የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w01 7/1 ገጽ 32
  • ጥሩ ትዝታ ጥሎባቸዋል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥሩ ትዝታ ጥሎባቸዋል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
w01 7/1 ገጽ 32

ጥሩ ትዝታ ጥሎባቸዋል

የይሖዋ ምሥክሮች በየአገሮቻቸው በየዓመቱ በሚያደርጓቸው ትልልቅ ስብሰባዎች አማካኝነት አንድ ላይ ይሰበሰባሉ። እንዲህ የሚያደርጉት በመንፈሳዊ የሚገነባ ትምህርት ለማግኘትና እርስ በርስ ለመቀራረብ ነው። ሆኖም የስብሰባዎቻቸው ሌሎች ገጽታዎችም ተጋብዘው በሚመጡ እንግዶች ላይ ጥሩ ትዝታ ሊጥሉባቸው ይችላሉ።

ለምሳሌ ያህል ሐምሌ 1999 በሞዛምቢክ ያሉ በሺህ የሚቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮች “የአምላክ ትንቢታዊ ቃል” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ መንፈሳዊነታቸውን የሚያበለጽጉ ሦስት አስደሳች ቀናት አሳልፈዋል። ብዙዎቹ በአውራጃ ስብሰባ ላይ ሲገኙ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነበር። እነዚህ ሰዎች ከመድረክ በቀጥታ በቀረቡ ንግግሮች ብቻ ሳይሆን እዚያ ተገኝተው በተመለከቷቸው ነገሮችም በጣም ተነክተው ነበር።

በማፑቶ የትልቅ ስብሰባ አዳራሽ የተገኘች አንዲት ሴት የሚከተለውን አስተያየት ሰጥታለች:- “በሕይወቴ ሙሉ እንደዚህ ያለ ማራኪ ሥፍራ አይቼ አላውቅም! በመታጠቢያ ክፍሎቹ ውስጥ ሳሙና እንዲሁም መስታወት ያለ ሲሆን ክፍሎቹ ንጹህ ከመሆናቸው የተነሳ ደስ የሚል ሽታ አላቸው። እርስ በርስ የሚጣሉ ልጆች ጫጫታ ስለሌለ ምንም የሚረብሽ ነገር አልነበረም። ግፊያ የለም! ደስተኛ የሆኑ ወጣቶች እርስ በርስ የሚያበረታቱ ጭውውቶችን ሲያደርጉ ተመልክቻለሁ። እያንዳንዱ ሰው የነበረው ጥሩ አለባበስ አስደንቆኛል። በሚቀጥለው ጊዜ ልጆቼንም ይዤአቸው እመጣለሁ እንዲሁም ሁላችንም በዚህ የአውራጃ ስብሰባ ላይ መገኘት እንደሚገባን ባለቤቴን አሳምነዋለሁ።”

አዎን፣ የይሖዋ ምሥክሮች የሚያሳዩት ሐቀኝነት፣ የአቋም ጽናትና አካላዊ ንጽሕና የሰዎችን ትኩረት ይስባል። የይሖዋ ምሥክሮች የተለዩ የሆኑት ለምንድን ነው? ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማሩትን ተግባራዊ ለማድረግ ከልብ ጥረት ስለሚያደርጉ ነው። በዚህ ዓመት በሚያደርጓቸው የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ወይም በመንግሥት አዳራሾቻቸው ውስጥ በሚያደርጓቸው ሳምንታዊ ስብሰባዎች ላይ ተገኝተህ ለምን ሁኔታውን አትመለከትም?

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ዛምቢያ

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኬንያ

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ሞዛምቢክ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ