የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g04 2/8 ገጽ 32
  • ‘ትንሽ ቢሆንም ብዙ እውቀት ይዟል’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ትንሽ ቢሆንም ብዙ እውቀት ይዟል’
  • ንቁ!—2004
ንቁ!—2004
g04 2/8 ገጽ 32

‘ትንሽ ቢሆንም ብዙ እውቀት ይዟል’

አንዲት ሴት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘውን ብሮሹር የገለጸችው ከላይ ባለው መንገድ ነበር። እንደዚህ ያለ አስተያየት ለመስጠት የተነሳሳችበትን ምክንያት ስትናገር እንዲህ ብላለች:- “ግሎሪያ የተባሉ አንዲት አረጋዊት ሴት ይህንን ብሮሹር ማጥናታቸው መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ፍላጎታቸውን አነሳስቶታል። ቀደም ሲል ትኩረታቸውን አሰባስበው መቀመጥ ያስቸግራቸው የነበረ ሲሆን አሁን ግን በአንድ ጊዜ ለሁለት ሰዓት ያህል ማጥናት ችለዋል። ከጥናቱ አስቀድመው ትምህርቱን የሚዘጋጁ ከመሆኑም በላይ ጥቅሶቹን በሙሉ አውጥተው ያነብባሉ።”

አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር 32 ገጾች ያሉት ሲሆን መጠኑ ይህንን መጽሔት ያክላል። ብሮሹሩ አምላክ ለሰው ዘር ያለው ዓላማ ምን እንደሆነ በግልጽ ያሳያል እንዲሁም የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን ይናገራል። በብሮሹሩ ላይ ከሚገኙት አስደሳች ትምህርቶች መካከል “እውነተኛው አምላክ ማን ነው?፣” “ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?፣” “አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?” እንዲሁም “የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?” የሚሉት አንዳንዶቹ ናቸው።

ይህን ብሮሹር ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ