የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g05 12/8 ገጽ 32
  • የክፍል ጓደኞቿ አመለካከት ተቀየረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የክፍል ጓደኞቿ አመለካከት ተቀየረ
  • ንቁ!—2005
ንቁ!—2005
g05 12/8 ገጽ 32

የክፍል ጓደኞቿ አመለካከት ተቀየረ

◼ በዩክሬን የምትኖር ቪክቶሪያ የተባለች የ11 ዓመት ልጅ (ከላይ የምትታየው) በጣም የምትወደውን መጽሐፍ የክፍል ጓደኞቿ ሁሉ ለማንበብ እንዲጓጉ በሚያደርግ መንገድ ሪፖርት እንድታቀርብ ተነገራት። እንዲህ ብላለች:- “ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የሚለውን መጽሐፍ ለክፍል ጓደኞቼ ለማስተዋወቅ ወሰንኩ። ንግግሬን በማቀርብበት ጊዜ የመጽሐፉን አጠቃላይ ይዘትና በየትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ እንደተመሠረተ አብራራሁ። በመጨረሻም የትምህርት ክፍለ ጊዜው ሲያልቅ መጽሐፉን መውሰድ እንደሚችሉ ገለጽኩላቸው።”

የክፍል ጓደኞቿ ምን ስሜት አደረባቸው? ቪክቶሪያ በመቀጠል እንዲህ ብላለች:- “በዚያን ቀን 20 መጽሐፎችን አበረከትኩ። የክፍል ጓደኞቼ የይሖዋ ምሥክሮች መናፍቃን እንደሆኑ ይሰማቸው ነበር። አሁን ግን አመለካከታቸው ተቀይሯል፤ እንዲያውም ሁለት የመጽሔት ደንበኞች አግኝቻለሁ!”

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የሚለው መጽሐፍ ግሩም የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት የወጣቶችን አስተሳሰብና ስሜት በጥልቅ ይመረምራል። “ወላጆቼ ተጨማሪ ነፃነት እንዲሰጡኝ ለማድረግ የምችለው እንዴት ነው?”፣ “እውነተኛ ጓደኞች ላፈራ የምችለው እንዴት ነው?”፣ “ከጋብቻ በፊት የጾታ ግንኙነት ቢፈጸም ምናለበት?” ለሚሉትና ወጣቶች ለሚያነሷቸው ሌሎች ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣል። መጽሐፉ ባካተታቸው 39 ምዕራፎች ውስጥ ሌሎች ብዙ ርዕሰ ጉዳዮችም ይብራራሉ።

ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የሚለውን መጽሐፍ ማግኘት እፈልጋለሁ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ