ውሳኔ
ጥሩ ውሳኔ ማድረግ እንድንችል አእምሯችንን እና ልባችንን ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?
መዝ 1:1-3፤ ምሳሌ 19:20፤ ሮም 14:13፤ 1ቆሮ 10:6-11
በተጨማሪም ዕዝራ 7:10ን ተመልከት
ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ውሳኔ ስናደርግ መቸኮል የሌለብን ለምንድን ነው?
ውሳኔ ስናደርግ ፍጹም ያልሆነውን ልባችንን መስማት የሌለብን ለምንድን ነው?
በተጨማሪም ዘኁ 15:39፤ ምሳሌ 14:12፤ መክ 11:9, 10ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
2ዜና 35:20-24—ጥሩው ንጉሥ ኢዮስያስ ከይሖዋ የመጣን ምክር ችላ ብሎ ከፈርዖን ኒካዑ ጋር ጦርነት ገጠመ
ከባድ ውሳኔ ስናደርግ መጸለያችን ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ሉቃስ 6:12-16—ኢየሱስ 12ቱን ሐዋርያት ከመምረጡ በፊት ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልይ አድሯል
2ነገ 19:10-20, 35—ንጉሥ ሕዝቅያስ ከአቅሙ በላይ የሆነ ጠላት ሲገጥመው ወደ ይሖዋ ጸልዮአል፤ ይሖዋም ታድጎታል
ውሳኔ ስናደርግ ከሁሉ የተሻለውን መመሪያ የምናገኘው ከማን ነው? ውሳኔ ለማድረግ የሚረዳንስ እንዴት ነው?
መዝ 119:105፤ ምሳሌ 3:5, 6፤ 2ጢሞ 3:16, 17
በተጨማሪም መዝ 19:7፤ ምሳሌ 6:23፤ ኢሳ 51:4ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ሥራ 15:13-18—በኢየሩሳሌም የሚገኘው የበላይ አካል ውሳኔ የሚጠይቅ ከባድ ሁኔታ ሲያጋጥመው መመሪያ ለማግኘት ቅዱሳን መጻሕፍትን አመሣክሯል
ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮች፦
ሁሉም የሕይወት ጉዳዮች
ሕክምና
ዘሌ 19:26፤ ዘዳ 12:16, 23፤ ሉቃስ 5:31፤ ሥራ 15:28, 29
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ሥራ 19:18-20—የኤፌሶን ክርስቲያኖች ከአስማትና ከመናፍስታዊ ድርጊቶች ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ እንዲኖራቸው አልፈለጉም
መንፈሳዊ ግቦች
መዝናኛ
“መዝናኛ” የሚለውን ተመልከት
ሥራ
“ሥራ” የሚለውን ተመልከት
ትዳር
“ትዳር” የሚለውን ተመልከት
የጊዜ አጠቃቀም
የጎለመሱ የአምላክ አገልጋዮች ውሳኔ ስናደርግ ሊረዱን የሚችሉት እንዴት ነው?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
1ነገ 1:11-31, 51-53—ቤርሳቤህ፣ ነቢዩ ናታን የሰጣትን ምክር ሰምታለች፤ ይህም የራሷንም ሆነ የልጇን የሰለሞንን ሕይወት አትርፎላቸዋል
ሌሎች በእኛ ቦታ ውሳኔ እንዲያደርጉልን መጠየቅ የሌለብን ለምንድን ነው?
የአምላክን ምክር አቅልለን ከመመልከት ይልቅ ተግባራዊ ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?
በተጨማሪም ሉቃስ 7:30ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘፍ 19:12-14, 24, 25—ሎጥ ለልጆቹ እጮኞች ጥፋት እየመጣ መሆኑን አስጠነቀቃቸው፤ እነሱ ግን አልሰሙትም
2ነገ 17:5-17—እስራኤላውያን የይሖዋን ምክር በተደጋጋሚ ችላ በማለት በክፉ ድርጊታቸው ስለገፉበት በግዞት ተወስደዋል
ውሳኔ ስናደርግ ሕሊናችን የሚለንን መስማት ያለብን ለምንድን ነው?
ውሳኔያችን የኋላ ኋላ የሚኖረውን ውጤት አስቀድመን ማሰባችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?
በሌሎች ላይ የሚኖረው ውጤት
በወደፊት ሕይወታችን ላይ የሚኖረው ውጤት
በተጨማሪም ምሳሌ 2:20, 21፤ 5:3-5ን ተመልከት