የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 10/1 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ሕያው የሆነው አምላክ የሚሰጠውን መመሪያ ተከተል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ንዑሳን የደም ክፍልፋዮችና የቀዶ ሕክምና ሂደቶች
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 10/1 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

ከሰው ደም ውስጥ የተወሰደ አልቡሚን ያለበትን ክትባት ወይም ሌላ በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት መውሰድ ተገቢ ነውን?

እንደ እውነቱ ከሆነ ይህን በተመለከተ እያንዳንዱ ክርስቲያን በግሉ መወሰን አለበት።

የአምላክ አገልጋዮች ከደም ራቁ የሚለውን በሥራ 15:28, 29 ላይ የሚገኘውን መመሪያ መታዘዝ ይፈልጋሉ፤ ይህም ተገቢ ነው። በዚህም መሠረት ክርስቲያኖች ደሙ ከውስጡ ያልፈሰሰ ሥጋ ወይም ደም ተጨምሮባቸው የሚዘጋጁ ምግቦችን አይበሉም። ይሁን እንጂ የአምላክ ሕግ በሕክምናውም መስክ ቢሆን ይሠራል። የይሖዋ ምሥክሮች መላውን ደምም ሆነ ቀይ የደም ሴል፣ ነጭ የደም ሴል፣ ፕሌትሌት ወይም የደም ፕላዝማ እንደማይወስዱ የሚገልጽ ሰነድ ይዘው ይሄዳሉ። ሆኖም ጥቃቅን የደም ፕሮቲኖችን የያዙ በመርፌ የሚሰጡ መድኃኒቶችን በተመለከተስ አቋማቸው ምንድን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች ይህ ጉዳይ እያንዳንዱ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ከሠለጠነ ሕሊናው ጋር በሚስማማ መንገድ የሚያደርገው የግል ውሳኔ እንደሆነ ቀደም ብለው ተገንዝበዋል። ይህ ጉዳይ አንድ ሰው ለአንዳንድ በሽታዎች ቢጋለጥና አንድ ሐኪም በመርፌ የሚሰጡ መድኃኒቶችን ቢያዝ ስለሚያጋጥመው ሁኔታ በሚያብራራው በ11–111 መጠበቂያ ግንብ የአንባብያን ጥያቄዎች ላይ ወጥቷል። እንዲህ ያሉት በመርፌ የሚሰጡ መድኃኒቶች የሚቀመሙት ከደም ፕላዝማ ከራሱ ሳይሆን በሽታውን የመከላከል ኃይል ካዳበረ ሰው ወይም ሌላ እንስሳ ከተወሰደ የደም ፕላዝማ ከሚገኙ ፀረ እንግዳ አካሎች (አንቲቦዲስ) ነው። እንደነዚህ ያሉትን በመርፌ የሚሰጡ መድኃኒቶች በጥሩ ሕሊና መቀበል እንደሚችሉ የሚሰማቸው አንዳንድ ክርስቲያኖች በአንዲት እርጉዝ ሴት ደም ውስጥ ያሉት ፀረ እንግዳ አካሎች (አንቲቦዲስ) በማኅፀኗ ውስጥ ወዳለው ሕፃን ደም እንደሚገቡ ተረድተዋል። “የአንባብያን ጥያቄዎች” ይህንን እንዲሁም የተወሰነ አልቡሚን ከአንዲት እርጉዝ ሴት በማኅፀኗ ውስጥ ወደሚገኘው ሕፃን እንደሚያልፍ ጠቅሷል።

ከደም የማይዘጋጁ አንዳንድ ክትባቶች በሚቀመሙበት ጊዜ የሚጨመሩት ቅመሞች እንዳይበላሹ ሲባል በአንፃራዊ ሁኔታ ሲታይ አነስተኛ መጠን ያለው የፕላዝማ አልቡሚን ስለሚጨመር ብዙዎች ይህ ጉዳይ እዚህ ላይ አግባብነት ያለው ሆኖ አግኝተውታል። በአሁኑ ጊዜ ኢፒኦ (ኤሪትሮፖየቲን) የተባለው ሰው ሠራሽ ሆርሞን በመርፌ በሚሰጥበት ጊዜ ጭምር አነስተኛ መጠን ያለው አልቡሚን ይጨመራል። የቀይ ደም ሴልን መባዛት ሊያፋጥን ስለሚችል አንዳንድ ምሥክሮች ኢፒኦ የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት ተቀብለዋል። ይህም ደም መስጠት ሊያስፈልግ ይችል ይሆናል ብሎ የሚሰጋውን ሐኪም ከጭንቀት ሊያሳርፈው ይችላል።

የመድኃኒት መቀመሚያ ድርጅቶች አዳዲስ መድኃኒቶችን እየሠሩ አለዚያም ቀድሞ የነበሩት መድኃኒቶች ይሠሩበት የነበረውን አሠራር እየለወጡ ስለሆኑ ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ መጠን ያለውን አልቡሚን ጨምሮ ሌሎች የሕክምና መድኃኒቶች ወደፊት በጥቅም ላይ ይውሉ ይሆናል። ስለሆነም ክርስቲያኖች አንድ ሐኪም የሚያዘው ክትባትም ሆነ ሌላ ዓይነት በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት አልቡሚን እንዳለውና እንደሌለው ማጣራት ሊፈልጉ ይችላሉ። ጥርጣሬ ካላቸው ወይም አልቡሚን መድኃኒቱ የተቀመመበት አንዱ ክፍል መሆኑን ለማመን የሚያስችላቸው ምክንያት ካገኙ ሐኪማቸውን መጠየቅ ይችላሉ።

ከላይ እንደተገለጸው ብዙ ምሥክሮች አነስተኛ መጠን ያለው አልቡሚን ያለበትን በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት መቀበልን አይቃወሙም። ሆኖም ግን የግል ውሳኔ ከማድረጉ በፊት ስለ ጉዳዩ ለማጣራት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በ11–111 መጠበቂያ ግንብ ላይ “የአንባብያን ጥያቄዎች” በሚለው አምድ ሥር የቀረበውን ሐሳብ እንደገና መከለስ ይኖርበታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ