የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 107-108
  • ጥበብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥበብ
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 107-108

ጥበብ

እውነተኛ ጥበብ ለማግኘት የግድ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምንድን ነው?

ምሳሌ 9:10፤ 15:33

እውነተኛ ጥበብ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

ምሳሌ 2:6፤ መክ 2:26፤ ኤር 8:9፤ 2ጢሞ 3:15

ጥበብ እንዲሰጠን ወደ አምላክ መጸለይ ተገቢ ነው?

ቆላ 1:9፤ ያዕ 1:5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 1:8-12—ወጣቱ ንጉሥ ሰለሞን፣ የእስራኤልን ብሔር ጥሩ አድርጎ ለማስተዳደር የሚያስችል ጥበብ እንዲሰጠው ጸልዮአል፤ ይሖዋም በጠየቀው ነገር ስለተደሰተ ጥበብን ሰጥቶታል

    • ምሳሌ 2:1-5—ጥበብ፣ ማስተዋልና ጥልቅ ግንዛቤ ልንፈልገው ከሚገባ የተሸሸገ ሀብት ጋር ተመሳስለዋል፤ ይሖዋ ይህንን ውድ ሀብት ተግተው የሚፈልጉ ሰዎችን ይባርካቸዋል

ይሖዋ ጥበብ የሚሰጠን በማን በኩል እና በምን አማካኝነት ነው?

ኢሳ 11:2፤ 1ቆሮ 1:24, 30፤ 2:13፤ ኤፌ 1:17፤ ቆላ 2:2, 3

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 8:1-3, 22-31—ጥበብ በሰውኛ ዘይቤ ተገልጻለች፤ ለጥበብ የተሰጠው መግለጫ የፍጥረታት በኩር የሆነውን የአምላክ ልጅ ያመለክታል

    • ማቴ 13:51-54—ከኢየሱስ አድማጮች ብዙዎቹ ኢየሱስ በእነሱ መካከል አድጎ እንዲህ ያለ ታላቅ ጥበብ ከየት ሊያገኝ እንደቻለ ግራ ገብቷቸዋል

የአምላካዊ ጥበብ አንዳንድ መገለጫዎች ምንድን ናቸው?

መዝ 111:10፤ መክ 8:1፤ ያዕ 3:13-17

በተጨማሪም መዝ 107:43፤ ምሳሌ 1:1-5⁠ን ተመልከት

ጥበብ ለሕይወታችን መሪና ጠባቂ የሚሆንልን እንዴት ነው?

ምሳሌ 2:10-13፤ 3:21-23፤ 4:5-7

በተጨማሪም ምሳሌ 7:2-5፤ መክ 7:12⁠ን ተመልከት

ከአምላክ የሚገኘው ጥበብ ምን ያህል ውድ ነው?

ምሳሌ 3:13, 14፤ 8:11

በተጨማሪም ኢዮብ 28:18⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 28:12, 15-19—ኢዮብ ሐዘን፣ ሥቃይና መከራ ውስጥ በነበረበት ጊዜም እንኳ መለኮታዊ ጥበብ ያለውን የላቀ ዋጋ በአድናቆት ተናግሯል

    • መዝ 19:7-9—ንጉሥ ዳዊት፣ የይሖዋ ሕግና ማሳሰቢያ ተሞክሮ የሌለውን እንኳ ጥበበኛ እንደሚያደርግ ገልጿል

አምላክን ከግምት የማያስገባው ዓለማዊ ጥበብ ለጉዳት የሚዳርገን እንዴት ነው?

1ቆሮ 1:19, 20፤ 3:19፤ ቆላ 2:8፤ 1ጢሞ 6:20

በተጨማሪም መክ 12:11, 12፤ ሮም 1:22, 23⁠ን ተመልከት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ