የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w05 2/15 ገጽ 9
  • የቤርለቡርክ መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የቤርለቡርክ መጽሐፍ ቅዱስ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “አዲሲቱ ዓለም ትርጉም”​—ምሁራን እውነተኛ ሆኖ አግኝተውታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • የአምላክ ቃል አፍቃሪዎች ትልቅ ግምት የሚሰጡት ክንውን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • በዓለም ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆት ያተረፈው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ሕያው የሆነ የአምላክ ቃል ትርጉም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
w05 2/15 ገጽ 9

የቤርለቡርክ መጽሐፍ ቅዱስ

በ17ኛው እና በ18ኛው መቶ ዘመን በጀርመን ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተጀመረ ፓየቲዝም የሚባል ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ነበር። የዚህ እንቅስቃሴ ተከታዮች የሆኑ አንዳንድ ሰዎች በእምነታቸው ምክንያት ይፌዝባቸው ነበረ፤ አልፎ ተርፎም ስደት ደርሶባቸዋል። የፓየቲዝም ተከታዮች የነበሩ በርካታ ምሑራን በሰሜን ፍራንክፈርት ከሚገኘው ሜይን ወንዝ 150 ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ ወደምትገኘው ቤርለቡርክ ተሰደዱ። ለሃይማኖት አክብሮት የነበረው ካውንት ካዚሚር ቮን ቪትገንሽታይን ቤርለቡርክ የተባለ የአካባቢው መስፍን እነዚህ ሰዎች ጥገኝነት እንዲያገኙ ፈቀደላቸው። እነዚህ ሰባኪዎችና ምሑራን በቤርለቡርክ እንዲኖሩ መፈቀዱ አሁን የቤርለቡርክ መጽሐፍ ቅዱስ የሚባለውን አዲስ ትርጉም ለማዘጋጀት መንገድ ጠረገ። የትርጉም ሥራው እንዴት ሊከናወን ቻለ?

ጥገኝነት ከጠየቁት መካከል በስትራስቡርግ ከተማ የነበሩት የሃይማኖት ምሑራን አላስቆም አላስቀምጥ ስላሉት መኖሪያውን ለቅቆ እንዲወጣ የተገደደው ዮሐን ሃውግ የተባለ ሰው ይገኝበታል። ሃውግ በጣም የተማረና ጥሩ የቋንቋ ችሎታ ያለው ሊቅ ነበር። በቤርለቡርክ ለሚገኙት ምሑራን “ፈጽሞ ያልተበረዘ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የማዘጋጀት፣ የሉተርን ትርጉም የማረም፣ የአምላክን ቃል በትክክል የመተርጎምና ሊተላለፍ የተፈለገውን መልእክት በሚገባ የማስተላለፍ” ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ነገራቸው። (ዲ ጌሺክተ ዴየ ቤርለንቡርገ ቢበል [የቤርለቡርክ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ]) ዋነኛ ዓላማው ማብራሪያና ትንታኔ የሚሰጥ ማስታወሻ የያዘና ተራው የኅብረተሰብ ክፍል ሊረዳው የሚችል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ማዘጋጀት ነበር። ሃውግ በሌሎች የአውሮፓ አገሮች የሚገኙ ምሑራን እንዲያግዙት የጠየቀ ሲሆን ሥራውን ለማጠናቀቅ 20 ዓመት ፈጅቶበታል። ከዚያም የቤርለቡርክ መጽሐፍ ቅዱስ ከ1726 አንስቶ መታተም ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱሱ ሰፊ ማስታወሻዎችን ስለያዘ በስምንት ጥራዞች መታተም ነበረበት።

የቤርለቡርክ መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ትኩረት የሚስቡ ነጥቦችን ይዟል። ለምሳሌ ያህል ዘፀአት 6:2, 3 እንዲህ ይላል:- “እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለው:- እኔ እግዚአብሔር ነኝ! ለአብርሃም/ለይስሐቅና ለያዕቆብ/ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን ይሖዋ በተባለው ስሜ አልታወቅሁላቸውም።” ለዚህ ጥቅስ የቀረበው ማስታወሻ እንዲህ ይላል:- “ይሖዋ የሚለው ስም . . . የተለየ/ወይም/በአዋጅ የተነገረ ስም ነው።” በተጨማሪም ይሖዋ የሚለው የአምላክ የግል ስም ለዘፀአት 3:15 እና ለዘፀአት 34:6 በተሰጠው ትንታኔ ላይ ይገኛል።

የቤርለቡርክ መጽሐፍ ቅዱስ በዋናው ጥቅስ ላይ ወይም በግርጌ ማስታወሻቸው አሊያም ደግሞ በማብራሪያቸው ላይ የይሖዋን ስም ከጠቀሱት በተከታታይ ከታተሙት የጀርመንኛ መጽሐፍ ቅዱሶች አንዱ ሆኗል። ለአምላክ የግል ስም ተገቢውን አክብሮት ከሰጡት እጅግ በጣም ዘመናዊ ከሆኑት ትርጉሞች ውስጥ በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀው የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም ይገኝበታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ