የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 6/13 ገጽ 12-13
  • ፓናማን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፓናማን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2013
ንቁ!—2013
g 6/13 ገጽ 12-13

አገሮችና ሕዝቦች

ፓናማን እንጎብኝ

[በገጽ 12 ላይ የሚገኝ ካርታ]

ፓናማ ይበልጥ የምትታወቀው የአትላንቲክና የፓስፊክ ውቅያኖሶችን የሚያገናኝ የባሕር መተላለፊያ ቦይ ያላት በመሆኑ ሳይሆን አይቀርም። ፓናማ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካን የምታገናኝ እንደመሆኗ መጠን ውቅያኖሶቹን ብቻ ሳይሆን ሕዝቦችንም ታገናኛለች። የበርካታ ዘርና ባሕሎች መናኸሪያ ነች። አብዛኞቹ ዜጎቿ ጥንታዊ የአገሬው ተወላጆችና የአውሮፓውያን ድብልቅ ናቸው።

ይህን ታውቅ ነበር? የፓናማው ወርቃማ እንቁራሪት (አቴሎፐስ ዜቴኪ) ተጓዳኙን ለመማረክና ተፎካካሪዎቹን ለማስፈራራት የፊት እግሮቹን ሰላምታ የሚሰጥ በሚመስል መንገድ ያወዛውዛል

ከስፔን የመጡ አገር አሳሾች በ1501 ፓናማ ሲደርሱ የአገሬው ተወላጅ የሆኑ በርካታ ጥንታዊ ማኅበረሰቦችን ያገኙ ሲሆን አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል ቀደም ሲል ኩና ተብለው ይጠሩ የነበሩት ጉናዎች ይገኙበታል። ብዙዎቹ ጉናዎች የሚኖሩት በሳን ብላስ ደሴቶች እንዲሁም በፓናማና በኮሎምቢያ ወሰን አቅራቢያ በሚገኘው የፓስፊክ ጠረፍ አካባቢ ነው። ጉናዎች አደን የሚወጡ ከመሆኑም ሌላ ከግንድ በተፈለፈሉ ታንኳዎች ታግዘው ዓሣ ያጠምዳሉ፤ እንዲሁም ለቀለብ የሚሆን እህል ያመርታሉ።

በጉና ማኅበረሰብ አንድ ወንድ ሚስት ሲያገባ የሚስቱን ቤተሰቦች በሥራ እያገዘ አብሯቸው ይኖራል። ሚስቱ ሴት ልጅ በምትወልድበት ጊዜ ግን ቤተሰቡን ይዞ ከአማቶቹ በመለየት የራሱን ቤት ማስተዳደር ይችላል።

በፓናማ 300 የሚያክሉ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች ይገኛሉ። ከስፓንኛ በተጨማሪ በቻይንኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በጉጃራቲ፣ በጉና፣ በሄይቲኛ ክሪኦል፣ በንጋቤሬ እንዲሁም በፓናማ የምልክት ቋንቋ ስብሰባዎች ይመራሉ።

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 3,629,000

  • ዋና ከተማ፦ ፓናማ ሲቲ

  • የሥራ ቋንቋ፦ ስፓንኛ

  • መንግሥቱ የሚመራው፦ ሕገ መንግሥታዊ ዲሞክራሲ

  • የአየር ንብረት፦ ሞቃታማ

  • መልክዓ ምድር፦ በደን የተሸፈኑ ነፋሻማ ተራሮች፣ የሣር ምድር እና እርጥበት አዘል አየር ያለባቸው ጥቅጥቅ ያሉ ጫካዎች። በሁለቱም አቅጣጫዎች ባሉት ውቅያኖሶች ላይ ከ1,600 የሚበልጡ ደሴቶች ተሰበጣጥረው ይገኛሉ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ