የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g02 6/8 ገጽ 32
  • የሚመለከታቸው ሰው ነበረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሚመለከታቸው ሰው ነበረ
  • ንቁ!—2002
ንቁ!—2002
g02 6/8 ገጽ 32

የሚመለከታቸው ሰው ነበረ

በኦሃዮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በአንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ሁለት ወጣቶች ቁርስ ለመብላት ወደ አንድ ምግብ ቤት ጎራ ይላሉ። ቁርሳቸውን ከመብላታቸው በፊት እንደ ልማዳቸው ሁለቱም ጎንበስ ብለው ድምፃቸውን ሳያሰሙ ጸለዩ።

ብዙም ሳይቆይ ትመለከታቸው የነበረች አንዲት ሴት ወደ ጠረጴዛቸው መጣችና ሒሳቡን የሚከፍሉበትን ደረሰኝ አንስታ እንዲህ አለቻቸው:- “በጊዜያችን ስላሉት ወጣቶች በርካታ መጥፎ ነገሮች በምንሰማበት ዓለም ውስጥ ሁለት ወጣቶች ጊዜ ወስደው ለቀረበላቸው ምግብ አምላክን ሲያመሰግኑ መመልከት በጣም የሚያስደስት ነው። ቁርሳችሁን የተመገባችሁበትን ሒሳብ እኔ መክፈል እፈልጋለሁ።”

ልጆቹ በከፍተኛ የመገረም ስሜት ቢዋጡም ሴትዮዋን ሳያመሰግኗት አላለፉም። በኋላ ግን የጸለዩት እንዲያው ለማንኛውም አምላክ እንዳልሆነ ሊነግሯት ፈለጉ። ስለዚህ ከወጣቶቹ አንዱ ሴትዮዋ ወደ ተቀመጠችበት ቦታ ሄደና በድጋሚ ካመሰገናት በኋላ የይሖዋ ምሥክሮች መሆናቸውን ነገራት።

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማጥናት ልማድ አላቸው። የእነዚህ ወጣቶች ወላጆችም እንደዚህ አድርገዋል። እነዚህ ቤተሰቦች ካጠኗቸው መጻሕፍት አንዱ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለው መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ካሉት 19 ምዕራፎች መካከል “ከአምላክ ጋር መቀራረብ የምትችለው እንዴት ነው?” የሚል ርዕስ ያለው ስለ ጸሎት የሚናገር ምዕራፍ ይገኝበታል።

ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዳውን ይህን ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት ትችላለህ።

□ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ