የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w03 6/15 ገጽ 30
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ንቁ ሆናችሁ ኑሩ—ሰይጣን ሊውጣችሁ ይፈልጋል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ጠላታችሁን እወቁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ሰይጣን
    ንቁ!—2013
  • ሰይጣን ማን ነው? በእርግጥ እውን አካል ነው?
    ንቁ!—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
w03 6/15 ገጽ 30

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ሰይጣን ዲያብሎስ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን ማወቅ ይችላልን?

በእርግጠኝነት መናገር ባንችልም ሰይጣንም ሆነ አጋንንቱ በልባችን ውስጥ ያለውን ማወቅ እንደሚችሉ የሚያሳይ ማስረጃ አናገኝም።

ለሰይጣን የተሰጡትን የሚከተሉትን ስሞች ተመልከት። ሰይጣን (ተቃዋሚ)፣ ዲያብሎስ (ስም አጥፊ)፣ እባብ (አታላይ ለማለት ነው)፣ ፈታኝ እንዲሁም ሐሰተኛ ተብሎ ተጠርቷል። (ኢዮብ 1:6፤ ማቴዎስ 4:3፤ ዮሐንስ 8:44፤ 2 ቆሮንቶስ 11:3፤ ራእይ 12:9) ከእነዚህ ስሞች መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ ሰይጣን በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን ማወቅ እንደሚችል አይጠቁሙም።

ከዚህ በተቃራኒ ግን ይሖዋ አምላክ ‘የሰዎችን ልብ የመመርመር’ ችሎታ እንዳለው ተገልጿል። (ምሳሌ 17:3 አ.መ.ት ፤ 1 ሳሙኤል 16:7፤ 1 ዜና መዋዕል 29:17) ዕብራውያን 4:13 “እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ፣ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም” በማለት ይናገራል። ይሖዋ የሰዎችን ልብ የመመርመር ችሎታ ለልጁ ለኢየሱስም ሰጥቶታል። ትንሣኤ ያገኘው ኢየሱስ “ኵላሊትንና ልብን የምመረምር . . . ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ” በማለት ተናግሯል።​—⁠ራእይ 2:23

መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣን የሰዎችን ልብና አእምሮ የመመርመር ችሎታ እንዳለው አይናገርም። ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች “የእርሱን [የሰይጣንን] ዕቅድ አንስተውምና” በማለት ከሰጠው ሐሳብ ይህንን መገንዘብ ይቻላል። (2 ቆሮንቶስ 2:11 አ.መ.ት ) በመሆኑም ሰይጣን እኛ የማናውቀው አንድ ልዩ ችሎታ እንዳለው በማሰብ መፍራት አይገባንም።

ይህ ማለት ግን ባላጋራችን ደካማ ጎናችንን ማወቅ አይችልም ማለት አይደለም። ሰይጣን ላለፉት በርካታ ዘመናት የሰው ልጆችን ባሕርይ ሲያጠና ቆይቷል። ምን ዓይነት ባሕርይ እንዳለን፣ ምን ዓይነት መዝናኛ እንደምንወድ ወይም ስለ ምን ነገሮች እንደምናወራና ስለ መሳሰሉት ነገሮች ለማወቅ በልባችን ውስጥ ያለውን ማንበብ አያስፈልገውም። በፊታችን ላይ የሚነበበው ስሜትና አካላዊ ሁኔታችን ስለ ምን ነገር እንደምናስብና ስለ ውስጣዊ ስሜታችን ፍንጭ ሊሰጡ ይችላሉ።

በአጠቃላይ ሲታይ ሰይጣን እንደ መዋሸት፣ ማታለልና መረጃን አዛብቶ ማቅረብ ያሉትን በኤደን ገነት የተጠቀመባቸውን ዘዴዎች ይጠቀማል። (ዘፍጥረት 3:1-5) ክርስቲያኖች ሰይጣን በልባቸው ውስጥ ያለውን ማወቅ እንደሚችል በማሰብ መፍራት ባይኖርባቸውም ወደ አእምሯቸው ለማስገባት ስለሚፈልጋቸው ነገሮች ግን ማሰብ ይኖርባቸዋል። ሰይጣን፣ ክርስቲያኖች ‘አእምሯቸው የረከሰና እውነት የጠፋባቸው’ እንዲሆኑ ይፈልጋል። (1 ጢሞቴዎስ 6:5 የ1980 ትርጉም ) የሰይጣን ዓለም በረከሱ ሐሳቦችና መዝናኛዎች የተሞላ መሆኑ ምንም አያስገርምም። ክርስቲያኖች ‘የመዳንን ራስ ቊር’ በመልበስ አእምሯቸውን ከዚህ ጥቃት መጠበቅ ይገባቸዋል። (ኤፌሶን 6:17) አእምሯቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በመሙላትና መጥፎ ተጽዕኖ ከሚያሳድረው ከሰይጣን ዓለም ጋር የማያስፈልግ ቅርርብ ከመፍጠር በመቆጠብ ይህንን ማድረግ ይችላሉ።

ሰይጣን ኃይለኛ ጠላት ነው። ሆኖም እሱንም ሆነ አጋንንቱን ልንፈራቸው አይገባም። ያዕቆብ 4:7 “ዲያብሎስን . . . ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል” በማለት ይናገራል። ይህንን ምክር ከተከተልን እኛም እንደ ኢየሱስ በእኛ ላይ አንዳች የለውም ለማለት እንችላለን።​—⁠ዮሐንስ 14:30

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ