“ማበረታቻና ተስፋ ያስፈልገኛል”
አንተም እንዲህ ተሰምቶህ ያውቃል? በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች እንደዚህ ይሰማቸዋል። በአርካንሳስ ክፍለ ሀገር በፎርት ስሚዝ ከተማ የምትኖር አንዲት ሴት ብሩክሊን ኒው ዮርክ ወደሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ዓለም አቀፍ ዋና መሥሪያ ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ እንዲህ ብላለች:-
“ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለው መጽሐፋችሁ ትምህርታዊ ቁም ነገር የያዘና መንፈስን የሚያነቃቃ ነው። መጽሐፉን በሁለት ቀናት ውስጥ ከዳር እስከ ዳር አንብቤ ጨረስኩ። በኢየሱስ ክርስቶስ አመራር አማካኝነት ቃል የተገባው አዲሱ ሥርዓት በቅርቡ እንደሚመጣ ተስፋ ሰጥቶኛል። ያንን ቀን ለማየት እጓጓለሁ።
“እስከዚያው ድረስ ግን በዚህ ዓለም ውስጥ በሕይወት ለመቆየት እየታገልሁ ተስፋው እስኪፈጸም እጠባበቃለሁ። ይህ አሰልቺና ምንም የሚስብ ነገር የሌለበት ዓለም ተስፋ ያስቆርጠኛል። ማበረታቻና ተስፋ ያስፈልገኛል። ፍላጎት ያላቸው ሁሉ በድርጅታችሁ አማካኝነት በነፃ መጽሐፍ ቅዱስን ሊማሩ እንደሚችሉ ገልጻችኋል። ይህን ለማግኘት ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ልትገልጹልኝ ትችላላችሁ? ይህ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያበረታታኛል ብዬ አስባለሁ።”
ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ለማግኘት ወይም እቤትዎ መጥቶ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምርዎት ሰው የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም ገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች ወደሚቀርብዎ ይጻፉ።