የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 16-17
  • ሐዘን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሐዘን
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 16-17

ሐዘን

መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ሲሞትብን ማዘን ምንም ስህተት እንደሌለበት የሚያሳየው እንዴት ነው?

ዘፍ 23:2፤ 24:67፤ 37:34, 35፤ 42:36፤ ዮሐ 11:19, 31, 33-36

በተጨማሪም 2ሳሙ 1:17-27፤ ሥራ 9:36-39⁠ን ተመልከት

ይሖዋ ሐዘን የደረሰባቸውን ሰዎች ማጽናናት እንደሚፈልግ የሚያሳየው ምንድን ነው?

መዝ 34:18፤ ኢሳ 57:15፤ 61:1, 2

የሞቱ ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ማወቃችን የሚያጽናናን እንዴት ነው?

መክ 9:5, 10፤ 1ተሰ 4:13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 20:37, 38—ትንሣኤ በእርግጠኝነት የሚፈጸም ተስፋ ከመሆኑ የተነሳ የሞቱ ሰዎች በአምላክ ዓይን አሁንም ሕያው የሆኑ ያህል እንደሆነ ኢየሱስ ተናግሯል

    • ዮሐ 11:5, 6, 11-14—ኢየሱስ የቅርብ ወዳጁ አልዓዛር በሞተበት ወቅት ሞትን ከእንቅልፍ ጋር አመሳስሎታል

    • ዕብ 2:14, 15—ሐዋርያው ጳውሎስ የሞት ፍርሃት ባሪያ ሊያደርገን እንደማይገባ ተናግሯል

አንድ ሰው በሕይወቱ ከሚያተርፈው ስም አንጻር ከልደት ቀኑ ይልቅ የሞተበት ቀን የሚሻለው እንዴት ነው?

ምሳሌ 22:1፤ መክ 7:1, 2

መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን ምን ብሎ ይገልጸዋል? አምላክ ሞትን ምን ያደርገዋል?

ኢሳ 25:8፤ 1ቆሮ 15:26፤ ራእይ 20:14፤ 21:3, 4

ወደፊት ትንሣኤ እንደሚኖር እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?

ኢሳ 26:19፤ ዮሐ 5:28, 29፤ ሥራ 24:15

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዘጠኝ ትንሣኤዎች ተጠቅሰዋል፤ ስምንቱ ከሞት ተነስተው የኖሩት ምድር ላይ ነው። እያንዳንዱ ዘገባ ሐዘን ለደረሰባቸው ሰዎች መጽናኛና ተስፋ ይሰጣል

      • 1ነገ 17:17-24—ነቢዩ ኤልያስ በሲዶና ከተማ፣ በሰራፕታ መንደር የምትኖርን የአንዲት መበለት ልጅ አስነሳ

      • 2ነገ 4:32-37—ነቢዩ ኤልሳዕ በሹነም፣ አንድን ልጅ ከሞት አስነስቶ ለወላጆቹ ሰጣቸው

      • 2ነገ 13:20, 21—ከሞተ ብዙም ያልቆየ የአንድ ሰው አስከሬን የነቢዩ ኤልሳዕን አፅም እንደነካ ሰውየው ሕያው ሆነ

      • ሉቃስ 7:11-15—በናይን ከተማ ኢየሱስ ለቀብር የሚሄዱ ሰዎችን አስቁሞ የአንዲትን መበለት ልጅ አስነሳ

      • ሉቃስ 8:41, 42, 49-56—ኢየሱስ የምኩራብ አለቃ የሆነውን የኢያኢሮስን ሴት ልጅ ከሞት አስነሳ

      • ዮሐ 11:38-44—ኢየሱስ የቅርብ ወዳጁን አልዓዛርን ከሞት አስነሳው፤ ከእህቶቹ ከማርታና ከማርያም ጋርም አገናኘው

      • ሥራ 9:36-42—ሐዋርያው ጴጥሮስ በደግነቷ በጉባኤው ውስጥ ተወዳጅ የነበረችውን ዶርቃን ከሞት አስነሳት

      • ሥራ 20:7-12—ሐዋርያው ጳውሎስ ከመስኮት ወድቆ የሞተውን አውጤኪስ የተባለ ወጣት ከሞት አስነሳው

    • ኢየሱስ ክርስቶስ የማይሞት መንፈሳዊ አካል ይዞ ከሞት ተነስቷል፤ ይህም ተስፋችን ሁሉ እንደሚፈጸም ዋስትና ይሆናል

      • ሥራ 17:31፤ 1ጴጥ 3:18

    • ኢየሱስ ትንሣኤ አግኝቶ ወደ ሰማይ ለመሄድና የማይሞት መንፈሳዊ አካል ለማግኘት የመጀመሪያው ነው፤ ሆኖም የመጨረሻው አይደለም፤ 144,000 ቅቡዓን ተከታዮቹም ተመሳሳይ ትንሣኤ ያገኛሉ

      • 1ቆሮ 15:20, 23, 51-53፤ 1ተሰ 4:16, 17፤ ራእይ 14:1

የሚወዱትን ሰው በሞት አጥተው በሐዘን የተደቆሱትን ማጽናናት የምንችለው እንዴት ነው?

ሮም 12:15፤ 2ቆሮ 1:3, 4፤ 1ጴጥ 3:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ