የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w02 10/15 ገጽ 3
  • ክፉ ኃይሎች አሉን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ክፉ ኃይሎች አሉን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩ ምግባር ክፋትን ድል የሚያደርግበት ቀን ይመጣ ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • በጥሩና በክፉ ድርጊት መካከል ለዘመናት የቀጠለ ጦርነት
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ጥሩ ወይም ክፉ ሰዎች እንድንሆን የሚያደርገን ምንድን ነው?
    ንቁ!—2010
  • ዓለምን እየገዛ ያለው ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
w02 10/15 ገጽ 3

ክፉ ኃይሎች አሉን?

“ዓለም ልክ አንድ ምትሃታዊ ኃይል ሆነ ብሎ መንገዱን ሁሉ የዘጋበት ያህል መውጫው ጠፍቶበታል።”​—ጋዜጠኛው ዣን ክሎድ ሱሌሪ

‘ነገሮች ከአቅማችን በላይ እንደሆኑ ሲሰማን አንድ ክፉ ኃይል እየተቆጣጠረን እንዳለ እናስባለን።’—ታሪክ ጸሐፊው ጆሴፍ ባርተን

መስከረም 11, 2001 የተሰነዘረው የሽብርተኞች ጥቃት ያስከተለው ከፍተኛ ድንጋጤ ብዙዎች በዓለም ላይ እየተከናወኑ ስላሉት ነገሮች በቁም ነገር እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። ፋይናንሻል ታይምስ በተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ ላይ ሚካኤል ፕራዉስ የተባሉ ሰው ‘እንስሳት እንኳን እንደዚህ ያለ አረመኔያዊ ድርጊት አይፈጽሙም’ ሲሉ ጽፈዋል። በኒው ዮርክ ታይምስ መጽሔት ላይ የወጣ አንድ ርዕሰ አንቀጽ ጥቃቱን የሰነዘሩት ሰዎች ድርጊቱን ለመፈጸም ከነደፉት እቅድ በተጨማሪ “ይህንን ድርጊት እንዲፈጽሙ የገፋፋቸውን ከፍተኛ የጥላቻ ስሜትም ልብ ማለት ያሻል። ይህ ተቀባይነት ያገኙ የጦርነት ደንቦችን የጣሰ፣ ገደብ የለሽና ከየትኛውም ስምምነት ውጭ የሆነ ጥላቻ የተንጸባረቀበት ጥቃት ነው” ብሏል።

የተለያየ እምነት ያላቸው ሰዎች አንድ ክፉ ኃይል እንዳለ ይሰማቸዋል። በጎሳ ጥላቻ ምክንያት በቦስንያ የደረሰውን ሰቆቃ የተመለከቱ በሳራዬቮ የሚኖሩ አንድ ነጋዴ እንዲህ ብለዋል:- “በቦስንያ ለአንድ ዓመት ያህል የዘለቀውን ጦርነት ከተመለከትኩ በኋላ ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ ያለው ሰይጣን መሆኑን አምኛለሁ። ይህ የለየለት እብደት ነው።”

ዣን ዴሉሞ የተባሉት ታሪክ ጸሐፊ በዲያብሎስ መኖር ያምኑ እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል:- “ከ40 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት፣ በኦውሽቪትስ የማጎሪያ ካምፖች የተፈጸመውን ከፍተኛ እልቂት፣ በካምቦዲያ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣ የቻውሼስኩን ጨቋኝ አገዛዝ፣ በመላው ዓለም መንግሥታት በሰዎች ላይ የሚፈጽሙትን ጭካኔ የተሞላበት ቅጣት እና ተዘርዝረው የማያልቁትን በእኔ የሕይወት ዘመን የተፈጸሙና እየተፈጸሙ ያሉ አሰቃቂ ድርጊቶች እየተመለከትኩ አንድ ክፉ ኃይል መኖሩን እንዴት መካድ እችላለሁ? በእርግጥም እንደዚህ ዓይነቶቹን ድርጊቶች ‘ዲያብሎሳዊ’ ብለን ለመጥራት በቂ ምክንያት እንዳለን ይሰማኛል። ሆኖም እነዚህን ድርጊቶች የሚቆሰቁሰው ዲያብሎስ ቀንዳምና የተሰነጠቀ ሰኮና ያለው ሳይሆን በዓለም ላይ ያለው የክፋት መንፈስና ኃይል ተምሳሌት ነው።”

እንደ ዣን ዴሉሞ ሁሉ ብዙ ሰዎችም ዛሬ ከቤተሰብ ክልል ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰብዓዊው ሕብረተሰብ ውስጥ የሚፈጸሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች “ዲያብሎሳዊ” ብለው ይጠሯቸዋል። ይሁን እንጂ ይህ ምን ማለት ነው? ለእንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ድርጊቶች ተጠያቂ የሚሆኑት የተወሰነ አካል የሌላቸው የክፋት ኃይሎች ናቸው? ወይስ ሰብአዊው ሕብረተሰብ በራሱ ሊፈጽማቸው የማይችላቸውን አሰቃቂ ወንጀሎች እንዲፈጽም የሚገፋፉት ክፉ አካላት አሉ? እንደዚህ ዓይነቶቹን ኃይሎች የሚመራቸው የክፋት አለቃ የሆነው ሰይጣን ዲያብሎስ ነውን?

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ልጆች:- U.S. Coast Guard photo

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ