በቤተ ክርስቲያን ምድር ቤት የተገኘ ውድ ሀብት
ባለፈው ዓመት በኒው ዮርክ ዩ ኤስ ኤ የምትኖር አንዲት ሴት በቤተ ክርስቲያን ምድር ቤት ውስጥ አንድ ትልቅ ሃብት እንዳገኘች ሪፖርት አድርጋ ነበር። “ለሚመለከተው ሁሉ” ብላ በላከችው ደብዳቤ ላይ እንዲህ አለች:- “በአቅራቢያችን ባለው ቤተ ክርስቲያን ምድር ቤት ውስጥ ይህን ትንሽ መጽሐፍ አገኘሁና ወደ ቤቴ ይዤው ሄድኩ። ርዕሱ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የሚል ነው።”
በመቀጠልም ሴትዮዋ እንዲህ አለች:- “አሁን መጽሐፉን በድጋሚ አንብቤ ለመጨረስ የቀሩኝ አራት ምዕራፎች ብቻ ናቸው። መጽሐፉን በጣም ስለወደድኩት የያዘውን ሐሳብ ሙሉ በሙሉ መረዳት እችል ዘንድ ረጋ ብዬ ለሁለተኛ ጊዜ ማንበብ ጀመርኩ። ከመጽሐፉ ያገኘሁት እውቀት እስከ ዛሬ ድረስ በቤተ ክርስቲያን ከተማርኩት ይበልጣል። እንዲሁም ከዚህ በፊት የማላውቃቸውን አዳዲስ ነገሮች ማወቅ ችያለሁ። ይህን ዓይነት ሌሎች ትናንሽ መጻሕፍት ቢኖሩኝ ደስ ይለኛል።”
ሴትዮዋ ያገኘችው መጽሐፍ ከ20 ዓመታት በፊት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ ሲሆን በ112 ቋንቋዎች ከ81 ሚልዮን ቅጂዎች በላይ ታትሟል። ይህን መጽሐፍ ወይም የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? እና አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባሉትን የመጽሐፉን መልእክት ጠቅለል አድርገው የያዙ ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማዘዝ ይችላሉ።
የመጽሐፉን ወይም የእነዚህን ብሮሹሮች አንድ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።
□ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? እና አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባሉትን ብሮሹሮች ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።