የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 3/1 ገጽ 32
  • ዓለምን የሚቆጣጠረው ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዓለምን የሚቆጣጠረው ማን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 3/1 ገጽ 32

ዓለምን የሚቆጣጠረው ማን ነው?

“ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?” አንድ ሰው ይህን ጥያቄ ቢያቀርብልህ ምን ብለህ ትመልሳለህ? አብዛኞቹ ሃይማኖታውያን ሰዎች “አምላክ” ወይም “ኢየሱስ” ነው ብለው ይመልሱ ይሆናል። ዘ ፍሪፖርት ኒውስ በተሰኘው በባሃሚያን ቋንቋ በሚታተመው ጋዜጣ ላይ የወጣ አንድ አምድ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚያውቁት መልስ ይዞ ነበር።

“አንዲት ትራክት ደጃፌ ላይ ተቀምጣ አገኘሁ” በማለት የአምዱ ጸሐፊ ትጀምራለች። “አብዛኛውን ጊዜ በደጃፍ ላይ የሚቀመጡ ጽሑፎችን አንስቼ አላነብም ነበር። በዚህ ጊዜ ግን ለማንበብ ወሰንኩ። ዋናው ርዕስ ‘ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?’ የሚል ጥያቄ ያቀርባል።” ይህች ሴት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ማብራሪያ የያዘውን ትራክት በማንበቧ ይህን ዓለም የሚገዛው አምላክ ወይም ኢየሱስ ሳይሆን ሰይጣን ዲያብሎስ መሆኑን ተገነዘበች።​— ዮሐንስ 12:​31፤ 14:​30፤ 16:​11፤ 1 ዮሐንስ 5:​19

“ያላንዳች አዘኔታ የሚፈጸሙትን እጅግ የሚሰቀጥጡ የጭካኔ ድርጊቶች ይመልከቱ” በማለት ትራክቱ ያብራራል። “ሰዎች ያለምንም ርኅራኄ እርስ በርሳቸው ለመገዳደልና ለመተራረድ በመርዘኛ ጋዞች የተሞሉ ክፍሎችን፣ የማጎሪያ ካምፖችን፣ እሳት የሚተፉ መሣሪያዎችን፣ የናፓልም ቦምቦችንና ሌሎች እጅግ የሚዘገንኑ መሣሪያዎችን ይጠቀማሉ። . . . ሰዎች እንዲህ ያሉ የሚቀፉ ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ የሚገፋፏቸው ወይም የሚሰቀጥጡ ሁኔታዎችን እንድፈጽም አስገድደውኛል ወደሚሏቸው መጥፎ ሁኔታዎች የሚከቷቸው ኃይሎች እነማን ናቸው? ሰዎች እንዲህ ያሉ የዓመፅ ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ የሚገፋፋቸው አንድ ክፉ የሆነ በዓይን የማይታይ ኃይል ይኖር ይሆናል ብለው አስበው ያውቃሉን?” መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣንን “የዚህ ዓለም አምላክ” ብሎ መጥራቱ የሚያስደንቅ ነውን?​— 2 ቆሮንቶስ 4:​4

የሚያስደስተው ግን ሰይጣንና አጋንንቱ የሚጠፉበት ጊዜ ቀርቧል። “ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።” (1 ዮሐንስ 2:​17) አዎን፣ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉ ሁሉ ጽድቅ በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ ለዘላለም የመኖር ተስፋ እንደሚኖራቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጣል። (መዝሙር 37:​9-11፤ 2 ጴጥሮስ 3:​13፤ ራእይ 21:​3, 4) ሰይጣንና አጋንንቱ የሚያሳድሩት ክፉ ተጽዕኖ ሁሉ ሲወገድ እንዴት ያለ ግልግል ይሆናል!

ዘ ፍሪፖርት ኒውስ የተባለው ጋዜጣ ጸሐፊ የዚህን ትንሽ ትራክት ይዘት ባጭሩ ከገለጸች በኋላ አምዱን እንዲህ በማለት ደመደመች:- “የዓለም ሁኔታና ዓለምን የሚቆጣጠረው ማን ስለመሆኑ ከሚያሳስቧቸው ሰዎች መካከል አንዷ ስለሆንኩ . . . ይህን ትራክት በማንበቤ በጣም ተደስቻለሁ።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ