የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 8/1 ገጽ 3-4
  • ጊዜው ተለውጧል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጊዜው ተለውጧል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰለሞን ጠቢብ ንጉሥ ነበር
    መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
  • ጥሩ አርዓያም የማስጠንቀቂያ ምሳሌም ሊሆነን የሚችል ሰው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ድህነትን ለማስወገድ የተደረጉ ጥረቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • እርዳታ ለማግኘት የሚጮኹትን የሚታደገው ማነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 8/1 ገጽ 3-4

ጊዜው ተለውጧል

በጥንቷ እስራኤል በታማኙ ንጉሥ ሰሎሞን አስደሳች ግዛት ሥር መኖር እንዴት ልብን በደስታ የሚያሞቅ ነበር! የሰላም፣ የብልጽግናና የደስታ ዘመን ነበር። ሰሎሞን በታማኝነት ከእውነተኛ አምልኮ ጎን በቆመበት ወቅት ይሖዋ ሕዝቡን አትረፍርፎ ባርኮታል። አምላክ ለንጉሥ ሰሎሞን ትልቅ ሀብት ብቻ ሳይሆን በጽድቅና በፍቅር መግዛት እንዲችል “ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና” ሰጥቶታል። (1 ነገሥት 3:12) መጽሐፍ ቅዱስ “የምድርም ነገሥታት ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበቡን ይሰሙ ዘንድ የሰሎሞንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር” በማለት ይተርካል።—2 ዜና መዋዕል 9:23

ይሖዋ ለሕዝቡ ደህንነትን፣ ሰላምንና የተትረፈረፉ መልካም ነገሮችን ሰጥቷል። የአምላክ ቃል “ይሁዳና እስራኤልም እንደ ባሕር አሸዋ ብዛት ብዙ ነበሩ፤ በልተውም ጠጥተውም ደስ ብሎአቸው ነበር” በማለት ይናገራል። ቃል በቃልም ይሁን በምሳሌያዊ ሁኔታ ሕዝቡ “ከወይኑና ከበለሱ በታች ተዘልሎ ይቀመጥ ነበር።”—1 ነገሥት 4:20, 25

ጊዜው ተለውጧል። በአሁኑ ጊዜ ያለው ኑሮ በጥንት ጊዜ ከነበረው አስደሳች ሕይወት ፈጽሞ የተለየ ነው። በሰሎሞን ዘመን ከነበረው ሁኔታ በተለየ መንገድ በጊዜአችን ያለው ዋነኛ ችግር ድህነት ነው። ሀብታም በሚባሉ አገሮችም እንኳን ድህነት አለ። ለምሳሌ በዩናይትድ ስቴትስና የጋራ ገበያ በፈጠሩት የአውሮፓ አገሮች 15 በመቶ የሚሆኑት ኑሯቸውን የሚገፉት በድህነት እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ገልጿል።

የዓለምን ገጽታ በተመለከተ ዩኒሴፍ (የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት) ዘ ስቴት ኦቭ ዘ ዎርልድስ ችልድረን 1994 በሚል ባቀረበው ሪፖርት ላይ የዓለም አንድ አምስተኛ ሕዝብ ኑሮውን የሚገፋው በድህነት ተቆራምዶ እንደሆነ ገልጾ ኑሮው በዓለም የሚኖሩ ድሀ ሰዎች ሕይወት “ይበልጥ አስቸጋሪና ተስፋ የሚያስቆርጥ” ሆኖባቸዋል በማለት ዘግቧል።

በአንዳንድ አገሮች የዕቃ ዋጋ መናር ድሀ ሰዎችን የባሰ አዘቅጥ ውስጥ ጨምሯቸዋል። በአንድ የአፍሪካ አገር የምትኖር አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “በገበያ አንድ ነገር ትመለከታላችሁ፣ ከዚያም ‘እቤት ሄጄ ገንዘብ ላምጣና እገዛዋለሁ’ ትላላችሁ። እቤት ደርሳችሁ ከአንድ ሰዓት በኋላ ስትመለሱ ቀደም ሲል ያያችሁትን ነገር ልትገዙ እንደማትችሉ ይነገራችኋል። ምክንያቱም ዋጋው ወዲያው ጨምሮ ይጠብቃችኋል። በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ሊያደርገው የሚችለው ነገር ምንድን ነው? በጣም የሚያበሳጭ ነው።”

ሌላዋም ሴት ‘ሕይወታችንን ለማቆየት ስንል ከምግብ በስተቀር አስፈላጊ የሆኑ ሌሎቹን ነገሮች ከአእምሯችን እናወጣቸዋለን። አሁን በጣም የሚያሳስበን ነገር ምግብ እንዴት ማግኘት እንደምንችል ነው’ በማለት ተናግራለች።

እንደ ተባበሩት መንግሥታት አገላለጽ የወደፊቱ ጊዜ የጨለመ ይመስላል። ለምሳሌ በአሁኑ ጊዜ ያለው የሕዝብ ብዛት ጭማሪ በዚሁ ከቀጠለ በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ድሀ ሰዎች ቁጥር “በአንድ ሰው ዕድሜ ውስጥ” በአራት እጥፍ እንደሚያድግ ዩኒሴፍ ገምቷል።

ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ የሚሄዱ የኢኮኖሚና ማኀበራዊ ችግሮች ቢኖሩም የአምላክ አገልጋዮች የወደፊቱን ጊዜ ይበልጥ ብሩህ በሆነ ተስፋ የሚመለከቱበት ምክንያት አላቸው። ምንም እንኳ የወደፊቱ ጊዜ ተስፋ አስቆራጭ በሆነባቸው ሰዎች መካከል ቢኖሩም የአምላክ አገልጋዮች የወደፊቱን ጊዜ በደስታና በልበ ሙሉነት ይጠባበቃሉ። የሚቀጥለው ርዕስ ይህ የሆነበትን ምክንያት ያብራራል።

[ምንጭ]

De Grunne/Sipa Press

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ