የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 7/15 ገጽ 32
  • ጥሩ ጓደኞች ለመምረጥ የሚያስችል መመሪያ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥሩ ጓደኞች ለመምረጥ የሚያስችል መመሪያ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 7/15 ገጽ 32

ጥሩ ጓደኞች ለመምረጥ የሚያስችል መመሪያ

ወጣቶች ልብስና ሙዚቃን በተመለከተ ከወላጆቻቸው ይልቅ እኩዮቻቸውን እንደሚያማክሩ ሪደርስ ዳይጀስት ላይ የወጣ አንድ ሪፖርት ዘግቧል። ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ከእነማን ጋር እና የት እንደሚውሉ ማወቃቸው በጣም አስፈላጊ ነው።

በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ልቦና ክፍለ ትምህርት ለረጅም ዓመታት ያስተማሩት ኤዝሜ ፎን ሬንስቦርክ “ጉዳዩን አጣርቶ ማወቅ የእናንተ ኃላፊነት ነው” ብለዋል። አክለውም “ልጃችሁ ሊበሳጭባችሁ እንደሚችል መጠበቅ ቢኖርባችሁም በኋላ ግን ንዴቱ ይጠፋላቸዋል” ብለዋል። ከዚያም ለወላጆች የሚከተለውን ምክር ለግሰዋል። የምታወጧቸው መመሪያዎች ምክንያታዊና ግልጽ በሆኑ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ የተመሠረቱ መሆን አለባቸው፤ ልጃችሁን በጥሞና አድምጡት፤ በቁጣ ከመገንፈል ይልቅ ስሜታችሁን ተቆጣጠሩ፤ እንዲሁም ምን መናገር እንደምትፈልጉ እወቁ። ልጃችሁ መጥፎ ባልንጀርነት ገጥሞ ከሆነ እንዲሁ በደፈናው ግንኙነቱን ማቋረጥ እንዳለበት ከመንገር ይልቅ ይህ ባልንጀርነት ባስገኘው መጥፎ ባሕርይ ላይ ትኩረት አድርጉ።

የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከረጅም ጊዜ አንስቶ ለወላጆች የሚጠቅም ሚዛናዊ ምክር ይገኛል። ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- “ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ይሁን።” (ያዕቆብ 1:​19) በተጨማሪ ቅዱሳን ጽሑፎች የጓደኛ ምርጫን በተመለከተ ቀጥሎ የተጠቀሰውን ጠቃሚ ምክር ይሰጣሉ:- “ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።” (ምሳሌ 13:​20) እነዚህ ምሳሌዎች መጽሐፍ ቅዱስን በአድናቆት የሚያነቡና በውስጡ የያዘውን መመሪያ በዕለታዊ ሕይወታቸው የሚያውሉ ሰዎች ሊያገኙት የሚችሉትን ጥበብ ያሳያሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ