የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g96 10/8 ገጽ 32
  • ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?
  • ንቁ!—1996
ንቁ!—1996
g96 10/8 ገጽ 32

ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?

ይህ አሳሳቢ ጥያቄ የይሖዋ ምሥክሮች የሚያሠራጩት የአንድ ትራክት ርዕስ ነው። ባለፈው ዓመት በሚሲሲፒ ዩ ኤስ ኤ የምትኖር አንዲት ሴት “አንድ ወጣት ሰው ይህን ጥያቄ ባቀረበልኝ ጊዜ ምን መልስ እንደምሰጥ ግራ ገብቶኝ ነበር” ስትል ጽፋለች። “ዓለም አምላክ በሚፈልገው መንገድ በመመራት ላይ እንዳልሆነ ይሰማኝ ነበር” ብላለች።

በመቀጠልም “በዚህ ትራክት ውስጥ ከቀረቡት ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረውን ሙሉ በሙሉ እንደማላውቅ ለመገንዘብ ችዬአለሁ። በገና በዓል ከምንዘምራቸው መዝሙሮች አንዱ የሆነው ‘ደስታ ለዓለም ይሁን’ የሚለው መዝሙር እግዚአብሔር ዓለምን እንደሚገዛ ይናገራል። ይህ ግን እውነቱን እንዳናስተውል የሚያደርግ ነው” ብላለች።

ይህች ሴት ደብዳቤዋን ስትደመድም “ይህን ዓይነት ደብዳቤ የመጻፍ ልማድ እንኳን አልነበረኝም። ይሁን እንጂ ቢያንስ በእኔ በኩል ሥራችሁ አድናቆት እንዳተረፈላችሁ ላረጋግጥላችሁ ስለፈለግኩ ነው” ብላለች።

የይሖዋ ምሥክሮች ከሕይወታችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላላቸው ጉዳዮች መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሰዎች እንዲያውቁ ጥረት ያደርጋሉ። ከላይ የተጠቀሰውን ትራክት ለማግኘት ወይም በነጻ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲደረግልዎ ከፈለጉ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም በገጽ 5 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ