የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 10/1 ገጽ 32
  • “እግዚአብሔርን ፈሩ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “እግዚአብሔርን ፈሩ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 10/1 ገጽ 32

“እግዚአብሔርን ፈሩ”

እስራኤላውያን ግብፅ ውስጥ በባርነት ሥር በነበሩበት ጊዜ የዕብራውያን አዋላጆች የነበሩት ሲፓራና ፉሐ አስቸጋሪ ሁኔታ ተደቅኖባቸው ነበር። ፈርዖን ቁጥሩ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የሄደውን የሌላ አገር ሕዝብ እድገት ለመግታት ባደረገው ሙከራ ለእነዚህ ሴቶች “የዕብራውያንን ሴቶች ስታዋልዱ . . . ወንድ ቢሆን ግደሉት” የሚል መመሪያ ሰጣቸው።​—⁠ዘጸአት 1:​15, 16

ሲፓራና ፉሐ ‘እግዚአብሔርን ስለፈሩ’ ‘የግብፅ ንጉሥ እንዳዘዛቸው ሳያደርጉ’ ቀሩ። ይህ ድፍረት የተሞላበት አቋማቸው አደጋ ላይ ሊጥላቸው ቢችልም ወንዶቹ ሕፃናት በሕይወት እንዲተርፉ አድርገዋል። ከዚህ የተነሳ ይሖዋ ‘ለአዋላጆቹ መልካም ያደረገላቸው’ ሲሆን ሕይወት ላዳኑበት ተግባራቸውም ወሮታ ከፍሏቸዋል።​—⁠ዘጸአት 1:​17-21

ይህ ዘገባ ይሖዋ እርሱን ለሚያገለግሉ ሰዎች ያለውን አድናቆት በጉልህ ያሳያል። ምንም እንኳ ሲፓራና ፉሐ ድፍረት የተሞላበት ነገር ቢያደርጉም ይሖዋ እንዲሁ በሰብዓዊነት ብቻ እንዳደረጉት አድርጎ ሊቆጥረው ይችል ነበር። ደግሞም የትኛዋም ጤናማ አስተሳሰብ ያላት ሴት ጨቅላ ሕፃናትን አትገድልም! ሆኖም አንዳንዶች ሰዎችን በመፍራት እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ድርጊቶች የመፈጸማቸውን ጉዳይ ይሖዋ ግምት ውስጥ እንዳስገባ አያጠራጥርም። ይሖዋ እነዚህ አዋላጆች እንዲህ ለማድረግ የተነሳሱት በሰብዓዊ ርኅራኄ ብቻ ሳይሆን አምላክን በመፍራታቸውና ለእርሱ ያደሩ በመሆናቸው ምክንያት እንደሆነ ያውቃል።

በታማኝነት የምናከናውናቸውን ነገሮች በቁም ነገር የሚመለከት አምላክ በማገልገላችን ምንኛ አመስጋኞች መሆን እንችላለን! እርግጥ ማናችንም ብንሆን ሲፓራና ፉሐ የተደቀነባቸው ዓይነት የእምነት ፈተና አልገጠመን ይሆናል። ሆኖም በትምህርት ቤትም ሆነ በሥራ ቦታችን ወይም በሌላ በማንኛውም ሁኔታ ሥር ሆነን ትክክል ለሆነው ነገር ጽኑ አቋም ስንወስድ ይሖዋ በታማኝነት ያሳየነውን ፍቅር አቅልሎ አይመለከተውም። ከዚህ ይልቅ ‘አጥብቀው ለሚፈልጉት ዋጋ ይሰጣል።’ (ዕብራውያን 11:​6) አዎን፣ “እግዚአብሔር፣ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፣ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለም።”​—⁠ዕብራውያን 6:​10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ