የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 4/1 ገጽ 30
  • ፖለቲካ​—የወንጌሉ ሥራ ክፍል ነውን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፖለቲካ​—የወንጌሉ ሥራ ክፍል ነውን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 4/1 ገጽ 30

ፖለቲካ​—የወንጌሉ ሥራ ክፍል ነውን?

የኮሎኝ ጳጳስና ታዋቂ የምሥራቅ ጀርመን ቄስ የነበሩት ጆአኪም ሜንሰር “ፖለቲካን ቆሻሻ፣ የአንድን ሰው እጆች የሚያሳድፍ ጉዳይ ብሎ መጥራቱ መናፍቅነት ነው” ብለው ገልጸዋል። በ1989 በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ብለው ነበር፦ “ፖለቲካ ከሕይወታችን የማይነጣጠል እውነታ ነው፣ ስለዚህም የወንጌላዊነት ሥራችን ክፍል መሆን ይገባዋል። ትግል ውስጥ ገብተን ለመወጣት መነሳት አለብን። ገንቢ በሆነ መንገድ በሁሉም የፖለቲካ ተቋም፣ ከሠራተኛ ማኅበራት ጀምሮ እስከ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድረስ መግባት ይኖርብናል። በእነዚህ እንቅስቃሴዎችና ፓርቲዎች ውስጥ በመግባት ግለሰቦች የጀርመንንና የአውሮፓን ፖለቲካ ለማራመድ የመሪነቱን ቦታ እንዲይዙ ክርስቲያናዊ ኃይል መፍጠር ይኖርብናል።”

በጀርመን ከሚታተሙት ዋነኛ ጋዜጦች አንዱ የሆነው ፍራንክፈርተር አልገማይን ሳይቱንግ የተወሰዱት የሚከተሉት አንቀጾች ካቶሊክና ፕሮቴስታንት የሆኑ ብዙ የአውሮፓ ቄሶች የሜይንሰር ዓይነት አመለካከት እንዳላቸው ያሳያሉ።

“ከተመረጡ ከስድስት ቀናት ብቻ በኋላ [ጥቅምት 1978] እርሳቸው [ጳጳሱ] ምሥራቅ አውሮፓዊ እንደመሆናቸው በአውሮፓ ያለውን ሁኔታ ለመቀበል ዕቅድ እንደሌላቸው ገልጸዋል። . . . አንዳንዶች እንደ ስብከት አድርገው ወሰዱት፤ ሆኖም ነገሩ የፖለቲካ ፕሮግራም ነበር።”​—ኅዳር 1989

“በአንዳንድ ቦታዎች [በቼኮዝሎቫኪያ] ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ ዓመፅ ቀዳሚ በመሆን ከፍተኛውን ቦታ ይዛለች። በሰሜናዊ የቦሄሚያ ካቴድራል ከተማ በሌቶሜሪስ ለካህናት በሚሰጥ ሃይማኖታዊ ሰሚናር ላይ የሚካፈሉ ተማሪዎች . . . ባለፈው ኅዳር የተደረገውን ደም ያልተፋሰሰበት ዓመፅ መርተዋል።”​—መጋቢት 1990

“ለአሥራ ዓመታት በየሳምንቱ የሰላም ጸሎት ሲደረግበት የነበረው የኒኮላይ [የፕሮቴስታንት] ቤተክርስቲያን ምንም ያህል ትኩረት አልሳበም ነበር፤ በዚህ ዓመት ግን በድንገት በጀርመን ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ውስጥ ለሰላማዊው አብዮት እንቅስቃሴ አርማ ሆኖአል። . . . ብዛት ያላቸው ቄሶችና የጉባኤ ምዕመናን ከዚያ በኋላ በተደረጉት ሰልፎች ላይ ያለማቋረጥ ተካፍለዋል።”​—ታህሣሥ 1989

ጳጳስ ሜይስነር በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ ላይ እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል፦ “ክርስቲያን ፖለቲከኞች ከሰማይ እንዲመጡልን ልንጠብቅ አንችልም። . . . ወጣት ክርስቲያኖች በፖለቲካ ሕይወት ውስጥ እንዲገቡ ከማበረታታት፣ ወይም ታዋቂ የሆኑ ዜጎችን፦ ምርጫ በሚደረግበት ጊዜ ሳትሳተፉበት ማለፍ የለበትም ብዬ ከመንገር በፍጹም አልታክትም።”

በዚህ መሠረት ለምሥራቅ ጀርመን ቮልስካመር (ፓርላማ) በ1990 ከተመረጡት ውስጥ 19 አባሎች ቄሶች ነበሩ። ሃይማኖት በካቢኔው ውስጥ የሰላማዊ ለውጥ እንቅስቃሴ አባል ስለሆኑት የመከላከያ ሚኒስትር ራይነር ኤፕልማን ናሳውር ታግብላት የተባለው ጋዜጣ እንዲህ ሲል ጽፎአል፦ “ብዙ ሰዎች ለሰላማዊ አብዮት አባቶች ከሆኑት አንዱ እንደሆኑ አድርገው ይቆጥሩአቸዋል።”

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በምሥራቅ አውሮፓ የሚገኙ የይሖዋ ምስክሮች አሁን ባገኙት ሰፊ ሃይማኖታዊ ነፃነት ይደሰታሉ። ይሁን እንጂ ይህንን ነፃነት በፖለቲካዊ ወይም በማኅበራዊ ውዝግቦች ውስጥ ጣልቃ ለመግባት አይጠቀሙበትም። በማቴዎስ 24:14 ላይ ከተገለጸው የወንጌል ስብከት ሥራ ጋር በመስማማት የአምላክ መንግሥት የሰው ዘር ብቸኛ ተስፋ መሆኗን በቅንዓት እየሰበኩ ከሰብዓዊ ፖለቲካ ስለ መራቅ ኢየሱስ የተወላቸውን ምሳሌ ይከተላሉ። በምሥራቅ አውሮፓም ሆነ በሌላ ቦታ የሚገኙት የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት ተመሳሳይ አቋም ቢይዙ ይበጃቸዋል።​—ዮሐንስ 6:15፤ 17:16፤ 18:36፤ ያዕቆብ 4:4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ