ጥሩነት
ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?
በተጨማሪም ኤር 31:12, 13፤ ዘካ 9:16, 17ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘፀ 33:17-20፤ 34:5-7—ይሖዋ ለነቢዩ ሙሴ ጥሩነቱን በራእይ አሳይቶታል፤ ሌሎች ማራኪ ባሕርያቱንም ገልጦለታል
ማር 10:17, 18—ኢየሱስ፣ ለጥሩነቱ እውቅና ሊሰጠው የሚገባው ይሖዋ ብቻ እንደሆነ ተናግሯል፤ ምክንያቱም ይሖዋ የጥሩ ነገሮች ሁሉ ምንጭ ከመሆኑም ሌላ ጥሩ የሆነውን ነገር በተመለከተ መሥፈርት የማውጣት መብት ያለው እሱ ነው