንዲህ አላቸው፦ 24 “እስቲ አንድ ዲናር* አሳዩኝ። በላዩ ላይ ያለው ምስልና የተቀረጸው ጽሑፍ የማን ነው?” እነሱም “የቄሳር” አሉ። 25 እሱም “እንግዲያው የቄሳር የሆነውን ለቄሳር፣+ የአምላክ የሆነውን ደግሞ ለአምላክ+ ስጡ” አላቸው። 26 እነሱም በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ ከዚህ ይልቅ በመልሱ በመገረም ዝም አሉ።
27 ሆኖም በትንሣኤ ከማያምኑት+ ሰዱቃውያን መካከል አንዳንዶቹ መጥተው ጥያቄ አቀረቡለት፦+ 28 “መምህር፣ ሙሴ ‘አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ ሚስትየዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር መተካት አለበት’ ብሎ ጽፎልናል።+ 29 እንግዲህ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ። የመጀመሪያው ሚስት አገባ፤ ሆኖም ልጅ ሳይወልድ ሞተ። 30 ሁለተኛውም እንደዚሁ፤ 31 ሦስተኛውም አገባት። በዚሁ አኳኋን ሰባቱም አግብተዋት ልጆች ሳይወልዱ ሞቱ። 32 በመጨረሻም ሴትየዋ ሞተች። 33 እንግዲህ ሰባቱም ስላገቧት በትንሣኤ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?”
34 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የዚህ ሥርዓት* ልጆች ያገባሉ እንዲሁም ይዳራሉ፤ 35 ሆኖም የሚመጣውን ሥርዓት መውረስና የሙታን ትንሣኤን ማግኘት የሚገባቸው አያገቡም እንዲሁም አይዳሩም።+ 36 እንዲያውም እንደ መላእክት ስለሆኑ ከዚያ በኋላ ሊሞቱ አይችሉም፤ የትንሣኤ ልጆች ስለሆኑም የአምላክ ልጆች ናቸው። 37 ይሁንና ሙሴም እንኳ ስለ ቁጥቋጦው በሚገልጸው ታሪክ ላይ ይሖዋን* ‘የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ’+ ብሎ በጠራው ጊዜ ሙታን እንደሚነሡ አስታውቋል። 38 እሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፤ በእሱ ፊት* ሁሉም ሕያዋን ናቸውና።”+ 39 በዚህ ጊዜ አንዳንድ ጸሐፍት “መምህር፣ ጥሩ ብለሃል” አሉ። 40 ከዚያ በኋላ አንድም ጥያቄ ሊጠይቁት አልደፈሩም።
41 እሱ ደግሞ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “ሰዎች ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ?+ 42 ምክንያቱም ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብሏል፦ ‘ይሖዋ* ጌታዬን እንዲህ ብሎታል፦ “በቀኜ ተቀመጥ፤ 43 ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ሁን።”’+ 44 ስለዚህ ዳዊት ‘ጌታ’ ብሎ ጠርቶታል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል?”
45 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ 46 “ዘርፋፋ ልብስ ለብሰው መዞር ከሚወዱ፣ በገበያ ቦታ ሰዎች እጅ እንዲነሷቸው ከሚሹ እንዲሁም በምኩራብ ከፊት መቀመጥ፣* በራት ግብዣ ላይም የክብር ቦታ መያዝ ከሚፈልጉ+ ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ 47 እነሱ የመበለቶችን ቤት* ያራቁታሉ፤ ለታይታ ብለውም* ጸሎታቸውን ያስረዝማሉ። እነዚህ የከፋ* ፍርድ ይጠብቃቸዋል።”
21 ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታሞች በመዋጮ ሣጥኖቹ* ውስጥ መባቸውን ሲከቱ አየ።+ 2 ከዚያም አንዲት ድሃ መበለት በጣም አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች* ስትከት+ አይቶ 3 እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ የበለጠ የሰጠችው ይህች ድሃ መበለት ነች።+ 4 ሁሉም መባ የሰጡት ከትርፋቸው ነውና፤ እሷ ግን በድሃ አቅሟ ያላትን መተዳደሪያ ሁሉ ሰጥታለች።”+
5 በኋላም አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ ውብ በሆኑ ድንጋዮችና ለአምላክ በተሰጡ ስጦታዎች እንዴት እንዳጌጠ+ በተናገሩ ጊዜ 6 “ይህ የምታዩት ነገር ሁሉ የሚፈርስበት ጊዜ ይመጣል፤ እንዲህ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ አይኖርም” አለ።+ 7 እነሱም “መምህር፣ እነዚህ ነገሮች በእርግጥ የሚፈጸሙት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙበትን ጊዜ የሚጠቁመው ምልክትስ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+ 8 እሱም እንዲህ አለ፦ “እንዳያሳስቷችሁ ተጠንቀቁ፤+ ብዙዎች ‘እኔ እሱ ነኝ’ እንዲሁም ‘ጊዜው ቀርቧል’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና። እነሱን አትከተሉ።+ 9 በተጨማሪም ስለ ጦርነትና ብጥብጥ* ስትሰሙ አትሸበሩ። በመጀመሪያ እነዚህ ነገሮች መፈጸም አለባቸውና፤ ፍጻሜው ግን ወዲያው አይመጣም።”+
10 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣+ መንግሥትም በመንግሥት ላይ+ ይነሳል። 11 ታላላቅ የምድር ነውጦች ይከሰታሉ፤ በተለያየ ስፍራም የምግብ እጥረትና ቸነፈር ይሆናል፤+ ደግሞም የሚያስፈሩ ነገሮች እንዲሁም ከሰማይ ታላላቅ ምልክቶች ይታያሉ።
12 “እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ግን ሰዎች ይይዟችኋል፤ ስደት ያደርሱባችኋል+ እንዲሁም ለምኩራብና ለወህኒ ቤት አሳልፈው ይሰጧችኋል። በስሜም ምክንያት በነገሥታትና በገዢዎች ፊት ያቀርቧችኋል።+ 13 ይህም ለመመሥከር የሚያስችል አጋጣሚ ይከፍትላችኋል። 14 የምትሰጡትን መልስ አስቀድማችሁ መዘጋጀት እንደማያስፈልጋችሁ ልብ በሉ፤+ 15 ተቃዋሚዎቻችሁ ሁሉ በአንድነት ሆነው ሊቋቋሙት ወይም ሊከራከሩት የማይችሉት አንደበትና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።+ 16 ከዚህም በተጨማሪ ወላጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁና ጓደኞቻችሁ እንኳ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤* አንዳንዶቻችሁንም ይገድላሉ፤+ 17 በስሜ የተነሳም ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል።+ 18 ይሁን እንጂ ከራሳችሁ ፀጉር አንዷ እንኳ አትጠፋም።+ 19 ከጸናችሁ ሕይወታችሁን ታተርፋላችሁ።*+
20 “ይሁንና ኢየሩሳሌም በጦር ሠራዊት ተከባ ስታዩ+ መጥፊያዋ እንደቀረበ እወቁ።+ 21 በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤+ በከተማዋ ውስጥ ያሉም ከዚያ ይውጡ፤ በገጠር ያሉም ወደ እሷ አይግቡ፤ 22 ምክንያቱም የተጻፈው ነገር ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይህ የፍትሕ እርምጃ የሚወሰድበት ጊዜ* ነው። 23 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!+ ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቁጣ ይመጣል። 24 በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ተማርከውም ወደየአገሩ ይወሰዳሉ፤+ የተወሰኑት የአሕዛብ* ዘመናት እስኪፈጸሙ ድረስም ኢየሩሳሌም በአሕዛብ* ትረገጣለች።+
25 “እንዲሁም በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክቶች ይታያሉ፤+ በምድርም ላይ ሕዝቦች ከባሕሩ ድምፅና ነውጥ የተነሳ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ይጨነቃሉ። 26 የሰማያት ኃይላት ስለሚናወጡ ሰዎች ከፍርሃትና በዓለም ላይ የሚመጡትን ነገሮች ከመጠበቅ የተነሳ ይዝለፈለፋሉ። 27 ከዚያም የሰው ልጅ+ በኃይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።+ 28 ሆኖም እነዚህ ነገሮች መከሰት ሲጀምሩ መዳናችሁ እየቀረበ ስለሆነ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ቀና አድርጉ።”
29 ከዚያም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “የበለስ ዛፍንና ሌሎች ዛፎችን ሁሉ ተመልከቱ።+ 30 ዛፎቹ ሲያቆጠቁጡ ራሳችሁ አይታችሁ በጋ* እንደቀረበ ታውቃላችሁ። 31 በተመሳሳይ እናንተም እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ ስታዩ የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ እርግጠኞች ሁኑ። 32 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ ፈጽሞ አያልፍም።+ 33 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።+
34 “ይሁንና ከልክ በላይ በመብላትና በመጠጣት+ እንዲሁም ስለ ኑሮ በመጨነቅ+ ልባችሁ ሸክም እንዳይበዛበት ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ አለዚያ ያ ቀን ድንገት ሳታስቡት 35 እንደ ወጥመድ+ ይመጣባችኋል። ይህ በመላው ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይደርስባቸዋልና። 36 እንግዲያው መፈጸማቸው ከማይቀረው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ማምለጥና በሰው ልጅ ፊት መቆም እንድትችሉ+ ሁልጊዜ ምልጃ እያቀረባችሁ+ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።”+
37 ኢየሱስ ቀን ቀን በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሲመሽ ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ ያድር ነበር። 38 ሕዝቡም ሁሉ በቤተ መቅደስ እሱን ለመስማት በማለዳ ወደ እሱ ይመጡ ነበር።
22 ፋሲካ የሚባለው የቂጣ* በዓል+ የሚከበርበት ጊዜ ተቃርቦ ነበር።+ 2 የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም ሕዝቡን ይፈሩ+ ስለነበር እሱን የሚገድሉበትን+ ከሁሉ የተሻለ መንገድ እየፈለጉ ነበር። 3 ከዚያም ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ሆኖ በተቆጠረውና አስቆሮቱ ተብሎ በሚጠራው በይሁዳ ሰይጣን ገባበት፤+ 4 ይሁዳም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደሱ ሹሞች ሄዶ ኢየሱስን ለእነሱ አሳልፎ መስጠት ስለሚችልበት መንገድ ተነጋገረ።+ 5 እነሱም በጉዳዩ ተደስተው የብር ገንዘብ* ሊሰጡት ተስማሙ።+ 6 እሱም በዚህ ተስማምቶ ሕዝብ በሌለበት እሱን አሳልፎ መስጠት የሚችልበትን ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር።
7 የቂጣ በዓል የሚከበርበት ቀን ደረሰ፤ በዚህ ዕለት የፋሲካ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤+ 8 ስለዚህ ኢየሱስ “ሄዳችሁ ፋሲካን እንድንበላ አዘጋጁልን”+ ብሎ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው። 9 እነሱም “የት እንድናዘጋጅ ትፈልጋለህ?” አሉት። 10 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ከተማው ስትገቡ የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። እሱን ተከትላችሁ ወደሚገባበት ቤት ሂዱ።+ 11 የቤቱንም ባለቤት ‘መምህሩ “ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሎሃል’ በሉት። 12 ሰውየውም የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁ።” 13 እነሱም ሄዱ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።
14 ሰዓቱ በደረሰ ጊዜም ከሐዋርያቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።+ 15 እንዲህም አላቸው፦ “መከራ ከመቀበሌ በፊት ይህን ፋሲካ አብሬያችሁ ለመብላት በጣም ስመኝ ነበር፤ 16 እላችኋለሁና፣ የዚህ ፋሲካ ትርጉም በአምላክ መንግሥት ፍጻሜውን እስኪያገኝ ድረስ ፋሲካን ዳግመኛ አልበላም።” 17 ከዚያም ጽዋ ተቀብሎ አምላክን ካመሰገነ በኋላ እንዲህ አለ፦ “እንኩ፣ ይህን ጽዋ እየተቀባበላችሁ ጠጡ፤ 18 እላችኋለሁና፣ ከአሁን ጀምሮ የአምላክ መንግሥት እስኪመጣ ድረስ ከዚህ ወይን ዳግመኛ አልጠጣም።”
19 በተጨማሪም ቂጣ+ አንስቶ አመሰገነ፣ ከቆረሰውም በኋላ ሰጣቸውና “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠውን+ ሥጋዬን ያመለክታል።+ ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት”+ አላቸው። 20 በተጨማሪም ራት ከበሉ በኋላ ጽዋውን አንስቶ ልክ እንደዚሁ አደረገ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ+ በሚፈሰው ደሜ+ አማካኝነት የሚመሠረተውን አዲሱን ቃል ኪዳን+ ያመለክታል።
21 “ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ ከእኔ ጋር በማዕድ ነው።+ 22 እርግጥ የሰው ልጅ አስቀድሞ በተወሰነው መሠረት ይሄዳል፤+ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!”+ 23 ስለዚህ ከመካከላቸው በእርግጥ ይህን የሚያደርገው ማን ሊሆን እንደሚችል እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር።+
24 ደግሞም ‘ከመካከላችን ታላቅ የሆነው ማን ነው?’ በሚል በመካከላቸው የጦፈ ክርክር ተነሳ።+ 25 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “የአሕዛብ ነገሥታት በእነሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ፤ እንዲሁም በሕዝባቸው ላይ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች በጎ አድራጊዎች ተብለው ይጠራሉ።+ 26 እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ።+ ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን፤+ አመራር የሚሰጥም እንደ አገልጋይ ይሁን። 27 ለመሆኑ በማዕድ ከተቀመጠና ቆሞ ከሚያገለግል ማን ይበልጣል? በማዕድ የተቀመጠው አይደለም? እኔ ግን በመካከላችሁ ያለሁት እንደ አገልጋይ ሆኜ ነው።+
28 “ይሁን እንጂ እናንተ በፈተናዎቼ+ ከጎኔ ሳትለዩ ቆይታችኋል፤+ 29 አባቴ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን እንዳደረገ ሁሉ እኔም ከእናንተ ጋር ለመንግሥት ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ 30 ይኸውም በመንግሥቴ ከማዕዴ እንድትበሉና እንድትጠጡ+ እንዲሁም በዙፋን ተቀምጣችሁ+ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ እንድትፈርዱ ነው።+
31 “ስምዖን፣ ስምዖን፣ ሰይጣን ሁላችሁንም እንደ ስንዴ ያበጥራችሁ ዘንድ ጥያቄ አቅርቧል።+ 32 እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ምልጃ አቀረብኩ፤+ አንተም በተመለስክ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።”+ 33 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ወደ ወህኒ ለመውረድም ሆነ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው።+ 34 እሱ ግን “ጴጥሮስ ሆይ፣ እውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ ዶሮ ከመጮኹ በፊት፣ አላውቀውም ብለህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው።+
35 በተጨማሪም እንዲህ አላቸው፦ “ያለገንዘብ ኮሮጆ፣ ያለምግብ ከረጢትና ያለትርፍ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ+ የጎደለባችሁ ነገር ነበር?” እነሱም “ምንም አልጎደለብንም” አሉ። 36 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ግን የገንዘብ ኮሮጆ ያለው ኮሮጆውን ይያዝ፤ የምግብ ከረጢት ያለውም እንዲሁ፤ ሰይፍ የሌለው ደግሞ መደረቢያውን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ። 37 ይህን የምላችሁ ‘ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ’+ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ላይ መፈጸም ስላለበት ነው። ስለ እኔ የተነገረው ነገር ፍጻሜውን እያገኘ ነውና።”+ 38 እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ይኸው ሁለት ሰይፎች አሉ” አሉት። እሱም “በቂ ነው” አላቸው።
39 ከዚያ ወጥቶም እንደ ልማዱ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት።+ 40 እዚያም በደረሱ ጊዜ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ” አላቸው።+ 41 እሱም የድንጋይ ውርወራ ያህል ከእነሱ በመራቅ ተንበርክኮ መጸለይ ጀመረ፤ 42 እንዲህም አለ፦ “አባት ሆይ፣ ፈቃድህ ከሆነ ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ። ይሁንና የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም።”+ 43 ከዚያም አንድ መልአክ ከሰማይ ተገልጦለት አበረታታው።+ 44 ሆኖም በከፍተኛ ጭንቀት ተውጦ ከበፊቱ ይበልጥ አጥብቆ መጸለዩን ቀጠለ፤+ ላቡም መሬት ላይ እንደሚንጠባጠብ ደም ሆኖ ነበር። 45 ከጸለየም በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲሄድ ከሐዘን የተነሳ ደክሟቸው ስለነበር ሲያንቀላፉ አገኛቸው።+ 46 እሱም “ለምን ትተኛላችሁ? ተነሱ፤ ደግሞም ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ” አላቸው።+
47 ገና እየተናገረ ሳለ ብዙ ሰዎች መጡ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ የተባለውም ሰው ይመራቸው ነበር፤ ሊስመውም ወደ ኢየሱስ ተጠጋ።+ 48 ኢየሱስ ግን “ይሁዳ፣ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህ?” አለው። 49 በዙሪያው የነበሩትም አዝማሚያውን ሲያዩ “ጌታ ሆይ፣ በሰይፍ እንምታቸው?” አሉት። 50 እንዲያውም ከመካከላቸው አንዱ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው።+ 51 ኢየሱስ ግን መልሶ “ተዉ!” አለ። ጆሮውንም ዳሶ ፈወሰው። 52 ከዚያም ኢየሱስ እሱን ለመያዝ የመጡትን የካህናት አለቆች፣ የቤተ መቅደሱን ሹሞችና ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ መጣችሁ?+ 53 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ አብሬያችሁ ሳለሁ+ እኔን ለመያዝ እጃችሁን አላነሳችሁብኝም።+ ይሁንና ይህ የእናንተ ሰዓትና ጨለማ የሚነግሥበት ሰዓት ነው።”+
54 ከዚያም ሰዎቹ ይዘው ወሰዱትና+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት አመጡት፤ ጴጥሮስም በርቀት ይከተል ነበር።+ 55 በግቢው መካከል እሳት አንድደው አንድ ላይ ተቀምጠው ሳለ ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ተቀመጠ።+ 56 ይሁንና አንዲት አገልጋይ እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሲሞቅ አየችውና ትኩር ብላ ከተመለከተችው በኋላ “ይህ ሰውም ከእሱ ጋር ነበር” አለች። 57 እሱ ግን “አንቺ ሴት፣ እኔ አላውቀውም” ሲል ካደ። 58 ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ ሰው አየውና “አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ አይደለሁም” አለ።+ 59 አንድ ሰዓት ያህል ካለፈ በኋላ ደግሞ አንድ ሌላ ሰው “ይህ ሰው፣ የገሊላ ሰው ስለሆነ በእርግጥ ከእሱ ጋር ነበር!” በማለት አጥብቆ ይናገር ጀመር። 60 ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ ምን እንደምታወራ አላውቅም” አለ። ገና እየተናገረም ሳለ ዶሮ ጮኸ። 61 በዚህ ጊዜ ጌታ ዞር ብሎ ጴጥሮስን ትክ ብሎ አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ የተናገረውን ቃል አስታወሰ።+ 62 ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።
63 ኢየሱስን የያዙት ሰዎችም እየመቱት+ ያሾፉበት+ ጀመር፤ 64 ፊቱንም ከሸፈኑት በኋላ “እስቲ ትንቢት ተናገር! የመታህ ማን ነው?” እያሉ ይጠይቁት ነበር። 65 በእሱም ላይ ሌላ ብዙ የስድብ ቃል ይሰነዝሩ ነበር።
66 በነጋም ጊዜ የካህናት አለቆችንና ጸሐፍትን ጨምሮ የሕዝቡ ሽማግሌዎች ጉባኤ አንድ ላይ ተሰበሰበ፤+ ኢየሱስንም ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ አዳራሻቸው አምጥተው እንዲህ አሉት፦ 67 “አንተ ክርስቶስ ከሆንክ ንገረን።”+ እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ብነግራችሁም እንኳ ፈጽሞ አታምኑም። 68 ብጠይቃችሁም አትመልሱም። 69 ያም ሆነ ይህ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ+ በኃያሉ አምላክ ቀኝ ይቀመጣል።”+ 70 በዚህ ጊዜ ሁሉም “ስለዚህ የአምላክ ልጅ ነህ ማለት ነው?” አሉት። እሱም “የአምላክ ልጅ መሆኔን እናንተው ራሳችሁ እየተናገራችሁ ነው” አላቸው። 71 እነሱም “ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ያስፈልገናል? እኛ ራሳችን ከገዛ አፉ ሰምተነዋል” አሉ።+
23 ስለዚህ በዚያ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች በሙሉ ተነስተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱት።+ 2 ከዚያም እንዲህ እያሉ ይከሱት ጀመር፦+ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያሳምፅ፣ ለቄሳር ግብር እንዳይከፈል ሲከለክልና+ ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ’+ ሲል አግኝተነዋል።” 3 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “አንተው ራስህ እኮ እየተናገርከው ነው” አለው።+ 4 ከዚያም ጲላጦስ ለካህናት አለቆቹና ለሕዝቡ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም” አለ።+ 5 እነሱ ግን “በመላው ይሁዳ፣ ከገሊላ አንስቶ እስከዚህ ድረስ እያስተማረ ሕዝቡን ይቀሰቅሳል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ። 6 ጲላጦስ ይህን ሲሰማ ሰውየው የገሊላ ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቀ። 7 ከሄሮድስ+ ግዛት የመጣ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ወደነበረው ወደ ሄሮድስ ላከው።
8 ሄሮድስ ኢየሱስን ሲያየው በጣም ደስ አለው። ስለ እሱ ብዙ ነገር ሰምቶ ስለነበር+ ለረጅም ጊዜ እሱን ለማየት ይፈልግ ነበር፤ አንዳንድ ተአምራት ሲፈጽም ለማየትም ተስፋ ያደርግ ነበር። 9 በመሆኑም ብዙ ጥያቄ ይጠይቀው ጀመር፤ እሱ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።+ 10 ይሁን እንጂ የካህናት አለቆቹና ጸሐፍት በተደጋጋሚ እየተነሱ አጥብቀው ይከሱት ነበር። 11 ከዚያም ሄሮድስ ከወታደሮቹ ጋር ሆኖ አቃለለው፤+ እንዲሁም ያማረ ልብስ አልብሶ ካፌዘበት+ በኋላ መልሶ ወደ ጲላጦስ ላከው። 12 በዚያን ዕለት ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ፤ ከዚያ በፊት በመካከላቸው ጠላትነት ነበር።
13 ከዚያም ጲላጦስ የካህናት አለቆቹን፣ ገዢዎቹንና ሕዝቡን በአንድነት ጠርቶ 14 እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁት ሕዝቡን ለዓመፅ ያነሳሳል ብላችሁ ነበር። ይኸው በፊታችሁ መረመርኩት፤ ሆኖም በእሱ ላይ ያቀረባችሁትን ክስ የሚደግፍ ምንም ነገር አላገኘሁም።+ 15 ሄሮድስም ቢሆን ምንም ጥፋት ስላላገኘበት ወደ እኛ መልሶ ልኮታል፤ በመሆኑም ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር አልፈጸመም። 16 ስለዚህ ቀጥቼ+ እፈታዋለሁ።” 17 *—— 18 ሕዝቡ ሁሉ ግን “ይህን ሰው ግደለው፤* በርባንን ግን ፍታልን!” እያሉ ጮኹ።+ 19 (ይህ ሰው በከተማው ውስጥ በተከሰተ የሕዝብ ዓመፅና በነፍስ ግድያ የታሰረ ነበር።) 20 ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታው ስለፈለገ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደገና ለሕዝቡ ተናገረ።+ 21 እነሱ ግን “ይሰቀል! ይሰቀል!”* እያሉ ይጮኹ ጀመር።+ 22 እሱም ለሦስተኛ ጊዜ “ለምን? ይህ ሰው ምን ያጠፋው ነገር አለ? ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ” አላቸው። 23 በዚህ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ኢየሱስ እንዲገደል* አጥብቀው ወተወቱት፤ ድምፃቸውም አየለ።+ 24 ስለዚህ ጲላጦስ የጠየቁት እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላለፈ። 25 ሕዝብ በማሳመፅና በነፍስ ግድያ ታስሮ የነበረውንና እንዲፈታላቸው የጠየቁትን ሰው ለቀቀው፤ ኢየሱስን ግን የፈለጉትን እንዲያደርጉበት አሳልፎ ሰጣቸው።
26 ይዘውትም እየሄዱ ሳሉ ከገጠር እየመጣ የነበረውን ስምዖን የተባለ አንድ የቀሬና ሰው ያዙትና የመከራውን እንጨት* አሸክመው ከኢየሱስ ኋላ እንዲሄድ አደረጉት።+ 27 ብዙ ሕዝብም ይከተለው ነበር፤ ከእነሱም መካከል በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ የሚያለቅሱለት ሴቶች ነበሩ። 28 ኢየሱስም ወደ ሴቶቹ ዞር ብሎ እንዲህ አለ፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፣ ለእኔ አታልቅሱ። ይልቁንስ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ፤+ 29 ሰዎች ‘መሃን የሆኑ ሴቶች፣ ያልወለዱ ማህፀኖችና ያላጠቡ ጡቶች ደስተኞች ናቸው!’+ የሚሉበት ቀን ይመጣልና። 30 በዚያን ጊዜ ተራሮችን ‘በላያችን ውደቁ!’ ኮረብቶችንም ‘ሸሽጉን!’ ይላሉ።+ 31 ዛፉ እርጥብ ሆኖ ሳለ እንዲህ ካደረጉ በደረቀ ጊዜማ ምን ይከሰት ይሆን?”
32 ወንጀለኞች የሆኑ ሌሎች ሁለት ሰዎችም ከእሱ ጋር ሊገደሉ እየተወሰዱ ነበር።+ 33 የራስ ቅል+ ወደተባለ ቦታ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስን በዚያ ከወንጀለኞቹ ጋር በእንጨት ላይ ቸነከሩት፤ ወንጀለኞቹም አንዱ በቀኙ ሌላው ደግሞ በግራው ተሰቅለው ነበር።+ 34 ኢየሱስም “አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው” ይል ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ልብሶቹን ለመከፋፈል ዕጣ ተጣጣሉ።+ 35 ሕዝቡም ቆሞ ይመለከት ነበር። የሃይማኖት መሪዎቹ ግን* “ሌሎችን አዳነ፤ የተመረጠው የአምላክ ክርስቶስ እሱ ከሆነ እስቲ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌዙበት ነበር።+ 36 ወታደሮቹ እንኳ ሳይቀሩ ወደ እሱ ቀርበው የኮመጠጠ የወይን ጠጅ በመስጠት+ አፌዙበት፤ 37 እንዲሁም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ከሆንክ ራስህን አድን” ይሉት ነበር። 38 በተጨማሪም ከበላዩ “ይህ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነው” የሚል ጽሑፍ ነበር።+
39 ከዚያም በዚያ ከተሰቀሉት ወንጀለኞች አንዱ “አንተ ክርስቶስ አይደለህም እንዴ? እስቲ ራስህንም እኛንም አድን!” እያለ ይዘልፈው+ ጀመር። 40 ሌላኛው ግን መልሶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፦ “አንተ ራስህ ተመሳሳይ ፍርድ ተቀብለህ እያለ ትንሽ እንኳ አምላክን አትፈራም? 41 እኛስ ላደረግነው ነገር የሚገባንን ቅጣት በሙሉ እየተቀበልን ስለሆነ በእኛ ላይ የተፈጸመው ፍርድ ተገቢ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም የሠራው ጥፋት የለም።” 42 ቀጥሎም “ኢየሱስ ሆይ፣ ወደ መንግሥትህ ስትመጣ አስበኝ” አለው።+ 43 እሱም “እውነት እልሃለሁ ዛሬ፣ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” አለው።+
44 ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ የነበረ ቢሆንም ምድሪቱ በሙሉ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በጨለማ ተሸፈነች፤+ 45 ይህም የሆነው የፀሐይ ብርሃን በመጥፋቱ ነው፤ ከዚያም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ+ መሃል ለመሃል ተቀደደ።+ 46 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ “አባት ሆይ፣ መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ”+ አለ። ይህን ካለ በኋላ ሞተ።*+ 47 መኮንኑም የተፈጸመውን ነገር በማየቱ “ይህ ሰው በእርግጥ ጻድቅ ነበር”+ በማለት ለአምላክ ክብር ይሰጥ ጀመር። 48 ይህን ለማየት በቦታው ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ሁሉ የተከሰቱትን ነገሮች ሲመለከቱ በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ወደ ቤታቸው ተመለሱ። 49 በቅርብ የሚያውቁትም ሁሉ በርቀት ቆመው ነበር። እንዲሁም ከገሊላ አንስቶ አብረውት የተጓዙት ሴቶች በዚያ ተገኝተው እነዚህን ነገሮች ይመለከቱ ነበር።+
50 እነሆም፣ የሸንጎ* አባል የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ጥሩና ጻድቅ ሰው ነበረ።+ 51 (ይህ ሰው ሴራቸውንና ድርጊታቸውን በመደገፍ ድምፅ አልሰጠም ነበር።) እሱም የአይሁዳውያን ከተማ የሆነችው የአርማትያስ ሰው ሲሆን የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር። 52 ይህም ሰው ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ። 53 አስከሬኑንም አውርዶ+ በበፍታ ገነዘው፤ ከዚያም ማንም ሰው ተቀብሮበት በማያውቅ ከዓለት ተፈልፍሎ በተሠራ መቃብር ውስጥ አኖረው።+ 54 ዕለቱ የዝግጅት ቀን ነበር፤+ ሰንበት+ የሚጀምርበት ጊዜም ተቃርቦ ነበር። 55 ከገሊላ ከኢየሱስ ጋር አብረው የመጡት ሴቶች ግን ተከትለው በመሄድ መቃብሩን አዩ፤ አስከሬኑም እንዴት እንዳረፈ ተመለከቱ።+ 56 ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞችና ዘይቶች ለማዘጋጀትም ተመልሰው ሄዱ። ሆኖም ሕጉ በሚያዘው መሠረት በሰንበት አረፉ።+
24 ይሁን እንጂ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ ያዘጋጇቸውን ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞች ይዘው ጠዋት በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄዱ።+ 2 ሆኖም ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፤+ 3 ወደ ውስጥ ሲገቡም የጌታ ኢየሱስን አስከሬን አላገኙም።+ 4 በሁኔታው ግራ ተጋብተው እያሉ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ። 5 ሴቶቹ ፈርተው ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ ሰዎቹ እንዲህ አሏቸው፦ “ሕያው የሆነውን ለምን ከሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ?+ 6 እሱ እዚህ የለም፤ ከሞት ተነስቷል። ገና በገሊላ በነበረበት ጊዜ ምን እንዳላችሁ አስታውሱ፤ 7 ‘የሰውን ልጅ ለኃጢአተኞች አሳልፈው ሊሰጡት፣ በእንጨት ላይ ሊሰቀልና በሦስተኛው ቀን ሊነሳ ይገባል’ ብሎ ነበር።”+ 8 በዚህ ጊዜ ሴቶቹ የተናገረውን ቃል አስታወሱ፤+ 9 ከዚያም መቃብሩ ካለበት ስፍራ ተመልሰው እነዚህን ነገሮች በሙሉ ለአሥራ አንዱና ለቀሩት ሁሉ ነገሯቸው።+ 10 እነሱም መግደላዊቷ ማርያም፣ ዮሐናና የያዕቆብ እናት ማርያም ነበሩ። ከእነሱ ጋር የነበሩት ሌሎቹ ሴቶችም እነዚህን ነገሮች ለሐዋርያት ነገሯቸው። 11 ይሁን እንጂ እንዲሁ የሚቀባጥሩ ስለመሰላቸው ሴቶቹ የሚናገሩትን አላመኗቸውም።
12 ጴጥሮስ ግን ተነስቶ ወደ መቃብሩ ሮጠ፤ ጎንበስ ብሎም ወደ ውስጥ ሲመለከት በፍታውን ብቻ አየ። በሆነውም ነገር እየተገረመ ከዚያ ሄደ።
13 ይሁንና በዚያው ቀን ከመካከላቸው ሁለቱ ከኢየሩሳሌም አሥራ አንድ ኪሎ ሜትር* ያህል ርቃ ወደምትገኝ ኤማሁስ ወደምትባል መንደር እየተጓዙ ነበር፤ 14 እነሱም ስለሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው እየተነጋገሩ ነበር።
15 ስለዚህ ጉዳይ እየተነጋገሩና እየተወያዩ ሳሉም ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ አብሯቸው መሄድ ጀመረ፤ 16 ሆኖም ማንነቱን እንዳይለዩ ዓይናቸው ተጋርዶ ነበር።+ 17 እሱም “እየተጓዛችሁ እንዲህ እርስ በርስ የምትወያዩበት ጉዳይ ምንድን ነው?” አላቸው። በዚህ ጊዜ በሐዘን እንደተዋጡ ባሉበት ቆሙ። 18 ቀለዮጳ የተባለውም መልሶ “በኢየሩሳሌም ውስጥ ለብቻህ የምትኖር እንግዳ ሰው ነህ እንዴ? ሰሞኑን በዚያ የተፈጸመውን ነገር አታውቅም ማለት ነው?”* አለው። 19 እሱም “ምን ተፈጸመ?” አላቸው። እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በአምላክና በሰው ሁሉ ፊት በሥራም ሆነ በቃል ኃያል ነቢይ ከሆነው ከናዝሬቱ ኢየሱስ+ ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ነገር ነዋ!+ 20 የካህናት አለቆቻችንና ገዢዎቻችን ለሞት ፍርድ አሳልፈው ሰጡት፤+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ቸነከሩት። 21 እኛ ግን ይህ ሰው እስራኤልን ነፃ ያወጣል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር።+ ከዚህም በላይ ይህ ነገር ከተፈጸመ እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ነው። 22 ደግሞም ከእኛው መካከል አንዳንድ ሴቶች በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄደው ስለነበር+ የሚያስገርም ነገር ነገሩን፤ 23 አስከሬኑንም ባጡ ጊዜ ተመልሰው መጥተው በተአምር የተገለጡላቸውንና እሱ ሕያው እንደሆነ የነገሯቸውን መላእክት እንዳዩ ነገሩን። 24 ከዚያም ከእኛ መካከል አንዳንዶች ወደ መቃብሩ ሄደው ነበር፤+ እነሱም ሴቶቹ እንደተናገሩት ሆኖ አገኙት፤ እሱን ግን አላዩትም።”
25 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁና ነቢያት የተናገሩትን ሁሉ ከማመን ልባችሁ የዘገየ! 26 ክርስቶስ እነዚህን መከራዎች መቀበልና+ ክብር ማግኘት አይገባውም?”+ 27 ከዚያም ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ+ ጀምሮ ስለ እሱ በቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን በሚገባ አብራራላቸው።
28 በመጨረሻም ወደሚሄዱበት መንደር ተቃረቡ፤ ይሁንና እሱ አልፎ የሚሄድ ይመስል ነበር። 29 እነሱ ግን “ቀኑ እየተገባደደና ምሽቱ እየተቃረበ ስለሆነ እኛ ጋ እደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት። እሱም እነሱ ጋ ለማደር ገባ። 30 ከእነሱ ጋር እየበላ ሳለም ዳቦውን አንስቶ ባረከ፤ ቆርሶም ይሰጣቸው ጀመር።+ 31 በዚህ ጊዜ ዓይናቸው ሙሉ በሙሉ ተከፈተና ማን መሆኑን በሚገባ አወቁ፤ እሱ ግን ከአጠገባቸው ተሰወረ።+ 32 እነሱም እርስ በርሳቸው “በመንገድ ላይ ሲያነጋግረንና ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ ሲገልጥልን* ልባችን እንደ እሳት ይቃጠልብን አልነበረም?” ተባባሉ። 33 በዚያኑም ሰዓት ተነስተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ አሥራ አንዱንና ከእነሱ ጋር የነበሩትንም አንድ ላይ ተሰብስበው አገኟቸው፤ 34 እነሱም “ጌታ በእርግጥ ተነስቷል፤ ለስምዖንም ተገልጦለታል!” ይሉ ነበር።+ 35 ሁለቱ ደግሞ በመንገድ ላይ ያጋጠማቸውን ነገርና ዳቦውን በቆረሰበት+ ጊዜ እንዴት እንዳወቁት ተረኩላቸው።
36 እነዚህን ነገሮች እየተነጋገሩ ሳለ እሱ ራሱ በመካከላቸው ቆመ፤ ከዚያም “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።+ 37 እነሱ ግን ከመደንገጣቸውና ከመፍራታቸው የተነሳ መንፈስ ያዩ መሰላቸው። 38 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ለምን ትረበሻላችሁ? ለምንስ በልባችሁ ውስጥ ጥርጣሬ ያድራል? 39 እኔ ራሴ መሆኔን እንድታውቁ እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ ደግሞም ዳስሳችሁኝ እዩ፤ መንፈስ በእኔ ላይ እንደምታዩት ሥጋና አጥንት የለውምና።” 40 ይህን እያለም እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። 41 እነሱ ግን በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ለማመን ተቸግረው በነገሩ እየተገረሙ ሳሉ “የሚበላ ነገር አላችሁ?” አላቸው። 42 እነሱም የተጠበሰ ቁራሽ ዓሣ ሰጡት፤ 43 እሱም ተቀብሎ በፊታቸው በላ።
44 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ‘በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙራት ስለ እኔ የተጻፉት ነገሮች ሁሉ+ መፈጸም አለባቸው’ ብዬ የነገርኳችሁ ቃሌ ይህ ነው።”+ 45 ከዚያም የቅዱሳን መጻሕፍትን ትርጉም መረዳት እንዲችሉ አእምሯቸውን ከፈተላቸው፤+ 46 እንዲህም አላቸው፦ “እንደሚከተለው ተብሎ ተጽፏል፤ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳል፤+ 47 በስሙም የኃጢአት ይቅርታ የሚያስገኝ+ ንስሐ ከኢየሩሳሌም አንስቶ+ ለብሔራት ሁሉ ይሰበካል።+ 48 እናንተም ለእነዚህ ነገሮች ምሥክር ትሆናላችሁ።+ 49 እኔም አባቴ ቃል የገባውን ነገር እልክላችኋለሁ። እናንተ ግን ከላይ የሚመጣውን ኃይል እስክትለብሱ+ ድረስ በከተማዋ ውስጥ ቆዩ።”
50 ከዚያም እስከ ቢታንያ ይዟቸው ሄደ፤ እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው። 51 እየባረካቸውም ሳለ ከእነሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ተወሰደ።+ 52 እነሱም ሰገዱለት፤* ከዚያም በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።+ 53 ዘወትር በቤተ መቅደስ እየተገኙም አምላክን ያወድሱ ነበር።+
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ልማዱ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “በእናቱ ማህፀን ውስጥ ካለበት ጊዜ ጀምሮ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች ለመመለስ።”
ወይም “ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “አምላክ የሚሳነው ነገር የለምና።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ሁለንተናዬ ይሖዋን ከፍ ከፍ ያደርገዋል።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ዝቅተኛ ኑሮ ያላት ሴት መሆኗን ያመለክታል።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ኃያል አዳኝ።” የቃላት መፍቻው ላይ “ቀንድ” የሚለውን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ይህ ቃል አራቱን የሌሊት ክፍለ ጊዜያት ያመለክታል። ማር 13:35 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ማህፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ክርስቶስን።”
ይኸውም በኩር ለሆነ ወንድ ልጅ።
ወይም “በነፍስሽም ውስጥ።”
ቃል በቃል “ከድንግልናዋ ጊዜ አንስቶ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ለማለፍ በዓል።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ይታዘዛቸው።”
ሄሮድስ አንቲጳስን ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “የአራተኛው ክፍል ገዢ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ሰውም።”
ወይም “አምላክ የሚያድንበትን መንገድ።”
ወይም “ትርፍ ልብስ።”
ወይም “አትሰብስቡ።”
ወይም “ማንንም አትንጠቁ።”
ወይም “ደሞዝ።”
እህልን ከገለባው ለመለየት የሚያገለግል ከእንጨት የሚሠራ እንደ አካፋ ያለ መሣሪያ ነው።
አንዳንድ በእጅ የተጻፉ ጥንታዊ ቅጂዎች “የዮሴ” ይላሉ።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “በጣሪያው ዙሪያ ያለ ግንብ፤ ጫፍ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “አልተፈወሰም።”
ወይም “አድነው።”
ገሊላ ባሕርን ያመለክታል።
ወይም “በሕይወት ያለን ሰው።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ሽባ የሆነ።”
ወይም “ሽባ የሆነበትን።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “ስማችሁን በሚያጥላሉበት።”
ወይም “ልታገኙ የምትችሉትን ነገር።”
ያለወለድ ማበደርን ያመለክታል።
ወይም “መፍረዳችሁን ተዉ።”
ወይም “በነፃ ልቀቁ።”
ወይም “በነፃ ትለቀቃላችሁ።”
ወይም “ደቀ መዝሙር።”
ወይም “መቶ አለቃ።”
ወይም “ለስላሳ ልብስ።”
ወይም “መመሪያ።”
ወይም “ትክክል።”
ወይም “በውጤቷ።”
ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ታላቅ።”
“ለረጅም ጊዜ ይዞት ነበር” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ገደላማ ከሆነው የባሕሩ ዳርቻ።”
ወይም “የሕይወት ኃይል።”
ቃል በቃል “ብር።” ብር ከተባለው ማዕድን የተሠራ ገንዘብ።
ወይም “ትርፍ ልብስ።”
የእግርን አቧራ ማራገፍ ከኃላፊነት ነፃ መሆንን ያመለክታል።
ቃል በቃል “የአራተኛው ክፍል።”
ሄሮድስ አንቲጳስን ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ክርስቶስ ነህ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሱን።”
ወይም “ነፍሱን።”
ቃል በቃል “ቀኖቹ ሲሞሉ።”
ቃል በቃል “ፊቱን እንዳቀና።”
በእጅ የተጻፉ አንዳንድ ጥንታዊ ቅጂዎች “ሰባ ሁለት” ይላሉ።
ወይም “ማንንም እያቀፋችሁ ሰላም አትበሉ።”
የፍርድን ቀን ያመለክታል።
እነዚህ የአይሁዳውያን ከተሞች አልነበሩም።
ወይም “ሐዲስ።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
“ባልንጀራ” ተብሎ የተተረጎመው ግሪክኛ ቃል የአንድን ሰው የቅርብ ጓደኛ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ሰው ሊያመለክት ይችላል።
ለ14ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ቃሉን።”
ወይም “የተሻለውን ድርሻ።”
ወይም “በቅድስና ይያዝ።”
ቃል በቃል “ዳቧችንን።”
ቃል በቃል “ዕዳ ያለባቸውን።”
ለሰይጣን የተሰጠ ስያሜ ነው።
እንደ ስንዴ ያሉ የእህል ዓይነቶችን ለመስፈር የሚያገለግል ዕቃ።
ወይም “አጥርቶ የሚያይ ሲሆን።” ቃል በቃል “ቀላል ሲሆን።”
ወይም “በብርሃን የተሞላ።”
ቃል በቃል “መጥፎ፤ ክፉ።”
ሃይማኖታዊ ሥርዓትን በተከተለ መንገድ አለመንጻቱን ያመለክታል።
ቃል በቃል “የምሕረት ስጦታ።” ወይም “ለድሆች ስጦታ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “የተሻለውን መቀመጫ መያዝ።”
ወይም “ምንም ምልክት የሌለው።”
ይህ አባባል የአዳምንና የሔዋንን ዘሮች ያመለክታል።
ወይም “የፈሰሰው የነቢያት ደም ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል።”
ወይም “በቤተ መቅደሱ።”
ወይም “ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “በሁለት አሳሪዮን።” ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ችላ አትባልም።”
“በምኩራቦች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ከመጎምጀትም።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍስህን።”
ወይም “ነፍሳችሁ።”
ወይም “መጨነቃችሁን ተዉ።”
ወይም “ነፍስ።”
ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ከልክ በላይ ማሰብ አቁሙ፤ መጨነቃችሁንም ተዉ።”
ቃል በቃል “የምሕረት ስጦታ።” ወይም “ለድሆች ስጦታ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ይህ አባባል ለሥራ መዘጋጀትን ያመለክታል።
ወይም “ከታጠቀና።”
ሁለተኛው ክፍለ ሌሊት፣ ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ አንስቶ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ነው።
ሦስተኛው ክፍለ ሌሊት፣ ከእኩለ ሌሊት እስከ ሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ ድረስ ነው።
ወይም “በቤቱ ሠራተኞች።”
ወይም “ጥበበኛ።”
ወይም “የቤት አስተዳዳሪ።”
ወይም “ለሁለት ይቆርጠዋል።”
ወይም “ከጌታው ፈቃድ ጋር የሚስማማ ነገር ያላደረገው።”
ቃል በቃል “የመጨረሻዋን ሌፕተን።” ለ14ን ተመልከት።
ወይም “በዚያም ለ18 ዓመት የሚያሽመደምድ መንፈስ ያደረባት።”
ቃል በቃል “የሲህ መስፈሪያ።” አንድ ሲህ 7.33 ሊትር ነው። ለ14ን ተመልከት።
ወይም “መገደሉ የማይታሰብ ነገር ስለሆነ።”
ቤተ መቅደሱን ያመለክታል።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
በሰውነት ውስጥ ከልክ በላይ ፈሳሽ እንዲጠራቀም የሚያደርግ በሽታ ነው።
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “አሳንሶ የማይወድ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ይህ ቃል አንድን ገዢ ወይም አገር በመወከል ቃል አቀባይ ሆኖ የሚያገለግልን ሰው ያመለክታል።
ወይም “የማይተው።”
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ሴቶች ጓደኞቿንና ጎረቤቶቿን።”
ለ14ን ተመልከት።
ወይም “የንዝህላልነት።”
ቃል በቃል “በሰማይና።”
ቃል በቃል “የበላው።”
ወይም “የቤት አስተዳዳሪ።”
አንድ የባዶስ መስፈሪያ 22 ሊትር ነው። ለ14ን ተመልከት።
አንድ የቆሮስ መስፈሪያ 220 ሊትር (170 ኪሎ ግራም ገደማ ስንዴ) ነው። ለ14ን ተመልከት።
ወይም “በብልሃት፤ በልባምነት።”
ወይም “የዚህ ዘመን።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
እንዲህ ዓይነት ቀለም ያለው ልብስ ከሀብት፣ ከክብርና ከሥልጣን ጋር የተያያዘ ነበር።
በአይሁዳውያን ዘንድ ውሻ ርኩስ እንስሳ እንደሆነ ተደርጎ ይታይ ነበር።
ልዩ ሞገስ ማግኘትን ያመለክታል።
ወይም “በሐዲስም።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ማቴ 24:17 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ነፍሱን።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ3ን ተመልከት።
ወይም “ነዝንዛ ትገድለኛለች።”
ወይም “እንዲህ ያለ እምነት።”
ወይም “ምሕረት አድርግልኝ።”
ወይም “በሚመጣው ዘመን።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “በሐሰት ክስ ከሰው የቀማሁትንም።”
አንድ የግሪክ ምናን 340 ግራም የሚመዝን ሲሆን ወደ 100 ድራክማ የሚጠጋ ዋጋ አለው። ለ14ን ተመልከት።
ወይም “መንግሥቱን።”
ቃል በቃል “ብር።” ብር ከተባለው ማዕድን የተሠራ ገንዘብ።
ቃል በቃል “ብሬን።” ብር ከተባለው ማዕድን የተሠራ ገንዘብ።
ገንዘብ ተቀብለው የሚያስቀምጡና የሚያበድሩ ሰዎች።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ከሰማይ።”
ወይም “አቃለው።”
ቃል በቃል “የማዕዘኑ ራስ።”
ቃል በቃል “ለአገረ ገዢው ሥልጣን።”
ወይም “ትክክል ነው ወይስ አይደለም?”
ለ14ን ተመልከት።
ወይም “የዚህ ዘመን።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ከእሱ አመለካከት አንጻር።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “በምኩራብ የተሻለውን መቀመጫ።”
ወይም “ንብረት።”
ወይም “ማሳበቢያ እንዲሆናቸውም።”
ወይም “ይበልጥ ከባድ የሆነ።”
ወይም “ዕቃዎቹ።”
ቃል በቃል “ሁለት ሌፕተን።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ረብሻ፤ ዓመፅ።”
ወይም “ይከዷችኋል።”
ወይም “ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ።”
ወይም “የበቀል ቀን።”
ወይም “የብሔራት።”
ወይም “በብሔራት።”
በጳለስጢና ምድር ዕፀዋት የሚለመልሙት በበጋ ነው።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ብር ከተባለው ማዕድን የተሠራ ገንዘብ።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ3ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ይህን አስወግደው።”
ወይም “እንጨት ላይ ይሰቀል! እንጨት ላይ ይሰቀል!”
ወይም “በእንጨት ላይ እንዲሰቀል።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ገዢዎቹ ግን።”
ወይም “እስትንፋሱ ቆመ።”
ወይም “የሳንሄድሪን።”
ቃል በቃል “60 ስታዲዮን።” አንድ ስታዲዮን 185 ሜትር ነው። ለ14ን ተመልከት።
“ሰሞኑን በኢየሩሳሌም የተፈጸሙትን ነገሮች የማታውቅ እንግዳ አንተ ብቻ ነህ?” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በግልጽ ሲያብራራልን።”
ወይም “እጅ ነሱት።”