የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 11/15 ገጽ 3-4
  • ሙታን ሊያዩን ይችላሉን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሙታን ሊያዩን ይችላሉን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሞቱ አያት፣ ቅድመ አያቶቻችን ያሉት የት ነው?
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ አግኝተኸዋል?
  • ሙታን የት ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • አንድ ባላባት የወደፊት ዕጣቸውን መረመሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የቀድሞ አባቶችን ማምለክ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 11/15 ገጽ 3-4

ሙታን ሊያዩን ይችላሉን?

አንዲት ሴት ባሏን ትገድላለች። ከዚያም ከሰባት ዓመት በኋላ በጣም የሚያስፈራ ሕልም አየች። ይህ ሕልም የሞተው ባሏ መቆጣቱን የሚያመለክት እንደሆነ አድርጋ አሰበች። የባሏን “መንፈስ” ቁጣ ለማብረድ ሴት ልጅዋን መቃብሩ ላይ የመጠጥ መሥዋዕት እንድታቀርብ ትልካታለች።

መሥዋዕቱ የተላከው አባቷን ከገደለችው እናቷ ስለሆነ ልጅቷ ለአባቷ መንፈስ ምን እንደምትለው ግራ ይገባታል። ወንድሟ ተደብቆ የምታደርገውን ያይ ነበር። ከዚያም ከተደበቀበት ወጥቶ ይመጣና እሱና እኅቱ ሆነው ገዳዩን እንዲበቀሉለት እንዲረዳቸው ወደ አባታቸው ጸለዩ።

ይህ ሁኔታ ከ2,400 ዓመት በፊት ከተጻፈ የመጠጥ መሥዋዕት አቅራቢዎች ከተባለ አንድ የግሪክ ቲያትር የተወሰደ ነው። በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች በተለይም በአፍሪካ በዛሬውም ጊዜ ቢሆን በመቃብር አጠገብ ተመሳሳይ የሆነ መሥዋዕት ይቀርባል።

ለምሳሌ ያህል በናይጄሪያ የሚኖረውን የአይቢን ተሞክሮ ተመልከት። አይቢ ሦስት ልጆቹን በሞት ስላጣ በአካባቢው ወደሚገኝ አንድ ጠንቋይ ይሄድና ሁኔታውን ያማክራል። ጠንቋዩም የአይቢ ልጆች የሞቱት ያለ ምክንያት እንዳልሆነ ይኸውም ቀደም ሲል ሞቶ የነበረው የአይቢ አባት የቀብሩ ሥርዓት በተገቢው መንገድ ባለመፈጸሙ ስለተቆጣ እንደሆነ ይነግረዋል።

አይቢ የአካባቢው ጠንቋይ የሰጠውን ምክር በመከተል በአባቱ መቃብር ላይ የፍየል፣ የአረቄና የወይን ጠጅ መሥዋዕት አቀረበ። ይቅርታ እንዲያደርግለት በመለመን፣ እንደሚወደው በመግለጽና እንዲባርከው በመጠየቅ የአባቱን መንፈስ ጠራ።

አይቢ አባቱ ሊያየውና ሊሰማው እንደሚችል ምንም ጥርጥር አልነበረውም። አባቱ ምንም የማይሰማ በድን እንደሆነ አያምንም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ሲሞት ከሚታየው ዓለም ወደማይታየው ዓለም “እንደተሸጋገረ” ያምናል። አይቢ አባቱ ሥጋና ደም ያለው ሰው ከሚኖርበት ዓለም የቀድሞ አባቶች ወደሚኖሩበት መንፈሳዊ ዓለም እንደተለወጠ ያምናል።

አይቢ እንዲህ እያለ ያስባል፦ ‘አባባ ምንም እንኳን በዚህ ዓለም ላይ ባይኖርም አሁንም ቢሆን እኔን አይረሳኝም፤ እንዲሁም ስለ ደህንነቴ ያስባል። አሁን ከበፊቱ የተሻለ ኃይል ያለው መንፈስ ስለሆነ ሰው ሆኖ በምድር ላይ ይኖር ከነበረበት ጊዜ በበለጠ ሊረዳኝ ይችላል። ከሁሉም በላይ ደግሞ አምላክም መንፈስ ስለሆነ አምላክን ስለ እኔ በቀጥታ ሊያነጋግረው ይችላል። አባባ አሁን በጣም ተናድዶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ተገቢውን አክብሮት ካሳየሁት ይቅርታ ያደርግልኝና ይባርከኛል።’

በአፍሪካ ውስጥ ሙታን በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያያሉ፤ እንዲሁም በሕይወታቸው ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚለው እምነት ባሕላዊ ሃይማኖት በሚከተሉ ሰዎች ዘንድ በጣም ተስፋፍቷል። ክርስቲያኖች በሚባሉትም ዘንድ ይህ እምነት አለ። ለምሳሌ ያህል አንዲት ሴት በቤተ ክርስቲያን ካገባች በኋላ ባሕላዊ ምርቃት ለመቀበል ወደ ወላጆቿ ቤት መሄዷ የተለመደ ነገር ነው። እዚያም ለቀድሞ አባቶች ልመና ይቀርባል፤ እንዲሁም የመጠጥ መሥዋዕት ይፈስላቸዋል። ይህን አለማድረግ በጋብቻው ላይ መጥፎ ነገር ያስከትላል ብለው ብዙዎች ያምናሉ።

የቀድሞ አባቶች ወይም የእነሱ መንፈስ በምድር ላይ ያሉትን ቤተሰቦቻቸውን ከጥፋት እንዲድኑና እንዲበለጽጉ ይረዳሉ ተብሎ ይታመናል። በዚህ አመለካከት መሠረት እነዚህ የቀድሞ አባቶች አዝመራው ጥሩ እንዲሆን፣ የቤተሰባቸው ደህንነት እንዲጠበቅና ሰዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ማድረግ ይችላሉ። ለሰዎች አማላጅ ይሆናሉ። ችላ ካሏቸው ወይም ካስቀየሟቸው ግን መቅሰፍት ያመጣሉ። በሽታ፣ ድህነት አልፎ ተርፎም ሞት ሊያመጡ ይችላሉ ተብሎ ይታመናል። ስለሆነም ሰዎች መሥዋዕት በማቅረብና አንዳንድ የአምልኮ ሥርዓቶችን በማከናወን ሁልጊዜ ከሙታን ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ይጥራሉ።

ሙታን በሕይወት በሚኖሩ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ይህን ያህል ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ብለህ ታምናለህን? በምታፈቅረው ሰው መቃብር አጠገብ ቆመህ እሱ ወይም እሷ ምናልባት ይሰማኝ ወይም ትሰማኝ ይሆናል ብለህ በማሰብ ጥቂት ቃላትን ተናግረህ ታውቃለህን? ሙታን የሚያዩንና የሚሰሙን መሆን አለመሆናቸው የተመካው ሲሞቱ በሚሆነው ሁኔታ ላይ ነው። ስለዚህ አስፈላጊ ርዕሰ ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እስቲ እንመርምር።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ